October 31, 2011

“የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” በሦስቱ አህጉረ ስብከት ሥር እንዲሆን አልያም እንዲዘጋ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ


አርእስተ ዜና
 (ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 20/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 31/2011. PDF)፦
 • የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን በሰሜን አሜሪካ ያሏትን ሦስት አህጉረ ስብከት “ከመንበረ ፓትርያኩ ጋራ ለማገናኘት” በሚል ተጠሪነቱ ለመንበረ ፓትርያኩ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሆኖ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና የተቋቋመው “የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” አገልግሎቱና ጥቅሙ በሚገባ ተመርምሮ በሦስቱ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ሥር እንደ አንድ የመረጃ ክፍል ሆኖ እንዲዋቀር፣ ይህ ካልሆነ ግን እንዲዘጋ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡

ቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬም ይቀጥላል፤ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ በቋሚነት በሚመደብ ሊቀ ጳጳስ ይመራል


 • READ IN PDF.
 • ሊቀ ጳጳሱ ተደራቢ ሥራ ሳይኖራቸው የማደራጃ መምሪያው መዋቅራዊ አሠራር በሰው ኀይል እና በፋይናንሳዊ አቅሙ ለማጠናከር የሚያስችል መመሪያ የማስቀረጽ፤ በ1986 ዓ.ም የወጣው የማደራጃ መምሪያው ውስጠ ደንብ እና በ1994 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የጸደቀው የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ከሚሻሻለው ቃለ ዐዋዲ፣ ሌሎች ሕጎች እና ከጊዜው ጋራ በማጣጣም እንዲሻሻል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተላለፈውን ውሳኔ የማስፈጸም፤ በዚህም ሕፃናትን፣ ወጣቶችንና ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ አስተባብሮ የመምራት ሓላፊነት ይጠብቃቸዋል።
 • አባ ሰረቀ ከዋና ሓላፊነታቸው ተነስተው ሃይማኖታዊ ሕጸጻቸው እንዲመረመር የተላለፈው ውሳኔ የቤተ ክህነቱን ቢሮክራሲ (የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያን ጭምር) ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ደጋፊዎች ለማጽዳት በቀጣይነት በመካሄድ ላይ ለሚገኘው ተጋድሎ አብነታዊ ርምጃ ተደርጎ ተወስዷል፤

ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀ ላይ ከሥልጣን ማውረዱ የፓትርያርኩ ሐውልት ላይ እንደተወሰነው ውሳኔ እንዳይሆን ሥጋት አለ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 20/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 31/2011, PDF)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወል ሳሙኤል ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ እንደወሰነባቸው ከታወቀ ጀምሮ ምዕመናን ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ላይ ሲሆኑ ቅ/ሲኖዶስ ከረዥም እልፍ አስጨራሽ ስብሰባ በኋላ እዚህ መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ምሥጋናቸውን እየቀረቡ ነው። 

October 29, 2011

(ሰበር ዜና) ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀን ከሥልጣናቸው አወረደ


Adios Abba Sereke!!!!!!!!!!!!!!
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 29/2011, PDF)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወደል ሳሙኤል ዛሬ ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነባቸው። ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣

ቅዱስ ሲኖዶስ ለ4ኛ ተከታታይ ቀን በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ እና ማ/ቅዱሳን መካከል ባሉት ችግሮች ዙሪያ እየተወያየ ነው

አርእስተ ዜና
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 29/2011/ PDF)፦
 • ምልአተ ጉባኤው የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት በተሰጠው መመሪያ መሠረት ባለመቅረቡ አልተቀበለውም፤ ኮሚቴው የአባ ሰረቀን በማስረጃ ያልተደገፉ 20 ክሶች በማጉላት የማኅበሩን 10 ተጨባጭ አቤቱታዎች በማኮሰስ አቅርቧል
 • የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ማ/መምሪያው ቋሚ ሊቀ ጳጳስ እንዲመደብለት፣ አባ ሰረቀ ከዋና ሓላፊነታቸው እንዲነሡ፣ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ አባ ሰረቀ ካቀረቧቸው ክሶች አንጻር የማ/መምሪያውን ሥልጣን በሚያጠናክር አኳኋን እንዲሻሻል በመፍትሔ ሐሳብ አቅርቧል

October 28, 2011

(ሰበር ዜና) ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን በመቃወም ከተደረገው ትዕይንት ጋራ በተያያዘ የታሰሩት ወጣቶች ተፈቱ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 16/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 27/2011/ PDF)፦ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከውስጥና ከውጭ እየተካሄደ የሚገኘውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ በመቃወም እና ቅዱስ ሲኖዶስ በእንቅስቃሴው አራማጆች ላይ የቀረቡ ማስረጃዎችን መርምሮ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ለመጠየቅ ከተጠራው የተቃውሞ ትዕይንት ጋራ በተያያዘ ከጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ማታ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ከታሰሩት ወጣቶች መካከል በተባባሪነት የተከሰሱት ስድስቱ ዛሬ ማምሻውን ተፈተዋል፤ በብር 800 ዋስ እንዲወጡ የተወሰነላቸውና ‹ዋነኛ› የተባሉት ሁለቱ ወጣቶችም በነገው ዕለት እንደሚለቀቁ ይጠበቃል፡፡

October 26, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ 17 አጀንዳዎችን በማጽደቅ መወያየቱን ቀጥሏል


 • READ IN PDF.
 • በቤተ ክርስቲያን ሥርዐተ እምነት ላይ ያለውን ችግር በቀረበው ማስረጃ ላይ ተመሥርቶ መወያየት፣ የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ንግግር ፍጻሜ የሚገኝበት ሁኔታ፣ በቃለ ዐዋዲው መሻሻል የሚገባቸውን ክፍሎች መወሰንብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሞተ ሥጋ ሲለዩ [ሀብት፣ ንብረታቸው] ምን መሆን እንዳለበት፣ ስለ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ በአጣሪ ኮሚቴው ተጠንቶ በቀረበው ጽሑፍ ላይ መወያየት የሚሉት ከአጀንዳዎቹ ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው
 • የተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እና የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻል የአጀንዳ ሐሳቦች ተቀባይነት አላገኙም

October 25, 2011

ከቅዳሜው ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን የሚቃወም ትዕይንት ጋራ በተያያዘ ፖሊስ ተጨማሪ ወጣቶችን እየያዘ ነው


 • ፓትርያርኩ፣ ተሐድሶዎቹን ደግፈው ለቆሙትና በፖሊስ ለታሰሩት ወጣቶች ለቀለብ እንዲሆናቸው በሚል፣ ዛሬ 10 ሺህ ብር ልከዋል እየተባለ ነው 
 • ለሌሎቹ ወጣቶች ግን ስላደረጉት ነገር ምንም አልተሰማም፤
 • (READ IN PDF. and Youtube.)
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 25/2011)፦  “ተቻችሎ እና ተከባብሮ የኖረውን ሕዝብ ወደ ብጥብጥ በመምራት እና ሰው በመደብደብ የሚሉ ሁለት የወንጀል ክሦች የቀረቡባቸው “የአዲስ አበባ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ማኅበር” ስምንት አባላት ትላንት ጥቅምት 12 ቀን 2004 .ም ጠዋት  በአዲስ አበባ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ከስምንቱ መካከል ስድስቱ እያንዳንዳቸው በብር 600 ዋስ እንዲወጡ ሲወሰንላቸው፣ የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ለጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር - ዋነኛ አስተባባሪዎች ናቸው በሚል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳንን ከምሁራንና ከካህናት ጋር ለማጋጨት እየተሞከረ ነው


 •  ማኅበሩ ምላሽ አለመስጠቱ ብዙዎችን አበሳጭቷል፤ (TO READ IN PDF)
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 25/2011)፦ ተፋፍሞ በቀጠለው የፀረ ፕቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪ ነው የሚሉትን ማ/ቅዱሳንን በመቃወም ላይ የሚገኙት የተሐድሶ-መናፍቃን አሁን በያዙት አዲስ ስልት ማኅበሩ ከታዋቂ ምሁራን እና ካህናተ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማጋጨት እየሞከሩ ነው።  

“ተሐድሶን” የተቃወሙት ወጣቶች በእስር ላይ ናቸው


 • READ IN PDF
 • ወጣቶቹ “ሕዝብን ወደ ብጥብጥ የመምራት” እና “ሰውን የመደብደብ” ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል
 • ወጣቶቹ እርስ በርስ የማይተዋወቁ እና ከተለያየ አካባቢ የመጡ “የአዲስ አበባ ጥምቀት ተመላሽ ወጣት ማኅበር” አባላት ናቸው፤ ማኅበሩ ወጣቶቹ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል
 • የሕገ ወጡ ቡድን አባላት (በጋሻው ደሳለኝ፣ በሪሁን ወንደወሰን፣ ትዝታው ሳሙኤል. . .) እና ለወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ቀራቢ የሆኑ ባለሥልጣናት ወጣቶቹ የዋስትና መብታቸውን ተነፍገው በእስር እንዲሰነብቱ እየተሯሯጡ ነው
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 25/2011)፦  “በተለያዩ ዘዴዎች ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር ከውስጥና ከውጭ እየተከናወነ ባለው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተወያይቶ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ታሪካዊ ሚናውን እንዲጫወት” ለመጠየቅ ቅዳሜ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመሰብሰብ ድምፃቸውን ካሰሙት ከ1000 የማያንሱ ወጣቶች መካከል ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙት ስምንት ወጣቶች ጥቅምት 13 ቀን 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡ (Click this for Pictures)

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ


 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአጀንዳ ረቂቅ ላይ ሲወያይ ዋለ
 • READ IN PDF.
 • በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እና በዕርቀ ሰላም ጉዳይ አጀንዳ ላይ ልዩነቶች አሉ
 • የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እና ማኅበረ ቅዱሳን ከማ/መምሪያው ጋራ ስላለው ግንኙነት የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት በአጀንዳው ረቂቅ ውስጥ ተካተዋል
 • “ያረፉ ብፁዓን አበው ሀብት እና ንብረት ወራሾች ነን” በሚሉ ሐሰተኞች ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እየተቸገረ መሆኑ ተገለጸ
 • “በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት የካህናት እና የምእመናን ተሳትፎ ይጨመርበት፤ በጳጳሳት ሀብት እና ንብረት ውርስ ጉዳይ የቀድሞው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይመለስ” (የዜና ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አንቀጽ)፤
 • “ዛሬ ገንዘብም ጭምር የሚዘረፍባትና የሚነጠቅባት እንጅ ቅኔ ብቻ የሚዘረፍባትና የሚነጠቅባት የትንቷ ደሃ ቤተ ክርስቲያን የለችም” (ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ)፤

October 23, 2011

የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 30ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ተጠናቀቀ


30ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ 4ኛ ቀን ሪፖርታዥ
 • READ IN PDF.
 • የቅዱስ ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎት ተካሂዷል፤ “ዝክረ አበው” የጸሎት ሥነ ሥር ሥርዓት ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፡፡
 • 30ው አጠቃላይ ጉባኤ ባለ33 ነጥብ የውሳኔ ነጥቦች እና የጋራ አቋም የያዘ መግለጫ አውጥቷል፤ ከእኒህም መካከል፡-
Ø   የአብነት ት/ቤቶች ትምህርት ከዘመናዊው ትምህርት እና ሥርዓት ጋራ ተቀናጅቶ ሊሰጥ በሚችልበት ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሥርዓተ ትምህርት በትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ማዕከልነት እንዲዘጋጅ፤

ሊቃነ ጳጳሳቱ ፓትርያርኩን በበቀለኛነት እና ጣልቃ ገብነት ወቀሱ


 • READ IN PDF.
 • ሁለቱ የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በፓስፖርት እና በመኖሪያ ፈቃድ እድሳት እጦት እየተንገላቱ ነው፤ ሁለቱም ሊቃነ ጳጳሳት በ30ው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ይሁን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ አይገኙም
 • “ትኩረት ባለመስጠት ይሁን በሌላ ምክንያት አብዛኞቹ በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በጉባኤው ላይ አልተገኙም፡፡ በአርኣያነቱም ሆነ በምሳሌነቱ ልዩ በሆነው በዚህ ዓለም አቀፍ 30ኛው ጉባኤ ላይ በመገኘት አንድነትን አለመግለጽ ቅሬታን ከማሳደሩም በላይ ጥያቄን ሊያስከትል ስለሚችል ቅዱስ ሲኖዶስ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን የማስተካከያ መመሪያና ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጉባኤው በአጽንዖት ጠይቋል፡፡” (የስብሰባው የጋራ አቋም መግለጫ)
 • “ጥሪው ለሥራ ሳይሆን አሳስሮ ለማስቀመጥ ነው፤. . . እልህ አስጨራሽ ሥልጣንዎ በእምነት ካልሆነ በሥጋ አመለካከት የሚወጡት አልነበረም፤ . . .  በቀልን ለተጠማ አባት ራሴን አሳልፌ አልሰጥም” (ብፁዕ አቡነ አብርሃም)
 • የሰሜን አሜሪካው የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ሲኖዶሱ ያልወሰነበት ነው በሚል የሊቃነ ጳጳሳቱን ተቀባይነት አላገኘም

October 22, 2011

ሕገ ወጡ ሰባክያንና ዘማርያን የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴውን በመቃወም የተቃውሞ ትዕይንት ሊያካሂዱ ነው


 • READ IN PDF.
 • መላው የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አባላት የሕገ ወጦቹን የተቃውሞ ትዕይንት በፀረ-ተቃውሞ ትዕይንት እንዲመክቱ ተጠርተዋል
 • ሕገ ወጦቹ ሰባክያንና ዘማርያን የፀረ-ተሐድሶ ሰባክያን ጥምረት አባላትንና ማኅበረ ቅዱሳንን በስም አጥፊነት ከሰዋል
 • በመ/ር ዘመድኩን በቀለ ላይ ‹የጠፋ ስማቸውን የሚያድስ› ርምጃ እንዲወስድ በፍ/ቤቱ አካባቢ ውትወታ እያካሄዱ ነው፤ የፍ/ቤት ቀጠሮው ከጥቅምት 3 ወደ ጥቅምት 28 ተዛውሯል
 • ሕገ ወጦቹ በፊደል ሬስቶራንት ተሰብስበው ሲመክሩ አምሽተዋል
 • መናፍቃን በሁሉም አህጉረ ስብከት በሚያደርጉት ስልታዊ ዘመቻ የፓትርያርኩን ድጋፍ አግኝተዋል” (የፀረ-ተሐድሶ ሰባክያን ጥምረት የአቋም መግለጫ)፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 9/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 20/2011)፦ በ30ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የቀረቡት የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች በከፊል እንዳሳዩት፣ ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ወር 2001 ዓ.ም በሕገ ወጥ እና አጉራ ዘለል ሰባክያንና ዘማርያን (ማኅበራት) ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እየተደረገ ርምጃ እንዲወሰድ ለመላው አህጉረ ስብከት ያስተላለፈው ሰርኩላር (መመሪያ) አበረታች አፈጻጸም ታይቶበታል፡፡

October 21, 2011

30ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ 3ኛ ቀን ሪፖርታዥ


ቃለ ዐዋዲው እንዲሻሻል ተወሰነ
 • TO READ IN PDF, CLICK HERE.
 • በቋንቋው ጠንቅቆ የሚያስተምር መምህር ባጣው በአዲሱ የቄለም ወለጋ ሀ/ስብከት በተሐድሶ መናፍቃን ከተወረሩት ሰባት ወረዳዎች በአንዱ ወረዳ በሚገኙ ሰባት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሴቶች ካህናቱን አንበርክከው ይጸልዩላቸዋል፤ ‹ቅዳሴ አያስፈልግም፤ ቅዱሳን አያማልዱም› የሚል ክሕደት በግልጽ እየተነገረ ነው”/የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት/፤
 • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ፓትርያርኩን 35% ድርሻ ብር 24 ሚልዮን ገቢ አደረገ፤ “ኑሯችን ለምንሰብከው ምእመን ምሳሌ የሚሆን ነው ወይ?” ሲሉ የጠየቁት የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ “እጃችን መሰብሰብ አለበት” ሲሉም መክረዋል፤ ጉባኤው ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ አባ ገ/ማርያም ገ/ሥላሴ ከመቀመጫው ተነሥቶ ከፍ ያለ ጭብጨባ/standing ovation/ ችሯቸዋል
 • በከምባታ አላባ እና ጠንባሮ ሀ/ስብከት በአንድ ቀን እስከ 2228 ሰዎች ተጠምቀዋል፤ በዕለቱ የሀገር ሽማግሌዎች የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን ዝናም እንዲያዘንሙላቸው ጠይቀዋል፤ በተደረገውም እግዚኦታ ለ40 ደቂቃ ያህል ዝናም ዘንሟል፤
 • በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ከ70 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን 52ቱ ደቡብ አፍሪካውያን ካህናት የሚያስተዳድሯቸው ናቸው፤

October 20, 2011

30ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ 2ኛ ቀን ሪፖርታዥ


ጉባኤው ቤተ ክህነቱ ቃለ ዐዋዲውን ማስከበር እንዳልቻለ አመለከተ
 • TO READ IN PDF, CLICK HERE.
 • የቤተ ክርስቲያን ቃለ ዐዋዲ/ሕግ፣ ደንብ/ እና የኦዲት ሪፖርት ከቤተ ክህነቱ መዋቅር ውጭ ዕውቅና መነፈጉ በመንግሥት አካላት ፊት የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስጠበቅ ዕንቅፋት ፈጥሯል
 • “የመንበረ ፓትርያርኩ እና የሀገረ ስብከት ኦዲተሮች በመንግሥት ዘንድ ዕውቅና እና ተቀባይነት እንደሌላቸው በተግባር አረጋግጠናል” (የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ተሳታፊ)
 • “. . . ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተሰጣት ሕጋዊ መብት እና ግዴታ  በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ደንብ እንዲሠራበት በፍትሐ ብሔሩ ሕግ በተደነገገው መሠረት ቃለ ዐዋዲው በመንግሥት ዘንድ ተቀባይነት አለው፤ [ነገር ግን] የሕግ አገልግሎቱ ጠበቆቻችን የዕውቀት ችግር ይኖርባቸው ይሆን? ሁልጊዜ መረታት ነው ሥራቸው!!” (ብፁዕ አቡነ ናትናኤል)

በጀርመን በአንድ ቄስ ምክንያት አለመግባባት ሰፍኗል

 (ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 8/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 19/2011/ TO READ IN PDF, CLICK HERE)፦ በጀርመን የኢ/ኦተ/ ቤተ ክርስቲያን ከመናፍቅነት ተመልሷል በተባሉ የቀድሜ ቄስ ምክንያት የተፈጠረው አለመግባባት ሳይፈታ መቆየቱ የጀርመን ምንጮቻችን አስታውቀዋል። አለመግባባቱ በአዲስ መልክ ሊያገረሽ የቻለው የሰሜን ምእራብ አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ለኚሁ ከመናፍቃን ቤት ኖረው ተመለሱ የተባሉት ቄስ የትምቦታ ሄደው እንዳያስተምሩ፣ ውሳኔ እስኪያገኙ ድረስ በደብራቸው እንዲቆዩ በስልክ መመሪያ ከሰጡ በኋላ ነው ተብሏል።

October 18, 2011

30ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ሪፖርታዥ


 • TO READ IN PDF, CLICK HERE.
 • ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ቤተ ክርስቲያን ወጥ/ማእከላዊ/ የበጀት አስተዳደር በምትከተልበት አሠራር ላይ ጉባኤው ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጥሪ አድርገዋል
 • የሰበካ ጉባኤ ቃለ ዐዋዲ ይሻሻላል፤ በሁሉም የቤተ ክርስቲያን መዋቅር በዕቅድ መሥራት እንዲለመድ ይደረጋል
 • በ2004 ዓ.ም ተጠቃሎ በአንድ ጥራዝ የተዘጋጀው የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስ ይታተማል፤ በ2000 ዓ.ም በታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል አቀማመጥ በሆሄያት አገባብ እና በትርጉም ስልቶች ረገድ የክለሳ ምልክት ተደርጓል፤ የዐማርኛ መዝገበ ቃላትን የያዘ የሆሄያት አገባብ መጽሐፍ ይዘጋጃል
 • ጉባኤው ለውይይት እና ጥያቄ በተፈቀደው የአንድ ሰዓት ጊዜ አንዳችም ሐሳብ ሳያነሣ አህጉረ ስብከት ለመንበረ ፓትርያርኩ በሚያደርጉት የ35% ፈሰስ /የፐርሰንት ገቢ/ ላይ ያተኮሩ ሪፖርቶችን መስማቱን ቀጥሏል::

October 17, 2011

በሃይማኖት አክራሪነት እና ጽንፈኝነት ዙሪያ የተጀመረው ውይይት ቀጥሏል

 • “ሂቃብ”ን የሚከለክል መመሪያ ሊወጣ ነው::
(Addiss Admas):- ልማት ዴሞክራሲ እና የሃይማኖት አክራሪነት” በሚል ሰነድ ላይ በመመሥረት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መስከረም 25 ቀን 2004 ዓ.ም በፌዴራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ከመገናኛ ብዙሃን አካላት እና ባለሞያዎች ጋር የጀመረውን ውይይት በመቀጠል ከዘጠኝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ነው፡፡

October 15, 2011

ተሐድሶዎች በስም ሥርቆት ዘመቻ ተጠምደዋል፣ የእውነተኛ ኦርቶዶክሳውያንን ስሞች መጠቀም ጀምረዋል


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 3/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 14/2011)፦ ለብዙ ጊዜ በሐሰት ትምህርትቻው ምንም ነፍስ መማረክ ያቃታቸው አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም በማስመሰል፣ አርማቸውን እና ፎቶግራቻውን በመጠቀም ለማጭበርበር በመሞከር ላይ ናቸው። በዚህ በአዲሱ ዘዴ ስሙን እና ፎቶግራፉን በፌስቡክ መጠቀም የጀመሩት መ/ር ዘመድኩን በቀለ ነው። በእርሱ ስም ያወጡት መልእክት የሚከተለው ነው።

October 14, 2011

“የኢ/ኦ/ተ/ቤ ምእመናን ዓለም አቀፍ ማሕበር” ጉባዔውን አካሄደ፣ ውሳኔዎችንም አስተላለፈ

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 3/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 14/2011)፦ በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት መቀመጫውን ያደረገው እና “የኢ/ኦ/ተ/ቤ ምእመናን ዓለም አቀፍ ማሕበር” የሚል ስያሜ ይዞ የሚንቀሳቀሰው የምዕመናን እንቅስቃሴ ሁለተኛ ዓመታዊ ጉባዔውን በማካሄድ ጠቃሚ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የተላከልን መግለጫ ያመለክታል። ማሕበሩ ከዚህ በፊት የመጀመሪያ ጉባኤውን በ1999 ዓ.ም ያካሄደ ሲሆን አሁን የተደረገው ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

October 10, 2011

“በቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ዝም አንልም” (መግለጫ )


“ማኅበረ በዓለ ወልድ” የሚባለውና በሰሜን አሜሪካ በመንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የተሠማማኅበር ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች መነሻ አድርጎ “በቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ዝም አንልም” በሚል ርዕስ አቋም መግለጫ አውጥቷልየመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)