- ማኅበሩ ምላሽ አለመስጠቱ ብዙዎችን አበሳጭቷል፤ (TO READ IN PDF)
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 25/2011)፦ ተፋፍሞ በቀጠለው የፀረ ፕቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪ ነው የሚሉትን ማ/ቅዱሳንን በመቃወም
ላይ የሚገኙት የተሐድሶ-መናፍቃን አሁን በያዙት አዲስ ስልት ማኅበሩ ከታዋቂ ምሁራን እና ካህናተ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማጋጨት
እየሞከሩ ነው።
በዚህ አዲስ የማጋጨት ተግባር “ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ-መናፍቃን ናቸው ብሏችኋል” ከተባሉት መካከል ታዋቂዎች
ምሁራን ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሲገኙበት ከእነርሱም በተጨማሪ ካህሣይ ገብረ እግዚአብሔር፣ ግርማ ኤልያስ (ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ)፣ ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኀይሌ፣ ሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሣዬ፣ ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ እና ዲ/ን በእደ ማርያም እጅጉ ይገኙበታል።
ማኅበሩ ግን በፈንታው እየተካሄደበት ላለው ዘመቻ ምንም ዓይነት መልስ ባለመስጠቱ ቆይቶ ተጎጂ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።