October 21, 2011

30ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ 3ኛ ቀን ሪፖርታዥ


ቃለ ዐዋዲው እንዲሻሻል ተወሰነ
  • TO READ IN PDF, CLICK HERE.
  • በቋንቋው ጠንቅቆ የሚያስተምር መምህር ባጣው በአዲሱ የቄለም ወለጋ ሀ/ስብከት በተሐድሶ መናፍቃን ከተወረሩት ሰባት ወረዳዎች በአንዱ ወረዳ በሚገኙ ሰባት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሴቶች ካህናቱን አንበርክከው ይጸልዩላቸዋል፤ ‹ቅዳሴ አያስፈልግም፤ ቅዱሳን አያማልዱም› የሚል ክሕደት በግልጽ እየተነገረ ነው”/የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት/፤
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ፓትርያርኩን 35% ድርሻ ብር 24 ሚልዮን ገቢ አደረገ፤ “ኑሯችን ለምንሰብከው ምእመን ምሳሌ የሚሆን ነው ወይ?” ሲሉ የጠየቁት የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ “እጃችን መሰብሰብ አለበት” ሲሉም መክረዋል፤ ጉባኤው ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ አባ ገ/ማርያም ገ/ሥላሴ ከመቀመጫው ተነሥቶ ከፍ ያለ ጭብጨባ/standing ovation/ ችሯቸዋል
  • በከምባታ አላባ እና ጠንባሮ ሀ/ስብከት በአንድ ቀን እስከ 2228 ሰዎች ተጠምቀዋል፤ በዕለቱ የሀገር ሽማግሌዎች የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን ዝናም እንዲያዘንሙላቸው ጠይቀዋል፤ በተደረገውም እግዚኦታ ለ40 ደቂቃ ያህል ዝናም ዘንሟል፤
  • በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ከ70 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን 52ቱ ደቡብ አፍሪካውያን ካህናት የሚያስተዳድሯቸው ናቸው፤
  • ከሰሜን አሜሪካ ሦስት አህጉረ ስብከት የሁለቱ (የዋሽንግተን ዲሲ እና የካሊፎርኒያ) ሊቃነ ጳጳሳት በአቡነ ጳውሎስ ትእዛዝ “በዋሽንግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” በሚል ከሊቃነ ጳጳሳቱ የበላይ የሆነ አካል መቋቋሙን በመቃወም እና በፓትርያርኩ ደርሶብናል በሚሉት በደል ዙሪያ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለፓትርያርኩ የጻፏቸው ደብዳቤዎች በጉባኤተኛውና በሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆነዋል /መረጃዎቹ ደርሰውናል፣ ዝርዝሩን ወደፊት እናቀርባለን/፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 9/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 20/2011)፦ ሙስ፣ ጥቅምት ዘጠኝ ቀን 2004 ዓ.ም፤ ከተጀመረ ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው 30ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ1991 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ ለ13 ዓመታት ያህል በሥራ ላይ የቆየው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ቃለ ዐዋዲ እንዲሻሻል በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው የጀመረውን ውይይት ትንት ሙስም በመቀጠል በቃለ ዐዋዲው መሻሻል ላይ ሐሳብ በተለዋወጠበት ወቅት እንደተመለከተው፣ በሥራ ላይ በሚገኘው ቃለ ዐዋዲ ውስጥ የማይሠራባቸው ድንጋጌዎች በርካታ መሆናቸውን አስታውሶ ለአብነትም ያህል፣ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እስከ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ በየደረጃው እንዲቋቋም የታዘዘው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ (ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ/) ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በቀር በወረዳ እና በመንበረ ፓትርያርኩ ደረጃ አለመቋቋሙን ጠቅሷል፡፡

በማሻሻሉ ሂደት እንደ አርመን እና ሩስያ ያሉ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ልምድ /ምርጥ ተሞክሮ/ መዳሰስ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡ በውጭ ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን በየሀገሩ መንግሥት “ደንባችሁን አምጡ” እየተባሉ ሲጠየቁ ቃለ ዐዋዲው ከየሀገሩ ሕግ ጋራ በተገናዘበ መልኩ በዓለም አቀፍ ቋንቋ ባለመተርጎሙ ሲቸገሩበት ቆይተዋል፤ በመሆኑም የሚሻሻለው ደንብ ቢያንስ በእንግሊዝኛ ቋንቋም እንዲተረጎም ተጠይቋል፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ቤቱ ለቃለ ዐዋዲው መሻሻል ያለውን ድጋፍ እጅ በማውጣት እንዲያሳይ በጠየቁት መሠረት ቤቱ በሙሉ ድምፅ ድጋፉን በመግለጡ የማሻሻሉ ሥራ በመጪው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአጀንዳነት የመያዙ ጉዳይ ርግጥ ሆኗል፡፡

በውይይቱ ላይ ከተነሡት ሌሎች ጥያቄዎች ውስጥ በመንበረ ፓትርያርክ ደረጃ በ120፣ በሀገረ ስብከት ደረጃ በ72፣ በወረዳ ቤተ ክህነት ደረጃ በ36 እና በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ በ24 አባላት/ቤተሰብ በሚቋቋመው የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ኮሚቴ በየመዋቅሩ አንድ ከመቶ እንዲሰበሰብ ተላልፎ ስለነበረው ውሳኔ የሚመለከተው ይገኝበታል

ቀሲስ ዘሩባቤል ገብረ መድኅን ይህን አስመልክተው ባቀረቡት ጥያቄ፣ ከ48 አህጉረ ስብከት ይህ ውሳኔ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ብቻ ነው፤ በሌሎቹስ ስላልተቻለ ወይስ ስላልተፈለገ ነው በማለት ስለ አፈጻጸሙ እና ስለ ቀጣይነቱ ማብራሪያ ይሰጠኝ ብለዋል፡፡

ለጉባኤው በተዘጋጀው ቃለ ዐዋዲ መጽሔት ላይ በሰፈረው የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት፣ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያው እና ማጠናከሪያው የአንድ ከመቶ ሒሳብ ወደ ማዕከል የላኩት ሁለት አህጉረ ስብከት ብቻ ሲሆኑ መጠኑም ብር 9,837.27 ነው፡፡

ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በተቋቋመው ሀገር አቀፍ ም/ቤት ለፕሮጀክቱ ዕውን መሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የተለያዩ አካላት ሽልማት መሰጠቱን ያስታወሱት ቀሲስ ዘሩባቤል በግንቦት ወር አጋማሽ ከብር 21 ሚዮን በላይ ያበረከተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንስ ለምን አልተሸለመችም? የሰጠችው ገንዘብ አያሸልማትም ወይስ ገንዘቡ ከሚፈለገው ቦታ አልደረሰም? ውስጥ ውስጡን ከምንተማማ በግልጽ እንነጋገርበት ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ “ምኞቴን ለመናገር አልከለከልም” በሚል መቅድም “ቤተ ክርስቲያናችን የራሷ ቴሌቪንና ሬዲዮ ጣቢያ ስለምን በኬንያ እና በጅቡቲ አታቋቁምም?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ “ወደ አዲስ አበባ ለየስብሰባው ስንመጣ ቆባችንን ቀሚሳችንን እንደለበስን ማደሪያ ፍለጋ በየቦታው እንከራተታለን፤ እኔ በበኩሌ አንድ መነኩሴ ከምሸት 12 ሰዓት በኋላ መንገድ ላይ ሲዞር ባይታይ ደስ ይለኛል፤ እንዲያው በማርያም ለምን በአንድ ማደሪያ የሚሰበስበን ማረፊያ አይዘጋጅልንም?” በማለትም አክለዋል፡፡

የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ሓላፊ የሆኑት አቶ ይሥሐቅ ተስፋዬ ቀረቡት የአህጉረ ስብከቱ ሪፖርት ውስጥ መልካም አስተዳደር የፍጽምና ደረጃ ላይ የደረሰና ምንም ችግር የሌለ አስመስሎ የሚያሳየውን አቀራረብ ተችተዋል፤ “የአሠሪ እና ሠራተኛ ሕጉ እየተጣሰ እስከ ምባ ጠባቂ፣ ሰብአዊ መብት ኮምሽንና እስከ ቅዱስነታቸው ጽ/ቤት የደረሰ ጉዳይስ የለምን?” ሲሉ በአንድ ጊዜ ፍጹምና የተሟላ የመልካም አስተዳደር ሁኔታ ላይ መድረሳቸውን የተናገሩትን አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ሪፖርት አጠራጣሪነት ገልጸዋል፡፡

በሀገር ውስጥ የሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት (ከጉጂ ቦረና ሊበን በቀር) ሪፖርት መስማት ትንት ተጠናቋል፡፡ ሪፖርታቸውን ትንት ካቀረቡት 11 አህጉረ ስብከት ውስጥ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን - ሰቲት ሁመራ ሀ/ስብከት ለአብነት መምህራን ከሀ/ስብከቱ የአምስት ከመቶ ድጎማ መመደቡ፣ በማኅበረ ቅዱሳን የሀ/ስብከቱ ማዕከል ለአብነት መምህራን በየዓመቱ ብር 15,000 ማበርከቱ፣ ለካህናት ሥልጠና ብር 50,000 መስጠቱ ጉባኤው በጭብጨባ አመስግኗል፡፡ በወላይታ በሕገ ወጥ ሰባክያንና ማኅበራት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መካሄዱ፣ በከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀ/ስብከት ከ1030፤ በከንባታ አላባ እና ጠንባሮ ሀ/ስብከት በአንድ ቀን 2228 በላይ በሌላ እምነት የነበሩ መጠመቃቸው ተገልጧል፡፡

በከንባታ አላባ እና ጠንባሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት በአንድ ቀን በተደረገው 2228 ምእመናንን የማጥማቅ እና ማቁረብ ሥርት ወቅት የሀገሩ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ብፁዕነታቸው በመምጣት አንድ ጥያቄ ይጠይቋቸዋል - “ለብዙ ጊዜ ዝናም ሳይዘንም በመቆየቱ በድርቅ ተቸግረናል፤ ስለዚህ አባታችን ሆይ፣ ዝናም አዝንምልን?” ይሏቸዋል፡፡

የሥራ አስኪያጁ ሪፖርት እንደሚገልጸው የሀገር ሽማግሌዎቹ ጥያቄ እጅግ አስጨናቂ ቢሆንም ብፁዕነታቸው “ኑ፣ እግዚኦታ እናድርስ” ብለው እግዚኦታው ተደርጎ ትምህርትና ምክር ተሰጥቶ እንዳበቃ ለ40 ደቂቃ ያህል ዝናም ዘንሟል፡፡ በዚህም ተምር የተደነቁ 50 የሀገሩ ሰዎች ወዲያው መጥተው “እኛንም አጥምቁን” ብለው መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡ “አሁን እየሠራን ያለነው ሰው ላይ እንጂ ገንዘብ ላይ አይደለም” ያሉት ሥራ አስኪያጁ ለመንበረ ፓትርያርኩ ገቢ ያደረጉት የ35% ገቢ ብር 26,000 ነው - ‹ቢያንስም እንዳትቀየሙ› ማለታቸው ይሆን?

በሪፖርቱ አፈጻጸም ሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ያመሰገኑት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ቀድሞ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩትና በሞተ ዕረፍት የተለዩንን ብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅን በማስታወስ የሚከተለውን ቃል ተናግረዋል፡- “ብፁዕ አቡነ መልከ ዴቅ የማይሰለቹ የወንጌል ገበሬ ነበሩ፡፡ በእርሳቸው ቦታ የተተኩት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ሰምተነው የማናውቀው፣ ቤተ ክርስቲያናችንን የሚያኮራ ሥራ ሠርተዋል፡፡ በቁመተ ሥጋ ስናያቸው አጭር ደቃቃ ናቸው፤ ግን ትልቅ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋራ ይስጥልን፡፡”

የሆ ጉድሩ ሀ/ስብከት ‹አንዳንድ› ያላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት አድማ በመቀስቀስ እና በጣልቃ ገብነት ችግር እየፈጠሩ መሆኑን በመጥቀስ ከሷል፡፡ ሥራ አስኪያጁ ለምን በሪፖርታቸው ይህን እንዳሉ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከሆኑ የማኅበሩ ተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡- “አንድ የእናንተ አባል ተሐድሶ ስላለኝ ተናድጄ ነው፤” ማለታቸው ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል፡፡ ሀ/ስብከቱ ሕገ ወጥ ዘማርያንና ሰባክያንን በመቆጣጠር ረገድ ሥራዎችን መሥራቱ የተገለጸ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንም የሀ/ስብከቱን እንቅስቃሴዎች በመደገፍ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
በቅርቡ በአዲስ መልክ የተቋቋመው የቄለም ወለጋ ሀ/ስብከት ቀደም ሲል ከነበሩት 11 ወረዳዎች ሰባቱ በመናፍቃን የተወረሩ እንደነበር፣ በ1991 ዓ.ም መኪና አደጋ በሞተ ዕረፍት የተለዩንን እንደ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በነበሩት አባቶች እና በብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ላይ ድንጋይ ይወረወርበት እንደነበር በሥራ አስኪያጁ ሪፖርት ላይ ተመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአንጻራዊነት የተሻለ ሁኔታ ያለ ቢሆንም የአካባቢውን ቋንቋ ዐውቆ ጠንቅቆ ትምህርተ ሃይማኖትንና ሥርተ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስተምር መምህር በመታጣቱ በመናፍቃን ከተወረሩት ሰባት ወረዳዎች አንዱ ሙሉ በሙሉ በተሐድሶ መናፍቃን ተውጧል፤ በዚህ ወረዳ በሚገኙና በተሐድሶ መናፍቃኑ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር በዋሉት ሰባት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ውስጥ “ቅዳሴ አያስፈልግም፤ ቅዱሳን አያማልዱም፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ ጫማ ማውለቅ አያስፈልግም” የሚሉ ክሕደቶች በግልጽ እየተሰበከ ነው፤ ሰበካ ጉባኤያቱም በቃለ ዐዋዲው መሠረት የተቋቋሙ አይደሉም፡፡ ከዚህም የባሰው ደግሞ ሴቶች ‹ካህናቱ›ን አንበርክከው፣ እጃቸውን ጭነው ይጸልዩላቸው መባሉ ነው፡፡

በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ላይ በመመሥረት ከቤቱ በተሰጠ አስተያየት፣ “ሁኔታው ወንድ አጣ ነው የሚያሰኘው፤ ቢያንስ ጉዳዩን በማስረጃነት ይዞ ወደ ፍትሕ አካል ማቅረብ አይገባም ነበር ወይ?” የሚል ጥያቄ ቀርቧል፡፡ የጥያቄውን ምላሽ በዛሬው ውይይት እንሰማው ይሆናል፡፡ በቃለ ዐዋዲ መጽሔት ላይ በቀረበው ሪፖርት ግን ሀ/ስብከቱ በቀጣይ፡- በቂ የሰው ኃይል ለማፍራት፣ ለሠራተኞች፣ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት፣ በየወረዳው ሰበካ ጉባኤትን ለማጠናከር፣ አብያተ ክርስቲያናት የይዞታ ካርታ ማረጋገጫ እንዲያገኙ ለማድረግ፣ አብነት መምህራንን በመቅጠር ት/ቤቶችን ለማጠናከር፣ የሀ/ስብከቱን ጽ/ቤት ለመገንባት ዕቅድ መያዙ ተመልክቷል፡፡

ውዳሴ ከንቱ ሳያበዙና ወባ እንደያዘው ሰው ሳይንቀጠቀጡ ሥራቸውንና ስኬታቸውን ማዕከል ባደረገ መልኩ እጥር ምጥን ያለ ሪፖርት ያቀረቡት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገ/ሥላሴ፣ ሪፖርቱን እስከሚያቀርቡበት ዋዜማ ምሽት ድረስ ምክንያቱን በውል የማይረዱት አድማ እና ስም ማጥፋት በአንዳንድ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እየተካሄደባቸው መሆኑን በግልጽ ተናግረዋል፡፡ በሙስና እና አድልዎ ላይ ባላቸው የማይናወጥ አቋም በአዲስ አበባ ካህናት ዘንድ እንደ ልዩ ጸጋ የሚታዩት ሥራ አስኪያጁ፣ “የእኔና የብፁዕ አባታችን ዓላማ አንድና አንድ ነው -  ሥራን በቅንነትና በንጽሕና መሥራት የሚቻልበትን መንገድ አሳይቶ መሄድ” በማለት በጀመሩት የአስተዳደር ዘይቤ እንደሚቀጥሉበት ተናግረዋል፡፡ “እኛ መምህራን፣ ሰባኪዎች ነን፤ ለምእመኑ የምንሰብከውን በመኖር ምሳሌ ልንሆነው ይገባል፤ አለባበሳችን፣ አነጋገራችን ምሳሌ የሚሆን ነው ወይ?” በማለት ከጠየቁ በኋላ “ይቅርታ አድርጉልና እጃችን መሰብሰብ አለብን” ሲሉ ግልጽ ምክራቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ንቡረ ዱ መተጋገዙ ካለ የበለጠ ሊሠራ እንደሚችል ገልጸው “ከቆመ ሙዳዬ ምጽዋት ብቻ የተገኘ ነው” ያሉትንና ከፍተኛውን የ35% የመንበረ ፓትርያርክ ድርሻ የሆነውን የብር 24 ሚዮን ቼክ በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ አማካይነት ለፓትርያርኩ አስረክበዋል፡፡ ሪፖርታቸውን ሲጨርሱና ወደ ቦታቸው ሲመለሱም ሙሉ ጉባኤተኛው ከመቀመጫው ተነሥቶ በጋለ ጭብጨባ አድናቆቱን ገልፆላቸዋል፡፡

የሀገር ውስጥ ሪፖርት ከተጠናቀቀ በኋላ ከሀገር ውጭ የሱዳን፣ የኬንያ፣ የጅቡቲ እና የደቡብ አፍሪካ አህጉረ ስብከቶች ሪፖርት ቀርቦ ተሰምቷል፡፡ ፓትርያርኩ በደቡብ አፍሪካ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በዘጋቢ ፊልም መልክ ለጉባኤው ቀርቧል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ካሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን 52ቱ በደቡብ አፍሪካውያን፣ 22ቱ በኢትዮጵያውያን ካህናት እንደሚመሩ በፊልሙ ላይ ተዘግቧል፡፡ በቅዱስ ያሬድ ስም የካህናት ማሠልጠኛ ተገንብቷል፡፡ ደቡብ አፍሪካውያን ካህናት እና እናቶች መዝሙር ሲያቀርቡም ታይተዋል፡፡ ከኢየሩሳሌም ገዳም ሊቀ ጳጳሱም ተወካዩም ባለመገኘታቸው የቀረበ ሪፖርት የለም፡፡ በኬንያ ማኅበረ ቅዱሳን ለመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ገቢ ማስገኛ የገበያ ማዕከል ዲዛየን መሥራቱ፣ ከፀረ-ሰላም እና ሕገ ወጥ ሰባክያንና ካህናት ለመጠበቅ የሚያስችል ሥልጠና መሰጠቱ ተጠቅሷል፡፡ በሱዳን አንድ ካህን ቤተ ክርስቲያኑን ለመከፋፈል ያደረጉት ጥረት በምእመኑና በአስተዳደሩ ጥረት መገታቱ መገለጡ ተዘግቧል፡፡

ጉባኤው ዛሬም በመቀጠል የውጭ አህጉረ ስብከት ሪፖርቶችን ያዳምጣል፤ ውይይትም ያደርጋል፡፡ 
Picture Courtesy Of Mahibere Kidusan Website.

13 comments:

Anonymous said...

It should be 3rd day not 2nd day

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይስጥልን ደጀ ሰላማውያን ስብሰባውን የተሳተፍን ነው እሚመስለው።

ይች የእጅ መጫን ግን በጀርመንም ታይታለች ጊዜ ይገልጠዋል

lele said...

macherashawone yasamerelene

yemelaku bariya said...

በሱዳን ቤተ ክርስቲያን ለመክፈል ጥረት ያደረጉት ማን ይባላሉ? ደጀ ሰላሞች ስማቸው ካላችሁ እባካችሁ አሳውቁን::

ርብቃ ከጀርመን said...

ደጀላሞች እንደምን ዋላችሁ በጣምነው የምናመሰግነው በዘገባችሁ አርክታችሁናል አሁንም አደራ በርቱልን አሁን ወደውጭ ሀገር ዘገባ እንደምታልፉ ነው የገባን እናም እባካችሁ የጀርመንን ጉዳይ አጥብቃችሁ ያዙልን ነገሩ የከፋና አይንያወጣ ነውና በጉጉትነው የምንብቃችሁ እግዚአብሄር ስራችሁን ይባርክ!

Anonymous said...

"በሱዳን አንድ ካህን ቤተ ክርስቲያኑን ለመከፋፈል ያደረጉት ጥረት በምእመኑና በአስተዳደሩ ጥረት መገታቱ መገለጡ ተዘግቧል፡፡" Wid Dejeselamoch: Lemehonu Yihinin Report Yakerebut Man Nachew? Yagre Siktu Like Papases Yihinin Guday Yawkutal Woy? Egna Bekhartoum Sudan Yeminigegn Miemenan Eskeminawkew Dires Betekrstianuan Likefafil Yetensa Kahin Alsemanim. Honom Yebetekristianu Astedadari Betechristianuan Beteleyaye Wokt, yersachewn Yegil Tikim Lemastebek Bego Sira Yemiseru Mimenanin ena Kahinatn Endemiwenejilu ena Endemiabariru Yadebaby Mistir New::

ተስፋብርሃን said...

ከቀደሙት አበው ጋር የነበረ አሁንም ያለ ጉባኤያቸውን የባረከ ቸሩ አምላካችን በመካሄድ ላይ ያለውንም የአባቶቻችንን ጉባኤ ይባርክ:: አሁን ያለውን የመንፈስ ዝለት አስወግዶ ቤተክርስቲያናችንን ወደ ነበረችበት ክብር ለመመለስ ያብቃልን:: አሜን:: የሲኖዶሱ መሪ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም አባቶቻችንን ይምራልን:: ከግል ሃሳብና ዝና ይልቅ ለቤተክርስቲያን ሃሳብና ዝና የምንሰራ የድርገን::

Anonymous said...

ስለሱዳን ቤተክርስቲያን መከፈል የተሰጠው አስተያየት በካርቱም እንዳልተከሰተ ቀደም ያለው አስተያየት ያስረዳ ይመስለኛል፡ የተቀረው ሱዳን ደግሞ አዲሱ ሀገር ይመስለኛል ግን በዚህ ሀገር የራሳቸው ቤተክርስቲን የሌላቸው በራሳቸው ጥረት የሚታትሩ ጥቂት ሰዎች ከቶሊኮች በሰጡዋቸው ሕንጻ ውስጥ በየሳምንቱ ይሰበሰባሉ ፡፡ የመከፍለ አደጋ ግን በዚህ ደረጃ የገጠማቸው አይመስለኝም ምናልባት ውስጥ ውስጡን ለህዝቡ ሳይገልጡ ገጥሞአቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ሀገር ቤት ያለችው ቤተክርስቲን ዘወር ብላም ያየቻቸው አይመስለኝም እኔ በተመላለስኩባቸው ጊዜያት ምንም ያየሁት የተለወጠ ነገር ስለሌለ ማለቴ ነው፡፡ ይለቁንም ጎረቤት ኡጋንዳ ያሉት የዛኛው ሲኖዶስ ሰዎች ሰለባ እንዳይሆን ስጋት አለኝ ምክንያቱም እያሰቡ መሆኑን የሰማሁት ወሬ ስላለ. .. . . .ስለዚህ በሪፖረቱ የተሰማው ነገር ዝም ብሎ አልተናገሩም እንዳይባሉ ብቻ ባይሆን መልካም ነው ፡፡

Anonymous said...

ከካርቱም ሱዳን:
ደጀሰላሞች፡ ከሱዳን፡ የቀረበው፡ ሪፖርት፡ ከየትኛው፡ ከደቡብ፡ ወይስ፡ ከሰሜን፡ ያለ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ እንደሆነ፡ ግልጽ፡ አይደለም፡፡ ይሁን፡ እንጂ፡ በዚህ፡ በካርቱም፡ በምትገኝ፡ አንዲት፡ መድሃኔዓለም፡ ቤተ፡ ክርስቲያንን፡ ከሆነ፡ ሊከፋፍል፡ የተነሳ፡ ካህን፡ አላየሁም፤ "በምአመናኑ እና በአስተዳደሩ ጥረት መገታቱ ተገለጿል፡፡"፡ ለሚለውም፡ አልተደረገም፡፡ በእውነቱ፡ ይህ፡ መጣራት፡ ያለበት፡ ጉዳይ፡ ይመስለኛል፡፡ Yaltesera sira tesera bilo bereport makreb tegebim tikiklim aydelem besewm hone begziahber zend yasteyikal.

Dejeselamawyan betam amesegenalehu. Egziabher yabertachihu.

Anonymous said...

Luke 6:37-49 All these sayings Christ often used; it was easy to apply them. We ought to be very careful when we blame others; for we need allowance ourselves. If we are of a giving and a forgiving spirit, we shall ourselves reap the benefit. Though full and exact returns are made in another world, not in this world, yet Providence does what should encourage us in doing good. Those who follow the multitude to do evil, follow in the broad way that leads to destruction. The tree is known by its fruits; may the word of Christ be so grafted in our hearts, that we may be fruitful in every good word and work. And what the mouth commonly speaks, generally agrees with what is most in the heart. Those only make sure work for their souls and eternity, and take the course that will profit in a trying time, who think, speak, and act according to the words of Christ. Those who take pains in religion, found their hope upon Christ, who is the Rock of Ages, and other foundation can no man lay. In death and judgment they are safe, being kept by the power of Christ through faith unto salvation, and they shall never perish.

God be with You ALl.

Anonymous said...

be kenya slitena tsete yetebalewu ke ewunet yerake report newu

Anonymous said...

be kenya slitena tsete yetebalewu ke ewunet yerake report newu

Anonymous said...

reportochu ewnet mehonachew yalteregagete ena meregaget yemaichil bemehonu, yemogn chuhet new.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)