November 3, 2011

የአባ ሰረቀ ድረ ገጽ ደጀ ሰላምን በድጋሚ ከሰሰ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 23/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 3/2011/ PDF)፦ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳደረጉት፣ ከሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊነታቸው በመጨረሻ የወረዱት አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል “ብሎጎች (ጡመራዎች) ለወንጌል ወይስ ለወንጀል” ሲሉ ደጀ ሰላምን “አባ ሰላማ” ከተባለው የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ ጡመራ መድረክ ጋር ደብለው ከስሰዋል። አባ ሰረቀ ለነ“አባ ሰላማ” የመዝገብ ቤት ደብዳቤዎችን እና ወረቀቶችን “ስካን” እያደረጉ እንደሚልኩ እያወቅን “አባ ሰላማ”ን የከሰሱ ለመምሰል መሞከራቸው ፈገግ አድርጎናል። ደጀ ሰላምን ደግሞ “ለዘመናት በቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችና በሊቃውንት ከፍተኛ የስም ማትፋት ሲፈጥር የቆየውና ያለው ደጀ ሰላም የተሰኘው የጡመራ መድረክ … ቅዱስ ሲኖዶስ ተሳሳተ ወይም ቀኖና ጣሰ” አለ ሲል ከስሷል። ሁሉም እንደሚያውቀው የተሳሳተ ያልነው ከመስመር የወጣውን የአባ ሰረቀን ቡድን፣ ቀኖና ጣሰ ያልነው ደግሞ አቡነ ፋኑኤልን ነው። በሌላ ጊዜ፣ በተሻለ አማርኛ፣ የተሻለ ክስ ይዘው እስኪመለሱ ለአባ ሰረቀ ከዚህ በላይ ቦታና ጊዜ ለማጥፋት ቦታም ጊዜም የለንም።
አዲዮስ አባ ሰረቀ።

21 comments:

Anonymous said...

i like deyos aba serqe kkkkkkkkkkkkk thanks deje selam

IMHO said...

I'm sorry but I didn't like your usage of "adios ..." It makes you more of a sensationalist tabloid rather than a news source.

Try not to mix your emotions with your reporting.

just my view.

Anonymous said...

"It is better to remain silent and be thought a fool than to open one's mouth and remove all doubt." 
— Abraham Lincoln

Anonymous said...

God is watching us.

Anonymous said...

ሃሃሃሃሃሃሃ......... አዲዎስ አባ ሰረቀ....ሃሃሃሃሃሃ....

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

ከወደቁ ወዲያ መፈራገጥ ለመሰበር እንጂ ለመጠገን አይሆንም። አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በከንቱ ከመፍጨርጨር ንስሐ ቢገቡ መልካም ነዉ። ግድ የልዎትም የበደሉአትን ቤተ ክርስቲያን ለመካስ ጥፋትን አምኖ ንስሓ መግባት ብቸኛዉ መፍትኼ ነዉ። አሊያም ደግሞ በቃ አለ አይደል ወደ ዘመድዎት ጎራ መሄድ ነዉ።
ኑፋቄ ሲጸነስ ተሐድሶ ሲወለድ ሙሉ ወንጌል፣መካነ ኢየሱስ ፣ሲያድግ እግዚአብሔርን ክዶ ዓለማዊ መሆን። የእርሶ ዕጣ ፈንታ ከዚህ አይዘልም። ብዕሩ ዘ-አትላንታ

Anonymous said...

Adeyos SEREKE.kkkkkkkkkkkkkk

Anonymous said...

Dear DS Do you have another news about the situation. What is going on? Are these people invaded the EOTC in the USA? if so it is upsetting.

Desalew said...

"ADIOS"is the spanish word.the meaninig good bye.I like it!!.ADIOS "ABA"Serqe!!!!!

Anonymous said...

"Hode siyawk doro mata".
Aba serqe until that days come to be Ato/paster Serqe

God bless Ethiopia!

bob said...

guys keep aba serki's kiber do not say serke .

Anonymous said...

የተመጠነና የተመረጠ ቋንቋ።

ሁሉም እንደሚያውቀው የተሳሳተ ያልነው ከመስመር የወጣውን የአባ ሰረቀን ቡድን፣ ቀኖና ጣሰ ያልነው ደግሞ አቡነ ፋኑኤልን ነው።በሌላ ጊዜ፣ በተሻለ አማርኛ፣ የተሻለ ክስ ይዘው እስኪመለሱ ለአባ ሰረቀ ከዚህ በላይ ቦታና ጊዜ ለማጥፋት ቦታም ጊዜም የለንም።
አዲዮስ አባ ሰረቀ።

Anonymous said...

Ere Gobez eninesa! Wererun eko enezih tehadesowoch

Anonymous said...

Adeyos Aba sereke keahun behwala menem menferaget aysfelegem tesebsebeh tekemet.

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቸ : ዛሬ አንድ ቀጥተኛ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እና እስኪ መልሱልኝ:: እስካሁን በዌብሳይቶቻችን የሚጻፈውንና የሚነገረውን እየሰማሁ ነው:: ታዲያ አንድ ጥያቄ ግን አለኝ ያልተመለሰ:: የምችለውን ያክል ጥረት አደረግሁ እንደሚወራው እኔም ለመሆን ግን ትክክለኛ መረጃ ልቤ ፈለገ:: ጥያቄየ በእነ በጋሻውና በግብረአበሮቹ ላይ ነው::
እኔ እንደተረዳሁት:
1. በጋሻው ስድብ ይችላል:: የፈለገውን ነገር በድፍረት ይናገራል:: የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዓይነት ያነጋገር ለዛ ይጎድለዋል:: ግን መናፍቅ ያስባለው ነገር ምንድ ነው? መናፍቅ ለማለት እኮ ኑፋቄ ሲናገር መስማት አለብን:: ስላሴ አትበሉ ያለውን ስብከት አድምጨዋለሁ:: በእርግጥ ይህን ተመልክቶ በጋሻው መናፍቅ ነው ያለ ሰው ንስሃ ይግባ:: ሰውን በበደሉ መክሰው ተገቢ ነው ያለበደሉ መናገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ከተጠያቂነት አያስመልጥም:: በብሉይ ኪዳን ኢየሱስ እንዲህ አደረገ እንደማንለው ሁሉ በሃዲስ ኪዳን ጌታ በስጋው ወራት ያደረገውንም ስላሴ እንዲህ አደረጉ ማለት ለአረዳድ የሚያመች አይደለም:: እዚህ ላይ እንደተረዳነው መጠን እንጂ ልጁ ኑፋቄ ነው ያስተላለፈው የሚል ሰው ቢያስብበት እላለሁ:: አሁንም ግን ኑፋቄውን ማድመጥ እፈልጋለሁ:: በትክክል ለማመን እንዲያስችለኝ::
2. አባ ፋኑኤልንም እንዲሁ እንደተመለከትኋቸው ሰውየው ሃይለኝነት ይታይባቸዋል:: ከሌላኛው ወገን ተቃውሞ ስለደረሰባቸው ከነበጋሻው ጋር ወግነዋል:: ታዲያ መናፍቁ ጳጳስ ለማለት ያስበቃን ነገር ምን ይሆን? ምን ብለው ኑፋቄ አስተማሩ እስኪ ስሞት ጥቀሱልኝ::
3. የምንወዳቸው ዘማሪያን አሸናፊ ምርትነሽ ትዝታውና ቅድስትስ ኑፋቄቸው ምን ላይ ይኆን እባካችሁ እስኪ ተናገሩና እንስማ:: ኑፋቄቸውን ሳናውቅ መናፍቅ ማለት ይከብዳል:: ማናት ዘማሪት ዘርፌ ወደ አሜሪካ ስላቀናች ድምጽዋ ቢጠፋም: እርስዋስ ለምን ቀረች ወይስ እርስዋ የለችበትም::

እንደ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ሲደርስ ማየት አልፈልግም:: ኑፋቄ ያለበት ሰው ቤተ ክርስቲያንን ሲቆጣጠር ማየት አሳፋሪና አስጠይ ነገር ነው:: ሆኖም ግን ቤተ ክርስቲያንን ለመጥቀም ብለን ሰዎችን አንጉዳ:: በጋሻው ሃይለኛ ንግግሩ እንጂ ኑፋቄው አልታይ ያለኝ እውነት ፈላጊው ኦርቶዶክሳዊ የተዋህዶ ልጅ ነኝ::

Anonymous said...

hooo guud eko new belachehu belacheu ABA SELAMA teadeso blog new alachehu? Mafereyawoch gudachehun awechi new enji leka alemaweke new enji eskahun aba selama yemilew blog menorun bawek noro yihen dejeselam zor beye aleshenabetem neber menafik teadeso enanetew ds,or mk nachehu ayenachehun kifetuuuu

Anonymous said...

ebakoten gezawoten laneseha adergote.yasazanote makarewote nage

Anonymous said...

ADEYOS ABUNA FANUEL yekatelale

Anonymous said...

dear anonymousoch
nufakew yaltayeh asteyayet sechi minalbat endalkew silemtwedachew lemin tenekubigne kalhone nufakeyachew adebabay yeweta new,kelgebah cdwochun tewsehim bihon degmeh eyachew!!! lelagnaw anonymous aba selamn blog kefelek ezih lemin metah??? midre menafiq eski ewnetn keyazachihu hulum yemisetachihun ende dejeselam awetut?? hideh eziaw teqelakel betechirstianachinen asalfen ansetim!!!!!

yared said...

my neme is decon yared From canada. i always read Dejeselam but, i gave up now ;the reson is ;
1. i think you provide one side information
2. it seems personal fight
3. i found many things are not true information
so p/s provide information as an ortodox twhedo cheldernce manner. all i hered is that person....this person , all nigatives whay?
thank you

Anonymous said...

"ADIOS"is the spanish word.the meaninig good bye.I like it!!.
ADIOS Serqe!!!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)