November 15, 2011

በጋሻው ደሳለኝ በመ/ር ዘመድኩን በቀለ እና ዲ.ን ደስታ ጌታሁን ላይ የመሠረተው ክስ ተቋርጦ መዝገቡ ተዘጋ

  •  አሰግድ ሣህሉ በድብደባ ወንጀል ክስ መጥሪያ ወጥቶበት እየተፈለገ ነው
  • መ/ር ዘመድኩን በቀለ ለሰዓታት በእስር ቆይቶ ተለቀቀ
  • አሰግድ ሣህሉ ቅዱስ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ - ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ አጣጣለው
  • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በአሰግድ ሣህሉ እና ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ሊመሠርት ነው
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 5/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 15/2011/ READ IN PDF)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ባለችበት አዳክሞ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ አልያም ከውስጥ በማተራመስ ለመከፋፈል የሚካሄደውን ሤራ በድልድይነት በማስተሳሰር(ኔትወርኪንግ) እና ከአፅራረ ቤተ ክርስቲያን የሚጎርፈውን ከፍተኛ ፈንድ በማሠራጨት እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት አሰግድ ሣህሉ በድብደባ ሙከራ ወንጀል ክስ ተመሥርቶበት፣ መጥሪያ ወጥቶበት እየተፈለገ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት የመናፍቁ አሰግድ ሣህሉ የድብደባ ሙከራ ወንጀል የተፈጸመው ዛሬ፣ ኅዳር 5 ቀን 2004 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ላይ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ቅጽር ውስጥ ነው፡፡

መ/ር ዘመድኩን
ሰዓቱ መ/ር ዘመድኩን በቀለ "ማራኪ" ለተሰኘ መጽሔት በሰጠው ቃለ ምልልስ እና ዲያቆን ደስታ ጌታሁን "የሰባኪው ሕጸጽ" በተሰኘ መጽሐፋቸው "በሃይማኖት ጉዳይ ያልተማረ፣ ማይም እና ተሐድሶ ነው በሚል ሞራሌን ነክተዋል፤ ከሕዝብ ልብ እንድወጣ አድርገውኛል" በሚል በበጋሻው ደሳለኝ የተመሠረተባቸው ክስ ተቋርጦ መዝገቡ ለፍትሕ ሚ/ር እንዲመለስ ትንት ሚ/ር ዴኤታው ብርሃኑ ጸጋዬ ለቦሌ ፍትሕ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ መሠረት የወትሮውን ዐቃቤ ሕግ ሙሉ ግደይን ተክተው በተገኙት ሌላ ዐቃቤ ሕግ ፊት ይኸው ትእዛዝ በዳኛው ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡ ክሱ ተቋርጦ፣ መዝገቡ ተዘግቶ እንዲመለስ ምክንያት የሆነው መ/ር ዘመድኩንና ዲያቆን ደስታ ጌታሁን የተከሰሱበት ጉዳይ የሃይማኖት በመሆኑ እና ቅዱስ ሲኖዶስም ግል ተበዳዩንና መሰሎቹን ሃይማኖት በጥልቀት መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት በጥናት ላይ በመሆኑ ሃይማኖታዊ በሆነ መልኩ በቤተ ክህነቱ በኩል እንዲታይ በማለት እንደሆነ ተገልጧል፡፡

በፍትሕ ሚ/ሩ ማሳሰቢያ መሠረት ክሱ መቋረጡ እና መዝገቡ መዘጋቱ በዳኛው ተገልጾ ችሎት መልስ ከሆነ በኋላ ባለጉዳዮችና የችሎቱ ተከታታዮች በመውጣት ላይ ነበሩ፤ በዚህ መሀል ከችሎቱ በራፍ ውጭ በዳኞች ቢሮ ደጃፍ ከመ/ር ዘመድኩን ጋ ወደፊት ቀድመው በማለፍ ላይ የነበሩትን ዲያቆን ደስታ ጌታሁንን አንድ እጅ ከኋላ ማጅራታቸውን ጨምድዶ በመያዝ፣ "በዚህ ብታመልጠን በሌላ እናገሃለን፤ አታመልጠንም!!" እያለ አንገታቸውን ይወዘውዛቸዋል - አሰግድ ሣህሉ ነበር፡፡

እርሳቸውም በሕግ አምላክ በሚል ግለሰቡን ሥርዐት እንዲያደርግ በማስጠንቀቅና ጉዳዩን ለዳኛው በማስረዳት ዳግመኛ በችሎቱ እንዲሠየሙ ሆኗል፤ ዲ.ን ደስታና አሰግድ ወደ ችሎቱ ተያይዘው ገብተው በዳኛው ፊት ከቆሙ በኋላ ዲ.ን ደስታ የተፈጠረውን ነገር ለዳኛው አስረድተዋል፡፡ በሁኔታው ከፍተኛ ብስጭት የገባቸው ዳኛው ተደናግጦ ወደቆመው አሰግድ ፊታቸውን አቅንተው፣ የድብደባ ሙከራው የተፈጸመው በችሎቱ አዳራሽ ውስጥ ቢሆን ኖሮ እዚያው ውሳኔ ይሰጡ እንደነበር በመግለጽ ድርጊቱ ከችሎቱ ውጭ የተፈጸመ በመሆኑ ዲያቆን ደስታ ምስክሮቻቸውን አሰምተው ክስ መመሥረት እንደሚችሉ ገልጸውላቸዋል፡፡

በዚህም መሠረት በግብረ ገብ የለሹ አሰግድ ሣህሉ ላይ ክስ ተመሥርቶ፣ ምስክር ተሰምቶ የክስ መጥሪያ ወጥቶበት እየተፈለገ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ መጥሪያው አሰግድ ሣህሉ ለኅዳር ሰባት ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት እንዲቀርብ የሚያዝዝ ነው ተብሏል፡፡

አሰግድ
ከአሰግድ ጋ አብረው በችሎቱ የነበሩት ታሪኩ አበራ፣ ሀብታሙ ሽብሩ እና ናትናኤል የተባሉት ሲሆኑ የአሰግድ አነጋገር ሕገ ወጡ ቡድን እነ መ/ር ዘመድኩንን በተጨማሪ ክሶች በማሸማቀቅ ከፀረ ፕሮቴንታንታዊ-ተሐድሶ እንቅስቃሴያቸው ለመግታት እንደ አንዳንዶቹም ምኞት ከሀገር ወጥቶ እንዲሰደድ ለማስገደድ ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም መዝሙር ቤቱ እና መኖሪያ ቤቱ በፖሊስ የተበረበረውና ንብረቶቹ የተወሰዱበት መ/ር ዘመድኩን በቀለ ከዛሬው ችሎት መጠናቀቅ በኋላ ከ4፡30 - 6፡40 ድረስ በፖሊስ ተይዞ በቅጽሩ ውስጥ ከእስረኞች ጋር ከቆየ በኋላ ችሎቱን ለመከታተል ተገኝተው ከነበሩት የፀረ-ተሐድሶ ሰባክያንና ዘማርያን ጥምረት አባላት መካከል በዘማሪ ልዑል ሰገድ ጌታቸው(ቋንቋዬ ነሽ) የመኪና ሊቢሬ በቂ ዋስትና በቅረቡ የዋስ መብቱ ተጠብቆ ሊፈታ ችሏል፡፡

የሕገ ወጦቹ በተከታታይ ክሶች የማስጨነቅ ስልት - ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘና በፀረ - ተሐድሶ አጀንዳ ዙሪያ መሠረተ ሰፊ የምእመኑን ንቅናቄ እየፈጠሩ ከሚገኙት ሥራዎች ግንባር ቀደም ሆነው በ"አርማጌዶን ቪሲዲ" ምክንያት ጨርሶ በመጠላታቸውና ከቤተ ክርስቲያን መድረኮች ላይ ምእመኑ እያነቀ በማውረድ(‹‹በሐዲስ ኪዳን ታቦት አያስፈልግም›› ባዩን ጥላሁን አበበን በገዳመ ኢየሱስ፣ አሸናፊ ገብረ ማርያምን በቀራንዮ መድኃኔዓለም እንዲሁም የሕገ ወጦቹ ‹መዝሙር› እና ‹ስብከት› በማንኛውም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ እንዳይሰማ በመከላከል) የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ መተግበር በመጀመሩ ሳቢያ የተፈጠረ ቀቢጸ ተስፋ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ይህንኑ ቀቢጸ ተስፋ የሚያመለክት ንግግር ባለፈው ሳምንት ታትመው ከወጡት መጽሔቶች በአንዱ ላይ በተስተናገደው ቃለ ምልልስ ላይ በከፋ መልኩ ተስተውሏል፡፡ ቃለ ምልልሱን የሰጠው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ‹የሰላም አርበኛ› በማድረግ ግልጽ ተመጻዳቂነቱን በተለያዩ መጽሔቶች ላይ በሚሰጣቸው ቃለ ምልልሶች እያሳየ የሚገኘው ተሐድሶው አሰግድ ሣህሉ ነው፡፡

ተሐድሶው (በአንዳንዶች ዘንድ አቶ ፓስተር ይባላል) አሰግድ ሣህሉ በዚህ ቃለ ምልልሱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሐምሌ 2 ቀን 1990 ዓ.ም በአምስት የተሐድሶ ኑፋ አራማጆች ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ "ሕጋዊ ያልሆነ ፍትሕ፤ ትክክለኛ ዳኝነት ያልታየበት" በማለት አጣጥሎታል - ሕግን በሚያገለግለው የፍትሕ አካል ፊት ለድብድብ የሚጋበዘው አሰግድ ያለ አቅሙና ያለ ብቃቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን ለመተቸት መሞከሩ የለየለት ተመጻዳቂ እና በወቅቱ በሲኖዶሱ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ግለሰቦች (እነ ‹አባ› ዮናስ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ) ያለውን የጠበቀ የዓላማ አንድነት ፍንተው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን አስመልክቶ በመንፈሳዊ ኮሌጆች መምህራንና ደቀ መዛሙርት ቅጥር፣ ደባና የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ባስተላለፈበት በዚህ ታሪካዊ ዓመት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሚመረቀው አሰግድ ተመጻዳቂነቱን በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ዋዜማ በመንበረ ፓትርያክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቅጽር የፀረ ፕሮቴስታንታዊ - ተሐድሶ ትዕይንት በማሳየት ሲኖዶ ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም በሙሉ ድም ያለ ልዩነት ያስተላለፈውን ውሳኔ አስቀድሞ ለመጠየቅ የተሰበሰቡትን ሰላማዊ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ "የሰንበት ተማሪ ያልሆኑ፣ ስለ ሃይማኖታቸው በቂ ዕውቀት የሌላቸው፣ ምንም ዐይነት የሃይማኖት ዝንባሌ የሌላቸው፤ ኦ አባ እያሉ የዘመሩት መዝሙር ዐመፅ እና ድራማ እንጂ መዝሙር አይደለም" በማለት ነቅፏል፡፡

በወቅቱ በሕገ ወጦቹ በኩል የእንቀስቃሴው አስተባባሪ እንደነበር በቃለ ምልልሱ የተናገረው ግብዙ አሰግድ እርሱ ግን፣ "ማንም የነሱን (የተቃዋሚዎቹን) መንገድ እንዳይከተል ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲናገር እንደነበር" በመወሽከት ዋሽቷል፡፡ ለደጀ ሰላም የደረሰው ፊልም ግን አሰግድ ሣህሉ አንዱን የሰንበት ተማሪ ሲያመናጭቅና በቃሪያ ጥፊ ካልመታሁ እያለ ሲገለገል የሚያሳይ ነው፡፡
ማርሻል አርትስ ሥልጠና (ባለ ጥቁር ቀበቶ) እንደ ሆነ የሚነገርለት አሰግድ በቃለ ምልልሱ ላይ "እንደእነርሱ መደባደብም ይቻላል" ባለው መሠረት ነገሮች በሕግ እና በሕግ ብቻ በሚዳኙበት ችሎት ዛሬ ለጠብ ሲጋበዝ፣ ዛቻውን ማስፈራሪያውን ሲያንጎደጉደው አገኘነው፤ በዚህ ድርጊቱም ለእነ መ/ር ዘመድኩንና ዲያቆን ደስታ ያሰበው ክስ ወደራሱ ተገለበጠበት/ ዞረበት፤ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነትም በዚሁ የአሰግድ ቃለ ምልልስ እና ትዝታው ሳሙኤል ሰንበት ተማሪዎቹን ‹‹ደም አፍሳሾች›› በማለት በተመሳሳይ መልኩ ለማራኪ መጽሔት በሰጠው ቃለ ምልልስ ክስ ለመመሥረት እያሰቡበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የአሰግድን ቃለ ምልልስ፣ የፍትሕ ሚኒስቴርን ደብዳቤ እና የ1990 ዓ.ም የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ላይ ውሳኔ አስተላልፎበት የነበረውን ቃለ ጉባኤ ቀጥለው (HERE) መመልከት ይችላሉ።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

13 comments:

Anonymous said...

The given links in the following statements DON'T FUNCTION:

1) ተሐድሶው (በአንዳንዶች ዘንድ አቶ ፓስተር ይባላል) አሰግድ ሣህሉ በዚህ ቃለ ምልልሱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሐምሌ 2 ቀን 1990 ዓ.ም በአምስት የተሐድሶ ኑፋቁ አራማጆች ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ "ሕጋዊ ያልሆነ ፍትሕ" በማለት አጣጥሎታል

2) የአሰግድን ቃለ ምልልስ፣ የሚኒስትር ዴኤታውን ደብዳቤ እና የ1990 ዓ.ም የቅ/ሲኖዶስን ምልዓተ ጉባኤን ቃል መመልከት (HERE) ይችላሉ።

Please rectify them for proper use.
Thanks

Anonymous said...

mafetehawe kahege belay kahona ega mafeteha enefalege

Anonymous said...

Look at their strategies

1. Every day they are changing decisions and make themselves known.
One time Abune paulos, Ejigayehu ,sereke, Begashaw, sahilu, and so on.
2.They seemed to preach they know the God of word well and seemed to preach Jesus but see all what they are doing.

3.They try to show support to each other want to come to the public, whatever they are trying will not deceive Orthodox people including those are insulting.
4. They consider themselves "modern" and want to leave all orthodox beliefs. see all people,
is that what was preached by Jesus christ?

They use the church as a source of money to buy nice cars, have villas ,eat meat and beer using their deceiving voices as was written in the bible.

a person can not be under money and be with God at the same time.

I wish they sit and learn, we do not want to hear their preaching, even we do not want them to be our agenda , we have so many spiritual
job to do. They are wasting time and want to be important and want to be known.

We but do no need modernization in sprituality'Egziabher zarem neagem hulem ayilewetim'. It is not because we do not know how to be dressed well, eat well, seem spiritual, seem knowledgeable and mislead some innocent people.

But this is against God's word. You all will be judged and be thrown in the ocean due to misleading people.

If any body want to be powerful be under all people and polite.


5. Guys this is 21st century. Globalization is becoming sure and you (all mentioned above and others which are helping those)are becoming weapons for demolishing the churches identity set by God and by our real spiritual fathers
by earthly belief.

6.By the way, in this world there is a psychology that to put supporters together not to be alone and survive , they are doing the same.

7. If you have doubts about orthodox ask who knows or read true books.Do not extrapolate and assume it is wrong without much evidence with your no knowledge and no spirituality. how on earth they could see it. To see small things we need microscope so to see spiritual things we need spiritual eyes .

8. God be with you and help you to know yourself and do not insult the brave orthodox people.

Our believe is to be saved both by belief and good job.Do not make the church a place for empty dance, chifera,chibcheba for youself.


9. Beloved orthodox, always remember, know about how our leader Jesus challenged hasawi mesihan, and also how our spiritual fathers
deal with that and how our fathers are struggling now(ewnetegna menekosat). They will see all of us from heaven as Alazar and newi has been looking each other.


10.Go to the bible and read how it is in the end of the world

pray for each other

Anonymous said...

የእናንተ ያንድ አቅጣጫ ብቻ አጻጻፍ እጅግ ሚዛን የጎደለውና ፍጹም ጭፍን የሆነ ወገናዊነት መሆኑ በዳበሳ ይታወቃልና እባካችሁ ለሃገር ሰላምና ብልጽግና ብላችሁ ለእውነት ብቻ ቁሙ:: ማንም ቢሆን ሲሳሳት ስህተቱን በግልጽ መንገር መልካምና ለሕዝብ የሚጠቅመውን ሃሳብ ደግሞ እሰየው ማለቱ ብስለት ነውና ሁልጊዜ እራሳችሁን ብቻ ለወግን አሳቢዎች የሆናችሁ በማስመሰል በሬ ወለድ ዜናችሁን ብታስተካክሉት አንባቢ ታገኛላችሁ:: ወደዳችሁ ጠላችሁም እውነት በጨለማ አይሸነፍምና ከእግዚአብሔር ጋር አትጣሉ ትደቃላችሁና:
እንሆ ይህ የእግዚአብሔር ቃል አስደንግጦ ቢመልሳችሁ

የሐዋ/ሥራ 5:38-39

ቅን ፈራጁ እግዚአብሔር ለዚች ቤ/ክ ይፍርድላት!!
ጅራፉን ይዞ አንድ ቀን በነጋዴዎች ላይ እንደሚግለጥ አምነዋለሁ!!!

Anonymous said...

የእናንተ ያንድ አቅጣጫ ብቻ ላልከው፡- ለመሆኑ
በሀሰት ቤተ ክርስቲያንን ለመበጥበጥ ስለተነሱት ስለነ በጋሻው የውዳሴ ዜማ እንዲዘመርላቸው ነው የፈለከው፡፡ ያንንማ የበግ ለምድ ለብሰው በነበሩበት ሰዓት አግኝተውታል፡፡ ሰው አይደለም ያንን ስማቸውን የገፈፋቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ምክንያቱም ለምስጋና በተፈጠረላቸው አንደበታቸው በእግዚአብሔር አውደምህረት ላይ ቆመው አምላካችንን ዘለፍት፡ ከፋፈሉት ስሙንም አትጥሩት አሉን፡፡ ቀስ በቀስም የሚያሸማቅቅ ስድባቸውን ለያንዳንዳችን ይወረውሩልን ጀመር፡፡ በዚህ ሁሉ ድርጊት ከማዘንና ከመጸለይ ውጭ ምንም አልተናገርንም፡፡ እግዚአብሄር ግን ቀናተኛ ነውና ማንነታቸውን በራሳቸው አንደበት እስኪመሰክሩ ጠብቆ እርቃናቸውን አስቀራቸው፡፡ እግዚአብሔር የጣለውን እንግዲህ ማን ያነሳዋል፡፡ ይህን ማድረግ ማንም የሰው ልጅ ስልጣን የለውም፡፡ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ፡፡ እነሱ ግን በዘመኑ ባሉ ባለስልጣናት እየተመኩ ነው፡፡ የግለሰብ ቤት በመበርበርና ሴቶችና ሕጻናትን በማስፈራራት፡፡
በመቸረሻ ልነግርህ የምፈልገው የቅዱሱን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ተሸፍነው ከፊታቸው ባስቀደሙት የዳቢሎስ ግብራቸው ክርስቲያኑን ለመናጠቅ የተዘጋጁ የፍጻሜው ዘመን ተዋንያን መሆናቸውን ነው፡፡ አንተም በግዜ ሳይመሽብህ ከዚህ ጎራ ልትለይ ይገባሀል፡፡
በእግዚአብሔር ተመካ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡

Anonymous said...

Dear Anonymous..ምንው አንደዚ ኣብከነከነህ ጅራፉ ኣንተነም ሳያገኝህ ኣልቀረም መሰለኝ

Anonymous said...

Hi dejeselam
Hope everything is going well for you guys i really apreciate your relentles work to feed us with uptodate news of our church and i am sure tens of thounsends of milions orthodox christian open this page to learn something. please don't let ur focus on two individuals they are just orthodox belivers as a web page owners and christian and also as a responsible people feed your readers with the word of God. i say it again leave alone this two individuals to our fatheres be it Begashaw or zemedikun what ever they have in between them can be dealt there where the two guys live leave alone breaking news it is not even important for us readers, and i am sure you all know about it. ,my advice please if you guys really care about our church and let us see the fruit of holyspirit peace, forgiveness,politeness, love....etc
thease two guys are 2/all orthodox believers this news doesn't build any one.

Anonymous said...

ውሸታሞች ናችሁ!! የውሸት ቋቶች!!! አታፍሩም? እፈሩ እንጂ!!!

ALEME said...

<>
አንዳንዴ መጻፍ ስለቻልን ብቻ የማይረባ አስተያት መስጠት አይገባም ከላይ አስተያየት የሰጡት ወዳጄ ለመሆኑ ስንታአይነት አቅጣጫ ነው የሚያውቁት ፣እምነቶት ምን ይሆ ? እስቲ እርሶይ ስሩትና ሂሳቡን ይንገሩን
ባራ ሴግምት ተዋህዶ አይመስሉኝም ስለዜህ ለኛ ተዉልን ይሁሉ ነገር እየተበሸ ያለዉ የማይመለከታቸው
ሰዎች ጣልቃ እየገቡ ስለሆነ ዝም ቢሉ ይመረጣል . ደጀሰላም በውነቱ እመሰግናለሁኝ ምንያህል እንደማደንቃችሁ
ልገልጽ እፈልጋለሁ በርቱ ፤
እግዚአብሔር ይርዳን

Anonymous said...

enettagasena enetsaley eskazarea meemanone badebek banofake ttore yawagotena yadamotte yebaletale.anetama doctter nahe manefasawe lega madehanete enedettehone yamaratahe leanetama......................

Anonymous said...

kawedase kaneto yadenelen wanedemochachenen.asetayayate latehadeso yamesatoten enezanelachawe.ename bakerebo nawe yagabage kanaso ando nabareko

ዝምታው said...

ምነው ደጀሰላሞች ድምጻችሁ ጠፋ ስለጀርመን ጉዳይ እንመለስበታለን ብላችሁ በዚያው ቀልጣችሁቀራችሁ ነው እናንተምጋር ማስፈራሪያውና ዛቻው ደረሳችሁ ለማንኛውም ያልተነካካ የተቡካካ ብዙ ነገር ይኖራልና በረጅሙእጃችሁ ብቅበሉና ፈታትሹን እኛም መረጃ በመስጠት እንተባበራለን!

ዝምታው said...

ምነው ደጀሰላሞች ድምጻችሁጠፋ የጀርመንን ጉዳይ ነካክታችሁ እንመለስበታለን ብላችሁ ቀልጣችሁቀራችሁ ነው ወይስ እናንተም ጋር ማስፈራራቱና ዛቻው ደረሰ እባካችሁ ያልተነካካ የተቡካካ ብዙ ጉድ አለና በረጅሙ እጃችሁ ብቅበሉና እንደጉግል ጎልጉሉት መረጃ በመስጠት እኛም ያቅማችችንን እናግዛለን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)