November 25, 2011

ከደሴ ደብረ ቤቴል ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምረቃ የቀሩት አቡነ ጳውሎስ የጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መረቁ


  •  መኖሪያ ቤቱ ብር 1.5 ሚልዮን ያህል እንደወጣበት ተነግሯል 
  •  አቡነ ጳውሎስ ያለጥንቃቄ ባደረጉት ጉዞ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል
  •  “አይ ቅዱስነትዎ፣ ተዋረዱ!! አሁን ይህ ለእርስዎ ክብር ነውን? የመቂ ሕዝብ እርሱን [ጌታቸው ዶኒን] ከእኛ የተሻለ ጠንቅቆ ነው የሚያውቀው፤ እንግዲህ የጌታቸው ዶኒ ጓደኛ ነው የሚልዎ!” /አቡነ ጎርጎርዮስ በድርጊቱ ማዘናቸውን ለአቡነ ጳውሎስ የገለጹበት መንገድ/
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 15/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 25/2011/ PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ ኅዳር 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት መቂ ከተማ ተገኝተው የሊቀ ካህናትጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መርቀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ 98 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው መቂ ከተማ ከድልድይ በላይ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በ400 ሜትር ካሬ ስፋት ያረፈውና በ‹ሀ› ቅርጽ የተገነባው የሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ቪላ 1.5 ሚዮን ብር ማውጣቱን ግለሰቡ በምረቃው ዕለት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ባቀረበው አጭር ሪፖርት ገልጧል፡፡ በምረቃው ላይ በግለሰቡ ጥሪ የተደረገላቸው 200 ያህል እንግዶች የታደሙ ሲሆን ድግሱም ሞቅ ያለ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ወደ መቂ ያመሩት ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ገዳማት እና አድባራት በተዋጣው አራት ሚዮን ብር በተገዛው Vx8 ላንድክሩዘር መኪና ሲሆን ጉዟቸውም በምስጢር የተደረገ ነበር ተብሏል፡፡ ከፓትርያኩ ጋራ ብፁዕ አቡነ ገሪማ አብረዋቸው የነበሩ ሲሆን በመንገድም ለምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስልክ በመደወል ሞጆ ላይ እንዲቀላቀሏቸው አድርገዋል፡፡ በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በወንጂ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ ሥነ ሥርዐት ላይ እንደነበሩ ከፓትርያኩ ጋ ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ቢነግሯቸውም የተፈለጉበት ሳይነገራቸው በቀጭን ትእዛዝ እንዲያገኟቸው መደረጉ ተነግሯል፡፡
በአቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ አመጣጥ የተገረሙት ብፁዕነታቸው ጉዞው የጌታቸው ዶኒን ቤት ለመመረቅ እንደሆነ ከፓትርያኩ ሲነገራቸው፣ “ይህ ለእርስዎ ጥሩ አይደለም፤ ውርደት ነው፤ ዝቅ ማለት ነው፤ ሰዉም ግምት ይወስድብዎታል፤” በማለት ሐሳባቸውን ለማስቀየር ጥረት ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡ ይሁንና ቀደም ብለው በጉዟቸው የቆረጡበት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መንገዳቸውን በመቀጠል ወደ አንድ የቁጥጥር ኬላ ሲደርሱ [ዓለም ጤና አካባቢ] ያለ ጥበቃ/ አጀብ/ መጓዛቸው ጥሩ እንዳልሆነ ሲጠየቁ “ለሽምግልና ስለሆነ ነው” በሚል መልስ ሰጥተው አልፈዋል፡፡ መቂ ከተማ መግቢያ ላይ ሲደርሱ ጌታቸው ዶኒ ያሰለፋቸው ሞተርኬዶች አጅበው ለማስገባት ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም አጀቡን የተመለከቱት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ “አይ ቅዱስነትዎ፣ ተዋረዱ!! አሁን ይህ ለእርስዎ ክብር ነውን? የመቂ ሕዝብ እርሱን [ጌታቸው ዶኒን] ከእኛ የተሻለ ጠንቅቆ ነው የሚያውቀው፤ እንግዲህ የጌታቸው ዶኒ ጓደኛ ነው የሚልዎ!” በማለታቸው ሹፌራቸው ፍጥነቱን ጨምሮ ወደፊት (ወደ ዝዋይ) እንዲፈተለክ ፓትርያኩ ቀጭን ትእዛዝ ይሰጣሉ፡፡
ከመቂ በስተደቡብ 27 ኪ.ሜ ርቃ ወደምትገኘው ዝዋይ ከተማ አቅጣጫ የተፈተለከው ሹፌርም ትንፋሹን የያዘው መኪናዋ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ስትገባ ነበር፡፡ ቅዱስነታቸውን ከብፁዕ አቡነ ገሪማ እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ጋ በያዘችው Vx8 ላንድክሩዘር መኪና ሽምጠጣ ግራ የተጋቡት ሞተሪስቶች ወደ ኋላ ቢቀሩም በቅዱስነታቸው ግብታዊ ‹የጉብኝት ዜና› የተረበሹት ዝዋያውያንም ለአቀባበሉ ሽር ጉድ ለማለት መጀመራቸው አልቀረም ነበር - ብዙም ሳይቆዩ ቅዱስነታቸው ፊታቸው መልሰው በመጡበት አቅጣጫ በረሩ እንጂ፡፡ ብልሃቱ ለጊዜው ከሞተርኬዶቹ አጀብ ለማምለጥ ቢሆንም ፍጻሜው ግን በብፁዕነታቸው የማስጠንቀቂያ ቃል መሠረት የጌታቸው ዶኒን ቪላ ቤት ምረቃ “ከዝዋይ ገዳም መልስ በአልፎ ሂያጅ /እግረ መንገድ/” የተደረገ ለማስመሰል መሆኑን ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡
ሽጉጥ ታጣቂው 
ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ
ይሁንና ብልሃቱ የቪላ አስመራቂውን ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒን የድግስ መርሐ ግብር በማዛባቱ የዕለቱ ‹የክብር እንግዳ› በሰዓቱ ባይገኙም እድምተኛው መስተናገዱ አልቀረም፡፡ ከቀኑ 8፡00 እንዲገኙ ፕሮግራም የተያዘላቸው አቡነ ጳውሎስም በጉዞው ላይ በተደረጉት ታክቲካዊ መስተካክሎች ምክንያት ከአንድ ሰዓት በላይ ዘግይተው ይደርሳሉ፤ ብዙው እድምተኛ ከድግሱ ተቃምሶ፣ መርቆ እየተሰናበተ በመውጣቱ በተወሰነ መልኩ ጭር ማለቱ ደጋሹን አሳጥቷቸዋል፤ “የረባ ዝግጅትም የለህ፤ ለእኔ እንኳ ኩኪስ አላዘጋጀህልኝም” - የአቡነ ጳውሎስ ትችት ሲሆን “ቅዱስ አባታችን፣ በምን አቅሜ/ገንዘብ?” የጌታቸው ዶኒ መልስ ነበር፤ ታዲያ ቦታውን ተመርተው ቢያገኙትም ቪላውን ያሳነፁበትን 1.5 ሚልዮን ብር ከየት አገኙት? - የታዛቢዎች ጥያቄ ነው፡፡     
የሆነው ሆኖ በኢትዮጵያ ባንዲራ በደመቀው ቅጽር አልፈው ወደ ሳሎኑ የዘለቁት አቡነ ጳውሎስ በትልቅ አልበም ተሠርቶ የተሰቀለውን የራሳቸውን ምስል ለመመልከት ታድለዋል፡፡ ወዲያውም ጌታቸው ዶኒ ለፓትርያኩና ለቀሩት እንግዶች ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም ለቪላው 1.5 ሚዮን ብር ወጪ ማድረጉን ተናግሯል፤ በሥራውም ያገዙትን አምስት ያህል ሰዎች አመስግኗል፡፡
ከአንድ ሰዓት ላልበለጠ ጊዜ በጌታቸው ዶኒ ቪላ የቆዩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ወደ ሐዋሳም ለማምራት ዕቅድ ነበራቸው ቢባልም የምጽአታቸው ወሬ ቀደም ብሎ ተሰምቶ ኖሮ በከተማው ቀናዒ ምእመናንና በሌሎቹ መካከል ፍጥጫ የመፍጠር አዝማሚያ በመስተዋሉ ምክንያት፣ ከክልሉ የፍትሕ እና ጸጥታ ቢሮ ለፓትርያኩ በደረሳቸው ማሳሰቢያ መሠረት ዕቅዳቸው ሰርዘው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ታውቋል፡፡
ባለፈው ዓመት ግንቦት ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሃይማኖቱ እና ሃይማኖተኝነቱ ጥያቄ ተነሥቶበት የምልአተ ጉባኤውን አባላት ያከራከረው ጌታቸው ዶኒ፣ ከፕሮቴስታንት የእምነት ተቋማት ጋራ ያለው ያልተገባ ግንኙነት በማስረጃ መረጋገጡ ከተነገረና፣ ፓትርያኩ ያለ ሲዳሞ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዕውቅና የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አድርገው ከሾሙበት ሥልጣኑ በሐዋሳ ምእመናን ጠንካራ ተቃውሞና በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ከተነሣ በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ምክትል ሓላፊ ሆኖ መሾሙ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከፓትርያኩም ይሁን በዙሪያቸው ከተሰለፉ ሕገ ወጥ ግለሰቦች ራሱን ማግለሉን ሲነገርለት የቆየው ጌታቸው ዶኒ አሁን ቪላውን ለማስመረቅ ፓትርያኩን መጋበዙ፣ ፓትርያርኩም የቁርጥ ቀን ወዳጃቸውን ጥሪ ሳይንቁ መገኘታቸው አነጋጋሪ ሆኗል - ጌታቸው ዶኒ ለ18 ዓመት በዓለ ሢመታቸው ላሠራላቸው ሐውልተ ስምዕ ውለታውን ለመመለስ፣ በዚህ ዓመት በልዩ ሁኔታ እንዲከበር ‹ተወስኖ› ከወዲሁ እንቅስቃሴ ለተጀመረበት 20 ዓመት በዓለ ሢመታቸው ‹የላቀ ትብብሩን› የሚጠይቅ ፈለማ/ቅድሚያ ለመያዝ ይሆን?
ርግጡን ወቅቱ ሲደርስ የምናየው ሲሆን የሚዲያ ተቺዎች ግን ፓትርያርኩ የጌታቸው ዶኒን ቪላ መመረቃቸው ከመንፈሳዊ አባትነታቸው፣ ከቀረቤታቸውም አኳያ የሚጠበቅ ቢሆንም መስከረም 18 ቀን 2004 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ በተከበረው በታላቁ የደሴ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በዓል ላይ ካለመገኘታቸው ጋራ በማያያዝ ክፉኛ ትችታቸውን ይሰነዝሩባቸዋል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት የነበራቸው ምንጮች እንደሚናገሩት ቅዳሴ ቤቱ ከተከበረበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዱስነታቸው መስከረም 15 ቀን በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ዘጠኝ የክልል ትግራይ ፖሊስ ኪነት ቡድን አባላት ቀብር ሥነ ሥርዐት በተከናወነበት መቐለ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ነበሩ፡፡
ደሴ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን አስከትለው በመሄድ በቀብር ሥነ ሥርዐቱ ላይ የማፅናኛ መልእክት ያስተላለፉት ቅዱስነታቸው በተከታዩ ቀን ለሚካሄደው የደሴ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ቀደም ብለው በራሳቸው ጥያቄ ፕሮግራም አስይዘው የነበረ ቢሆንም ሳይገኙ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡ 18 ዓመት እና ዘጠኝ ሚልዮን ብር በፈጀው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ላይ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስን ጨምሮ የደቡብ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ከደብረ ታቦር፣ የሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ከወልዲያ ማልደው ተጉዘው ተገኝተው ነበር፡፡ በደቡብ ትግራይ የማይጨው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴ ቤቱ ቡራኬ ላይ ለመገኘት አስበው የነበረ ቢሆንም በፓትርያርኩ ጥሪ ወደ መቐለ ተመልሰዋል፡፡
(ፎቶ) የደሴ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምረቃ፤ የእስልምና እና ፕሮቴስታንት እምነቶች ተወካዮች ባሉበት
በ2002 ዓ.ም በዚያው በደሴ ቅድስት አርሴማ ወአቡነ አረጋዊ ገዳም ይዞታ ጋ በተያያዘ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት 12 ምእመናን ቆስለው አራት ምእመናን ሲሞቱ ፓትርያርኩ ኀዘናቸውን አለመግለጻቸውን የሚስታውሱት የከተማው ነዋሪዎች፣ “አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም አሠርተን መርቁ ብለን ብንጠራቸው አልመጡም፤ አባትነታቸው ከወዴት አለ?” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ የምእመኑና የአገልጋዩ ጠንከር ያለ ቅሬታ በተለያየ መንገድ የደረሳቸው የሚመስሉት ፓትርያርኩም በ30ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ልካኑ በይፋ ይቅርታ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡
 ቃላዊ ይቅርታው የሚገፋ ባይሆንም በአስደናቂ ኪነ ሕንፃው ‹ዳግማዊ ላሊበላ› በተሰኘው፣ የክርስቲያን ሙስሊሙ ማኅበራዊ መግባባትና መረዳዳት ጎልቶ በታየበት በደሴ ደብረ ቤቴል ቅዱስ ገብርኤል ቅዳሴ ቤት ላይ “የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት” የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመቐለ - ደሴ 262 ኪ.ሜ ብቻ ገሥግሠው በክብረ በዓሉ ላይ አለመገኘት የግለሰቡን ጌታቸው ዶኒን ቪላ ለመመረቅ 98 ኪ.ሜ ለመጓዝ ካሳዩት ብልሃት አንጻር ዳግመኛ ጥያቄውን ማጫሩ አልቀረም፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

37 comments:

Anonymous said...

አይ አቡነ ጳውሎስ?
ስለ እናት ቤተ ክርስቲያን ብለው መስዋዕት የሆኑትን የጅማና የአርሲ. . .ምዕመናንን ለማጽናናት ሳይመቻቸው ሲቀር፤ የትግራይ ዘፋኞችን ፍትሐት ሊፈቱ ሄዱ። አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን መርቁ ሲባሉ የግለሰብ ቤት ለዚያውም የመናፍቅ! ለመሆኑ መቼ ይሆን ወደ ኅሊናቸው የሚመለሱት

lele said...

batame yasazenale abatachen edema laneseha nawe

Anonymous said...

betam tegremalachehum tasazenalachehumm be ewenet and keresteyan ayesadebem... ayekenam... wendemun yimekeral enji kifu ayasebebetem tadeya egziabeher endet new mitareken??? min alebet abatachen hedew betun bimerku? newer new? hateyat new? hateyates yewendemun dekimet eyaweta yemezerezer new yiker yebelachehuu

Anonymous said...

Guys, please leave Abba Paulos.
He is old man and he couldn't do anything as well as expected people.

Anonymous said...

Abo silefetrachihu atakuslun

Anonymous said...

Dear anonymous, Abune Shinoda is old too but you know what he does for his church right?

Anonymous said...

Abba shinoda is different than Abba Paupos. Please don't similar both. Abba Shinoda is real father and he lives for soul of memenan, but Abba Paulos live for himself and he follows opposite of Abba Shinoda

Anonymous said...

"Enanete worobelawoch, leave me alone, MONEY TALKS. Let me enjoy. Ahune yehe keAserahute hawoletea yebeltale? Atenchachu, Synodosme alechalegne!"

Anonymous said...

1. I think aba poaulos should say it is enough for him as a patriarch and just be away from administration and be by himself to pray, to fast ,to repent save himself .It is not good for him tobe a leader and be bad model for the church and make the churche's value, people's strength to lose trustfulness.

2. This is a big strategy by tehadiso and other menafikans. we know it aba ,you feel as if you are leading smartly. you are hiding from meki miimen ,could you hide in front of God either now or when you die.
3. Prevoiusly I was blaming aba paulos but now I am really and deeply sad and start saying he will be in hell and I wish him to be better and live true christianity and repent.

4.Aba paulos,if you do not want your sins be open in all the people mind and you may fear that you will be judged and go to jell ,please hide somewhere in gedam(monastery)

5.how many times you hide from people and lie to yourself and to God always all in your life . Do you feel happy while you do this in all your life. money will not make you satisfy ,please be with yourself listen to your internal hilina/mind.

6.Please may be you could not tolerate the pressure by your relatives, ajabis and body guards,
leave them and go hide somewhere and pray for them too.

7. do you have best and good friends or relatives who can consult you ,leave them and be by youself as menekuse, you are always with people and do not have time to thinkof your sins and repent.please aba paulos

all miemenen pray for ourselves and the church

Anonymous said...

[ዓለም ጤና አካባቢ] and መቂ ከተማ መግቢያ are in different direction. The first is in west addis and the later in south/south east?

Anonymous said...

1.5 million birr, how can a priest have that much money? I do not even know this priest,never heard his name but that amount of money, it raises doubt.The priest spirituality is questionable.

Anonymous said...

ሁልጊዜ ስለ አቡነ ሺኖዳ ታላቅ አባትነት፣ ስለ ሕዝባቸው አሳቢነት ስትናገሩ እሰማለሁ፣ ስትጽፉም አያለሁ። ዕውነተኛ አባት ከሆኑማ እስቲ የኢየሩሳሌም ገዳማችንን ሰላም ይስጡት። እባካችሁ ስለማታውቁት የሰው ቤት አትናገሩ። ስለራሳችን ተገቢውን ነገር እንነጋገር።
እነ ተቆርቋሪ ነን ባዮችም እስቲ ራሳችሁን ቆም ብላችሁ ተመልከቱ። ፍየል የጓደኛዋን ታየብሽ አለቻት ይባላል።
ክርስትና ሕይወት እንጂ ወሬ አይደለም፤ ክርስትና ራስን ትቶ ለሌላው ሕይወት ማሰብ እንጂ በአስተሳሰብ የማይስማማን ማሳደድ አይደለም።

Anonymous said...

ደሴን እንኳን ደስ አለሽ በሉልኝ:: አባ ጳውሎስ ቢረግጧት በረከትን አታገኝም ነበር:: እሳቸው መጡ አልመጡ የቀረብሽ የለም በሉልኝ::የተዋህዶ ጠላት መጡ አልመጡ ምንም አያመጡ:: የሙሉወንጌል ጸሎት ቤት የሚከፈትበት ቦታ ካለ ያንን ተገኝተው ይባርኩ:: በጌታቸው ዶኒ እያለማመዱን ነው:: የመንፈስ ልጃቸውስ ስደተኛ የለ ገለልተኛ የለ የሁሉም አባት ነኝ አይደል ያሉ:: እናም ደሴን ስላልረገጧት ደስ ብሎናል:: ኃይማኖት የሌለው ሰው ሕዝብን አያጽናና ( የዛሬ ሁለት ዓመት ደሴ አርሴማን አስመልክቶ ለሞቱት ወገኖቻችንን ሞት እንደሞት ሳይቆጥሩት በመኪና አደጋ የሞቱትን የክልላቸው ሰወች ሃዘን ግን ሊያጽናኑ ሄዱ:: እዚህ ላይ የደረሰውን አደጋ እና ህይዎታቸውን ያጡትንኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ሰዎች ማጽናናት አግባብ አይደለም ለማለት አይደለም ለንጽጽር ያቀረብኩት የሳቸውን ለሁሉም አባት ለመሆን አለመፈለግ እንጅ:: ለኔ ግን የሁሉም አሟሟት አሳዝኖኛል:: የአርሴማዎቹን የዞኑ ባለስልጣናት የተሻለ ውሳኔ መወሰን እየቻሉ ራሳቸው በሰጡት ፈቃድ ሕዝቡን ማሳመን እና የተሻለ አማራጭ መውሰድ እየቻሉ ባለማድረጋቸው ጥፋተኝነታቸውን የምናውቅ እናውቀዋለን:: የትግራይ ፖሊስ የኪነት ቡድን አባላትም ስንቱ በአውሮፕላን በሚንቀባረርበት ዘመን ከትግራይ እስከ ሱዳን በአውቶብስ ያውም በአሮጌ እንድጓዙ መደረጉ ወጭን ለመቆጠብ ነበርን? እነዛን ብርቅየ የባህል አምባሳደሮች ያስጨረሰው የተሳሳተ የጉዞ አቀናጅ አካል ከጥፋተኝነት አያመልጥም አባ ጳውሎስ ግን የጥፋተኞቹን ኃጢአት ለመደበቅ ይሁን ወይንም የጥፋቱ አካል ሁነው እንደሁ አላውቅም የሚመጥናቸውን መስራት አልቻሉም:: ለነገሩ የሚመጥናቸውንማ እየሰሩ ነው ኃይማኖትን ማጥፋት:: እርሱ ራሱ የሚበጀውን ያድርግ::

Weyra said...
This comment has been removed by the author.
Weyra said...

How come you say "... ፓትርያርኩ የጌታቸው ዶኒን ቪላ መመረቃቸው ከመንፈሳዊ አባትነታቸው፣ ከቀረቤታቸውም አኳያ የሚጠበቅ ቢሆንም...". Rather the Patriarch could have asked Getachew 'how could he build a 1.5 million villa with his mingling salary?' That clearly indicates he did it by corruption. And this shows Aba Paulos supports corruption in a day light.

Question to Dejeselam, is Getachew a 'monk' or 'married priest'? Is he is a monk.... then Aba Paulos encourages monks to build personal buildings.... so sad.

Anonymous said...

MEKI is 130 KM South of Addis

Angesom said...

i'm always surprised with Dejeselam for it brings Newest news for us. thank you !! may God gave your pay in his coming Heaven.
i heard one holy fathers says when a papas made wrong let a girl correct him. So i call for all those who can correct him from his way. with the help of pray and daily advice. may God help you so that we can hear good news about our church.
Angesom from Asmara

Angesom said...

i'm always surprised with Dejeselam for it brings Newest news for us. thank you !! may God gave your pay in his coming Heaven.
i heard one holy fathers says when a papas made wrong let a girl correct him. So i call for all those who can correct him from his way. with the help of pray and daily advice. may God help you so that we can hear good news about our church.
Angesom from Asmara

Anonymous said...

i'm always surprised with Dejeselam for it brings Newest news for us. thank you !! may God gave your pay in his coming Heaven.
i heard one holy fathers says when a papas made wrong let a girl correct him. So i call for all those who can correct him from his way. with the help of pray and daily advice. may God help you so that we can hear good news about our church.
Angesom from Asmara

Anonymous said...

Crap Story!

Anonymous said...

ene yegeremegi ye muslim ena protestant min lihonu new orthodox cherch mirikat yehedut algebagim?

Anonymous said...

Where is the so called "Ethics and Anti Corruption Commission"

The PM, as he confirmed us, earns 6,000 and after deductibles made he is gonna receive nearly 4800. Does this worth to build a million Birr VILLA?

1. How could manager of a Diocese having very low
salary scale as compared with other high pay
firms build such first class VILLA?

2. What other income generating mechanisms does
he have that can make him boast about VILLA?

3. What do the Building and the Inauguration as well
exemplify the public at large? Doesn't it mean
that citizens are officially entitled the right to go
up the wealth ladder in the shortest possible way,
i.e "Mussena"

WHERE IS THE SO CALLED ''ETHICS AND ANTI CORRUPTION COMMISSION?

Anonymous said...

Abune Paulos is one of Getachew Doni's leader so it's obvious that they are doing their best to stop the growth of Tewahedo Church with the help and unconditional fund from Protestant church. All we have to do is to opose Abune Paulos where ever he goes, we should say no to his autocracy leadership. If the holy synodos does not do it's job the christians will do theirs let us all push towardes fighting Abune Paulos every where he goes, not only him his followers Aba Gerima, Aba Fanuel, Aba Sereke, Getachew doni, and not forgeting Begashaw and his gang group as well.
Good luck

Anonymous said...

dirom wusha bebelabet bet yichohal yibalal, andun kifil setoachew eziyaw benoru tiru neber

Anonymous said...

hahhahahahaha, kukis sayazegaji 1.5 million endet tekebele,min seto yihon yetekebelew, letehadiso enkisikassie sira masikeja ketemedebew yihon new kemudaye mitsiwat

ርብቃ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች ጠፍታችሁ ጠፍታችሁ ብቅስትሉ ይሄንንኑጉደኛ አባት ይዛችሁብቅአላችሁ እኔየሚገርመኝ እኝህሰውየ አሁንም ልባቸውአልተመለሰም እንደውለመሆኑ አቡነሽኖዳን ሲያዩዋቸው እኔስ እራሳቸውን ይመረምራሉ ለስከዛሬውም ንስሀይገባሉ ብየነበር ምክንያቱም ድፍን የግብጽ ክርስቲያን ካዋቂእስከጻን ተገኝቶ ለኖላዊ እረኛው ያለውን ትልቅፍቅር እንዲያበእንባና በልልታ ሰገልጽ እኔ(የኔስ ባእለሲመት) ቢሆን ብለው እራሳቸውን ቢጠይቁ የሚያገኙ መልስ የሚያስፈራ የሚያሳፍር አንገት የሚያስደፋ እንደሚሆን ሲያስቡ በቀራቸው እንጥፍጣፊ እድሜ ለንስሀ የሚያተጋቸው ጥሩቶርች ነው ብየ አስቤነበር ለዚያውም አላግባብ ሁለት መቶ ሽብር ለጎረቤት ሀገር ለግብጽ ትራንስፖርትና መዝናኛ ማውጣታቸው እንዳለሆኖ ግንሳ እሳቸው እቴ ያዳቆነ ሰይጣን እንደሚባለው እየባሰባችው ነው የሚሄዱት እርሱመድሀኒአለም ፍርዱን ይስጠን እንጅ ያስፈራል መጭውን ማስቡ!

Anonymous said...

GUYS I NEED ONLY GOSPEL , BOEING BORIONG GUYS OH ! MY GOD

Anonymous said...

መክሰስ፤ ኃጢአትን መቆጣጠር፣በደልን ማሰብ፣ ዐመጸኞችን መከታተል የክርስቲያን ምግባር ሳይሆን የሰይጣን ስራ ነው።
ለምን ይመስላችኋል ይህ ሁሉ ክፉ ነገር የደረሰብን?
ለእግዚአብሔር የማንመች የአፍ ክርስቲያኖች፣ የቅድስናና የንጽሕና ባዶዎች ስለሆንን ነው።
ከስድብ፤ ከማንቋሸሽ፣ የዐመጸኞችን ዐመጽ ከማሰብ የራቀ ልቡናን ይስጠን። ኢትዮጵያንን ሕዝቧን እግዚአብሔር ይባርክ።አሜን።

Anonymous said...

ለመሆኑ ጌታቸው ዶኒ ይህንን ያክል ገንዘብ አውጥቶ ሲሰራ ገንዘቡን ከየት አመጣው ብሎ የሚጠይቅ የለም ከየት እንደመጣ ውስጣችን ያውቀዋል:: ለመሆኑ ይህንን ያክል ገንዘብ ሲኖረው ለሃገራችን ምንያክል በታክስ ገቢ አድርጎ ይሆን:: የአገራችንን ልማት በገንዘብ ለመደገፍ ብዙ ገቢ ያላቸው ሠዎች በገቢያቸው ልክ በሕጉ መሰረት ታክስ ሊከፍሉ ይገባል:: ገቢ አሰባሳቢው አካል ሊያስብበት ይገባል:: ምንም ታክስ ያልከፈሉ ሰዎች የሚሊዮኖች ቤት ሲሰሩ፣ ሚሊዮኖች በባንክ ሲኖራቸው፣ ምንጩ ያልታወቀ ኢንቨስትመንት ሲኖራቸው ማጣራት ያስፈልጋል:: በአንድም በሌላም ከሕዝብ የዘረፉትን ገንዘብ ህጋዊ እያደረጉነውና ባይሆን የሃገሪቱን ድርሻ ታክስ ይክፈሉ:: የመንግስት ሰራተኛ እና ገበሬ ብቻ ሆነ እኮ በሕግ የተወሰነለትን የሚከፍለው:: የመንግሥት አካላት ልብ ሊሉት ይገባል:: ለሃገር የሚያስብ ካለ እንየው!!!!!!! ያን ጊዜ ሌባ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም እንዳሉት እጁን ከሙዳየ ምጽዋት ላይ ሊያነሳ ይችላል::

Anonymous said...

"አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ" ይሉሀል እንደዚህ ነው።

Anonymous said...

Egna gin besinfina ena dikimetachin yametabin fetena new. Menekosat ena yebetechristian astedadariwoch villa eyasmereku, patriarch yegileseb bet mirikat lezawum beminet bemitereter sew bet. Keyet amtito aseraw new tiyakew. Egziabher bizegeyim ayikerim. Menshun yanesal. Lehulum gizie alew. Egna gin yedirshachinin eniwota. Hulum beyeatibia betechristian tenkiro mesirat alebet. Brothers and sisters in Christ, please let us be strong in preying and to defend our church in whatever it is possible. Ken ena lelit lebetu mesirat yalebin seat new. Egziabher amlak birtatun yadilen.

Anonymous said...

ለመናፍቁ አባ ዲያብሎስ ተፅፎ ያላወጣው የኔ ግራሞት

መናፍቁ አንተ የተሀድሶ ልሳን አይደለህ እንዴ? አንተስ ከመናፍቅ ልሳን ጋር ትመጋገብ የለ እንዴ? 
ሌላው ማቅ በሌለው ውክልና እንዲህ አደረገ እያልክ ነጋ ጠባ ትከሳለህ:: አንተስ የትኛው ውክልናህ ነው ኢየሱስን አማላጅ ነው ያስባለህ? በየትኛው ውክልናህ ነው መላዕክት ፃድቃን ሰምአታትን በየእለቱ ስታንጔጥጥ የምትውለው? ነው ወይስ የሙሉ ወንጌል ውክልና ይቆጠራል? ሚዛን ላይ ተቀምጠህ ቀለህ ተገኝተሀል::

እንቁ ከደጀ ሰላም ጋር አንድ አይነት ነገር ስለፃፈ የማህበረ ቅዱሳን ከተባለ በራስህ ሂሳብ ነጋ ድራስ እና ማራኪ የተሀድሶ ናቸው ማለት ነው?
ማቅ= እንቁ
ተሀድሶ= ነጋ ድራስ ማራኪ የሙሉ ወንጀል ልሳኖች
በሽተኛ ግራ የተጋባህ ውሸታም መናፍቅ::

ortodxawiw said...

this is a trash story.Good for nothing!!... I don't want to lie,I never saw/read any thing biblical in this website...hamet,were... manin asadege... ebakachihu wede nefsachihu temelesu?!---How come a religious site goes down this deep?

Anonymous said...

Dear November 27, 2011 1:30 AM,

As you said defaming, insult and judging others is not a spiritual act. But what dejeselam is doing is that unraveling the realities about the Patriarch and Getachew Doni and awakening the fellow orthodox tewahedo people. Ende ergib yewahoch hunu gin demo endebab libamoch hunu tebilenal. We cannot sit idle and kept only preying while the church is embuzzled and encroached by others. God will help us only when we are doing our part. I accept your comment about avoiding some irrelevant words in mentioning the Patriarch. But, I encourage Dejeselam to bring these types of news to the public as these are crucial for our further movements. If you are a real tewahido person, donot get disappointed and disturbed by what is happening. This is part of christian life. it is a way to the cross and can't never be always a comfortable way. If you are from Tehadiso, you better prey and come back to your mother church. Apart from that, tehadiso protestant groups are being arrested because of these information exchange and we are now in a real preparation for more defense at different levels of the church. We have to make our level best to solve the problem of protestantism from the top (tekilay betekihinet) to individual church levels. We are also hoping the backups of the government in solving the real dangers of our church and the consequent national chaos. If not we will keep on struggling with the help of God. Egziabher kegna gar kehone man yashenifenal.

Anonymous said...

የአትትዎ ለኀጥእ ከመ ኢይርአይ ስብሐተ-እግዚአብሔር!
አያችሁ ገብርኤል ጀግናው ቤቱ እንዳይረክስበት ሲጠነቀቅ?

Anonymous said...

yigermal eko christian ayi getachewu done: GOD lebonawun yemelseln

Anonymous said...

+++
ከሃውልቱ ሥር ከተጸፉት ስሞች የመጀመሪያው ሥም የእርሱ ነው::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)