October 29, 2011

(ሰበር ዜና) ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀን ከሥልጣናቸው አወረደ


Adios Abba Sereke!!!!!!!!!!!!!!
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 29/2011, PDF)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወደል ሳሙኤል ዛሬ ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነባቸው። ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣
ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ናቸው።

አባ ሰረቀ ከሓላፊነታቸው እንዳይነሡ በጥብዓት ሲከራከሩላቸው የቆዩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይዘውት የነበረውን አቋም እንዲቀይሩ ወጣቱ በቅርቡ ያሳየውን ተቃውሞ የተረዳው መንግሥት ተጽዕኖ ሳያደርግ አልቀረም ተብሏል። መላው ኦርቶዶክሳዊ እና የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶው ቤተሰብ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እና ለቅ/ሲኖዶስ ያለውን አክብሮት በመግለጽ ላይ ይገኛል።
ዝርዝር ዜናውን ጠብቁ
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ከዚህ በፊት ከዘገብናቸው ዜናዎች መካከል የሚከተሉትን ይመልከቱ
የሰሞኑ የዜና ርዕስ የሆኑት አባ ሰረቀ ማን ናቸው? በአሜሪካ ምን ምን ሲሰሩ ኖሩ?

የሰሞኑ የዜና ርዕስ የሆኑት አባ ሰረቀ ማን ናቸው? በአሜሪካ ምን ምን ሲሰሩ ኖሩ?

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 27/2009)፦ ሰሞኑን በማኀበረ ቅዱሳንና በጠቅላይ ቤተ ክህነት አንድ መምሪያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ፈንድቶ መውጣቱንና መንግሥትን ማሳተፉን ከሰማን ወዲህ ስማቸውን በጉልህ መስማት ከጀመርናቸው ሰዎች መካከል አንደኛውና ግንባር ቀደሙ ሰሜን አሜሪካ የነበሩትና በደንብ የምናውቃቸው “አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል” ናቸው። ስለዚህ ይህ ጽሑፍ ስለኚሁ ሰው የአሜሪካ ቆይታ እውነተኛ እማኝነት ይሰጣል። ቤተ ክርስቲያናችንን የሚመሯትና ነገ ጳጳስ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት እኚህ ሰው ምን ዓይነት ሰው እንደሆኑ ያብራራል።

አባ ሰረቀ የዛሬ 15 ዓመት አካባቢ ወደ አሜሪካ ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሄዱት ወደ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ነበር። በዚያም አባ ኃ/ሥላሴ ከተባሉ አባት ጋር የጻድቁን የአቡነ አረጋዊን ቤተ ክርስቲያን ማገልገል ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ አባ ሰረቀ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የሄዱበት አካባቢ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ሰላም በማወክና በመበጥበጥ የታወቁ እንደመሆናቸው አቡነ አረጋዊንም ወዲያውኑ መበጥበጥ ጀመሩ። የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያንን ቦርድ በመቅረብ “መቀደስና ማገልገል የምፈልገው በትግርኛ ቋንቋ ብቻ ነው” ማለት ጀመሩ። በዚህም የዘወትር አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ግዕዝንና አማርኛን ዜሮ አደረጓቸው። ቦርዱን በመጠምዘዝና በማሳመን በትግርኛ ብቻ እንዲቀደስ ለማድረግም ችለው ነበር።

በዚህ መልክ ከ6-8 ወራት ከቆዩ በኋላ በቦርዱ አባላት መካከል እንደገና ጥርጥር፣ አለመግባባትና ልዩነት በመፍጠር ለመክፈል ሞከሩ። ወደ ትግርኛ የቀየሩት ቅዳሴ አላዋጣ ሲላቸው ወይም “ስልታዊ ለውጥ” ማድረግ ሲፈልጉ እንደገና “ወደ አማርኛና ግዕዝ” መመለስ ፈለጉ። በዚህ ጊዜ ቦርዱ እምቢ አለ። “ለምን መጀመሪያ ወደ ትግርኛ ወሰዱን ለምን ይመልሱናል? እኛ የእርስዎ መጫወቻ አይደለንም። ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ለምደውታል” ብለው እምቢ አሉ።

አባ ሰረቀ ይህ አልሳካላቸው ሲል ዲሲ አካባቢ ከሚገኘው የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጋጭተው የወጡ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በማስተባበር “ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት” ተስማሙ። ይህ ከመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የወጣው ቡድን ያን ጊዜ የአሜሪካ ሀ/ስብከት አሁን የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ማትያስን በማነጋገር “በትግርኛ ብቻ አገልግሎት የሚሰጥበት ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት” ሞክረው ሳይሳካላቸው የቀሩ እንደነበሩ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። እናም በሎስ አንጀለስ አቡረ አረጋዊ ያልተሳካላቸው አባ ሰረቀ ቨርጂኒያ ሌላ የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን “ከፈቱ”። የሎስ አንጀለስ ምዕመናንን ያሳሳቱት ሳይበቃ የቨርጂኒያዎችንም አጭበርብረው በዘረኛ መንፈሳቸው የዋኃኑን አጠመዷቸው። ትናንትና አባ ሰረቀ “የከፈቱት አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን” ዛሬ ደግሞ አባ ኃ/ሚካኤልን የመሰሉ መናፍቅ መነኩሴ አቅፎ ይዟል። (አስተዳዳሪው ቀሲስ ተከስተ የተባሉ ወጣት ቄስ ናቸው)። አባ ኃ/ሚካኤል ከአባ ሰረቀ ሚሽን ተቀብለው ወደ አሜሪካ የመጡ መሆናቸው በስፋት ይነገራል፤ ይታወቃልም።

አባ ሰረቀ ወደ ቨርጂኒያ እንደመጡ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስን በመቃወም ማስተማር ጀመሩ። ብፁዕ አቡነ ማትያስን ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ጵጵስናንና ፕትርክናን በመቃወም “ጳጳስም፣ ፓትርያርክም አያስፈልግም” እያሉ ዐውደ ምሕረቱን ከያዙ ጀምሮ በትግርኛ ብቻ በመቀደስና ማስተማር ክፍፍልን መዝራት ጀመሩ። “ጳጳስ አያስፈልግም አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ከሆነ እኔ ራሴ ‘መባረክ’ና መክፈት እችላለሁ” ማለት ጀመሩ። በዚህ የተጀመረው ልዩነት ሰፍቶ አቡነ አረጋዊን ራሱን ለሁለት ለመከፈል አበቁት።

ከዚያም የቤተ ክርስቲያኑን ስምና ንብረት በመውሰድ ጥለው ወደ አሌክሳንደሪያ (ቨርጂኒያ) ሄዱ። በዚያው ስም አቡነ አረጋዊ ብለው በመሰየም “አዲስ ቤተ ክርስቲያን ከፈቱ”። በአባ ሰረቀ ጎትጓችነት ተታለው ከመድኃኔዓለም ወጥተው የነበሩትም ምእመናን ልዩነታቸው በማቻቻል ከቀደመው ቤተ ክርስቲያናቸው ጋር ታረቁ። ይሁን እንጂ አባ ሰረቀ ንብረታቸውን በሙሉ ዘርፈው እንደወጡ እንዲቀሩ አልፈቀዱላቸውም። የሕግ ዕውቀት ያላቸው ሰው በማነጋገርና ርዳታ በማግኘት አባ ሰረቀን ሕግ ፊት አቆሟቸው። አባ ሰረቀም የወሰዱትን ሀብትና ስም በሙሉ በግድ ለመመለስ ተገደዱ። በሕግ ፊት የተዋረዱት አባ ሰረቀም አቡነ አረጋዊን አስረክበው ሲያበቁ በቅ/ጊዮርጊስ ስም “አዲስ ቤተ ክርስቲያን በቨርጂኒያ ከፈቱ”። ይህ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም በቨርጂኒያ እንደሚገኝ ይታወቃል።

አባ ሰረቀ በዚህ መልክ ቤተ ክርስቲያንን ሲከፋፍሉና ሲያዋርዱ ቆይተው ጊዜ እየተቀየረ ሲሄድ “ጳጳስ የመሆን ሌላ ጾር ሲነሣባቸው” በፊት “አያስፈልግም” ሲሉት የነበረውን “ጵጵስና፣ ፕትርክና እና ቅዱስ ሲኖዶስ” ሸውደው “እጅ ሰጥተው” የአቡነ ጳውሎስ ጋሻ ጃግሬ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ። አባ ሰረቀ የዲሲና አካባቢው ማህበረ ካህናት ጉባዔ አባል በነበሩባቸው ዘመናት ሁሉ እያጥላሉ ሲሳደቡ የነበሩትን ፓትርያርክ “ካለ እርስዎ ሰው የለም፣ ቅዱስ የለም” ብለው ጫማ ስመው የመምሪያ ኃላፊነት ሽልማት ተሰጣቸው። ይሁን እንጂ ሲጓጉለት የነበረው ጵጰስና ሳይሳካላቸው ቀረ። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑ ብፁዓን አባቶች “እንዲህ ዓይነቱን ወንበዴ፣ ቤተ ክርስቲያንን ሲያሰቃይ የኖረ ሰው እንዴት ጵጵስና እንሾመዋለን” በማለታቸው ሳይሳካ ቆይቶ ነበር። ውስጥ አዋቂዎች እንደሚናገሩት ከሆነ በመጪው ጥቅምት በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጵጵስና እንዲሾሙ ይቀርባሉ ከሚባሉት አባቶች መካከል አንደኛው እኚሁ ዘረኛ መነኩሴ አባ ሰረቀ ብርሃን እንደሚሆኑ ታውቋል።

አይ ዘመን፤ የሚገርመው እኚህኑ አባ ሰረቀን ዛሬ እሑድ በተላለፈው የሀገር ፍቅር ሬዲዮ ላይ ድምጻቸውን ሰማነው። ያውም የቤተ ክርስቲያን “ጠበቃና ተቆርቋሪ” ሆነው። አይ ቤተ ክርስቲያን!!! መከራሽ አያልቅ!!!
ቸር ወሬ ያሰማን


ይህ ሰው (አባ ሰረቀ) ማን ነው?
Dejeselamoch,
Who is Aba Sereke? Please post an article about him and what he did to our church, if you get information.
September 22, 2009
++++++++++++++++++++++++++++
(ከዘመቻ)
(September 25, 2009) አንድ ደጀ ሰላማዊ “አባ ሰረቀ የሚባለው ስው ማነው? ይህን ያህልስ ማቅን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳበትስ ዓላማው ምንድር ነው?” ሲል መጠየቁን መነሻ አድርጌ የህሊና የውልደት ስብራት ስለገጠመው አባ ሰረቀ (ስም ግብርን ይመራዋል እንዲሉ በ“ሠ” ስሙን አለመጣፌን ልብ ይሉዋል) ማንነት ጥቂት ለማለት ፈለግሁ።

ለነገሩ ይህን ያህል አጀንዳ ሊሆን የሚገባው ሰው እንኳን አልነበረም። አባ ጳውሎስ እንደ ጫማ ውስጥ ጠጠር እየቆረቆረ ዘወትር እረፍት የሚነሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ “ሳልጠራው አቤት ሳልከው ወዴት የሚል፣ ህሊናውን የተነሳ ሰው ፈልጉልኝ” ብለው ወዳጆቻቸውን፣ (መቼም የልብ ወዳጅ እንደሌላቸው የታወቀ ነው፣ እንደ ንጉሴ ያሉ ጥቅመኞች ያሉትን ለማለት ነው) አደራ ባሉት መሰረት ግዕዛን ከሌላቸው እንስሳት የሚመደብ፣ እውነትን እንኳን በተግባር በስም እንኳን የማያውቃት፣ የሥልጣን ጥም ያናወዘው፣ በፍቅረ ነዋይ ልቡ የታወረ፣ አባ ሰረቀ በመብራት ተፈልጎ ተገኘ። አባ ጳውሎስም “ልቤ በሰረቀ ጸና” አሉ።

በእርሱም ልባቸውን አኖሩ። ማኅበረ ቅዱሳንን ባልዋለበት እንደዋለ አድርጎ እንዲከስ ግዳጅ ተጣለበት። ከላባው አባ ላይ ታች ማለቱን ተያያዘው። የማኅበሩን በጎ ስም የሚያጠፋ የሥድብ መጥሀፍ አጻፈና በውድቅት ሌሊት በገንዘብ የገዛቸው ግብር አበሮቹ ፖስተሩን ሲለጥፉ ሁሉ በፖሊስ አስከመያዝ ደርሰዋል። ዳሩ ግን ውሎው ከኢሕአድግ ባለስልጣኖች ጋር የሆነው አባ ሰረቀ ማህበሩን የቅንጅት ቀኝ እጅ እንደሆነና በሚድያዎቹም የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ምእመኑ በመንግስት ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ እንደሁኑ አቀረበ (ለምሳሌ በጅማውና በኢሊባቡር በክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ውድመት መግለጹን) ።

በተለያዩ ግዜያት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በአክራሪ ሙስሊሞች አማካይነት የደረሱትን ጭፍጨፋዎች፣ አባ ጳውሎስና መሰሎቻቸው እፍን አድርገው ልክ እንደ ተረቱ “አትናገሩ ጅቡ እኔን እየበላኝ ነው” እንደሚለው ገዳማውያኑ አባቶች እየተገደሉ፣ ክርስቲያኖች ከነ ማተባቸው እየታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ፣ እነ አባ ጳውሎስ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ደም ለስልጣናቸው ማቆያ ገፈራ አድርገው ሲያቀርቡ ኖረዋል።

ዛሬም አይናቸውን በጨው አጥበው የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እንደለመዱት መሬት ላይ ጥለው ሄሮድሳውያን ጌቶቻቸው ሲረጋግጡት ዓለም ሁሉ እንዲያይና ቤተ ክርስቲያኒቱን መሳቅያ መሳለቂያ እንዲያደርጋት ሲያደርጉ በቴሌቪዥን መስኮት ለማየት በቃን። በሲኖዶስ መንበር ላይ ቄሳሮች ተሰይመው ሲዳኙ ለማየት በቃን በአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ምን ያልታየ ጉድ አለ የቤተ ክርስቲያኒቱን እድገት የማይሻውና ሰበባሰበብ እየፈለገ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያጣጥላት የኢሃድግ መንግስት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመናፍቃንና ከአክራሪዎች ወከባ ይታደጋት ዘንድ እግዚአብሄር ያቆመውን ማኅበር በማፍረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዳከም በያዘው ስትራቴጂ መሰረት አስቀድሞ በአባ ጳውሎስ አቀነባባሪነት በአባ ሰረቀ ተላላኪነት የተዘጋጀው ትርኢት መድረኩ ላይ እሰከሚገኙ ድረስ ተሳታፊዎቹ እንኩዋን አያውቁም ነበር። አስቀድሞ የተቀነባበረው ቅንብር በህሊና አልባው በመነኩሴ አምሳል በተሰረው ሮቦት በአባ ሰረቀ ቀርቦ በፖለቲካው አጋፋሪ መመሪያ ሰጪነት በአባ ጳውሎስ አሳራጊነት የትርኢቱ ፍጣሜ ሆነ።

በጠቅላላው አባ ሰረቀ ማለት አባ ጳውሎስ ሰራሽ ሮቦት ነው፤ አልቦ ኅሊና።

+++++++

የሊ/ካህናት ጌታቸው ዶኒ እና የአባ ሰረቀ ምስጢራዊ ደብዳቤ

    . ‹‹ወጣቱን በተሐድሶአውያን ኅብረት አዲስ ጥምቀት በማድረግ በ‹ቅን ልቦና የመንፈሳዊ የፈውስ አገልግሎት› ሥር መሰብሰብ፤››
    . ‹‹ሐሳባችንን የሚያደናቅፉ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎችን ተቋቁመን ልንጥላቸው ይገባል፤››
    . ‹‹ወላጅ በሌላቸው ሕፃናት ስም የገንዘብ እና አልባሳት ርዳታን ከሙሉ ወንጌል አማኞች ማኅበር በመቀበል እና የቤት ለቤት ማጥመቅ ተግባራትን በመፈጸም እንቅስቃሴውን ማጠናከር፤››

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 30/2010)፦ ራሳቸውን ‹‹የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሕጋዊ ወኪል›› በማለት በይፋ የሚጠሩት እና የሰፋሪ ገነት አቃቂ ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ፣ ቤተ ክርስቲያንን ‹‹በተሐድሶአውያን ኅብረት›› ለማጥመቅ በሚል ያቀዱበት፣ ለዚህም እንቅስቃሴያቸው ማጠናከርያ የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት በአጥቢያቸው ከማሠራት ጀምሮ ሌሎች የገንዘብ
ማሰባሰቢያ ስልቶችን የነደፉበት እና ይህንኑ ውጥናቸውንም በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መ ሐላፊ ከሆኑት ከአባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጋራ በሐሳብ የተስማሙበት እና የመከሩበት መሆኑን የሚገልጽ በእጃቸው የተጻፈ ደብዳቤ ለደጀ ሰላም ደርሶ ተመልክተነዋል፡፡
በቀን 05/02/2002 ዓ.ም እንደ ተጻፈ የተመለከተበት ይኸው ደብዳቤ የሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ የግል ማኅተም እና ፊርማ ያረፈበት ነው፡፡ የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ዳግመኛ ታይፕ በማድረግ ከእጅ ጽሑፉ ጋራ አባሪ በማድረግ ያቀረብንላችኹ ሲኾን በይዘቱ ላይ የተመሠረተ ዝርዝር ሐተታ በቀጣዮቹ ቀናት የምናስነብብ መኾኑን እንገልጻለን፡፡
                                                     ቀን፡- 05/03/2002

ለአባ ሠረቀ ብርሃን
ለሰንበት ት/ቤቶች መምሪያ ሐላፊ፤

       የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኹ፣ እንደሚታወቀው ባለፈው በተነጋገርነው መሠረት ጉዳዩን እየሄድኩበት እገኛለሁ፡፡
እንደሚታወቀው አንዳንድ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች የግል ማኅደሬን ለማበላሸት የፓትርያሪኩን ሕጋዊ ወኪልነቴን ለመሻር ደብዳቤ ጽፈውብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ሐሳባቸውን አክሽፌባቸዋለሁ፡፡ በመሆኑም አቡነ ይስሐቅ እንድነሣ ሊያደርጉኝ ቢያስቡም በአቡነ ገሪማ ጸሐፊነት ደብዳቤው እንዲመለስልኝ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም ጋዜጣ ላይ የጻፍኹት ራሴን ለማስተዋወቅ አይደለም፡፡ የፀረ ሰላም ኀይሎችን ምስጢር ነው ያወጣሁት፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን በእርስዎ በኩል ይጠበቅብዎታል፣ ምክንያቱም በርካታ ሰንበት ት/ቤቶችን በመምሪያው ሥር ማግኘት ስለምትችሉ፣ ቤተ ክርስቲያንን በወጣት ኀይል ነውና ማደስ የሚቻለው ጠንክረን መሥራት እንችላለን፡፡
እኛ ሣራ የወለደችን በመሆኑ እናታችንን ከኋላ ቀር አሠራር እና ባህል አላቀን፣ ወጣቱን በተሐድሶአውያን ኅብረት አዲስ ጥምቀት በማድረግ ‹‹ቅን ልቦና የመንፈሳዊ የፈውስ አገልግሎት›› ሥር ልንሰበስባቸው እንችላለን፡፡
የካናቴራ አልባሳት ማሠርያ ለማሠራት በጎ ፈቃደኞችን እየጠቆሙኝ ነው፡፡ ስለዚህ እኔም የማጥመቅ ሥራ በየቤቱ እየዞርኹኝ እያጠናከርኩኝ ነው፡፡ እርስዎም ይህን መንገድ በተሻለ መንገድ አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፤ ስለ ገንዘቡ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ 170 ሺሕ የሚያወጣ ሐውልት በእኛ ደብር ስለምናሠራ ከዚያ ላይ በሚገኘው ገንዘብ ልናጠናክረው እንችላለን፡፡ በዙሪያው ያሉ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎች ይህን ሐሳባችንን ሊያደናቅፉ ቢችሉ እንኳን ተቋቁመን ልንጥላቸው ይገባል፡፡
በመጨረሻም የሙሉ ወንጌል አማኞች ወላጅ ለሌላቸው ሕፃናት የገንዘብ እና የልብስ ድጋፍ ስለሚያደርጉልን ሕፃናትን መመዝገብ አለብን፡፡ በዚህ እኔ ባለሁበት ደብር አባ ገብረ ሥላሴ የተባሉት በስማቸው የመሠረቱት የሕፃናት ማሳደጊያ በርካታ ልጆች ስላሉ፣ በዚህ ማሳደጊያ ስም ልናገኝ እንችላለን፡፡ ስለዚህ በገንዘቡ በኩል በእንዲህ ዐይነት ኹኔታ ላይ ስለሆንን እርስዎ ወጣቱን በማነሣሣት ትልቅ ሥራ ሊሠሩ ይገባል፡፡ በተረፈ አዳዲስ ነገር ሲኖር በስልክ በመደዋወል እንጨርሰዋለን፡፡
                                      
 ‹‹ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር››
                                         ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ
                                   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሕጋዊ   ወኪል           

40 comments:

Anonymous said...

Oh, the Almighty God is with us! Thanks to our fathers and for those who fought bravely for our beloved church, at least one wolf has been dethroned.

Anonymous said...

Kalayehu alaminim .Thank you Dejeselamoch, Betwatu cher wore endasemachihun cher wore yasemachew. Please can you do a photoshop of "Seber zena and the website" so that everybody can share the news and Wow!!!!!

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን፡
እግዚአብሔር አምላክ አባቶቻችንን ይጠብቅልን፡፡

Gebre Z Cape said...

You even made my day more happier than before. I pray that our fathers still make decisions for the sake of the church; not for the person they supporting, not for Mahiberekidusan or not for the patriarch or even for themselves.

For Aba Sereke libonachewuin amilak yigobign, asiteway libonan ena tsegan yisitachewu. No one happy is about the fall of someone( የማንንም መውደቅ አንፈልግምና አባ ሰረቀ እውነቱን አውቀው እንዲመለሱ እንጸልይ:: የማይመለስ ሲሆን እና ሕጸጽ ሲኖር ከቤተ/ያን አመራርነት አይደለም ከአባልነትም ማባረር ተገቢ ነው:: ሲኖዶስም ይህንን እያደረገ ይመስለኛል::).

So let us pray for Aba Sereke so that he can come to the truth and worship GOD in faith not for money or fame or something else, Amen!

Anonymous said...

Egziabher yetegaretewun yebetechristian fetena hulum yastekakililin. tesfa wodemekuret ena wode kifu neger sanigeba amlak yebetechristianin chigir beselam yifitalin. legna tesfachin betechristian bicha nech. Woladite amlak tirdan.

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን፡
እግዚአብሔር አምላክ አባቶቻችንን ይጠብቅልን፡፡

Anonymous said...

Days are shining coz z root of tehadiso has fallen

Anonymous said...

I never liked him Fanuel too from the begining. The later one from many now is still out here messing up our church; Abba Fanuel. Check him out properly too. The evil once will be casted out no matter how long it takes.

Anonymous said...

ተመስገን...ተመስገን...ተመስገን...ተመስገን...ተመስገን...ተመስገን...ተመስገን...ተመስገን...ተመስገን... ሌላ ምን ይባላል?
አሁንም ቸር ወሬን ያሰማን!!!!

Anonymous said...

Egziabher yetemesegene yihun betam tiru zena new yesemanew. Mechem endexhristian leaba serekem metseley tiru new wondimoche.Ersachewum yegna wondmi nachew. Gin Kemanignawum siltan ansito Nisiha endigebu ena temelisew betechristianin endiagelegilu madireg tegebi yihonal. Lelaw degmo, dejewoch, ebakachihu ezih yalenew yeteleyaye yepolitica akuam endalen ewokuna silebetechristian bicha tsafu. Mengist balesiltanatim wust endezaw new. Andandochu sile eminet gid yelelachew ena politica bicha hiwot yemimesilachew alu. Andandochu betechristianin yemiwodu ena yemidegifu alu. Abizitew demo yemiteluat ena kifu mignot yalachewum alu. Silezih betikikil mereja sinoren bicha new silemengist manisat ena menegager yalebin. MInalibat.....lihon yichilal yemil atsatsaf alasidesetegnim. Mengistim tiru neger siaderg mamesgen, siabelash betikikil lemimenu megilets, mereja kale bicha. wanaw neger gin, mengist degefenim aldegefenim egna lebetechristian megadelachinin anakomim. Silezih betselot, begenzeb, ena eskehiwot mesiwatinetim diresim bihon mebertat alebin. Egziabher lehulachinim mastewal ena Selamun yabizalin.

Semaynesh said...

በአባ ሰረቀ የተወሰነ ውሳኔ ይህ ከሆነ በማሕበረ ቅዱሳን ምንያህል ከባድ ውሳኔ እንደተወሰነ ያሳየናል።
እግዚአብሔር እንደ ግብራችሁ ያውጣችሁ!

ZeGiyorgis said...

የአባቶቻችን አምላክ ዛሬም ከእኛ ጋር ነው፡፡ አባቶቻችን እናመሰግናችኋለን፡፡ አምላካችን አማናዊ ዳኛ ነውና እንዲህ በጉባኤ ያዋርዳል፡፡ ሰው ከሰው ምክርና ተግሣጽ ካልተማረ ከመከራው ቢያንስ መማር አለበት፡፡ ሰውየው አሁንም ጊዜ አላቸው፡ ቀሪ ዘመናቸውን ለንስሃ ቢያደርጉት፡፡ሌሎች የተሃድሶ ጭፍራዎችና የቤ/ክ ጠላቶች እባካችሁ ከአባ ሠረቀ ተማሩ፡፡

ZeGiyorgis said...

የአባቶቻችን አምላክ ዛሬም ከእኛ ጋር ነው፡፡ አባቶቻችን እናመሰግናችኋለን፡፡ አምላካችን አማናዊ ዳኛ ነውና እንዲህ በጉባኤ ያዋርዳል፡፡ ሰው ከሰው ምክርና ተግሣጽ ካልተማረ ከመከራው ቢያንስ መማር አለበት፡፡ ሰውየው አሁንም ጊዜ አላቸው፡ ቀሪ ዘመናቸውን ለንስሃ ቢያደርጉት፡፡ሌሎች የተሃድሶ ጭፍራዎችና የቤ/ክ ጠላቶች እባካችሁ ከአባ ሠረቀ ተማሩ፡፡

Temelkach said...

What if Paulos put him to that same position tomorrow? Havent we seen similar cituations before ( YEPAULOS HAWLT KINTAT LEWT ALASAYEM)

Remeber, whatever Synod decide does not mean it become practical as far as paulos is in power.

I will be pleased when this decission is implemented not now.


Let us simply keep praying.

Temelkach said...

What if Paulos put him to that same position tomorrow? Haven't we seen similar cituations before ( YEPAULOS HAWLT KINTAT LEWT ALASAYEM)

Remeber, whatever Synod decide does not mean it become practical as far as paulos is in power.

I will be pleased when this decission is implemented not now.


Let us simply keep praying.

ተዋህዶ said...

የተሃድሶው አቀንቃኝ አባ ሰረቀ መነሳቱ ጥሩ ቢሆንም ማህበረ ቅዱሳን ግን ችግሮቹን እስካልፈታ ድረስ ችግር ወደፊትም ይገጥመዋል:: እኔ በግሌ ከምሰጣቸው አስተያየቶች ውስጥ (ማስተባበያ ሊቀርብባቸው የማይችሉ)

1 የማህበሩ አባል ወይንም ደጋፊ ያለሆነን ሰው ሁሉ አትኮንኑ
በግልጥ ስለምትኮንኑ
2 ማህበረ ቅዱሳን ወንጌል ጠለቅ ተብሎ ሢነገር ነገር አለ አትበሉ

3 ዶግማና ቀኖናን ትውፊትና ሃይማኖትን ለይታችሁ እወቁ:: ለይተው የሚያስተምሩ ሰዎችንም አትንቀፉ

4 ኢየሱስ ክርስቶስ ሲነገር ሲሰበክ አትደንግጡ አትፈሩ:: ኢየሱስ የኦርቶዶክስ እንጂ የጴንጤ አይደለምና::

5 በቤተ ክርስቲያን ገድላትና አዋልድ መጽሃፍት ውስጥ ያሉ ስህተቶች በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲስተካከሉ ተባበሩ::

ይህንን ስናደርግ ቤተ ክርስቲያንን አንድ ወደ ሚያደርግ የተቃና የወንጌል ጉዞ መምራት እንችላለን::

የእግዚአብሔር ቸርነት አይለየን

Anonymous said...

Deje Selam,
cher were yasemachihu!!! Melkam zenan yemitaders blog endet yetadelech nat!! Nefse Hasetn adrigech. Ahunm betselot besira eniberta!
Yekidusan amlak ayileyen, Amen!

Anonymous said...

thanks GOD

Orthodoxawi said...

Thanks to God! He knows how to clean his house!
Lets hope that the other tehadso-protestants will also be pushed out of our mother church!

Long Live Tewahedo!

lele said...

enamenalane BAMELAKACHEN tamasegan
tamasegan tamasegan............

Anonymous said...

we will be back!!!!!
we love aba sereke

Desta said...

"...ክርስቲያኖች ከነ ማተባቸው እየታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ፣ እነ አባ ጳውሎስ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ደም ለስልጣናቸው ማቆያ ገፈራ አድርገው ሲያቀርቡ ኖረዋል።"

ይህቺ ነጥብ በጣም ልቤን ነካችኝ:: ባለፈው ለትግራይ ኪነት አባላት ግን ሄደው አስቀብረው "አጽናንተው" ተመልሰዋል:: ፈራጅ እግዚአብሔር ነው:: በየትኛውም መልኩ ነፍሳቸው ከስጋቸው የተለየችው ሁሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን እንደሆኑ ውስጤ ሁሌም ያዝናል:: እኚህ አባት ግን የሚያሳዩትን አድልዎ ፈጣሪ ያያል:: ለእርሳቸውም ልቦና ይስጣቸው::

ልሳነ ሳህል ከሎንዶ said...

ግሩም ድንቅ ነው የአምላክ ሥራ:: ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏልና የአባ ሰረቀ "ስምን መልአክ ያወጣዋል ማለት እንዲህ ነው እውነትም ሰረቀ ለሌቦች አባት እርሱንና መሰሎቹን ከቤተ ክርስቲያናችን ጠራርጎ ለማስወጣት ትግሉ ይቀጥል የሚታደስ ሃይማኖት የለንም በርቱ እንበርታ::

Anonymous said...

አጽናን እኛን አጽናን እኛን አጽናን እኛን በእምነታችን

Balemlay said...

አንድ ቀበሮ ከቤተክርስትያን ዉስጥ ተባረረ ማለት ነው:: ይሄን ያሳየን አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

lele said...

tamasegane abate hoy

Unknown said...

ተመስገን እባክህ ፈጣሪ ታደገን!

Anonymous said...

ሰላ ደጀ ሰላሞች....የአባ ሰረቀን መሻር ያሰማን አምላክ ይክበር ይመስገን.......በሎሳንጀለሱ የጥፋት ተልኳቸው ላይ ግን ጥቂት ማስተካከያ ለመስጠት እፈልጋለሁ...እሳቸው ሎሳአጀለስ በነበሩበት ጊዜ ሊቀ ጉባኤ አባ ኃይለ ሥላሴ ገና አልመጡም ነበር። አባ ሰረቀ እዚያ እያሉ ብዙ ጥፋቶች ከማጥፋታቸው በተጨማሪ ምእመኑ ተንኮላቸውን እንደተገነዘበ ሲረዱ እሄዳለሁ ብለው ተነሱ ታቦቱንም በወቅቱ በሳንዲያጎ ሲያገለግሉ ለነበሩት አባት (ለአሁኑ ብጹእ አቡነ ኢሳይያስ)በአደራ እሰጣለሁ እንጂ ለዲያቆን ትቼ አልሄድም በማለት ታቦቱን አሻግረው በሳምሶናይት ውስጥ ወንጌል አድርገው ራይድ በሰጧቸው ምእመናን ፊት በማስረከብ አታለውና ህዝቡን አሳዝነው ኮብልለዋል። ከዚህ በኋላ ለ3 ወራት ያለ ካህን የሎሳንጀለስ ምእመናን በየሰንበቱ እየተገናኙ የሚችሉትን ጸሎት እያደረሱ ከቆዩ በኋላ ነው ሊቀ ጉባኤ አባ ኃይለ ሥላሴ የመጡት። ሊቀ ጉባኤ ያዘነውን የሎሳንጀለስ ምእመን በማጽናናት ላለፉት 14 ዓመታት አገልግለዋል/እያገለገሉ ናቸው ከኪራይ ቤት ወጥተው የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ለመግዛትም በቅተዋል። እኚህ አባት በቤተ ክርስቲያን ትምህርት የበለጸጉ መንፈሳዊ አባት ናቸው። የትምህርታቸው በረከትም በሎሳንጀለስ ብቻ ተውስኖ እንዳይቀር በማሰብ በተወሰኑ ወንድሞች ርዳታ www.debelo.org ብ
በተሰኘ ድረ ገጽ እንቁ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ጸሎት በዓይነት በዓይነት አድርገው በማቅረብ ካህናትና ዲያቆናት ለአገልግሎት እንዲሁም ምእመናን እንዲጠቀሙበት አድርገዋል።

እንግዲህ ሊቀ ጉባኤ እንዲህ ያሉ አባት ሲሆኑ ...ከላይ የወጣው ጽሁፍ ....ከወንበዴው ‹አባ› ሰረቀ ጋር ነበሩ በሚል የቀረበው ስህተት ነውና እንዲታረም አደራ እላለሁ።

ገ/እግዚአብሔር ዘሎሳንጀለስ
ሰላም....

Anonymous said...

አዬ ግብዞች አሁን በእውነት የተፈረደላችሁ ይመስላችሁ ይሆናል። ነገር ግን አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
በገንዘብና በሐሰት ምስክር ነው አምላካችንን የገደሉት። እናም የእግዚአብሔርን ሰው አባ ሰረቀን፡ ለሆዳቸው
ባደሩ፣ እንደ ይሁዳ በገንዘብ የተገዙ ፣ ቤተክርስቲያናችንን የሚያዋርድና የሚያሳፍር ሥራ እየሰሩ ፣በሐጢያት
በተጨማለቁ፣ አንዳንድ ጳጳሳት፡ ከዚህ ከወንድሞች ከሳሽ ጋር በመተባበር የሙት ሙታቸውን በበላ አፋቸው
ለፍልፈውና ውሸቱን እውነት አስመስለው ተናግረው በአባ ሠረቀ ላይ በአድማ ቢያስወስኑም፤ እሳቸውም ሆነ
እኛ የመድሐኒያለም ልጆች ግን ቀደም ሲል ከመምህራችንና ከጌታችን የተማርነው \በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ\
ነውና ምንም አይደንቀንም። ነገር ግን አይሁድ ክርስቶስን በሐሰት ከገደሉት በኃላ ትዝ ሲላቸው በሶስተኛው ቀን
እነሳለሁ ብሎ ተናግሩአልና ንጉስ ጲላጦስ ሆይ የመጀመሪያው ስህተት ከኃለኛው እንዳይብስ እባክዎን የመቃብሩ
ጠባቂዎች ይታዘዙልን ብለው ጠየቁ፤ ጠባቂም ታዘዘላቸው፡ ነገር ግን ጌታችን በትንሳኤ መነሳቱ አልቀረም።
የኛ ጌታ የአሸናፊዎች አሸናፊ ነውና። አሁንም እናንተ በሐሰት የመሰከራችሁ የዘመኑ ፈሪሳዊያን ጳጳሳት፤
የመጀመሪያው ጥፋት ከሁዋለኛው እንዳይብስ ለተመረጣችሁለት አገልግሎት በሐቅና በፍቅር ሆናችሁ እራሳችሁን
መርምሩ። አለዚያ ግን ቤተክርስቲያናችሁንና እራሳችሁን የባሰ ነገር ውስጥ እያስገባችሁት ነው።

\አትፍረድ ይፈረድብሃል ስለ ሆነ \ የወንድሞች ከሳሽ የሆነው ማህበር ዛሬ በእጄ ስለእናንተ ጉድና የሐጢያት
ወንጀል ስራ ማስረጃ አለኝ፡ እንደምንም ብላችሁ የኛን ጉዳይ ካላስፈፀማችሁ እኛም ጉዳችሁን እናወጣዋለን፡
በማለት ሲያስፈራሩአችሁና በገንዘብ ስለገዙአችሁ በሐሰት አስፈፀማችሁላቸው። ለዚህ ነው አይሁድ ፈሪሳዊያን
እግዚአብሔር ባወቀ ከመጀመሪያው ስህተት የኃለኛው እንዳይብስ ብሎ ያናገራቸውና ፡ እናንተም የማቅን ሥራ
ስለሰራችሁለት ለጊዜው ጉዳችሁን ባያጋልጠውም፤ የሚቀጥለው የጉዞ ሂደት ግን እራሱ ሰይጣን ብቻውን መቃጠል
ሰለማይፈልግ ወደ እናንተ ደግሞ ይመጣል። የማይገለጥ የተከደነ የለምና።

በመጨረሻም አባ ሠረቀና ለእውነት የቆማችሁ ፓትሪያሊክ አቡነ ጳውሎስ፣አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እንዲሁም
እህቶቻችን አይዙአችሁ በርቱ። \ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ\ አይደል ያለው አምላካችን፡፡ እኔ ለእናንተ
ይህንን መናገር አይገባኝም ነበር፤ ነገር ግን የተሰማኝን ያህል ለመገለፅ በማለት ነው እንጂ በድፍረት አይደለም።

እግዚአብሔር እንደ እናንተ ያሉ ሐቀኛና አስተዋይ አባቶች
አያሳጣን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። አሜን።

Anonymous said...

የኢትዮጵያ፡አምላክ፡ቤቱን፡ማጽዳት፡ጀምሯል!
ውሎ፡ማደሩም፡ለኛ፡ትምህርትነት፡እንጂ፡ተዋሕ
ዶ፡ላይ፡የጥፋት፡ርኩሰት፡የተበተበውን፡ሁሉ፡መድ
ኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ሳየይውና፡ሳይቆጭ፤ቀርቶ፡አ
ይደለም።ሰረቀ፡ብቻ፡አይደለም፡ገና፡ተዋሕዶ-ኢት
ዮጵያን፡ለማጥፋት፡የዳከሩትን፡ሁሉ፡ይደመስሳቸ
ዋል!

ክብርና፡ምስጋና፡ለቅዱሳን፡አባቶቻችን፡አምላክ፡
መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ይሁን!

የተስፋችን፡መሠረትና፡ሥራችን፡ሁሉ፡ሊገለጽበት፡
የሚገባው፡የተዋሕዶ፡ሕግና፡ሥነ፡ሥርዓት፡ነው!ይ
ህ፡ነው፡የመስቀሉ፡ምሥጢር!

መስቀላችንን፣ሊነጥቁን፣ማኀተባችችንን፡ሊያስፈቱ
ንና፡እምነታችንን፡ሊያስክዱን፡በውስጣችን፡የተሰገ
ሰጉትንና፡የተፈለፈሉትን፡እየጠረጉ፡የማባረሩ፡ጊዜ
ው፡አሁን፡ጀምሯል!ተንግዲህ፡ወደ፡ኋላ፡ማለት፡የለም!

እነ፡ጌታቸው፡ዶኒና፡ግብረ፡አበሮቻቸውም፡ከቤታች
ን፡ይወገዱ!ውስጣችን፡ገብተው፡ጦርነትን፡ያወጁብ
ን፡የአጽራረ፡ተዋሕዶ፡ምንደኞች፡ተመንጥረው፡ይወ
ገዱ!እኛ፡ወደ፡እምነት፡ቤቶቻቸው፡ሂደን፡ጦርነት፡
አላወጅንባቸውም!እነርሱ፡ግን፡ስለትህትናችን፡ሞ
ኞች፡አደረጉ፤ናቁን፤ውስጣችን፡ገብተው፡ተጫወቱ
ብን!

ተንግዲህ፡ይህ፡ማብቃት፡አለበት!ሰረቀ፡ብቻውን፡
አይደለም፡ጓዳችንን፡የሰረሰረው!ግብረ፡አበሮቹን
ም፡ስለምናውቃቸው፡ይወገዱ!

በዚህ፡ተጋድሎ፡በቆራጥነት፡ቆማችሁ፡ለተዋሕዶ፡
ክብርና፡ሥርዓት፡የምትደክሙትን፡ብፁአን፡አባቶ
ች፡በርቱ፡እንላለን!አብረናችሁ፡ቆመናል!እንደ፡
ቅዱሳን፡ስማዕታት፡ለተዋሕዶ፡እምነታችን፡የሚከ
ፈለውን፡ሁሉ፡ለመክፈል፡በዝግጅ፡ቆመናል!

ኪዳነ፡ምሕረት፡የተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ጉዳይ፡
አደራሽን!ከመሳለቂያነት፡አውጭን!

ማኅበረ፡ተክለ፡ሃይማኖት፤
(ደቂቀ፡አያሌው፡ታምሩ)

Anonymous said...

Hey,yoo,he is gonne like binladen.I wonder the patience and endurance of mk leadership.you are saints for the generation.I wish I am a member.

Unknown said...

Dear G/Egziabher,

Thank you for the correction. we will update all minor facts as soon as possible.

Anonymous said...

በሲኖዶስ ውሳኔ ለማደራጃ መምሪያው ሊቀጳጳስ በዋናነት ሲመደብ አባ ሠረቀ ብርሃን ደግሞ በምክትል ኃላፊነት ይመደባል። ይህንን ለማድረግ ሥልጣኑ የሲኖዶስ አይደለም። ለዚህ ደግሞ አባ ጳውሎስ አይሰንፉም። ወይም ለእርሳቸው በሚስማማ ሥራ እዚያው አካባቢ እንደሚመደብ አይጠረጠርም። የሚጠሉት ሰዎች ምን ይሉ ይሆን? ሃይማኖቱንም በተመለከተ በእርግጠኝነት ለመናገር ተባለ፤ ተወራ፤ተነገረ የሚል እንቶ ፈንቶ ካልሆነ በስተቀር ተጨባጭ መረጃ ሳይሆን ማስረጃ የሚያገኝበት የለም። የዶኒ ደብዳቤ ዶኒ እንደጻፈ እንጂ አባ ሠረቀ አምኖ እንደተቀበለ ወይም ደርሶት ድጋፉን እንደሰጠ አያሳይም። ይህ መጠየቅም ካለበት ጽፏል ተብሎ የሚጠረጠረውን እንጂ ደብዳቤው በእጁ ላይ ባልተገኘው በአባ ሠረቀ ላይ ሊሆን አይችልም። በሕግ ፊትም በስም አጥፊነት ያስከስሳል። እስካሁን አባ ሠረቀ ተሃድሶ ነው የሚል ወሬና በአሜሪካ እንዲህ አለ፤ እንዲያ ተናገረ ከሚባል የጥላቻ ዘመቻ ባሻገር በተጨባጭ እኔ ተሃድሶ ሆኛለሁ ወይም የተሃድሶን ዓላማ አራምዳለሁ ብሎ በቃልና በጽሑፍ ወይም በምስል እስካላረጋገጠ ድረስ አንድ ሰው ክዷል ተብሎ አይከሰስም። እነአርዮስ፤ መቅደንዮስ፤ንስጥሮስ፤አውጣኪ፤ ሰባልዮስ ወዘተ ሁሉም በቃላቸው ስለካዱት ተናግረውና አስተምረው እንጂ ጉባዔ የተሰራባቸው እንጂ ሰዎቹ ነገረ ሥራቸው ይመስላል፤ ልባችን ይጠረጥራል ብለው አይደለም። በጥቅሉ እኔ አባ ሠረቀን በአካል ከማያቸው በስተቀር ምንም ግንኙነት ባይኖረኝም እስካሁን ከማነበውና ከምሰማው ተነስቼ ስገመግም የሰውዬውን ግትርነት ተንተርሶ የሚመጡ የጥላቻና ጠልፎ ለመጣል የሚደረግ ሩጫ ካልሆነ በስተቀር የተጨበጠ ነገር የለም። ጉዳዩን ወደፊት የምናየው ሆኖ ወደባሰ ጭቅጭቅና የሕግ ክርክር እንደሚያስነሳ ከወዲሁ ለመገመት አይከብድም።
ለማንኛውም ሰላምና ፍቅርን እግዚአብሔር ያድለን። ለሁላችንም አስተዋይ ልቡናን ይስጠን አሜን።

Anonymous said...

ከላይ አንድ አስተያየት ሰጪ በጥሩ ገልጸኸዋል፣ ። እኔ እሳቸው ነበሩበት በሚባለው ቤተ ክርስቲያን ነኝ ያለሁ፤ ከሳቸውም አንግባባም። ነገር ግን ስለ ሐቅ መስክር ከተባልሁ አባ ሰረቀ የስሜትነት ጠባያቸው ትተህ ትጉህ አገልጋይና የስራ ሰው ናቸው። እንዲያው በእውነቱ በኦርቶዶክስ አክራሪነታቸው ከሆነ’ንጂ በሕጸጸ ሐይማኖት ተጠርጥረዋል የተባለው ‘ወስ’ ስለማያስብሉ አጀንዳ ማስቀየሻ ሆኖ ይሆናል ;እኔ’ኮ እንኳን በኢትዮጵያ በዚሁ በአሜሪካም መንቻካ አመል እንደነበራቸው ግልጽ ይታወቃል አሰራራቸው ለሁሉም ነገር መረጃ ይፈልጋሉና።
ስለዚህ ጥቅመኞችን ለማስደሰት ሲባል ሗላግን በእግዚአብሔር ፊት የምናፍርበት ወሬ ማውራትና አስወቃሽ ሐሳብ ጠንስሶ ሰው ወዳልሆነ መንገድ መምራት መልካም መስሎ አልተሰማኝም።

Anonymous said...

Aba Sereqe is kicked out because of his evile did. Above all his disobedient to GOD. Miss use of his little power. I read abaselama.com and saw that they were his followers and are very upset to the extent that they tried to disfame the commitee abotch and Mahebere Kidusan. We know who is who now. Well his is dead from the Sembet Tmehert bet Maderaja. Just go for the funeral to tehadiso gudgwad. We heard you saying bere welede. Live walking lie. Any way EOTC is not like you guys, we will pray for his and your mercy.

Anonymous said...

dear asteyayet sechi anonymous
"ayy enante gibzoch yeteferedelachihu endaymeslachihu" kkkkkkkkkkk ayy enante tehadsowoch egziabher yemaysera mesloachihu neber mezebecha yaderegachihut???? enaznalen kezih behuala abeqalachihu!!! betechirstianachin west meqeled yelem.ahun wanachihun... degmo entseliyalen egziabher zim aylem enamnalen!!!!yilek gudachihun silaweta mahberun bitkesum egna gin mahberachihun yibark,bertu,tsegachihu yibza bilenachewal...silederesebachihu hazen gin metsinanat enimegnalen..

lelr said...

yahaiemanotachohe nagare gede anegabegebochohe yamayechalawen AMELAKA KEDOSANE asechelochohe lazeh yabakachohe lamanegesto yabekachohe.yeha yala dame samaetenate nawe atawekotem beya ayedalame dasetayen yamegalesebate kalate bata enje.

Anonymous said...

The truth has many enemies. However, no matter how isolated perscuted the truth becomes, never dies. There is no comort in the truth. I do not want to relate this to any biblical story because you might know better than me. This is a victory for MK not for the church. Becuase you think you eleminated one of the strongest obstacles you had in your 20 years history. But please do not rejoice that much. If you think you are going to play a game in the existence the church, you will be disappointed. Her savior is in charge. He was the first one to pass through organized mob justice. He defeated them all. You might be next if you do not obey him and protect the people according to his words.

Anonymous said...

እኔም እንደሌሎች ወገኖቼ በአባ ሰረቀ (ሠ) ያይደለ ለመጠቆም ነው ዛሬ ከአንባቢነት ወደ አስተያየት ሰጪነት ትንሽ እራሴን ከፍ ያደረኩት። እኔ በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ነዋሪ ነኝ እና አባ ሰረቀን የቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይ ሀላፊ በነበሩ ጊዜ እንደማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ በቅዱስ ጊዮርጊስ እየተገኘሁ የአገልግሎቱ ተካፋይ ነበርኩ፣ በመቀጠል ለምን ተገልጋይ ብቻ እንሆናለን፣ ለምንስ እኛም ለቤተ ክርስቲያን አናገለግልም ብለን እኔና ባለቤቴ የበኩላችንን ለማድረግ አንድ ብለን ጀመርን። ወዲያው እንደጀመርን እርሳቸውን ማነጋገር እና የንሰሐ ሕይወት እንዲኖረን ለብዙ ዘመናት እንመኝ ነበርና ይህንኑ ነግረናቸው ለዚህ መልካም መንገዶችን እንዲያሳዩን አመልካች መንገዶችን ይጠቁሙናል ብለን ጉዞችንን (የንሰሐ) ለመጀመር የመጀመሪያው ተግባራችን አባ ሰረቀን ማነጋገር ነበር እና፥ ልክ አንድ ሰንበት ከአግልግሎት በኃላ አነጋገርናቸው በተለይ ከእኔ ጋር መጠነኛ መግባባት ስለነበረን ችግር አልገጠመንም፣ ምክንያቱም በወቅቱ ይመስለኛል በፈረንጆች አቆጣጠር 2000 ላይ እኔ እና አባ ሰረቀብርሃን አንድ ክፍል ቁጭ ብለን ተምረናል በNOVA የESL (English as Second Languge) ክፍል እንወስድ ስለነበር ያለምንም ውጣ ውረድ እኔ እና ባለቤቴን በ South Wakefield Street በሚገኘው አፓርትመንታቸው እንድንመጣ ቀጠሮ ሰጥተውን ቡራኬያቸውን ተቀብለን ተለያየን።

እለቱ እሮብ ይመስለኛል እራት ይዘን ስንሄድ የፆም ምግብ ነበር እና እንደደረስን እራታቸውን አብልተን እንደው የፆም ምግብ ሆነ ስንላቸው እርሳቸውም “እንደው ዝም ብላችሁ ነው፣ በፍስክ ይበላ ነበር እኮ” ብለውን ትንሽ በእኔ እና በባለቤቴ አይምሮ ውስጥ ትንሽ ብዥታን ፈጥረውብን ነበር፥ እራት እንደጨረስን ወደ መጣንበት እንድንገባ እንደው ለመግቢያ እንዲሆን ብለን የኖርነውን ሕይወት አንስተን አሁን ግን በንሰሐ ሕይወት እንዲኖረን በልባችን ወስነን የንሰሐ አባት እንዲሆኑን እና መንገዶችን እንዲያሳዩን ነበር ብለን ጀመርን፣ እርሳቸውም የተለያዩ ነገሮችን ነገሩን እና በስተ መጨረሻ “በአሁን ሰዓት እኮ፣ ንሰሐ የሚባል ነገር የለም” “እኔ የእናንተ councilor መሆን እችላለሁ” ብለውን በጣም አስደነገጡን በመጨረሻ ስንሰነባበት በአሁን ዘመን ብዙ ንሰሐ የሚባለው ቀርቷል ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ነገሮችን እየተወች እና አዳዲስ አሰራሮችን እያመጣች እንደሆነና እኛም እነዚህን አሰራሮች ልብ ልንላቸው እንደሚገባ ዲስኩር ሰጥተው በዚያ ምሽት ተለያየን ከዛን ምሽት በኃላ እኒህን ሰው ማየት እንደሌለብን ወስነን ከዚህ አገር ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ እስከ ሄዱበት ጊዜ አንስቶ ሳንገናኝ ቆይተን አባ ጽጌ የሚባሉ የሀገራቸውን ሰው ተክተው እንዴሄዱ ቆይተን ሰምተን ዛሬ ነገ ስንል አንድ ሰንበት እንደለመደው ስንሄድ እኒሁ ሰረቀ እንደገና እዛው ተገናኘን ከአገልግሎቱ በኃላ ተገናችተን ተወቃቅሰን በዛጊዜም ብዙ ነገሮችን ስለእርሳቸው ሰምተን ስለነበር ፍላጎቱም አልነበረንም በመጨረሻ ከአባ ጽጌ ጋር አስተዋውቀን እንዲደውሉላቸውም ነግረውን ተለያይተናል በኃላ ስንሰማ እኚህኛውም ከሳቸው ብዙም የተሻሉ እንዳልሆኑ እና የአላማ ግንኙነት እንዳላቸው አንዳንድ ወንድሞች ስለጠቆሙን እርሳቸውም ጋር ከመደወል እራሳችንን ቆጥበን ይህንን ዜና እስክናይ ድረስ አልተገናኘንም፣
አሁን ይህንን ዜና ስናይ እኛም ሰው የሚማርበት ከሆነ የሆነውን ሁሉ ለመጠቆም ተነጋገርን እና ይሕው ወረቀቱን ከብዕሩ ወይም ጣትን ከኪቦርዶ አገናኘን፡፡

Anonymous said...

እውነት ያለችው በእግዚያር "ልቦና" እንደሆነ ነው የማምነው:: ያን ሃቅ እርሱ ሲፈቅድ በሆነው መንገድ ማውጣtu የታመነ ነው:: በ እ ኛ የሆነ ኣንዳች እንደሌለ መቀበሉ ሸጋ ነው:: ሲለጥቅ፡ ስለ ቤቱ መቅናታችን ሰማያዊቷን ርስት ባልዘነጋ መንፈስ ቢሆ ን እመኛለሁ:ለሁላችንም:: ዜና ማለት የቤተ ከረስቲያን ፈተና ብቻ እnዳልሆነ ለማታጡት አሰናኞች በሙሉ:የኦርቶዶክስ ኣንባቢን ልክ ቤተ መቅደስ ውስት እንደተቀመጠ ምስኪን ቁተሩትና የተደራሲነት መልኩን ለመቀየር /ለማሻሻል ብትሞክሩ ማለፈያ ነው እላለሁ:: ባለሙያዎቹ ምን ለማለት እነደፈለኩ አይተፋችሁም ቢዬ አስባለሁ አዳዲስ መረጃ ላከላችሁልኝ፡ በደጀ ሰላም ስም ክብረት ይስጥልን እላለሁ:: ታናሽ መንደማቹ!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)