October 15, 2011

ተሐድሶዎች በስም ሥርቆት ዘመቻ ተጠምደዋል፣ የእውነተኛ ኦርቶዶክሳውያንን ስሞች መጠቀም ጀምረዋል


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 3/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 14/2011)፦ ለብዙ ጊዜ በሐሰት ትምህርትቻው ምንም ነፍስ መማረክ ያቃታቸው አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም በማስመሰል፣ አርማቸውን እና ፎቶግራቻውን በመጠቀም ለማጭበርበር በመሞከር ላይ ናቸው። በዚህ በአዲሱ ዘዴ ስሙን እና ፎቶግራፉን በፌስቡክ መጠቀም የጀመሩት መ/ር ዘመድኩን በቀለ ነው። በእርሱ ስም ያወጡት መልእክት የሚከተለው ነው።

በሚቀጥለው የሊቃውንት ጉባኤ ላይ እነ በጋሻው በተለያዩ የተሃድሶ ደጋፊዎች ጥረት ነጻ የሚወጡ ከሆነ በየቦታው ያሉ ሰንበት ተማሪዎችን በማስተባበር ሸቃሾጮችን ከቤተክርስቲያን ጠርገን በሃይል ማስወጣት አለብን፡፡ በጋሻውም ሆነ ግብር አበሮቹ ተጠራርገው ሊወጡ ይገባል፡፡ ሳይሆን ማንኛችንም መተኛት የለብንም፡፡ ተሃድሶዎች የሚጫወቱብን ፓትሪያርኩን ተገን አድርገው ነው፡፡ እሳቸውንም ቢሆን ልንለቃቸው አይገባም፡፡ ሽጉጣቸውን አስጥለን ወደ መጡበት እንመልሳቸዋለን፡፡

ዘመድኩን ይህንን እንደማይል ለመገመት ብዙም ሊቅነት አይጠይቅም። ነገር ግን ፎቶግራፉን የተመለከተ እና ጥንቃቄ ያላደረገ ሰው በቀላሉ ሊሳሳት እንደሚችል መገመት ይቻላል። ከዚህ አስቀድሞ የዚህ ዓይነቱ የማታለል ዘመቻ ሰለባ የነበረችው ደጀ ሰላም ስትሆን በፌስቡክ ላይ “ደጀ ሰላም” በሚል አርማዋን እና የምትጠቀምባቸውን ፎቶዎች ኮፒ በማድረግ ለማሳሳጥ የሚሞክሩ ብዙ ግለሰቦች ከመኖራቸውም በላይ በብሎግ እና በዌብሳይት ደረጃ ከሁለት ያላሱ “ደጀ ሰለሞች” መከፈታቸውን ለማወቅ ችለናል።

ከደጀ ሰላም ውጪ ስም ጠፍቶ ሳይሆን አንባብያንን በለመደው ስም ለማሳሳት የተጠቀሙበት የበግ ለምድ ስርቆት ነው። ለምዱ የበግ ቢሆንም ተኩላዎች መሆናቸውን ማንም ኦርቶዶክሳዊ ያውቀዋል። ከዚህ አስቀድሞ አባ ሰረቀ በሚመሩት የቤተ ክህነት ድረ ገጽ ላይ ደብዳቤውን “ፎርጅድ” ሰርተው ለማታለል የሚከሩበት ማ/ቅዱሳን ጉዳዩን በይፋ በማስታወቁ አባ ሰረቀ እና ድረ ገጻቸው ፎርጅዱን ደብዳቤ ቶሎ ለማውረድ ቢገደድም የተሐድሶ-መናፍቃን ብሎጎች ግን አሁንም ድረስ ያንን ፎርጅድ ደብዳቤ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ።

7 comments:

sisay said...

ሰላም ደጀሳሞች፡-

በጣም አስገራሚውን ትይንት በማውጣታችሁ እጅግ አመሰግናችዃለሁ። በዚህ አጋጣሚ ወንድማችን መ/ር ዘመድኩን ና ሌሎች ለተመሳሳይ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ወንድሞች፤እህቶችና ድርጅቶች የእነሱ መግለጫ የሆኑውን ፎቶና ተመሳሳይ ዶክመንት በመላክ ብሎክ ማስደረግ ይችላሉ። ዘመድኩን ይህ ባስቸካይ ቢያደርግ ጥሩ ይመስለኛል።

Anonymous said...

በጣም የሚገርመዉ ነገር በተመሳሳይ ሁኔታ የኔንም ጓደኛ የቅዱስ ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓግ ዲያቆን ሲሆን በስሙ ፌስ ቡክ ከፍተው እንዲሁም የሚጠቀምበትን ፎቶ በመውሰድ እጅግ አጸያፊ መልእክቶችን እንዲሁም የተለያዩ ሰዎች ዎል(wall)ላይ ስድቦችን ሲጽፉበት ነበረ:: ሆኖም እደተነቃባቸው ሲያውቁ ትተዉታል ለጊዜው:: በእውነት እነዚህ ሰዎች አሁን ነገሩ ሁሉ ግራ እየገባቸው ስለሆነ አማራጭ የሚሉትን ሁሉ ከመጠቀም ወደኋላ አይሉም!!! የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሄር ቤተክርስቲናችንን ይጠብቅልን ልጆቿንም በእምነት እና በምግባር ያጽናልን አሜን!!!!
መ.ዘ ከሽሮ ሜዳ

Anonymous said...

sira yefeta siraw hulu tenkolina wushet new.sira yata aemiro yeseyitan labratory silehon minim bilu ansemachewum.B/c our effort is to clean tehadiso from our church.

Anonymous said...

yihea tegbar yemiyameleketiw ..tehadsowch min yahel tesefa bemekuret lay mehonachewn new ...egzabher lbona yisetachew ...diros leba yaw new siraw sirkotna haset

Anonymous said...

Why does not Dn. Zemedkun report to face book and telling them that they are using his identity. They will immediately suspend the account.

Anonymous said...

EGIZEABEHARE kaga gara nawena anefarame.ebakachohe neseha gebona tamalaseo gezachehone bamayadenacheohe nagare atatefo

Anonymous said...

Who are the real and the false orthodox? Do you have any other criteria apart what the church has set as a criteria to be an orthodox?

I think you want to say Tehadsos are using the real Mahibere Kidusan names. If that is so it makes real sense!

Don't try to lit too much as you may fail into the holes that you are digging for yourself.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)