November 5, 2011

ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን የሚጻረሩ ዝውውሮች እና ሹመቶች እያካሄዱ ነው

  • ከሓላፊነታቸው በተነሡት በአባ ሰቀረ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ምትክ በቅርቡ ከአሜሪካ ተመልሰው የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አባ ኅሩይ መሸሻ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዋና ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ ተመልክቷል፤ አባ ኅሩይ በፓትርያርኩ ከቀረቡት የጵጵስና ሹመት ተስፈኞች ዝርዝር ውስጥ እንደነበሩበት ምንጮች እየገለጹ ነው።
  • ውጤታማው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ ያለሲኖዶሱ ዕውቅና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ መሆናቸው ተገልጧል፤
  • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳውያን ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ያለሲኖዶሱ ውሳኔ ከሓላፊነታቸው ተነሥተው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 24/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 4/2011, READ IN PDF)፦ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 15 መሠረት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ እየመረጠ የመሾም ሥልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን ሥልጣንና ተግባር የሚዘረዝረው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ክፍል (አንቀጽ 30 ንኡስ አንቀጽ 9) ደግሞ የምክትል ሥራ አስኪያጁን አቀራረብ ሲያስረዳ “ሥልጣነ ክህነት፣ በቂ የትምህርት ደረጃና ችሎታ ያላቸውን ሦስት ሰዎች ለም/ሥራ አስኪያጅነት በእጩነት ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቦ ያስመርጣል፤ በምርጫውም ቅዱስ ሲኖዶስ ሲስማማበት የተመረጠው ሰው በፓትርያርኩ ይሾማል፤ የሚጻፍለት ደብዳቤም በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚፈረም ሆኖ በፓትርያርኩ ፈቃድ እንደተሾመ ይገለጻል” ይላል፡፡


ዛሬ የተገለጸው የጠ/ቤ/ክ የመንፈሳውያን ጉዳዮች ዘርፍ ም/ዋ/ሥራ አስኪያጅ ከሓላፊነታቸው የተነሡበት ይሁን የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በመ/ፓ/ም/ዋ/ሥራ አስኪያጅነት መሾም በቋሚ ሲኖዶስ ቀርበው ስለ መመረጣቸው አልተረጋገጠም፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አባላት ስምምነትም አልተገለጸበትም፤ በተቃራኒው ብዙዎቹ የምልአተ ጉባኤው አባላት ለዚህ መረጃ እንግዳ እንደሆኑ የጉባኤው ምንጮች አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም በሕገ ወጥ ሰባክያንና ዘማርያን የሚደረገውን ስምሪት በመግታት፣ በጉቦ እና በዝምድና የሚደረገውን ቅጥር፣ ዝውውር እና ምደባ በማስቀረት፤ አጥቢያዎች በገንዘብ እና ንብረት ቁጥጥር ረገድ ከሙስና እና ከዘረፋ የጸዳ አካሄድ የሚከተሉበትን አሠራር በመዘርጋት የአጥቢያዎቹ ይሁን የሀገረ ስብከቱ ገቢ እንዲሻሻል ብሎም በ2003 የበጀት ዓመት በእርሳቸው አገላለጽ “ከሌሎች ምንጮች የተገኘው ገቢ ሳይቆጠር ከቆመ ሙዳዬ ምጽዋት ብቻ” ለመንበረ ፓትርያርኩ 35/65 በመቶ ብር 24 ሚሊዮን ፈሰስ ያስገቡ ውጤታማ ሥራ አስኪያጅ እንደሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡ ንቡረ እዱን በግትርነት የሚከሱ ወገኖች በመርሕ የተገደበው አካሄዳቸው ለዓመታት በሀ/ስብከቱ ውስጥ ከተዘረጋው የጥቅመኞች ኔትወርክ እና አልፎም ከሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር እንዳላስማማቸው ነው የሚናገሩት፡፡

ይህም በቀደመው የዋና ዋና ዜና ጥቆማችን ላይ እንዳመለከትነው በአንዳንድ ሁኔታዎች የአቋም መለሳለስ አሳይተዋል የተባሉት እና ከሁሉም መግባባት የሚሹት ሊቀ ጳጳስ መልቀቂያ እንዲያቀርቡ ሳይገፋፋቸው እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡ የምልአተ ጉባኤው ምንጮች እንደሚያስረዱት በሥራ አስኪያጁ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መዘዋወር ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ በሚገምቱት ምክንያት አዲስ አበባ ሀ/ስብከትን ደርበው የያዙት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ያቀርቡታል የተባለው መልቀቂያ መታለፉን አስረድተዋል፡፡

በ30ው የመ/ፓ/አጠ/ሰ/መ/ጉ ስብሰባ ላይ ሥራ አስኪያጁ የሀ/ስብከቱን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ሊረዱት በማይችሉት ሁኔታ ሪፖርቱን እስከሚያቀርቡበት ዋዜማ ምሽት ድረስ በአንዳንድ አድባራት እና ገዳማት አለቆች አድማ እየተጎነጎነባቸው እንደሆነ በማስታወቅ ካህናት እና መምህራን “እጃችንን በመሰብሰብ” (ከሙስናው ለማለት ይመስላል) ለሚያስተምሯቸው ምእመናን ምሳሌያዊ መሪ መሆን እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ይህን በሐዘን የተሞላ ንግግራቸውን የሚያስታውሱ ሌሎች ታዛቢዎች፣ ለውጤታማው ሥራ አስኪያጅ መነሣት ከሙዳዬ ምጽዋት ቆጠራ ርቀው ታዛቢ እንዲሆኑ የተደረጉት የአንዳንድ አድባራት አለቆች፣ ፀሐፊዎችና ቁጥጥሮች ከእነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ጋር የሸረቡት ሤራ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 35 መሠረት ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የሁሉም አህጉረ ስብከት ማዕከል የሆነው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው ልዩ ደንብ እና መመሪያ እንደሚተዳደር፣ በቅዱስ ሲኖዶስ በተሾመ ሊቀ ጳጳስ፣ ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስ እንደሚመራ የተገለጸ ቢሆንም “የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት” በሚል የሚሾሙትም ሊቃነ ጳጳሳት “የፓትርያርኩ ረዳት /ሊቀ/ጳጳስ” እንደሚባሉ ይታወቃል፡፡  

በሌላ በኩል በሃይማኖት ሕጸጽ የተጠረጠሩት አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሆነው መሾማቸው እየተነገረ ነው፤ አሁን የመምሪያው ዋና ሓላፊ ሆነው የሚሠሩት መጋቤ ሥርዓት ዳንኤል ወልደ ገሪማ ወዴት እንደተዘዋወሩ አልተገለጸም፤ ቀደም ሲል አባ ሰረቀ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ የተጻፈላቸው ደብዳቤ በገጠመው ተቃውሞ ውድቅ ተደርጓል ተብሏል።

ዛሬ በተሰማው ሹመት አባ ሰረቀ በአቅማቸው ይሁን በመሠረታዊ ዓላማቸው ይቅርና ለዚህ ግዙፍና ውስብስብ ግብ ፍጻሜ ሊበቁ ራሳቸውን አደራጅተው በየአህጉረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የሚገኙትን ሰንበት ት/ቤቶች እንኳን አስተባብሮ ለመምራት እንደማይመጥኑ ስድስት ዓመት በተግባር ተፈትነው የወደቁበት ተመክሯቸው ምስክር ነው።

የቤተ ክርስቲያኒቱን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ኮሌጆች) እና የአብነት ትምህርት ቤቶች በበላይነት የማስተባበር ሥልጣን የተሰጠው ይህ መምሪያ በአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ከነበረበት በባሰ ሁኔታ እንዲዳከም ህልውናውም እንዲዘነጋ ከተፈረደባቸው መዋቅሮች አንዱ ስለመሆኑ የመምሪያው የቀድሞ ሓላፊዎች በምሬት እንደሚናገሩ ተዘግቧል፡፡

በ30ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የጋራ ውሳኔ ላይ እንደተመለከተው በተያዘው የበጀት ዓመት መምሪያው፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎት የሚያበቃ የዕውቀት ምንጭ የሆኑት የአብነት ት/ቤቶች ትምህርት ከዘመናዊው ጋር ተቀናጅቶ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሥርዐተ ትምህርት እንዲያዘጋጅ፤ ለአብነት ት/ቤቶች መምህራንና ደቀ መዛሙርት የሚደረገው ድጋፍና ክብካቤ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ ሦስቱ ኮሌጆች በበጀት ራሳቸውን ለማጠናከር በሚያደርጉት አበረታች ጥረት እንዲተጉና በሥነ ምግባር የታነጹ ደቀ መዛሙርትን ኮትኩተው እንዲያስመርቁ ብርቱ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ” አሳስቦ ነበር፡፡ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤም የመምሪያው በጀት ተሻሽሎ እንዲሠራለት ትእዛዝ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አባ ኅሩይ መሸሻ
በተያያዘ ዜና ከሓላፊነታቸው በተነሡት በአባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ምትክ በቅርቡ ከአሜሪካ ተመልሰው በመምጣት የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አባ ኅሩይ መሸሻ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ ተመልክቷል፤ አባ ኅሩይ በፓትርያርኩ ከቀረቡት የጵጵስና ሹመት ተስፈኞች ዝርዝር ውስጥ እንደነበሩበት ምንጮች እየገለጹ ነው። (ይህንን ጉዳይ ወደፊት በጥልቀት እንመለስበታለን)::

ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2004 ዓ.ም 13 ቀኑን ያስቆጠረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ቃለ ጉባኤዎቹን እየተናበበ በአንዳንድ አጀንዳዎች ላይ የተወሰነውና በጽሑፍ የሰፈረው ሲያወዛግብ በዋለበት ሁኔታ፣ ፓትርያርኩ ሰሞኑን ውድቅ የተደረጉባቸውን አጀንዳዎቻቸውን እና ሐሳቦቻቸውን በዐይነት ለመመለስ በሚያስመስል አኳኋን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚፃረሩትን እኒህን ዝውውሮች እና ሹመቶች እንዲከናወኑ ማድረጋቸው በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ እና ጉዳዩን ሲከታተሉ በሰነበቱት አካላት ዘንድ አነጋጋሪና ግራ አጋቢ ሆኗል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

30 comments:

Anonymous said...

ene emilew yekahinat ena menekosat shumet kegedam alneber ende minew aba pawlos keamerica adergut mistiru tehadison masfafat new

Anonymous said...

Woy guuuud, Lemehonu papasatu men honewal. I think yemetawen fetena mekuakuam yechalu ayimeslegnim. Enesu yewahan selehonu kehuala yalewen neger mayet alchalum....

Anonymous said...

UHH!!!!!!!. Ere Minew yibeqan!! Manim yihun manim Ahun bebetekristianachin yemeta hulu engafete. Tikit Abatochi gam chigir kale woushan wesha yemalete gize meselegne. Hulum yalagitalu. Ebakachihu le betekristanchi enimut!!!

Egiziabeher betkristanchini yitebeq!

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቸ : ዛሬ አንድ ቀጥተኛ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እና እስኪ መልሱልኝ:: እስካሁን በዌብሳይቶቻችን የሚጻፈውንና የሚነገረውን እየሰማሁ ነው:: ታዲያ አንድ ጥያቄ ግን አለኝ ያልተመለሰ:: የምችለውን ያክል ጥረት አደረግሁ እንደሚወራው እኔም ለመሆን ግን ትክክለኛ መረጃ ልቤ ፈለገ:: ጥያቄየ በእነ በጋሻውና በግብረአበሮቹ ላይ ነው::
እኔ እንደተረዳሁት:
1. በጋሻው ስድብ ይችላል:: የፈለገውን ነገር በድፍረት ይናገራል:: የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዓይነት ያነጋገር ለዛ ይጎድለዋል:: ግን መናፍቅ ያስባለው ነገር ምንድ ነው? መናፍቅ ለማለት እኮ ኑፋቄ ሲናገር መስማት አለብን:: ስላሴ አትበሉ ያለውን ስብከት አድምጨዋለሁ:: በእርግጥ ይህን ተመልክቶ በጋሻው መናፍቅ ነው ያለ ሰው ንስሃ ይግባ:: ሰውን በበደሉ መክሰው ተገቢ ነው ያለበደሉ መናገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ከተጠያቂነት አያስመልጥም:: በብሉይ ኪዳን ኢየሱስ እንዲህ አደረገ እንደማንለው ሁሉ በሃዲስ ኪዳን ጌታ በስጋው ወራት ያደረገውንም ስላሴ እንዲህ አደረጉ ማለት ለአረዳድ የሚያመች አይደለም:: እዚህ ላይ እንደተረዳነው መጠን እንጂ ልጁ ኑፋቄ ነው ያስተላለፈው የሚል ሰው ቢያስብበት እላለሁ:: አሁንም ግን ኑፋቄውን ማድመጥ እፈልጋለሁ:: በትክክል ለማመን እንዲያስችለኝ::
2. አባ ፋኑኤልንም እንዲሁ እንደተመለከትኋቸው ሰውየው ሃይለኝነት ይታይባቸዋል:: ከሌላኛው ወገን ተቃውሞ ስለደረሰባቸው ከነበጋሻው ጋር ወግነዋል:: ታዲያ መናፍቁ ጳጳስ ለማለት ያስበቃን ነገር ምን ይሆን? ምን ብለው ኑፋቄ አስተማሩ እስኪ ስሞት ጥቀሱልኝ::
3. የምንወዳቸው ዘማሪያን አሸናፊ ምርትነሽ ትዝታውና ቅድስትስ ኑፋቄቸው ምን ላይ ይኆን እባካችሁ እስኪ ተናገሩና እንስማ:: ኑፋቄቸውን ሳናውቅ መናፍቅ ማለት ይከብዳል:: ማናት ዘማሪት ዘርፌ ወደ አሜሪካ ስላቀናች ድምጽዋ ቢጠፋም: እርስዋስ ለምን ቀረች ወይስ እርስዋ የለችበትም::

እንደ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ሲደርስ ማየት አልፈልግም:: ኑፋቄ ያለበት ሰው ቤተ ክርስቲያንን ሲቆጣጠር ማየት አሳፋሪና አስጠይ ነገር ነው:: ሆኖም ግን ቤተ ክርስቲያንን ለመጥቀም ብለን ሰዎችን አንጉዳ:: በጋሻው ሃይለኛ ንግግሩ እንጂ ኑፋቄው አልታይ ያለኝ እውነት ፈላጊው ኦርቶዶክሳዊ የተዋህዶ ልጅ ነኝ::

Anonymous said...

Geta hoy ,Betekirstianachinin tarekat.......

Anonymous said...

Ebakachihu wogenoche atinawotu. Egziabher egna endinibereta lihon yichilal endezih zim yalew. Minim fetena bayinor ecko egna enitegnalen. Silezih negerun hulu lebego eyut enji betam besimet atitsafu. Silemefitihe bicha new mewoyayet yalebin enji, beminet wust tesfa mekuret ena merebesh asifelagi ayidelem. Tiglachinin gin atenkiren meketel alebin. Besimet gin ayihun. Hulum neger betselot keberetan ena kelib kerotin yistekakelal. Abiziten enitseliy, anirebesh, kegna belay lebetu yemiasibew amlak ecko kegna gara new. yegnan birtat ena tiret bicha new ersu yemifeligew. Kawassawoch timihirt wusedu. Belekiso ena betiret Amlak eredachew. Enantenim yirdachihu. Berrtu...

Anonymous said...

ስለ በጋሻውና ግብረ አበሮቹ የጠየከው እነዚህን ቪድዮዎች ሁሉንም ክፍሎች እስከ መጨረሻው ብትመለከት ትልቅ ግንዛቤ ታገኛለህ
ለሁሉም እግዚአብሔር ይርዳህ

http://www.youtube.com/watch?v=VoHHFOrfzBk&feature=related

http://www.youtube.com/watch?v=3lyuwlLgqdw&feature=related

http://www.youtube.com/watch?v=yl7k9xKArOg&feature=related

Anonymous said...

'Aba' sereke, ehiiiiiii.... befit mahibere kidusanin endiyafersu neber madakemim alchalum, egziabherin mashenef yemichil manim yelemina, ahun degmo abinet t/betoch lay memedeb kesir yalewun meseretun binberizew kirnchafum yaw yihonal bemil gimit yimeslal, aba pawlos ebakwotin ayidkemu kemayigafutn eyetegafu new egziabher betun ayzegam, sanay yamenin egnan,yeliju yeserg bet tadamiwoch egnan, yenatun yekal kidan lijoch egnan yemitil asalifom yemiseten yimeslwotalini????? mechem bihon ethiopia ejochuan wode egziabher tizeregalech(esuam tewahdo nat, anditua) manim matef aychilim bedemu yegezan getachinina amlakachin Eyesus christos eskimeta, bizu yedekemachihu hulu atilfu, derg'm dejuan lemezgat bertito neber egziabher gin besu mekabir lay yibelt atsenat enam tetenkeku, yeberetachihu simeslachihu mekabrachu eyetemase endehone asbu, zewer bilachihum gudguadun eyut, niseha gibu yegziabher mengist kerbalechina.(mechem ketach wedelay... minyidereg tenagari tefana new eko)

Anonymous said...

Min Yishalal Min Yibejal Layenorebet Hagere Sibket Fanuel Yifajal. Ere gud new eko Yetewahedo Lijoch. Ene gin yemelew Yekidus Sinodos Gubae Pateriarku becha new endea yemisebesebut?????????????????????

Anonymous said...

kelay tiyake yanorsh ehite hoy melsun lemeglets sefi ejig sefi geletsa yasfeligewal yihem aymechim silezih andin neger lingerish

Yam sile tehadiso betam mawok alebish, tehadiso malet min malet new yemilewun, esu sigebash ene begashawun eza wusit tagegnachewalesh, yezane ahaaa leka ...... tiyalesh

Tehadso malet batekalay hizbu sayneka yene haimanot new eyale eyasebe wustun gin bado maregina yelela haimanot sew mareg sihon sirachewum betam erekik behone melku new yemiyakenawunut eg.
enatachin mariam atamalidim sayhon simuan balemetrat enditiresa mareg(melaektinim, kidusaninim endihu)
mezmur be piyano yihun sayhon ezaw yegnan meslo gin yepiyano wubet endinorewuna behualam hizbun asresto mekelakel.

bicha zirziru ejig sefi sihon misalewun alkush anchi teyiki, wutetu gin betechristian hintsawa endale hono wusituan ye protestant lemareg protestantoch begenzeb digoma eyareguachew betalak capital yeminkesakesu afrash hailoch nachew sirachewum betekihnet new yalew, esti tekorkuari kehonsh tseliy enam teteratari hugni hulu beg aydelem yebeg koda yelebese sint wusha ale meselesh, ewnetu gin wusit lewusit besifat bitawekim lehizbu gilts alhonem yihem be egziabher fekad yihonal eskeza tseliy, egziabher yasben.

Anonymous said...

Dear Dejselam,

Thank you for your valuable information. I want to say a few words about Aba Hiruy, the new head of the Department of Sunday school. I know Aba Hiruy for quite long time. He is one of the father who can work with youth and Sunday schools.As a human being he might have his own weakness, but we can't question his belief. I have seen him, so many times fighting with other to protect the teaching of One orthodox church. There might be a pressure from very top, but trust me he can work very well with motivated and devoted youths. All Sunday school member take a chance to work with him with good spirit. I think this is a great chance to Aba Hiruy, to serve his church. I hope he will not give away the golden chance he got, to his own personal dignity, instead he will use it to contribute his best to the church and leave his name in the heart of millions.
Dear Dejselam, please encourage Aba Hiruy, to flow the foot steps of his fathers and grand fathers who passed us the teaching and the culture of the church, not blame him as he is just starting a new phase. Let us hope the best and see what will happen in near future.

Anonymous said...

Yetiyake balebet, atfru just tehadso malet min malet endehone tiyiku enam ye awassa church min endederesebet teyiku yanin degmo ene begashaw nachew yakenawenut esun yeminegro sew kagegnu melsu yigebawotal lelaw gin endih badebabay yemineger aydelem enji bizu balku egzer mistrun yigletlwo.

Anonymous said...

@Anonymous
November 4, 2011 7:46 PM

ስላሴ እንዲህ አደረጉ ማለት ለአረዳድ የሚያመች አይደለም


ስላሴ የሚለው ብቻ ነው የተሰማህ ማለት ነው? እግዚአብሔር አትበሉ ያለውስ::
እግዚአብሔርም በሐዲስ ኪዳን የለም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የስላሴም ምስጢር የተገለጠው በሐዲስ ኪዳን ነው:: አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ:: አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው? እግዚአብሔር ነው:: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: ሰውየው ያለው ስላሴ አትበሉ እግዚአብሔር አትበሉ ኢየሱስ በሉ ነው::
ካልሰማህ ድጋሚ ስማው:: ያለው ትክክል ነው ልዩነት አላቸው አንድ ነኝ ከሱ ጋር ካልክ ሌላ ነገር ነው:: አላለም ማለት ግን ጆሮህን እንድትመረምር ያስመክርሃል:: አባ ፋኑኤል እሱን መደገፋቸው ያስጠይቃቸዋል::

Desalew said...

wy yAbune paoulos eidmae merizem!!!!....

Anonymous said...

I think our behavior seems to reject every leader. If so, what our destiny?

Anonymous said...

Pls before you naming someone check his profile? Where did he came from? What does he did in life? What is background says? What is his main goal? Just to tell you the truth he issues not the right person for that passion? Ask the people is San Jose California.

tazabi said...

It's all sad. Those who work are transferred so that they will make way for "belategna".

I wasn't sure whether Aba Sereke would really be removed from his current post. But, who's he replaced with? I don't know anything about the new aba but for me, anyone returning from America and is given some sort of shumet is "guilty until proven otherwise".

Lemanim sayhon lebete kirstiyan yemiweginu yadrigachew.

Anonymous said...

አባ ኅሩይ መቼ ወደ ኢትዮጵያ ገቡ? ከአባ ሰረቀ በብዙው ይሻላሉ በዚህም አገር ሲኖሩ በእናት ቤተ ክርስቲያን ስር ነበሩ:: በስመ አሜሪካ ሁሉም እንደ አባ ሰረቀ ሲያምታቱ አድርገን መገመት የለብንም:: የአቅማቸውን ያክል ለቤተ ክርስቲያን ሰርተዋል:: የእናት ቤተ ክርስቲያንን በመደገፍም ቀና አመለካከት ነበራቸው::

Fker yebaltal said...

ENAM ESTY ZARY AND NEGAR LENAGER BMENEM NAGER KHLATUM YANESKOG NAGE AND NAGER LENAGER BERGTAG NAT KHLOME FEKER YEBLETAL BZH NAGER HLATENEM ENSMAMALEN MEKNYATOM AMLAKTENM SELAFKR NEW WADZH MEDER YAMETAW TADEYA MATY NEW FEKER YAMENSABEKAW ERA EBAKTU WANDEMOTY EHTOHY SELA FEKER ENAWRA MEKNYATOM YFEKR AMELAKEN NEW YMENAMELKEW LEBTKRSYANTHEN ZELALEMAW ERK LMAMETATE ENTALEY ZAWTER ENTEGA AMELKATEN YERDAN KATEFAW YEKRTA

Anonymous said...

selana Bagashawe yattayakawe malesone erasachawe protesttantwache yenagerohale.anamen belane nawe enjea enaso eko derom yenagerone nabara

Anonymous said...

EMA BEREHANE ATELAYEN

Orthodoxawi said...

Ye Enih sewu (ye Aba Paulos) edme merzem lemin yihon?

Anonymous said...

Yene wondem yet neberk eske ahune. Negereh yematawke temeslaleh. Tiyakehe gin ye enusu wendim mehonehin yamelekital. lemehonu lelwen teteh Selasie Atbelu yemilew bich aybeqahim. As the other bloger expained it Selasie means Abe, Wolde, Menfes Qedus new. Eyesus Egziabeher new. Selaseim yenesu meteria new. Tadiaya yehinen satawk new min aderege yemitilew? yeh eko hulunim yafersal malet new yal Selasie menun nornew? Degmo Bezu anbeb. Setefeleg bich aydelem menager. Yeqazehim temeslaleh. Tebelo tebelo yalekeletin amtiteh wede huwal tegotetenaleh. Meteyekih tiru bihonem yebeg lemde yelebesk teyaqi temeslegnale. Ahun yetiyaqe gize aydelem ye qorate wusane enji. Menalbat beewnet yalaweqeh kehonk degmo ayzoh berta anbeb, teweyay teyqe, tesatef, betekristian hid,qeduseneten feleg lekurban yabqah. Yetenagrkut enkifat Ayhunebeh yekir belgn.

Okay now Sinodos made many wrong decisions at this time, Aba Poulos did the same thing all the time Are they like two sides of a coin? If the truth is very clear to all that both decision are wrong and we accept that wrong stuff are we not liable to their wrong doing and to the rest of the population additional disaster? Nebiyu Esayas; knew something that was done wrong inside the church and kept quite as per the Holy Bible telling and GOD punished him and the other person. Don't you think we are doing the same thing in this age? Therefore, we need to object to the wrong decision made. We should not be like Eweren Ewer bimeraw abro gedel. Haqegn abatoch we need your honest openion on these. Say something to avoid more confusion.

Egziabeger libachewen yadendenew ena meqrezachewen yewesedebachew Patriarch Abune Poulos, Abune Fanuel, Aba Sereque and the rest of their followers are openly doing wrong on the church. That is it. They must go. Enie zim alelem for real yaskidachew ayaskidachew felagoten yasakalegn zend final firdun le Hayalu Egziabiher Esataleh. Egeziabeheren mefrat,Metsom, Metsley, Niseha megbat, Mequreb yeqetil elalehu.

Anonymous said...

what then??? good question. We should tell our leader to take note that things are going to be beyond their ability. They are all do not take seriously; be it synod or patriarch, they are working against the security of our church. Our church had been challenged so many times in history, but it has never been by its leaders. Let us all pray and die defending our church.I will repeat, pray and die defending our church! But this is not an easy. Let us stand up. Say some thing to our church leaders. They should stop or leave the church alone. I know that so many people do not like saying this. Ok, Did they(few leaders)understood our silence as respect? Rather abuse the respect we gave them. WAAAAAA!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

let us stop blaming persons. Focus to the source of problem. church leaders. Shame on our elder church leaders! We are in the 21 century. It is really disgusting to hear so many unprecedented earthly act.

May God help us fighting you!!!!!!!

Anonymous said...

We need Ethiopian Orthodox church revolution pls every one do their part we are planing to peace demonstration in city of Addis Ababa so in order to do this we have TO OPEN NEW FACEBOOK ACCOUT WITH DEFERENT "NAME" WHICH FOR OUR SAFTY AND SECURITY. here is plane how we make this happen. 1 everyone have post the on their real Facebook and share with friends. 2 meet personally friends, fathers, mothers sisters brothers in the neighbor and city. 3 use phone calls if you can to every Orthodox believers. we no longer site and watch while this father kill our church. it going to be hard but what we do. our father fight for this church until their death, so let keep our fathers dignity, faith,love for their believe, my mom always tells me when it comes to my believe not scared. i want everyone to join us tools you have make it happen. people die for political theory how about we we die for our believe. lets remember what he have done for us on the cross. site down and listen to ur self relieve it. what is left for us without orthodox let us make history not to happen in our church again. let us use "prayer" sigidet

Anonymous said...

This is really a good thing, I will day for my religion. I'm really happy by the above opinion and please let us know what we are suppose to do in dejeselam first, then we will share it for our facebook.

Anonymous said...

Congra Aba Hiruy, we will missed you here in san jose,ca but it's good serving there , they need you and it's the right time ,right place

Anonymous said...

"LET US ALL PRAY AND DIE DEFENDING OUR CHURCH."

Anonymous said...

ዘሩፋኤ ል........... ከላይ አንድ አስተያየት አንብቤ የነበጋሻውን ቃለ ምልልስ ወይንም ጭውውት ተመለከትኩ::በጣም ያስቃል::ደረጄ እና ሀብቴ መስለው ታዩኝ ::ትዝታው ጠያቂ በጋሻው ተጠያቂ :: አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ፣ አለ ያገሬ ሰው:: አሁን ማን ያምነናል ብላችሁ ነው ;የምትቀባጥሩት ብዙ ለማስተባበል ሞከራችሁ::ወይ ሌላ ጠያቂ ብታዘጋጁ ጥሩ ነበር::በጣም ያስታውቅባችኃል::በከንቱ ደከማችሁ:: ልብ ይስጣ ችሁ::አሜን,,

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)