October 23, 2011

ሊቃነ ጳጳሳቱ ፓትርያርኩን በበቀለኛነት እና ጣልቃ ገብነት ወቀሱ


  • READ IN PDF.
  • ሁለቱ የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በፓስፖርት እና በመኖሪያ ፈቃድ እድሳት እጦት እየተንገላቱ ነው፤ ሁለቱም ሊቃነ ጳጳሳት በ30ው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ይሁን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ አይገኙም
  • “ትኩረት ባለመስጠት ይሁን በሌላ ምክንያት አብዛኞቹ በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በጉባኤው ላይ አልተገኙም፡፡ በአርኣያነቱም ሆነ በምሳሌነቱ ልዩ በሆነው በዚህ ዓለም አቀፍ 30ኛው ጉባኤ ላይ በመገኘት አንድነትን አለመግለጽ ቅሬታን ከማሳደሩም በላይ ጥያቄን ሊያስከትል ስለሚችል ቅዱስ ሲኖዶስ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን የማስተካከያ መመሪያና ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጉባኤው በአጽንዖት ጠይቋል፡፡” (የስብሰባው የጋራ አቋም መግለጫ)
  • “ጥሪው ለሥራ ሳይሆን አሳስሮ ለማስቀመጥ ነው፤. . . እልህ አስጨራሽ ሥልጣንዎ በእምነት ካልሆነ በሥጋ አመለካከት የሚወጡት አልነበረም፤ . . .  በቀልን ለተጠማ አባት ራሴን አሳልፌ አልሰጥም” (ብፁዕ አቡነ አብርሃም)
  • የሰሜን አሜሪካው የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ሲኖዶሱ ያልወሰነበት ነው በሚል የሊቃነ ጳጳሳቱን ተቀባይነት አላገኘም
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 11/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2011)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ ካሏት ሦስት አህጉረ ስብከት የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የሰሜን ምዕራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቅዱስ ሲኖዶስ ሳያውቀው እና ሳይመክርበት በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ የበላይ የሆነ “የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” በዋሽንግተን ዲሲ እንዲቋቋም ያስተላለፉትን ትእዛዝ፣ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ያለቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ እና ከሁለቱ አህጉረ ስብከት ዕውቅና ውጭ ወደ ሰሜን አሜሪካ እየተመላለሱ በሚፈጥሩት ችግር ላይ ርምጃ ባለመውሰዳቸው በጣልቃ ገብነት ወቀሷቸው፡፡

አቡነ ፋኑኤል
ሊቃነ ጳጳሳቱ በአድራሻ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ከጻፏቸው ደብዳቤዎች ለመረዳት እንደተቻለው፣ መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በማድረግ “በሦስቱ አህጉረ ስብከት እና በመንበረ ፓትርያርኩ መካከል አገናኝ ድልድይ እንዲሆን” በሚል ሐምሌ13 ቀን 2003 ዓ.ም በቁጥር ል/ጽ/572/03 ሊቀ ሥዩማን ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ሞገስ ለተባሉ ሰው በተጻፈው የፓትርያርኩ ደብዳቤ እንዲቋቋም የታዘዘው የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ተግባራት በአህጉረ ስብከቱ ጽ/ቤቶች ሊፈጸሙ የሚገባቸው በመሆናቸው የጽ/ቤቱ መቋቋም የሐላፊነትንና የሥራ መደራረብን የሚያስከትል፣ ካህናትንና ምእመናንን ግራ የሚያጋባ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና በቅዱስ ሲኖዶስ ለሊቃነ ጳጳሳቱ የተሰጣቸውን ተግባር እና ሓላፊነት የሚጋፋ ሆኖ እንዳገኙት ተገልጧል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት እና በአንድ ሀገረ ስብከት መካከል የሚገባ ሌላ መዋቅር እንደሌለ በቃለ ዐዋዲው የተጠቀሰውን መሠረት በማድረግ “የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑ ሊቃነ ጳጳሳትን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋራ የሚያገናኝ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ያልሆነ ሰው የሚመራው አካል የማቋቋሙ አስፈላጊነት “ግልጽነት የጎደለው ነው፤ እንዲያውም ለአህጉረ ስብከቱ ህልውና የሚያሰጋ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ የማያዳግም እርምት እንዲሰጥበት” ጠይቀዋል፡፡

በቃለ ዐዋዲው መሠረት አንድ ሊቀ ጳጳስ በተሾመበት ሀገረ ስብከት ላሉ ካህናት እና ምእመናንን ሙሉ ሓላፊነት ያለበት መንፈሳዊ አባት እንደሆነ የተደነገገውን በመጣስ ተቋቋመ የተባለው ጽ/ቤት አብዛኛውን ውይይት የሚያደርገው ራሳቸውን ‹ገለልተኛ› ብለው ከሚጠሩ አብያተ ክርስቲያን እና መደበኛ ውክልና ከሌላቸው ካህናት ጋራ ነው፤ ይህንንም ጽ/ቤቱ እስከ አሁን ከሚያደርጋቸው መረዳታቸውን ያረጋገጡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ሁኔታው በሰሜን አሜሪካ “ራሱን የቻለ መዋቅር እየመሰለ የመጣውን ገለልተኝነት”ን በማስፋፋት እና በማጠናከር አህጉረ ስብከቱ ለአብያተ ክርስቲያን(ካህናት እና ምእመናን) አንድነት በሚያደርጉት ጥረት ላይ ዕንቅፋት እንደሚፈጥር በመጥቀስ የፓትርያርኩን ትእዛዝ ተቃውመውታል፡፡

ቀደም ሲል የሲዳሞ ሀገረ ስብከት የነበሩትና በኋላም የሕንጻዎችና ቤቶች አስተዳደር እና ልማት ድርጅት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ፋኑኤል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ወደ ሰሜን አሜሪካ በመመላለስ ያለዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ዕውቅና፡-
  • በአትላንታ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን(ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን) ተገኝተው የቅስና እና የዲቁና ማዕርግ ሰጥተዋል፡፡
  • በኖርዝ ካሮላይና ሻርለት መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን(ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን) ተገኝተው ቤተ ክርስቲያኑን ባርከው ከፍተዋል፡፡
  • በቨርጂኒያ አሌክሳንደርያ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት(ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን) ተገኝተዋል፤ ክህነትም ሰጥተዋል፡፡
  • እሑድ፣ ኦክቶበር 8፣ 2011 በናሽቪል ቴኔሲ ተገኝተው የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንደሚባርኩ ፕሮግራም እንደተያዘላቸው ተረጋገጧል፡፡
ሊቀ ጳጳሱ እየፈጸሟቸው በሚገኙት ከቀኖና ውጭ የሆኑ ተግባራት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የበለጠ የሚያናጋና ቤተ ክርስቲያን ወደልተፈለገ አቅጣጫ እንድታመራ የሚያደርግ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ከመስከረም 26 - 27 ቀን የተካሄደው የሀገረ ስብከት ሰበካ መንፈሳዊ ስብሰባው ማረጋረጡን አቡነ አብርሃም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የላኩት የመንፈሳዊ ጉባኤው ቃለ ጉባኤ ያብራራል፡፡

አቡነ ፋኑኤል እነኝህን ኢ-ቀኖናዊ ተግባራት ለመፈጸም ደብዳቤ ስለመመደባቸው[ከአቡነ ጳውሎስ] እንደማያውቁ የገለጹት አቡነ አብርሃም፣ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አቡነ ፋኑኤልንና ተባባሪ አስተባባሪዎችን ወደ ሰሜን አሜሪካ በመላክ እርሳቸው በማያውቁትና ባልተጠየቁበት የአድማ ክስ እና ወንጀል እንደተፈጸመባቸው፣ ይህን ሀገረ ስብከቱን የሚያዳክምና ሩጫቸውን የሚገታ ተጽዕኖ በቅዱስነታቸው ትእዛዝ እና ድጋፍ በቀጣይነት እየተፈጸመ እስከ ዛሬም ድረስ እያዘዙበትና እየደገፉት መቀጠሉን አመልክተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የፓትርያርኩን የበቀል ፍላጎት የሚገልጹት አሁን ከሚመሩት ሀ/ስብከት ጋራ በተያያዘ ብቻ ሳይሆን “ብዙ ኖሬበት ብዙ ሠርቼበታለሁ፤ በምእመናኑም ዘንድ መልካም ስም አግኝቼበታለሁ” ከሚሉት ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን በደብሩ አስተዳዳሪ እና ቄሰ ገበዝ ተጎትተውና ተዋርደው እንዲወጡ መደረጋቸውን በማውሳትም ነው፡፡ በወቅቱ የደረሰባቸውን በደል ለፓትርያርኩ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ አቡነ ጳውሎስ የተናገሯቸውን ቃል ለራሳቸው ኅሊና ከማስታወስ በቀር በጽሑፍ እንዲገልጹት ኅሊናቸው እንደማይፈቅድ ተናግረዋል፡፡ “የፓትርያርኩ ሕጋዊ ወኪል” በሚል ራሱን ይጠራ የነበረው መናፍቁ ጌታቸው ዶኒ ብፁዕነታቸው ባልፈጸሙትና ባልተረጋገጠ ነገር በጋዜጣ ስላጻፉባቸው ትችቶችና ወቀሳዎች አቡነ ጳውሎስ ዘንድ ለአቤቱታ ሲቀርቡ በፌዝና በስላቅ ለመስተናገድ ጠብቀው እንዳልነበረ አቡነ አብርሃም በቁጭት ገልጸዋል፡፡

በ2002 ዓ.ም በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በውጭ ከሚገኙ ጳጳሳት የተወሰኑት “በነፍስ ድረሱ” ዐይነት ጥሪ ሲደረግላቸው እርሳቸው ጥሪው እንዳልደረሳቸው፣ በስብሰባው ላይም እንዳይገኙ ተዘዋዋሪ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸው እንደነበር አቡነ አብርሃም አስታውሰዋል፡፡ የመጣውን ሁሉ በጸጋ ለመቀበል ወስነው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡም በኋላ በየትኛውም ቤተ ክርስቲያን እንዳያስቀድሱና እንዳያስተምሩ ስውር የስልክ ትእዛዝ ለአድባራት አስተዳዳሪዎች በመስጠት፣ የመጡበት የሲኖዶስ ስብሰባ ከተጠናቀቀም በኋላ “ወደ ሀገረ ስብከትህ መመለስ አትችልም፤ ተከሰሃል፤ ስምህ ይጠፋል፤ እኔ የምመክርህን ማድረግ ብቻ ነው” በሚል በፓትርያርኩ በመታገዳቸው ጉዟቸው ተስተጓጉሎ ለአላስፈላጊ ወጪና ለአካላዊ ሕመም መዳረጋቸውን፣ የነበራቸው የዲፕሎማት ፓስፖርት ጊዜው ስላለፈ ተለዋጩን የዲፕሎማት ፓስፖርት እና በሚኖሩበት አገር መውጣት መግባት የሚያስችል መኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ያቀረቡላቸውን ደብዳቤ ከፊታቸው ላይ ቀዳደው መጣላቸውንና ዛሬም ለአራተኛ ጊዜ አመልክተው ተቀባይነት አለማግኘታቸውን ዘርዝረዋል፡፡

በወቅቱ ከፓትርያርኩ ጋራ ውዝግብና ክርክር ከመፍጠር “ወደ አንድ ገዳም ሄጄ ለመቀመጥ እስከ መምረጥ ደርሼ ነበር” ያሉት ብፁዕነታቸው፡- የዲፕሎማቲክ ፓስፖርታቸው ካልታደሰላቸውና አገር መውጣት መግባት የሚያስችላቸው ከጥቅምት ሰባት ቀን ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና ከጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የተላለፈላቸውን ጥሪ “በቀልን ለተጠማ አባት ራስን አሳልፎ መስጠት” በመሆኑ በስብሰባዎቹ እንደማይገኙ አስታውቀዋል፤ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የተፈቀደላቸውን መብት ሲኖዶሱ እንዲያስከብርላቸው፣ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስም “ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው እንዲያስጠብቁ፣ ይቅር ባይነትን ተምረው እንዲያስተምሩ፣ ቁረጥ ጣል፣ ሰርዝ ደልዝ፣ ለውጥ በርዝ የሚለውን ባዕድ ቃል ትተው እንዲያስተው፤ አበው ቅዱሳን በተጓዙበት መንገድ ተጉዘው እንዲመሩ፣ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን የማያገናኘን ግለሰቦች አስመስለውና ቀምመው እንዲያቀርቡ የተደረገውን የአድማ መንገድ ዘግተው፣ ሀገረ ስብከቱን ወደ ቀደመ ክብሩ እንዲመልሱላቸው” ጠይቀዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከታቸውን በማጠናከር ላይ መሆናቸውን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስም የተሰጣቸውን ሓላፊነት በተሻለ መልኩ ለመወጣት የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን[ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቴዎሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው] እየተከታተሉ በመሆናቸው የመኖሪያ ፈቃድ እና ፓስፖርት እድሳት ለማስጨረስ የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ለሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ በመደረጉ የቤተ ክርስቲያንን ክብር በሚነካ እና አገልግሎቱን በሚጎዳ ሁኔታ እየተንገላቱ መሆናቸውን በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል፡፡

በአንጻሩ ከጥቅምት ሰባት ቀን ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 30 መደበኛ ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ተሲዓት ላይ ሲጠናቀቅ በወጣው ባለ33 ነጥብ የውሳኔ ሐሳብና የጋራ አቋም መግለጫ ላይ እንደተመለከተው በውጭ ከሚገኙ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት አብዛኞቹ አለመገኘታቸው ተመልክቷል፡፡ በዐይነቱ ልዩ በሆነው በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ አንድንትን አለመግለጽ “ቅሬታን የሚያሳድር እና ጥያቄን የሚያስከትል ነው” ያለ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን የማስተካካያ መመሪያ እና ውሳኔ እንዲያስተላልፍ አሳስቧል፡፡

13 comments:

Anonymous said...

አንድ፡ አድርጎ፡ የሚመራ፡ መሪ፡ ስላልሆኑ፡ አቡነ፡ ጳዉሎስ ፡ስለ ፡አንድነት፡ ይነጋገራሉ ፡ማለት፡ ድካም ነዉ።
“Adaamiin oollaa hagamsaa jiru himimaan ishee hinqooru”jedhama mittiree ?. Hanga hagamsi kuun buqqa’ee baduutti waldaan amantii keenyas huma boossi nutis niboonyaaf niboonyas.

MN irraa

Anonymous said...

እንግዲህ ምን እንላለን???
የቤተ ክርስትያን አምላክ የሚበጀውን ያምጣልን። እስኪ ከቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መልካም ዜና እንሰማ ዘንድ አምላካችንን በጸሎት እናሳስብ። በባዕድ አገር ያሉ አባቶቻችንንም አምላክ ጽናቱን ይስጥልን። አንድ አድርገን!!

ኃይሌ ዘማርያም

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ አይመስላችሁም ምክንያቱም እየተነሳባቸው ያለውን ተቃውሞ መሸከም ከሚችሉት በላይ እየሆነባቸው ስለመጣ መንገዳቸውን እያመቻቹ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ደግሞ ቅድመ ዝግጅት አባ ፋኑኤልን ቀድመው ልከው ለገለልተኛ ነን ባዮቹ ሰዎች ከመጎብኘትም አልፈው እውቅና እስከመስጠት አድርሰዋል ፡፡ እንደ እኔ ግምት በቀጣይ አባ ጳውሎስም ተገፋሁኝ ይሉና (ሲገፉ መኖራቸው ሳይዘነጋ) ከሀገር ወጥተው ገለልተኛውን ሰብስበው ሲኖዶስ አለኝ እንደሚሉን እጠብቃለሁ ስለዚህ ሦስተኛው ሲኖዶስ ይቋቋምልናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ጎበዝ ከወዲሁ መንቃት ይገባል እላለሁ ፡፡

sila tsion zim alilim said...

BAWUNAT ABATOCHACHIN BATAM YASAZINALU BATACHALA MATAN BATSELOT INASBACHAW.INE BATAM YAGARAMAGN ABUNE FANUEL OCTOBER 1 2011 GELELTAGNA BAMITBALAW PHOENIX AZ KIDIST MARIAM BETEKRSTIAN MATAW BAHIGA WAT MANGAD LE 3 LIJOCH YEDIKUNA MA'IREG SATAWAL. INEN YEGERAMAGN MAIREG MASTATACHAW SAYIHON BE ETHIOPIA SINODS SIR MAWAKRUN TABIKO LAMAKELAKEL KAFITAGNA FILAGOT LANABARA HIZ YASTELALEFUT MALIKT GIN BALACHUBAT KOYU NAW INJI WADA INAT BETEKRSTIAN TEKELAKELU NAW YALUN ASTEWULO YESEMACHAWUN MI'MEN BEMULU ASAZNEWAL,LEMIMELEKETEW HULU YEDMTS INA YE VIDIO MEREJA LEMELAK ZIGJU NEGN

Anonymous said...

እግዚአብሔር አምላክ የቅዱሳን አባቶቻችንን ፀሎት ሰምቶ ለቤተክርስቲያናችን ሰላምን ያውርድልን እኛም ለቤተክርስቲያናችን አንድነት በፀሎት ማሳሰብ አለብን የቅዱሳን አምላክ ይርዳን አሜን!!!

Anonymous said...

እግዚአብሔር አምላክ የቅዱሳን አባቶቻችንን ፀሎት ሰምቶ ለቤተክርስቲያናችን ሰላምን ያውርድልን እኛም ለቤተክርስቲያናችን አንድነት በፀሎት ማሳሰብ አለብን የቅዱሳን አምላክ ይርዳን አሜን!!!

Angel Berhanu said...

I would like to say may GOD be with you two fathers. I know what kind of challenging time you are facing. Please remember, your truth is sincerity in action, character, and utterance for us Orthodox christians.
Also remember Matthew 24. To bring a few of GOD's words:
"See ye not all these things? verily I say unto you, There shall not be left here one stone upon another, that shall not be thrown down.
All these are the beginning of sorrows.
And then shall many be offended, and shall betray one another, and shall hate one another.
And many false prophets shall rise, and shall deceive many.
But he that shall endure unto the end, the same shall be saved.
. But pray ye that your flight be not in the winter, neither on the sabbath day:"

Girum Ante said...

ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሲያለቅስ ይኖራል!!!

Anonymous said...

BESIME SILASE AHADU AMILAK AMEN

bene amelekaket eiyeteguwazinibet yalew akahed betiliket ketemeleketinew chigir yalebet yimesilenal bewnetu bisuan abatochachin betekirisitiyan besetechachew kibirina maeireg mebitachew tetebiko menor einidalebachew aminalehu neger gin einesum bihon lesiriatuwana lehiguwa megezat alebachew biye aminalehu leaba pawulos eina meselochachew eidezih bekelalu asirekibewat mekiret yalebachew ayimesilenim einideteredahut bevisa chigir mikiniyat einidetetalu new visachew eisikiyalik dires min eiyetebeku nebere ? mikiniyatum kidus sinodos silikachew eisikemechereshaw sayihon befelege gize literachew mehonun lemin zenegut ? degimom visachew einidaleke wedehagerachew bimelesu sinodosu kamenebachew beki mikiniyat akiribew memeles yemichilu yimesilenal berigit abune pawulos yesinodosun gudayi hulu yasifesimalu malet ayichalim neger gin kesachew gara yalitesimamawu hulu kafnegete lela sinodos mefeteru yemayiker new sidetena sinodos yelem eiyalin eina bevisa mikiniyat sidetena lemehon kasebin yena eiwunetena yebetekirisitiyan lijinet minu lay new? ahun eina einidemiredaw yetifozonet asiteyayet new eiyeseten yalenew asiteyayet yabatochachininim kibir zik eiyaderegin new kena yemitebekew abatochachin bemekakelachew selam sefino einan menigawochachewun beselot einidiredun new mehon yalebet

Anonymous said...

minewu, Patriarchu yebete Chiristian Abat nachewu woyis Telat; minewu kebete Christian Afrashoch gar endih ejina guant honu. Wodajachewu menafik, wuluachewu poletica, minale Bete Christian Biwulu

Anonymous said...

አቡነ ጳውሎስ እነ አባ ፋኑኤልን ይዘው የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ባለበት በዚህ ሰዓት፣ እባካችሁ ሁላችን የቤተ ክርስቲያናችን ነገር የሚገደን ክርስቲያኖች በሙሉ በጸሎት ቤተ ክርስቲያናችንን ከእነዚህ ቢጻሳዊያን እንዲጠብቅልን እንጸልይ ወደ ፈጣሪ እናመልክት ምናልባት ከእኛ ውስጥ አንድ ጻዲቅ ሰው አይጠፋም ይሆናል ስለዚህ በጸሎታችን እንትጋ መልስ ከመድኅኒዓለም መጠበቅ ነው። እነዚህ ግብረ በላዎች በሙሉ ጊዜና ሰዓት ይሰጣቸዋል አልመለስ ካሉ እንደሚያጠፋቸው የታመነ አምላክ ነው አባ ሰረቀም ለአባ ፋኑኤል አለቅላቂ ናቸው የፕሮቴስታንቱን አስተምህሮ ጀምረዋል ስለዚህ እኒህ የሕዝብ ጠላቶች እንዲታገሱልን ለፈጣሪ እናሳስብ።
ቸር ወሬ ያሰማን

Anonymous said...

የአቡነ ፋኑኤል ስራ ወደ እግዚአብሔር በእንባ
መግለጽ ነው ኡኡኡ!!!!!! ያሰኛል ለመሆኑ የራሳቸውስ ደብር እሳቸው በፈጠሩት ሴራ ፍርድ ቤት አይደል ወይ የደረሰው :: የአዋሳ ህዝብ እንባ እንደፈሰሰ ደግሞ በስደት የተንከራተተው ህዝብ ደም ተፍቶ እየገባ ድካሙን ብሶቱን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብበትን ቤ/ክ ሰላሙን ለምን ትነሱታላችሁ!!
አሁን ቤ/ክ እየጠበቋት ያሉት እንደ አቡነ ፋኑኤል ያሉ
አስመሳይ ሳይሆን የቀደሙ አባቶች ድካማቸውን ያስተዋሉ እውነተኛ ምዕምናን ናቸው:: አቡነ ፋኑኤል ያስታውሳሉ ያ ዲያቆን ያሎትን ምን ያድርግ ዲያቆኑ እኮ መነኮሳትን የሚያውቀው ሲጸልዩ ሲሰግዱ
ነው :: በአንጻሩ እርሶ ጋር ሲገቡ ያገኞት ፒዛ እየገመጡ ሬስሊንግ ከፍተው ሲጮሁ ነው:: እኔም ምንም እንኳን የሚኪያኤል ፍቅር ቢኖረኝም በሃይማኖቱ ስም ስለተሸፈናችሁን በጣም አዝኛለሁ:: ታድያ እርሶ የሰበሰቧቸው ወንድሞቾት አይን ላፈር ተባብላችሁ አልነበር የአትላንታውስ ቢሆን ተናቁራችሁ አልነበር የሻርለቱስ ቢሆኑ መች ትነጋገሩ ነበር ዛሬ ለክፉ ስራችሁ ትገባበዛላችሁ :: እኛ ምዕምን ከእንደእናንተ አይነቱ ብጹዕ ምን እንማር??? ውሸት? ክህደት?? ሃሜት??ለገንዘብ ማደር?? ሌላው ቀርቶ መቼ የይቅርታ መንፈስ እንኳን አላችሁ:: ስለዚህ ፈጣሪ አምላክ ለሚያውኩ ልብ ይስጥልን:: ለኢትዮጵያ ቤ/ክ በቃሽ ይበላት::

Anonymous said...

የአቡነ ፋኑኤል ስራ ወደ እግዚአብሔር በእንባ
መግለጽ ነው ኡኡኡ!!!!!! ያሰኛል ለመሆኑ የራሳቸውስ ደብር እሳቸው በፈጠሩት ሴራ ፍርድ ቤት አይደል ወይ የደረሰው :: የአዋሳ ህዝብ እንባ እንደፈሰሰ ደግሞ በስደት የተንከራተተው ህዝብ ደም ተፍቶ እየገባ ድካሙን ብሶቱን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብበትን ቤ/ክ ሰላሙን ለምን ትነሱታላችሁ!!
አሁን ቤ/ክ እየጠበቋት ያሉት እንደ አቡነ ፋኑኤል ያሉ
አስመሳይ ሳይሆን የቀደሙ አባቶች ድካማቸውን ያስተዋሉ እውነተኛ ምዕምናን ናቸው:: አቡነ ፋኑኤል ያስታውሳሉ ያ ዲያቆን ያሎትን ምን ያድርግ ዲያቆኑ እኮ መነኮሳትን የሚያውቀው ሲጸልዩ ሲሰግዱ
ነው :: በአንጻሩ እርሶ ጋር ሲገቡ ያገኞት ፒዛ እየገመጡ ሬስሊንግ ከፍተው ሲጮሁ ነው:: እኔም ምንም እንኳን የሚኪያኤል ፍቅር ቢኖረኝም በሃይማኖቱ ስም ስለተሸፈናችሁን በጣም አዝኛለሁ:: ታድያ እርሶ የሰበሰቧቸው ወንድሞቾት አይን ላፈር ተባብላችሁ አልነበር የአትላንታውስ ቢሆን ተናቁራችሁ አልነበር የሻርለቱስ ቢሆኑ መች ትነጋገሩ ነበር ዛሬ ለክፉ ስራችሁ ትገባበዛላችሁ :: እኛ ምዕምን ከእንደእናንተ አይነቱ ብጹዕ ምን እንማር??? ውሸት? ክህደት?? ሃሜት??ለገንዘብ ማደር?? ሌላው ቀርቶ መቼ የይቅርታ መንፈስ እንኳን አላችሁ:: ስለዚህ ፈጣሪ አምላክ ለሚያውኩ ልብ ይስጥልን:: ለኢትዮጵያ ቤ/ክ በቃሽ ይበላት::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)