November 2, 2011

የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት እና ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔውን እንዲያጤን ጠየቁ

 • TO READ THE ORIGINAL LETTER SENT TO THE HOLY SYNOD, CLICK HERE.
 • TO READ Deje Selam REPORT, click HERE IN PDF.
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 22/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 2/2011/ )፦ የቅዱስ ሲዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት 21/2004 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ለዲሲ እና ለካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነት የተመደቡትን የአቡነ ፋኑኤል ሹመት የቀሰቀሰውን የምዕመናንን ቁጣ ተከትሎ በሀ/ስብከቱ  ሥር የሚገኙ  11 አብያተ ክርስቲያናትም አስቸኳይ ስብሰባ አድርገው ድምጻቸውን አሰምተዋል፤ ለቅዱስ ሲኖዶስም ባለ 5 ገጽ መልእክት አስተላልፈዋል። “በሰሜን አሜሪካ አሁን የሚታየው ችግር ተወሳስቦ ተወሳስቦ አሁን ያለበት ደረጃ የደረሰው ከመጀመሪያው ጀምሮ  የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የማስጠበቅ ተግባር ተጠናክሮ ባለመሰራቱና በወቅቱ መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚገቡ  አስተዳደራዊ ችግሮች ሳይፈቱ በመቅረታቸው ነው” ያለው መግለጫው

ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ  ግን የተሻለ  የአህጉረ ስብከት አደረጃጀት እየታየ በመምጣቱና የቤተክርስቲያን አንድነት እንደሚያስፈልግ በመረዳት  በሀገረ ስብከት ሥር የሚካተቱ አብያተ ክርስቲያናትም ቁጥር” እየጨመረ መምጣቱን አስታውሶ “በየትኛውም መልኩ ቢሆን  በአሜሪካ ደረጃ የቤተክርስቲያንን መዋቅር ባልጠበቀ መልኩ የሚደረግ እንቅስቃሴ ቤተክርስቲያንን የመለያየት እና ለተለያዩ ከቤተክርስቲያን ውጭ ለሆኑ አመለካከቶችና አጀንዳዎች  ቤተክርስቲያንን አሳልፎ የሚሰጥና የቤተክርስቲያንን ክብር” የሚቀንስ መሆኑን አውስቷል።

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት በብዕ አቡነ አብርሃም በርካታ ተግባራት እንዳከናወኑ፣ በዋሽንግተን ዲሲ መንበረ ጵጵስና ማቋቋማቸውን፤ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት መባረካቸውን፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ የምእመናን ቁጥር መጨመሩን፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ያለው ግንዛቤ ማደጉን መግለጫው አውስቶ በብዕነታቸው የተጀመረውን መልካም ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቢደረግ ለቤተ ክርስቲያን ያለው ተጠሜታ ከፍተኛ መሆኑን የሀ/ስብከቱ አብያተ ክርስቲያናት እና ካህናት አስምረውበታል

በተለይም አሁን በቅ/ሲኖዶስ ተሹመዋል የተባሉ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ እንዲሔዱ መወሰኑ ሀ/ስብከቱ የጀመረውን አገልግሎት በብዙ ርምጃ ወደኋላ የሚጎትት መሆኑን አውስተው በሚከተሉት ምክንያቶች ማለትም፦
 • ከዚህ በፊት ያገለገሉበትና  አሁንም እየመጡ የሚያርፉበትን የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል በቤተክርስቲያን መዋቅር  ማስገባት ያልቻሉ ፤ቤተክርስቲያኑ በሀገረ ስብከት ስር ያልተካተተና ፓትርያርኩም ሆነ የብጹዓን አባቶች ስም የማይነሳ በመሆኑ
 • በሀገር ውስጥ በተለይም በሲዳሞ ሀገረ ስብከት የፈጸሙት አስተዳደራዊ ችግር በሰፊው እዚህ በሚኖሩ ምእመናን  የተሰማና ያሳዘነ ከመሆኑ በተጨማሪ እስካሁንም መፍትሔ ያላገኘ በመሆኑ
 • ከዚህ በፊት በአሜሪካን እንዲያገለግሉ ቢመደቡም  በነበራቸው  ችግር ምክንያት  ከካህናትና ከምእመናን  ባላቸው አለመግባባት የተነሳ በቅዱስ ውሳኔ መነሳታቸው  የሚታወስ በመሆኑ፦
 • በሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ለቅዱስ ሲኖዶስ እንደተገለጸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት  በመተላለፍ በአሜሪካ  የፈጸሙት ተግባር የታወቀና  በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም  እስከመወቀስ የደረሱበት ጉዳይ በመሆኑ
የእርሳቸው አሜሪካን መቆጣጠር አደገኛ መሆኑን፣ “በአሜሪካ የቤተክርስቲያንን አንድነት ለማጠናከር ሊኖራቸው የሚችለው ሚና በጣም አስቸጋሪ” እንደሚሆን አበክረው ገልጸዋል። ስለዚህም “ይህ ውሳኔ ተግባራዊ ይደረግ ከተባለ ግን የቤተክርስቲያን አንድነት የበለጠ የሚናጋ፤ የቤተ ክርስቲያን እና አህጉረ ስብከት መዋቅር የሚዳከምና ሕዝበ ክርስቲያኑንም ለአባቶች ላይ ላቸውን ክብር የሚቀንስ እና ምእመናንንም ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ” እንደሚፈጠር መግለጫው አትቷል።
በመጨረሻም “የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት እና ሰላም ለመጠበቅ ሲባልና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በአሜሪካ የሚገኙ ካህናትና ምእመናንን ድምጽ መስማት አባታዊ ኃላፊነት  እንዳለባችሁ በማመን  የሚከተሉት ሶስት አቤቱታ እናቀርባለን
1.      በቅድሚያ አሜሪካ ያለውን ችግር የሚያጠና  ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ  በመወከል  እንዲጠና እንዲደረግና ከሁሉም አቅጣጫ ያለሁን ሁኔታ እንዲመለከት እና ተደረሰውን ጥናት መነሻ በማድረግ ያሉትን አህጉረ ስብከት ለማጠናከር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ቢደረግ
2.     ይህ ጥናት እስከሚደረግ ድረስ  አሁን የተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምደባ በድጋሚ እንዲታይ እና ቢያንስ ለቀጣዩ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዲዘገይ ቢደረግ
3.     የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ አብርሃም በአካል ተገኝተው ዝርዝር ሁኔታውን እስኪያስረዱ ድረስ ጊዜ እንዲሰጣቸው፣” ሲል መግለጫው ይደመድማል።  

የመልእክቱ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ሠፍሯል።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።


++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
ቀን --- ጥቅምት 21 2004 ዓ. ም

በአሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር  ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት
 ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ የቀረበ  አስቸኳይ አቤቱታ

በስብሰባው የተገኙ ሀገረ ስብከቱ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ዝርዝር
 1. ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ባልቲሞር
 2.  ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለ ይማኖት አሌክሳንደሪያ
 3.   መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
 4.   ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ሉዊቪል
 5.  አንቀጸ ምህረት በዓታ ለማርያም ሻርለት
 6.  መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አትላንታ
 7.  ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወአቡነ አረጋዊ
 8. ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ  ታምፓ
 9.  ደብረ ዕንቁ ቅድስት ማርያም ሜምፊስ
 10.  ደብረ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ካንሳስ ሲቲ
 11.   ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ኦክላሆማ ሲቲ
 12.  የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን  ቨርጂኒያ
 13.  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ቨርጂኒያ ቢች

አቤቱታ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ  አገልግሎት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ለቤተክርስቲያኒቱ እድገት መሰናክል የሆኑ በርካታ ፈተናዎች ያጋጠሙ ሲሆን አብዛኛዎች እነዚህ ፈተናዎች በእምነቱ ተከታይ በሆኑ  አንዳንድ ሰዎች መሆኑ ደግሞ ልዩ ያደርገዋል። በአሜሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ፤ ካህናትና ምእመናን አንድነት ቢኖራቸው ኖሮ ዛሬ በኢትዮጵያ  ውስጥ ያሉ ገዳማትን አብነት ት/ቤቶችንና የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን በመርዳት ደረጃ  የሚኖራቸው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ይሆን ነበር ፤ ነገር ግን መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚገቡ የተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች በወቅቱ መፍትሔ ሊሰጣቸው ስላልተቻለ አሁን ለምንገኝበት የተወሳሰበ ሁኔታ ላይ ተደርሷል። 
በሰሜን አሜሪካ አሁን የሚታየው ችግር ተወሳስቦ አሁን ያለበት ደረጃ የደረሰው ከመጀመሪያው ጀምሮ  የቤተክርስቲያን መዋቅር የማስጠበቅ ተግባር ተጠናክሮ ባለመሰራቱና በወቅቱ መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚገቡ  አስተዳደራዊ ችግሮች  ሳይፈቱ በመቅረታቸው ነው። ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ  ግን የተሻለ  የአህጉረ ስብከት አደረጃጀት እየታየ በመምጣቱና የቤተክርስቲያን አንድነት እንደሚያስፈልግ በመረዳት  በሀገረ ስብከት ሥር የሚካተቱ አብያተ ክርስቲያናትም ቁጥር እየጨመሩ መጥቷል።  ከዚህም በመነሳት በአሁኑ ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የተጠናከረ የአብያተ ክርስቲያናት  አንድነት እየታየ የመጣ ሲሆን ምእመናን ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት ያላቸው ግንዛቤ አድጓል ።
አሁን በአሜሪካ  እየተደረገ ያለውን የቤተክርስቲያንን መዋቅር የማስጠበቅ ጉዳይ ከቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ ደጋፍ የሚያስፈልገው ሲሆን  በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ  የቤተክርስቲያንን መዋቅር የማስጠበቅ ጉዳይ መሆኑንም ማስገንዘብ እንወዳለን ።  በየትኛውም መልኩ ቢሆን  በአሜሪካ ደረጃ የቤተክርስቲያንን መዋቅር ባልጠበቀ መልኩ የሚደረግ እንቅስቃሴ ቤተክርስቲያንን የመለያየት እና ለተለያዩ ከቤተክርስቲያን ውጭ ለሆኑ አመለካከቶችና አጀንዳዎች  ቤተክርስቲያንን አሳልፎ የሚሰጥና የቤተክርስቲያንን ክብር የሚቀንስ መሆኑ የታወቀ ነው።
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በብጹዕ አቡነ አብርሃም በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን  በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ መንበረ ጵጵስና ተቋቁሟል፤ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተከፍተዋል፤ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡ የምእመናን ቁጥር ጨምሯል ፤ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት ያለው ግንዛቤ አድጓል። ይህንን ስንመለከት በብጹዕነታቸው  የተጀመረውን መልካም ተግባር   ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቢደረግ  ለቤተክርስቲያን ያለው ተጠሜታ ከፍተኛ ነው ብለን እናምናለን ።
 ከዚህ በፊት ለቅዱስ ሲኖዶስ መስከረም 30 2004 ዓ.ም  ቀን በተጻፈ ደበዳቤ ላይ እንደተገለጸው  የሀገረ ስብከቱን እንቅስቃሴ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ቅዱስ ሲኖዶስ  የበለጠ ግንዛቤ እዳገኘ እናምናለን። ይሁን እንጂ በትላንት እለት ጥቅምት 21 ቀን 2004 ዓ.ም  ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው  ውሳኔ በአሜሪካ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ብጹዓን አባቶች ተነስተው ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል መመደባቸውን ከተለያዩ ምንጮች ሰምተናል። ምንም እንኳን  ቅዱስ ሲኖዶስ ብጹዓን አባቶችን የማንሳትና የመመደብ ሙሉ ሥልጣን ቢኖረውም  እኛም እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነት  የተሰማንን ሐዘን ለቅዱስ ሲኖዶስ ስናቀርብ በቀና ልቦና ቅዱስ ሲኖዶስ ይመለከተዋል  ብለን በማመን ሲሆን  በተጨማሪም በዚሁ በአሜሪካ የምንኖር  እንደመሆናችን በሀገሩ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ፤ የአብያተ ክርስቲያናትን ችግርና የምእመናንን ስሜት በተመለከተ የተሻለ መረጃ ለቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት ማቅረብ እንችላለን ብለን በማመን ያለንን ሀሳብ ለመግለጽ ተገደናል።  
በእኛ አመለካከት ለቤተክርስቲያን አንድነት ለማጠናከር ጥሩ የሚሆነው በሰሜን አሜሪካ የሚመደቡ አባቶች ከዚህ በፊት በሰሜን አሜሪካ በተከሰቱ ችግሮች ያልተሳተፉ እና በበሰለ ሁኔታ ነገሮችን   ተመልክተው ውሳኔ የሚሰጡ፤ ካህናትና ምእመናንን የማግባባት መንፈስ ያላቸው ፤ በአባትነት ፍቅር ሰዎች መያዝ የሚችሉ ቢሆኑ መፍትሔ ለማምጣትና አንድነቱን ለማጠናከር አስተዋጽዖ ያደርጋል ብለን እናምናለን።
የሰማነው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማለትም ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ሁለት አህጉረ ስብከት  ተመድበው እንዲያገለግሉ  የተላለፈው  ውሳኔ በምን ሚዛን ታይቶ ውሳኔ ላይ እንደ ተደረሰ  ግራ ቢያጋባንም የተመደቡትን አባት (ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል)  በተመለከተ ግን የሚከተሉትን ነጥቦች ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ማስታወስ እንወዳለን፦
·        ከዚህ በፊት ያገለገሉበትና  አሁንም እየመጡ የሚያርፉበትን የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል በቤተክርስቲያን መዋቅር  ማስገባት ያልቻሉ ፤ቤተክርስቲያኑ በሀገረ ስብከት ስር ያልተካተተና ፓትርያርኩም ሆነ የብጹዓን አባቶች ስም የማይነሳ በመሆኑ
·        በሀገር ውስጥ በተለይም በሲዳሞ ሀገረ ስብከት የፈጸሙት አስተዳደራዊ ችግር በሰፊው እዚህ በሚኖሩ ምእመናን  የተሰማና ያሳዘነ ከመሆኑ በተጨማሪ እስካሁንም መፍትሔ ያላገኘ በመሆኑ፡
·        ከዚህ በፊት በአሜሪካን እንዲያገለግሉ ቢመደቡም  በነበራቸው  ችግር ምክንያት  ከካህናትና ከምእመናን  ባላቸው አለመግባባት የተነሳ በቅዱስ ውሳኔ መነሳታቸው  የሚታወስ በመሆኑ፦
·        በሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ለቅዱስ ሲኖዶስ እንደተገለጸው የቤተክርስቲያንን ሥርዓት  በመተላለፍ በአሜሪካ  የፈጸሙትን ተግባር የታወቀና  በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም  እስከመወቀስ የደረሱበት ጉዳይ በመሆኑ
በአጠቃላይ ከላይ በተጠቀሱትና ከሌሎችም ጉዳዮች በመነሳት በእኛ ግንዛቤ በአሜሪካ የቤተክርስቲያንን አንድነት ለማጠናከር ሊኖራቸው የሚችለው ሚና በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል ብለን እናምናለን። ይህ ውሳኔ ተግባራዊ ይደረግ ከተባለ ግን የቤተክርስቲያን አንድነት የበለጠ የሚናጋ ፤ የቤተክርስቲያን እና አህጉረ ስብከት መዋቅር የሚዳከምና ሕዝበ ክርስቲያኑንም  ለአባቶች ላይ አላቸውን ክብር የሚቀንስና እና ምእመናንንም ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ይፈጠራል ብለን እንሰጋለን ።
ለቅዱስ ሲኖዶስ በሀገረ ስብከቱ ሥር የምንገኝ አብያተ ክርስቲያናት በሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ ጉባኤ የደረስንበትን ውሳኔ በቃለ ጉባኤ በተደገፈ ሁኔታ ያቀረብነው ሪፖርት ሚዛን ሳይደፋ ከመዋቅር ውጭ የሆኑ አብያተክርስቲያናት ያቀረቡት ከሥርዓት የወጣ አቤቱታ ተደማጭነት አግኝቶ ይህ ውሳኔ  የሚያበቃ ውሳኔ መወሰኑ ከፍተኛ ሐዘን ፈጥሮብናል ።
የቤተክርስቲያንን  ውሳኔ ተግባራዊ  ለማደረግ  ሙሉ ኃላፊነት  ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ  የሚያስተላልፈው ውሳኔ  የምእመናንን ሐዘን የሚያስታግስ፤  አገልጋዮችን የሚያበታታ እና የቤተክርስቲያንን መዋቅር ለመስጠበቅ ከፍተኛ መስዋዕትነት ለከፈሉ ካህናትና ምእመናን መጽናኛ ይሆናል ብለን በማመን የሚከተለውን አቤቱታ በእግዚአብሐር ስም አቅርበናል ።
የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት እና ሰላም ለመጠበቅ ሲባልና  የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በአሜሪካ የሚገኙ ካህናትና ምእመናንን ድምጽ መስማት አባታዊ ኃላፊነት  እንዳለባችሁ በማመን  የሚከተሉት ሶስት አቤቱታ እናቀርባለን
4.    በቅድሚያ አሜሪካ ያለውን ችግር የሚያጠና  ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ  በመወከል  እንዲጠና እንዲደረግና ከሁሉም አቅጣጫ ያለሁን ሁኔታ እንዲመለከት እና ተደረሰውን ጥናት መነሻ በማድረግ ያሉትን አህጉረ ስብከት ለማጠናከር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ቢደረግ
5.    ይህ ጥናት እስከሚደረግ ድረስ  አሁን የተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምደባ በድጋሚ እንዲታይ እና ቢያንስ ለቀጣዩ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዲዘገይ ቢደረግ
6.    የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ አብርሃም በአካል ተገኝተው ዝርዝር ሁኔታውን እስኪያስረዱ ድረስ ጊዜ እንዲሰጣቸው  

በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን ።29 comments:

Mahlet (እሚ) said...

መዘ 125 - 1
በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።


Now we will wait and see what the Fathers will decide.And if push comes to shove we shall all still remain invincible in faith and be prepared to protect our Church and the newly sprang unity and oneness which we have strived to see for so long but which the Devil relentlessly tries to destroy.

Be still

Amaleke Teklehaimanot cher neger yaseman

Anonymous said...

besime silase ahadu amilak amen

BEHULUM AKITACHA YALEW NEGER LEBETEKIRISTIYAN BEMASEB YETEDEREGE AYIMESILIM AHUN EIWUNET ABUNE FANUEL AMERICA YALECHIWUN BETEKIRISITIYAN ANID ADIRIGEW YEMASITEDADER BIKAT ALACHEW TEBILO NEW YETELAKUT? YIGERIMAL

ANY WAY YEKIDUS SINODOS WUSANE SILEHONE BESEGA MEKEBELU YETESHALE YIMESILENAL YEABUNE ABIRIHAM AKAHEDIM ALAMARENIM BETIFOZO BIZAT AMERICAN ALEKIM YALU YIMESILALU YIHENIN KASEBU KEDEM BILEW MASITEKAKEL YEMIGEBACHEWUN NEGER MASITEKAKEL NEBEREBACHEW EISACHEWUM BIHONU HIZIBUN WEDEANIDINET KEMETIRAT YILIK YEMALEYAYET SIRA NEW EIYESERU YENEBEREW BIZU YEBETEKIRISITIYAN LIJOCH EISACHEWUN BILEW KEGELELITENA BETEKIRISITIYAN WETITEW YASEBUT NEGER HONO SILALAYUT BIZUWOCHU KEHULET YATA HONEW EIBETACHEW KERITEWAL YEABUNE PAWULOS SIM KALITETERA ALIHEDIM BEMALET YIZEWUT YENEBEREW AKUWAM HIZIBUN ALEYAYEW EINIJI MINIM ALITEKEMEWUM

BEGO ZEMEN YAMITALIN

danf said...

hopefully the holly synode if they care for our church unity, they will accept our question to do their best.

Moona said...

እግዚአብሄር በቸርነቱ ያስበን!

Moona said...

እግዚአብሄር በቸርነቱ ያስበን!

Anonymous said...

Eyesus wey Medhanealem's Min alu?

Anonymous said...

For how long we have been punished eme amilak?

Anonymous said...

Can somebody explain for me who is the Protestant....... I doubt if the Synod is the true Christians.....

Desalew said...

teshumae limeta new bilew hadu .deggimom aderegut.eignam lehulum neger zigigu nen!!!!

Anonymous said...

Dear God help us

Anonymous said...

beseme silasie

Seek peace and purse it said...

Mahlet, I concur.

Anonymous, I commend you to speak so boldly about your views. There may be truth somewhere in there, but the falsehood overcame any truth you may have written. Over all our comments are disturbing to those who know the truth about Bitsue Abba Abrham, so you are looking pretty bad right now, its good you are 'anonymous'... May God have mercy on you. You are a sad soul, who doesn't know what it says. Bitsue Abba Abrham never said he would not go to any Church who does not call the Patriarch's name, his Grace said "if you invite me I will come as I am, which is a Arch Bishop of the EOTC and if the occasion calls for it I will call the Patriarch's name," why did his Grace Abba Abrham say this? Its not because of any respect for any person, but because the Church canon law requires it. So before you run with your words in CAPS and what not, check what you are saying. Who told you Bitsue Abba Abrham doesn't want to leave this country? Unlike you, his Grace is highly intelligent and graced with God's Spirit, if that was his plan it would be achieved with out doubt; but its not his grace's plan as you say it is. The manner in which you write is baffling for a EOTC follower. Who are you? I know you are not a Bishop, but you talk like you are above a Bishop. You talk about a Bishop with out any reverence or fear of God, especially when your accusations are groundless, they are just your opinion, like you said, "YIMESILALU..." I suggest you back OFF, your naive comments will not save you from the judgment. Bitsue Abba Abrham did not seek the disunity of the church but its unity. This is proven in his grace's stern adherence of the Faith and Canon law of the Church. Its all about that my friend. In doing so many were disappointed because they wanted his grace to follow their own creations of church canon laws, bylaws, and what have you, so you are accusing his grace for refusing these lost souls? Where you there when the laity in this DC area, requested the EOTC, through his grace, to take legal action to stop the proliferation of churches and existing churches from their lawlessness? I no you were not there, his grace said "no, that is not what our Lord taught us, our Lord taught us patience and to teach by example"...again you think you know about what you wrote...but you don't, so stop trying to fool the innocent.

Anonymous said...

Even though we love and support Abune Abraham, as he has firm stand to bring the Churches together so that every Church will follow the cannon of Holy Synod, We will never support his refusal to go back to Ethiopia and need to remain in the USA. I hope people beside him don't push him to stay here contravening the instruction of the Holy Synod. Let the lucky Harerge people enjoy working with him. Regarding to Abune Fanuel and his eccentric venue with the collaboration of anti orthodox Tewahedo people, we should follow each and every step of his action and movement to stop him with tangible evidences. If the Holy Synod changes its mind and takes an immediate action to assign another Bishop, it will be much better to placate the people in North America. Our strength will be measured if we can work and keep our religion without having Abune Abraham beside us. Again I don't agree his refusal to go back to Ethiopia, as rumours are diffused that both Bishops like to stay against the will of the Holy Synod.

Anonymous said...

What I do not understand is why the synods do not focusing on the cause of the problem.
We all know that the cancer to E.O.T.C is Abune Paulos. Why the synods do not get it.
Just like Abune Merkorios, make Abune Paulos leave and elect another patriarch that can truly serve GOD and keep the E.O.T.C united. Just amend the “Qaleawadi” and make each patriarch serve for five or six years term.
Dear Synods, to solve the current problem we are facing, the only solution is to un-root Abune Paulos. I bet you agree with that, but you do not have the gut to say that. Amen!
GOD’s church is being destroyed by its own disciples. Satan is snatching fathers’ from GOD by their own choice. Remember the end is near and it is here.
Please, some body call SUBAEE, let us cry to GOD.

LeSelam said...

my dear beloved, all I ask is that our dear Fathers must respect each other as a human being. God ordained all of you for His holy Church and His glory. must have self respect. true familys is not one of blood, but respect of and joy in each other's life and service to Christ. Bishops, Archbishops, must hamble to the holy synod. specially to the Leaders. .."humble yourselves in the sight if the Lord" James 4:10
the Church is not institution or an organization. it is Body of Chrsit! of course, Our concern is the services and the choir, the social and cultural groups and the religious instruction and church-tourism and so forth. It is not that these questions aren’t sometimes important. But there is one thing needful: the purification of the heart and the acquisition of the Holy Spirit. We are the tample of the holy Spirit. "do you not now that your bodies are tamples of the Holy Spirit" 1 corinthians 6:19. This is a deviation from the essence of the matter that keeps those who are considered believers-- most priest, bishops, archbishops and flock equally like pagans, worshipping themselves, seeking their own glory eather here or there. They are only concerned with their own power and their own reputation and their own honor. [let us not forget this.."humble yourselves in the sight if the Lord" James 4:10]. They are satisfied with only the outward form of the worship of God. What is sought in any case, in the understanding of the people, is not change of heart but rather some practices and the keeping some obligations and giving lip service. In what pertains to the exterior of the church, today, it is sometimes, but not always, shine brightly by worldly standards, souls graze in their own impurities and lack of awareness. Is this not the ideal church the devil desires and lords over? A worldly church, ritualistic, like a museum, a nominal Christianity but without Christ and without holiness and without truth and without Spirit and without new life, filled with the thoughts of the world and the concerns of the world! Is this not the church that most people receive today and for which they work? please correct me if I am wrong and forgive me too..The devil has succeeded in making people think that this is the true and desirable church of modernity!

This is exactly a church against Christ! And we, without our attention to holiness, are building it contentedly, persistently and continuously!
The Church Loves you all so do Christ.
Jesus said, “There was a man who had two sons. And the younger of them said to his father, ‘Father, give me the share of property that is coming to me.’ And he divided his property between them. Not many days later, the younger son gathered all he had and took a journey into a far country, and there he squandered his property in reckless living. And when he had spent everything, a severe famine arose in that country, and he began to be in need. So he went and hired himself out to one of the citizens of that country, ...“But when he came to himself, he said, ‘How many of my father's hired servants have more than enough bread, but I perish here with hunger! I will arise and go to my father, and I will say to him, “Father, I have sinned against heaven and before you. I am no longer worthy to be called your son. Treat me as one of your hired servants.”’ And he arose and came to his father. compassion, and ran and embraced him and kissed him. And the son said to him, ‘Father, I have sinned against heaven and before you. I am no longer worthy to be called your son.’ But the father said to his servants, ‘Bring quickly the best robe, and put it on him, and put a ring on his hand, and shoes on his feet. And bring the fattened calf and kill it, and let us eat and celebrate. For this my son was dead, and is alive again; he was lost, and is found.’ And they began to celebrate.(Luke 15:11-24

May God protect His Church against division.
Abba

Anonymous said...

I totally support this letter to Synodos. It contains the whole truth nothing but the truth. These few numbered churches on the list worked together with both Papasat the whole time and know all the situation. I 100% believe that they didn't try to side to any body unfairly, but truthfully came to the same conclusion and produced this letter. I am nobody but one member of these churches and also know what is mentioned on the letter is true. I cannot seat back and keep quite. As I said it before, there must be some sort of sabotage or confusion at the end of their (Synodos) decision making time. No body with proper mind set will remove somebody who is working hard and truthfully, has strong back ground for the support of the church unity, before and current good standing history,etc. At the same time on the contrary up hold, support, and give even higher reponsibilities to some one who is actually acting weird and directly opposit to the church needs. As we heard from several sources, the removal of Abune Abrahm is the result of about 10 guleltegna churches deligates request. This is an other unbeliveble action taken by the Synodos. How on earth that became acceptable. Is the Synodos supporting geleltegnnet? or what? The last time removal was declined by Synodos, because of not accepting the guleltgna situation and now looks totally different. It is not long ago that we heard from the Synodos that these Papasat were to explain their situation in person. With out that decision being waited for, the removal decision came out. What is going on? Finally even though we accept the Synodos decision, it is easy to forcast that it is going to be living hell on earth for A. Fanuel. We already know from the letter sent that these churches requested for reconcideration of the decision. There are also so many behind the seen complication already which makes the decision not to be effective. By the way geleltegnoch enquan des alachihu. Geleltegnanet gin edmew achir mehonun ewekut. Hizbu sineqa geleltegnaneten endemitefaw ena endemiwenegiluachu new. Most of your members are not aware of your being geleltegna. If you don't see the result let me tell you!! they put A. fanuel on your head. That is what you begged for. Any way I hope we will come together to support one-ness and keep EOTC in good standing one day.

Anonymous said...

Besime silasie

Peace said...

To the last anonymous comment:

Your comment shows that you care for the EOTC. However, becareful with how you voice your concern, the words that you use. First of all, this is a public blog that can be viewed by anyone, including those outside the EOTC faith. We all know who the devil is using to destroy tewahedo and church canon; however, we aught to speak about these individualS (there is more than one person involved), in a clever manner just like our fathers, so our words do not become stumbling blocks for others. Its ok to be less discreet when in private with EOTC members, but not on the internet. More importantly, lets first get our inner church in order before the other church. I agree with the subayee, it aught to come from Bitsuan Abbatocachin.

Anonymous said...

Ye Synodos wesane mekeber binorebetem aheyawen ferto dawelawen indilu, Aboune Poulosenena haweltachewen A. Fanuelen atfiwochune teto menim yalatefuten menekakatu germognal. Kechinkelate liweta alchalem.

Anonymous said...

Tamasegan nawe ara Germany yamenenore tasabesebane end a USA yaAto Garamond nagare enasetawes.

Anonymous said...

psalm 135-6

Anonymous said...

ይድረስ ለአሜሪካ የሀገረ ስብከት ምዕመናንና ካህናት በሃይማኖት የምትመስሉኝ ሁላችሁ አባቶቼ እናቶቼ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንዲሁም ህፃናት የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በሙሉ ቤተክርሰቲያን አንድነቷ ተጠብቆ ታሪኳ ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁላችሁም የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድትወጡ የጀመራችሁትን ተጋድሎ በመተጋገዝ በመተባበር በመጠናከር ልታጎለብቱት ይገባችኋል እኔ የሚሰማኝ ለቅዱስ ሲኖዶስ የፃፋችሁት ደብዳቤ ጥሩ ነው ቅዱስ ሲኖዶስ የፃፋችሁትን ነገር ባይሰማ መልሱንም እንደምትፈልጉት ባይሆን ግን እራሳችሁ ተጠናከሩ እንጂ ቤተክርስቲያንን ሊከፋፍሏት ለተነሱት ጠላቶች አሳልፋችሁ አትስጡ እያንዳንዱ ምዕመን በአንድ ልብና በአንድ ሀሳብ ሆኖ ለቤተክርስቲያን ከቆመ ጥቂት ሰዎችን ጉልበት እንዳይኖራቸው ማድረግ ይችላል እነሱ ስልጣናቸውንና ገንዘባቸውን አምነው ቢነሱ ምዕመኑ ደግሞ እግዚአብሔርን ይዞ ያሸንፋልና አትደናገጡ ህብረታችሁንም አጠንክሩት እንጂ አትዳከሙ ሁልጊዜ ጥሩ ሥራ ከሰራችሁ እግዚአብሔር ይዋጋላችኋል አታስቡ እዚህ ያሉት ጳጳሳትም እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች የሆኑትን እንዳናጣቸው ያሰጋኛል አንዳንዴ ውሳኔው የሚያስደነግጥ ቢሆንም በጫናም ሊሆን ስለሚችል መፍረድ ከባድ ነው እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች በህይወት ቢኖሩ ደግሞ ወደፊት ሊያስተካክሉት ስለሚችሉ ለህሊናቸውና ለፈጣሪያቸው ታማኝ ከሆኑ ማለቴ ነው ምክንያቱም አሁን የተጠቀሙበት ዘዴ እኔ እንደሚመስለኝ አንዱን ሰጥቶ አንዱን መቀበል አንድ ለፓትሪያርኩ አንድ ለእውነተኛ የተዋህዶ ጳጳሳት አባ ሰረቀን ከማደራጃ መምሪያው ማንሳት አቡነ ፋኑኤልን አሜሪካ ላይ መሾም እኔ የሚያሰጋኝ ወደፊት ተሃድሶ ፕሮቴሰታንቱ ጉልበት አግኝቶ ቤተክርስቲያንን እንዳይከፍል ምእመኑ ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረግና ነቅቶ መጠበቅ ያለበት ይመስለኛል ምዕመኑ እኮ ከተጠናከረ መሪዎቹን ማስተካከል አያቅተውም ምክንያቱም የገንዘቡ ምንጭ ምእመኑ ነው እንጂ ጳጳሳቱ እኮ አይደሉም እግዚአብሔርን ማስደሰት የሚቻለው በአግባቡና በሥርኣት ሲሰሩ ነው

Anonymous said...

german Ato gedamone bagelse takawemo enda USA

Peace said...

Regarding: "Even though we love and support Abune Abraham, as he has firm stand to bring the Churches together so that every Church will follow the cannon of Holy Synod...". If you just stoped here you would have done a good thing...but you kept writing and made a huge mess of yourself!!! Why do people automatically assume America is so desirable and everyone whats to stay. Do you know for a fact Bitsu Abba Abrham refused to attend the Synod out of disobedience? You do not, because if you did you would not say what you said, research why his Grace did not attend the meeting, then talk. Do you think we will follow a father that does not follow Church cannon? We follow his grace because of the very reason you mentioned in your early statement, because his grace follows church cannon with out exeception, this my friend is why we love him, not because of ANY thing else.
By the way, "LeSelam" or "Abba", are you aware the blog you like to follow namely "Aba Selama" is Heretic? Meniynet zemen getemen? Our sins multiply like the USA national debt...we need a revolution of the spirit and mind.

Mahlet (እሚ) said...

Anonymous @ November 3, 2011 11:34 AM

I concur with what you said . As a body of Christ and laity of the EOTC we all have one cause that is common to us and that is the unity and purity of the Church which we need to protect and have a just response by this I dont mean being a vigilante all man by himself type of response but a collective spiritual response
and that we can only do by remaining unshaken in faith and by always remembering EOTC is not only the responsiblity of the Bishops and the power that be but that of the followers and all those called Christian in Christ.

Be still

Anonymous said...

We all know and happy about what bitsue Abune abreham did. But if any order come to place him back home, that will be for good and his grace must have to go to ethiopia and do his next job with God. for us let us pray God will give us good leader. Pleas let's believe in Gog!

Anonymous said...

እኔ የማይገባኝ አንድ ጥያቄ አለ ይኸውም ሲኖዶስ የሚለው ቃል ነው። ሲኖዶስ ማለት እኮ እኔ እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰባሰቡት ጳጳሳት ናቸው መሪውም አቡነ ጳውሎስ ናቸው። ታዲያ ባንድ ወቅት ሲኖዶሱ ተሰብስቦ የአቡነ ጳውሎስ ሃውልት ከቦሌ መድሃኔዓልም ቤተክርስቲያን በአንድ ወር ውስጥ እንዲፈርስ የወሰነውን ውሳኔ አቡነ ጳውሎስ ይኸው እስካሁን ተግባራዊ አይሆንም ብለው አሉ። ታዲያ የኛ ሲኖዶስ ሲኖዶስ እያሉ መንጫጫት ማንን ለማታለል ይሆን? ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖዶስ ሳይሆን አቡነ ጳውሎስ ፈላጭ ቆራጭ የሆኑበት ማህበር ነው ያለው። ለዚሁም ክርስቲያኖች መጸለይ እንጂ መበታተን የለብንም። አለ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን አንድም ነገር እንደሌለ አምነን እግዚአብሔር በሃገራችን ላይ ያንዣበበውን የመለያየት ጥላ እርስው ያንሳልን።

hiwi said...

Egziabeher amelak lemibetebetu abatoch astewayi libonan yisetelen!!!

hiwi said...

EGZIABEHER lemibetebetu abatoche astewayi libonan yistachew!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)