October 25, 2011

ከቅዳሜው ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን የሚቃወም ትዕይንት ጋራ በተያያዘ ፖሊስ ተጨማሪ ወጣቶችን እየያዘ ነው


  • ፓትርያርኩ፣ ተሐድሶዎቹን ደግፈው ለቆሙትና በፖሊስ ለታሰሩት ወጣቶች ለቀለብ እንዲሆናቸው በሚል፣ ዛሬ 10 ሺህ ብር ልከዋል እየተባለ ነው 
  • ለሌሎቹ ወጣቶች ግን ስላደረጉት ነገር ምንም አልተሰማም፤
  • (READ IN PDF. and Youtube.)
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 25/2011)፦  “ተቻችሎ እና ተከባብሮ የኖረውን ሕዝብ ወደ ብጥብጥ በመምራት እና ሰው በመደብደብ የሚሉ ሁለት የወንጀል ክሦች የቀረቡባቸው “የአዲስ አበባ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ማኅበር” ስምንት አባላት ትላንት ጥቅምት 12 ቀን 2004 .ም ጠዋት  በአዲስ አበባ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ከስምንቱ መካከል ስድስቱ እያንዳንዳቸው በብር 600 ዋስ እንዲወጡ ሲወሰንላቸው፣ የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ለጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር - ዋነኛ አስተባባሪዎች ናቸው በሚል፡፡


ይሁንና ቤተሰቻቸው የዋስ ሂደቱ ጨርሰው የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ወረዳ ዘጠኝ (ቀጨኔ) ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ቢሰጡም ፖሊስ “ይፈለጋሉ” በሚል ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ወስዷቸዋል፡፡ ስድስቱ ወጣቶች ትንት ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ከተወሰዱ በኋላ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት የፀረ - ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ትዕይንት ከተካሄደበት ከቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተይዘው በዚያው ከቆዩና ዋነኛ አስተባባሪ ናቸው ከተባሉ ሌሎች ሁለት ወጣቶች ጋራ ተቀላቅለዋል፡፡ ቀደም ሲል በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የነበሩት ሁለቱ ወጣቶች ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርበው እንደነበረ ተመልክቷል፡፡

ንት የተቀላቀሏቸው ስድስቱ ወጣቶች ደግሞ በዛሬው ዕለት እዚያው ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መቅረባቸው ታውቋል፡፡ ፖሊስ “ያልተያዙና መያዝ የሚገባቸው የቀሩ አስተባባሪ ወጣቶችን ለመያዝ” በሚል ተጨማሪ 15 ቀን እንዲሰጠው ጠይቆባቸዋል፡፡ ይሁንና ዳኛዋ ተጨማሪ ሰባት ቀናትን ብቻ በመፍቀድ ወጣቶቹ ለጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡

የወጣቶቹ በእስር መቆየት እንደሚያሳስበው የገለጸው “የአዲስ አበባ ጥምቀት ተመላሾች ወጣቶች ማኅበር” በበኩሉ የወጣቶቹ ጥያቄ ፖሊቲካዊ ወይም ብጥብጥ መፍጠር ሳይሆን እንደ አዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ሁሉ የተሐድሶ ኑፋቄን መግታት እና የኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መንነት ማስከበር ብቻ መሆኑን በማስረዳት ወጣቶቹ በተገቢው (በተፋጠነ) ፍትሕ ነጻ እንዲወጡ ጠይቋል፡፡ ይህንንም በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እያሰበበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በደረሰን መረጃ መሠረት አሁን በእስር ላይ ከሚገኙት ወጣቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ዘጠኙ የሚከተሉት ናቸው፡-
1.    ግዛቸው ዮሐንስ፣
2.   ቡሩክ ታደሰ፣
3.   ማዕርጉ በዛብህ፣
4.   ክንፈ ገብርኤል ከበደ፣
5.   ኀይሉ ይመር፣
6.   ደሳለኝ ሀብተ ወልድ፣
7.   መኮንን (?)፣
8.   መኮንን ገዛኸኝ
9.   ዳኛቸው ገዛኸኝ

በተያያዘ ዜና ቅዱስ ፓትርያኩ ተሐድሶዎቹን በመደገፍ ከሐዋሳ ለመጡት ወጣቶች ብቻ ብር 10,000 መላካቸው እየተነገረ ነውገንዘቡ በአቡነ ጳውሎስ ስም ከሌላ አካል የተሰጠ ይሁን በርግጥም ራሳቸው ፓትርያላኩት እየተጣራ ቢሆንም ለደጀ ሰላም የደረሰው የሞባይል ፉቴጅ ፊልም በቅድስት ማርያም በነበረው የሕገ ወጥ ቡድኑ ተቃውሞ አስተባባሪዎቹ ‹‹በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም የደረገውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የአገልጋዩን ዓላማ በመደገፍ የሰበሰቡ ምእመናን ዝርዝር›› በሚል ቅጽ ምዝገባ ሲካሄዱ እንደነበር ተረድተናል፡፡ ይህም የሕገ ወጥ ቡድኑ አባላት ለውጭ ተባባሪዎቻቸው የሚያቀርቡትና በየዋሁ ምእመን ስም እንዲህ ያሉ ድጋፎችን የሚያገኙበት የጥቅም ማካበቻ ስልት እንደሆነ እናስባለን፡፡

ወጣቶቹ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከተያዙ በኋላ ሌሊቱን ያሳለፉት በወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲገቡ ‹‹ለደኅንነት›› በሚል የአገታቸውን ማዕተብ እንዲበጥሱ መገደዳቸው ተነግሯል፡፡ ከእነርሱም መካከል አንዱ ወንድም በአንገት ማተብ ሊፈጸም የሚችል አደጋ የለም፤ ማተቤንም አልበጥስም በሚል ትእዛዙን መቃወሙ ተመልክቷል - እውን ይህ ትእዛዝ ለ‹ደኅንነት› ወይስ ሌላ ሰንሰለታዊ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ ፈቃድ ፈጻሚዎች (እጅ ጠምዛዦች) መኖራቸውን ማሳያ?

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

9 comments:

Anonymous said...

miemenan hulachin eskemot behaimanotachin yetsenan inhun!minm neger liyasdenegten ayigebam!

Anonymous said...

watatocheon lamerdate endatte yechalale?lawasetena yamehone birr enkone lamalake.mahebaro bank acc kalawe betenagerone?enanetta laye chegere kalettafatara or beloge alachawe waye?

Gebre Z Cape said...

ከሁሉም ጊዜያት ይበልጥ ወደ አምላካችን እንጩኽ: እንለምነው:: በስብሰባው ወቅት ለአባቶቻችን መቻቻልን: አስተዋይ ልቦናን እንዲያድልልን ሁላችንም እስቲ አባታችን ሆይን ጥዋትና ማታ እንጸልይ::

አምላክ የቤተክርስቲያንን አንድነት ይጠብቅ::

Anonymous said...

besemeab weweled wemenfes kidus ahadu amelak amenn selam dejeselamoch betam azenku benanete edme lekachehun me emenanen yemibetebet neger setetsefu becha new mayew lemehonu me emenane wede segawo demu yemeyakereb neger lemen atetsefum ? hule yemetestefut neger andem kum neger lay derso ayawekim lehulum tselot becha new mefteaw rasenem mawek melkam new DN danieal kibretm tenageroal wederas memelket teru new cher yaseman

Unknown said...

Ahun mecheresha asteyayet yesetut "Anonym",

Endih aynetun neger mesmat kalfelegu ezih ayemtu. Lela bota, yemifelegut website gar, mehed enna yemifeleguten manbeb yechelalu. Egna lerso aynetu aydelem yehenen yemenetsefew.

Anonymous said...

first of all how did abune paulos did send the money while he was on meeting with other pops? did he really do this kind of thing while he was talking against the tehadiso akenikagn? if he did then we no longer have father then. please Deje Selam try to give us some prove that how he did. i am tried of seeing this kind of stories. if this is " he say, she say" stories please keep your name clear out this. if this is the true then what is the sense of all pops meeting? i think someone making mistakes some where i just wanna heads up for deje selam use some common sense when you are posting any article. if it is true then true will send you free. lastly i would like to say for those who prison we have to find way to be released because they are fighting for our church and Deje Selam give us information how we can help them finically or psychically by asking where they are prisoned?

Unknown said...

Dear last annonym,
What You asked about the point that tha patriarch gave 10000 Birr should be validated. You are correct. We will try to substantiate what allegedly is said about His Holiness. If this claim is true, this will be a big point in the movement opposing the Tehadiso-Heretics.

Anonymous said...

My people, just let us try to understand the main causes of the problem. The strategic tactic of EPRDF to control and rule the country is division (Divid and rule policy of the colonizers). Aba Pawulos is the right hand of EPRDF. He tried to inistigate division and antagonism. This has been tried directly by EPRDF in many ways (based on religion, ethinic back ground, and others) since came to power but proved unworking. Now, it came through Abune Powlos who trying to divide the one church and divert the political presure to a church issue. The big picture is covered by some unrelated issues like such self conflicts. Peoples are put in jail on purpose to divert attention. I give respect to those people who are unfairly and un constitutionaly put in jail. Actually that is the behaviour of EPRDF. We have a lot of proplems (Inflation in which many people become unable to feed themselves, economic downturn, political unrest etc.) More importantly the Synode is on its annual meeting in which very important decissions are expected to be made. Therefore, let us see the problem in broader context and make our effort to curve it. Let God protect Ethiopia and showred His peace on us. Yekidusan Amlake Ethiopian Yitebikat, Amen.

Dn Haile Michael from Debretsige said...

Dear Brothers & sisters,

I don't understand what we are waiting for?
Who is terrorist ?It is clear for the government.Begashaw & his group collected gangsters from every corner of the country & tried to mess up.And "Abune"Pawlos is clearly supporting this gangsters who messed up in different parts of the country .
I think this issue is obvious to the government.
So why should our brothers and sisters who asked their religious fathers necessary questions within their diocese be in prison ,even for a day ?
Let us make a peace demonstration by asking the imprisoned brothers to be released as soon as possible.
Let us stop "Abune" Pawlos.
Look, next they are going to imprison Sunday school student.
All orthodexes around the world inform this issue to your brothers & sisters .Let us make peace demonstration through out the country one day not latter than a week for our religious freedom.
Let us work hard in informing all the laity & clergy to get ready for the peace demonstration.
They are testing us .This is the right time even for martyr.
Deselam please coordinate this issue as soon as possible.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)