October 31, 2011

ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀ ላይ ከሥልጣን ማውረዱ የፓትርያርኩ ሐውልት ላይ እንደተወሰነው ውሳኔ እንዳይሆን ሥጋት አለ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 20/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 31/2011, PDF)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወል ሳሙኤል ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ እንደወሰነባቸው ከታወቀ ጀምሮ ምዕመናን ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ላይ ሲሆኑ ቅ/ሲኖዶስ ከረዥም እልፍ አስጨራሽ ስብሰባ በኋላ እዚህ መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ምሥጋናቸውን እየቀረቡ ነው። 


የቅዱስ ሲኖዶሱን ያለፉ ውሳኔዎች አፈጻጸም በጥልቀት የሚመለከቱ አንዳንድ ደጀ ሰላማውያን ደግሞ “ይህ ደስታችን ዘላቂ የሚሆነው የቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ እንዳለፈው ዓመት የፓትርያርኩ ሐውልት ውሳኔ የወረቀት ላይ ነብር፣ ተግባር ላይ የማይውል፣ አለመሆኑን ስናረጋግጥ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። አንድ የፌስቡክ ተጠቃሚ በበኩላቸው ሌላ አወዛጋቢ ደግሞ አስቀምጠው እስኪያስጨንቁን በዚህ ዜና እንደሰትን? እኔምለው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሐሰትንና እኩዮችን በመቃወም ተጠምዶ ሌሎች ተግባራት እንዳይከወኑ ሲዘገይ አይታያችሁም።” ሲሉ ጠይቀዋል።


 ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ መሆናቸውን፣ እንዲሁም አባ ሰረቀ ከሓላፊነታቸው እንዳይነሡ በጥብዓት ሲከራከሩላቸው የቆዩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይዘውት የነበረውን አቋም እንዲቀይሩ ወጣቱ በቅርቡ ያሳየውን ተቃውሞ የተረዳው መንግሥት ተጽዕኖ ሳያደርግ አልቀረም መባሉን መዘገባችን ይታወሳል።

5 comments:

Anonymous said...

Yekdusan Amlak Eigzabhere yikber Yimesgen!!!Yehune yidereglen!!! Mechersahwen Yasmerelen!!! Abune Poulus Eqnquane Lebewten Eigzahbehre meleselen! yesu sera new!!!

Anonymous said...

እልኸኝነት፦ ልብን ለክፉ ነገር ማጽናት ነው፤ እኛ ያልነው ብቻ ይሁን ብሎ መድረቅ፥ መጨከን ነው፤ የያዝነው መንገድ ገደል ቢከተንም እኛ ትክክል ነን ማለት ነው። እልከኛ የሆኑ ሰዎች ከትዳር ጓደኞቻቸው፥ ከልጆቻቸው ፥ ከወላጆቻቸው፥ ከዘመዶቻቸው፥ ከጓደኞቻቸው፥ ከጎረቤቶቻቸው፥ ከመሥሪያ ቤት ባልደረቦቻቸው፥ ከሁሉም ጋር እልኽ ይያያዛሉ። የሌላውን በጎ የሆነ አሳብ መቀበል መሸነፍ፥ እጅ መስጠት ይመስላቸዋል። ከዚህም አልፎ ከእግዚአብሔር ጋር እልኽ ይያያዛሉ። እነርሱ ሲናገሩትና ሲያደርጉት ትክክል ነው ብለው ያመኑበትን ነገር ሌላው ሰው በእነርሱ ላይ ሲናገረውና ሲያደርገው ግን ፍጹም ስህተት ነው፥ ብለው በእልኽ ይናጣሉ። ከዚያ በኋላ ምንም ነገር ቢሆን ከማጥፋት ወደ ኋላ አይመለሱም።

Anonymous said...

ሃሰት መናገር ብቻ ሳይሆን ሃሰተኞችን አለመቃወም ወይም ሃሰተኞችን ለይቶ አለማወቅ ወይም ሃሰተኞችን እያወቁ አለመገሰጽ ወይም ደሞ ስራቸው ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ አለመናገር በራሱ ሃጢያት ነው:: አሁን በቤታችን እያየነው ያለው ነገር ከዚህ የተለየ አይደለም:: አቡነ ጳውሎስ ሃሰተኛ ትምህርት በቤተክርስቲያን ዉስጥ ሲያስተምሩ አናይም ነገር ግን ሃሰተኛ ትምህርትን የሚያስተምሩትን ሰዎች በቤተክርስቲያን ላይ ይሾማሉ፣ በይፋም አንተ እንዲህ ብለህ ያስተማርከው ስህተት ነው ብለው አያውቁም፣ አንዳንዴም ሃሰተኞች በቤታችን ዉስጥ መኖራቸው በማስረጃ ሲነገራቸው እንዴት ብለዉ ለጉዳዩ እንግዳ መስለው ይታያሉ ወይም ደሞ ሁሉንም ወደጎን በመተው ጉዳዩን ከጎጠኝነት ወይም ከዘረኝነት ወይም ከስልጣን ሽኩቻ ጋር በማያያዝ አሁን ላለንበት ትልቅ ችግር አብቅተዉታል::
ስለሆነም፣ በእኔ አመለካከት አሁን በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለተንሰራፋው ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ እንዲሁም በዋናነት ምንፍቅና ምንጩ አቡነ ጳውሎስ ናቸው:: ስለሆነም ሁሌም ቢሆን እርሳቸውን በጥርጣሬ መመልከት መልካም ነው እላለው:: ወደፊት ከሚፈጠረው ድንጋጤ ለመዳን እራስንም አጽንቶ አካሄድን ከቤተክርስቲን ጋር ለማድረግ አንዱ አማራጭ ነውና! የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያንን ሰላም ያድርግልን እኛንም እንድንጸና ይርዳን!!!
መ.ዘ ከሽሮሜዳ

Anonymous said...

The last anonym, i think the ETOC followers (memenan) are better than the fathers in terms of putting the church first...see how putting the words of the bible in action are difficult..even for the people who preached it to us

At first i was happy that he was withdrawn, fool me what will happen next..some one even 10 times bad or ..the future to God, in Him i trust

Anonymous said...

the point is not whether,aba sareke removed or not but the holy synod decided in favor of the church that is good.It is up to aba Paulos remove him but true church sons and daugthers will fight for ever not just one guy.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)