October 29, 2011

ቅዱስ ሲኖዶስ ለ4ኛ ተከታታይ ቀን በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ እና ማ/ቅዱሳን መካከል ባሉት ችግሮች ዙሪያ እየተወያየ ነው

አርእስተ ዜና
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 29/2011/ PDF)፦
 • ምልአተ ጉባኤው የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት በተሰጠው መመሪያ መሠረት ባለመቅረቡ አልተቀበለውም፤ ኮሚቴው የአባ ሰረቀን በማስረጃ ያልተደገፉ 20 ክሶች በማጉላት የማኅበሩን 10 ተጨባጭ አቤቱታዎች በማኮሰስ አቅርቧል
 • የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ማ/መምሪያው ቋሚ ሊቀ ጳጳስ እንዲመደብለት፣ አባ ሰረቀ ከዋና ሓላፊነታቸው እንዲነሡ፣ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ አባ ሰረቀ ካቀረቧቸው ክሶች አንጻር የማ/መምሪያውን ሥልጣን በሚያጠናክር አኳኋን እንዲሻሻል በመፍትሔ ሐሳብ አቅርቧል
 • ምልአተ ጉባኤው “አጣሪ ኮሚቴው በሁለቱም በኩል የቀረቡ ማስረጃዎችን ይዞ የማጣራቱን ውጤት እንዲያቀርብልን እንጂ ‹እገሌ እንዲህ አለ፤ እገሌ ደግሞ እንዲህ አለ› የሚል ሪፖርት እንዲያቀርብ አልጠበቅንም” በማለት ሪፖርቱን ተችቷል፤ የሪፖርቱን ተቀባይነት ማጣት በመመልከት ጉዳዩ በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጠው ፓትርያርኩ ያቀረቡትን ሐሳብ በመቃወምም የማ/መምሪያውን ሦስት ተወካዮች እና የማኅበረ ቅዱሳንን ሁለት ተወካዮች በመጥራት ጉዳያቸውን እንዲያስረዱ አድርጓል
 • የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ አባ ሰረቀ ከአስተዳደራዊ /ሥራ አመራር/ አቅም ማነስ እስከ ሃይማኖታዊ ሕጸጽ ድረስ ያለባቸውን ድክመት በጎላ በተረዳ መልኩ በማብራራት ችግሩ ከግለሰቡ ጋራ እንጂ ከማ/መምሪያው ጋራ እንዳልሆነ ምልአተ ጉባኤውን ያረካ መግለጫ ሰጥተዋል፤ አባ ሰረቀ በበኩላቸው ጠቅላይ ቤተ ክህነቱንም በሕይወተ ሥጋ የሌሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትንም ማኅበሩንም በማደበላለቅ የከሰሱባቸውን የበርካታ ደብዳቤዎችን ቁጥር እና ቀን በመጥቀስ አሰልቺና ተጨባጭነት የሌለው ገለጻ ሰጥተዋል፤
 • ሁለቱም አካላት ለየጉዳያቸው አሉን የሚሏቸውን ማስረጃዎች ለአንድ ሙሉ ቀን ያዳመጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚከተሉትን የውሳኔ ሐሳቦች አቅርቧል፡-
 1. የማ/መምሪያው ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ፤ ከሓላፊነታቸው መነሣት ብቻ ሳይሆን የሃይማኖት ሕጸጽ እንዳለባቸው የተጠቀሰ በመሆኑ ኮሚቴ ተቋቁሞ፣ ማስረጃውን መርምሮ፣ ሪፖርት እንዲያቀርብ
 2. ማደራጃ መምሪያው ራሱን የቻለ ሊቀ ጳጳስ (ሀገረ ስብከት የሌለው) እንዲመደብለት፤
 3.  የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ከቃለ ዐዋዲው መሻሻል ጋራ ተያይዞ እና በሚሻሻለው ቃለ ዐዋዲ ውስጥ ተካትቶ ማኅበሩን ሊያሠራው በሚችል መንገድ እንዲሻሻል፤
 • እንደተጠበቀው የአባ ሰረቀን ከዋና ሓላፊነት መነሣት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ተቃውመዋል፤ ከሓላፊነት እንዳይነሡ መቃወም ብቻ ሳይሆን የአባ ሰረቀን የሃይማኖት ሕጸጽ የሚመረምር በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ መርማሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው ያቀረበውንም የውሳኔ ሐሳብ አልተስማሙበትም፤ በምትኩ ማስረጃው ለሊቃውንት ጉባኤው ቀርቦ እንዲመረመር ነው የአቡነ ጳውሎስ ፍላጎት፡፡
 • ከሊቃውንት ጉባኤው አባላት መካከል የሚጠራጠራቸው እንዳሉ ያመለከቱት የምልአተ ጉባኤ አባላት በበኩላቸው የፓትርያርኩን ሐሳብ ባለመቀበል ውይይቱ ለአራተኛ ተከታታይ ቀን ቀጥሎ ይገኛል፤ ፓትርያርኩም አንገታቸውን ዘልሰው (አጽንነው) “አልስማማም” በማለት ብቻ በተለመደው የማዘግየት ታክቲካቸው የምልአተ ጉባኤው አባላት እንዲሰላቹና አቋማቸውም በቆይታ የሚከፋፈልበትን ሰዓት እየተጠባበቁ ነው፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዋና ሓላፊውን ማንሣት ይችላሉ፡፡
 • አንዳንድ የጉባኤው ታዛቢዎች እንደሚገልጹት አባ ሰረቀ ከዋና ሓላፊነታቸው ተነሥተው ሃይማኖታቸው እንዲመረምር የውሳኔ ሐሳብ መቅረቡ በተሐድሶ ኑፋቄው ፕሮጀክት ላይ ጠንካራ ምት በማሳረፍ ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርገው በመሆኑ አቡነ ጳውሎስ የሞት ሽረት አቋም ይዘዋል፡፡ በሌላም በኩል ምልአተ ጉባኤውን በዚህ አጀንዳ ላይ ቸክሎ በመያዝና አባላቱን በማሰላቸት በቀጣይ በተያዙት “የሥርዐተ እምነት ችግር” /ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን/ እና አስተዳደርን የተመለከቱ አጀንዳዎች እንዳይታዩ/በቅጡ እንዳይታዩ/ የማድረግ ስልት ነውም ብለዋል፡፡
 • በመሆኑም የምልአተ ጉባኤው አባላት በዛሬውና በቀጣዩ ቀናት ውሏቸው በፓትርያርኩ በማዘግየት የመከፋፈልና እና የማዳከም ስልት ላይ ነቅተው ሳይሰላቹ በመወያየት ቤተ ክርስቲያን ከተጋረጠባት ወቅታዊ አደጋ እንዲታደጓት ተማፅነዋል፡፡ በየአህጉረ ስብከቱ የሚገኙ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና ሌሎችም የፀረ ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ አደረጃጀቶች የጀመሩትን ሰላማዊ እንቅሰቃሴ በመቀጠል ከዚህ ጥረት ጎን እንዲሰለፉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የዜናውን ዝርዝር ሪፓርታዥ እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡


9 comments:

Anonymous said...

egiziabehere hayemanotachenene yetebeqelen.

yemenafeqanene siwere sera yastageselen.

Leababtochachen tseantun yestelen

1haymanot said...

Dear deje selam tnx for update information .Bitsuan Abatochachen bertulin menfeskidus kenante gar selale asekemaun lechanachulet alama enji le Aba paulos hasab endategezu bekidist betekirstiyan sim adera enlachualen.Ergit new Ewnet belelbet ketema sele ewnet menager hasetegna mehon new yemibal teret ale gen bertulin .

lele said...

ABATOCHACHEN YARADA AMELAKE YATAMASAGANA YEHONE.AHONEM ENDA ATENATEIOSE YALA ABATE YESETANE

Anonymous said...

kidus sinodos yalewun chigir leyito lewuyiyt siyakerb yepatriarku alemesmamat lemin yihon???

Aba sereke birhan yehayimanot hitsets alebachewu eyetebales kehalafinet endayinesu yemikawemut lemin yihon?

kezihm bealefe protestantawi_tehaiso_ lay yalachewu akuam lemin tehadison ende medegef asmeselebachehu?


yihe hulu tikuret linsetewu guday newu?

Egiabher Amlak bete christianachinin yitebkil!

Gebre Z Cape said...

This is the time to say Praise the Lord, Amen. I knew that we always have fathers who stand for the truth. Yesterday I was very frustrated, I checked every blogs and church websites for news and did not find anything except always unbelievable fake news from abaselama.org.

Dejeselamoch thank you for such news, keep updating. You have made my weekend joyful. But still I pray that the discussion goes fast and our fathers finish all the agendas' in time.

Praise the Lord He is the Almighty!
Amilak hulachininim yabertan, Le Abatochachin tsega menifeskidusin yabizalin, Amen!!!

ayyaanaa said...

thank you dejeselam. try your best to update us. may the HOLY SPIRIT MAKE OUR FATHERS COURAGIOUS!nga

Zakethiopia said...

እግዚአብሄር ይመስገን:: አምላካችን ለአባቶቻችን ሃይል ይሁናቸው::

Anonymous said...

በእግዚአብሄር ማመን እና መታመን ካለ አይደለም አባ ሰረቀን ከዛም በላይ ያሉ መናፍቃንን እርሱ ፈንቅሎ ያወጣቸዋል እኮ! እኛ ብቻ ለዉጥ በራሳችን ጥረት እና ጉልበት እንጂ በእግዚአብሄር እርዳታ እንደሚመጣ አቀድመን ስለማናስብ እኮ ነው! ወይም ደሞ ስንሸነፍ ብቻ እኮ ነው እግዚአብሄር የረሳን የሚመስለን ስናሸንፍማ....የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሄር ሁላችንንም ይጠብቀን አሜን::
መ.ዘ ከሽሮሜዳ

Anonymous said...

Ende enezih sewoch mindinew yemifeligut, lemin betachinin tilew enesu bichachewun tadsew ezaw ayhedum? lemin yibetebtunal, metades be tsidk enji yegziabherin bet bemafresna behatiat meselachew ende? enezih getan yesekelu ayhudoch, egziabher yastagsachu, egziabher mechem bihon zim ayilachihum lebetu kenategna newuna, hizbum yekalkidan lijochu nen manim matfatim mafresim aychalewum.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)