September 28, 2011

የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ አደጋ በቅኔም ሲጋለጥ

መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ

  • “በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን ስብከተ ወንጌል እንደበረታው ሁሉ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክናም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ ትምህርት ተስፋፍቶ መሰጠት ይኖርበታል፤” /መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በዘመን መለወጫ - ቅዱስ ዮሐንስ የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ላይ ቅኔያቸውን ሲያብራሩ ከተናገሩት/
  • “በቅኔው ካነሣችሁት አይቀር ስላሉት ችግሮች መናገር እፈልጋለሁ፤ የትኛው እግዚአብሔር ነው ያረጀው? የትኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት ያረጀችው? የሊቃውንቱ ዝምታ ምንድን ነው? አባቶችስ የማይገባ ትምህርት ሲሰጥ ዐውደ ምሕረታችሁን የማትጠብቁት ለምንድን ነው? ዝምድና፣ ጓደኝነት ወይስ ውለታ ይዟችኋል?. . . በ2004 ዓ.ም መሠራት የሚገባው ሥራ ይህችን ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ፣ በሚገባ ማስተዳደር ነው፤” (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቅኔውን መሠረት አድርገው ከተናገሩት)
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 17/2004 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 28/2011)፦መስከረም አንድ ቀን 2004 ዓ.ም በተከበረው የዘመን መለወጫ - ርእሰ ዐውደ ዓመት-እንቁጣጣሽ-ቅዱስ ዮሐንስ በዓል በመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያክ አቡነ ጳውሎስን እንኳን አደረ ለማለት የሚዘጋጅ ዓመታዊ መርሐ ግብር አለ። በዚሁ በዓል ላይ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆኑት መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ቀርበው ከሰጧቸው ቅኔዎች መካከል ከፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ የተነሣ ቤተ ክርስቲያናችን አደጋ እንደተጋረጠባት በመጠቆም የሐዋርያ እና ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስን ረድኤት የሚማፀነው አንዱ ቅኔ ዘመኑን የዋጀ ሆኗል።


ይኸው ጉባኤ ቃና ቅኔ እንዲህ ይላል፡-
ዘንስር ዮሐንስ ለኢትዮጵያ ዕቀባ
ለኦርቶዶክሳዊት ቅድስት እስመ ተሐድሶ ከበባ

መጋቤ ምስጢር መልደ ሩፋኤል ለቅኔያቸው በሰጡት ማብራሪያ፣ “በዚህ ዘመን እንደ ቀደሙት ሊቃውንት ተምሮ መገኘት ያስፈልጋል፤ አሁን ይህ እየታየ አይደለም፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን ስብከተ ወንጌል እንደበረታ ሁሉ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመንም [ዘመነ ፕትርክና] ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ ትምህርት ተስፋፍቶ መሰጠት ይኖርበታል፡፡ ይህ ባለመሆኑ ምክንያት ተዋሕዶን-ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ እየፈተናት ነው፤” ብለዋል፡፡

በእዚህና በመሳሰሉት የመጋቤ ምስጢር ቅኔዎች መከፋት የሚነበብባቸው አቡነ ጳውሎስም ለመርሐ ግብሩ ታዳሚዎች አሻሚ መልእክት የሚያስተላልፍ፣ በአንዳንዶች አገላለጽ ምርቅና ፍትፍት የሆነ ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል፤ ይህም በንግግራቸው መካከል ከታዳሚው በተሰማው ጉምጉምታ ግልጽ ሆኗል፤ መጋቤ ምስጢርንም ‹የትኛው ኦርቶዶክስ ነው በተሐድሶ የተከበበው? ቅኔው በአሉባልታ እና ባልተረጋገጠ ወሬ ላይ የተመሠረተ ነው› በሚያሰኝ የቃለ ምዕዳናቸው መንፈስ ሊገሥጧቸው ሞክረዋል፡፡

“በዚህ ዕለት እንኳን አደረሳችሁ ማለት ነው የሚገባኝ” በማለት ቃለ ምዕዳናቸውን የጀመሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ የፕሮቴስንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አደጋ ካለ መንሥኤው “የሊቃውንቱ ዝምታ” እና “የአባቶች /መምህራን/ ዐውደ ምሕረታቸውን ያለመጠበቅ” መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ይሁንና ይህች ቤተ ክርስቲያን ዝም ብላ የመጣች ባለመሆኗ በሃይማኖት ጉዳይ ቸልታን አስወግዶ እስከ ሰማዕትነት ሊደረስ እንደሚችል መክረዋል፡፡

በቃለ ምዕዳናቸው መጨረሻም “አባቶች፣ አስተዳዳሪዎች፣ አለቆች ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻችሁን የክብር ልብስ ለብሳችሁ ቅዳሴ ማስቀደስ፣ የትኛው ቀደሰ/ አልቀደሰም ብሎ መቆጣጠር፣ ቢሮ ገብቶ መውጣት ብቻ አይደለም ተግባራችሁ፤ በ2004 ዓ.ም መሠራት የሚገባው ሥራ ይህችን ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ፣ በሚገባ ማስተዳደር መሆን ይኖርበታል፤” ብለዋል፡፡

ፓትርያኩ ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን በሚመለከት በተለያዩ መድረኮች ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች ዋነኛው የማስረጃ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በማኅበረ ቅዱሳን፣ በሐዋሳ ምእመናን፣ አሁን በቅርቡ ደግሞ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተዘጋጁ በርካታ ማስረጃዎች በገለጻ መልክ ቀርበውላቸዋል የተባለ ሲሆን፤ በጽሑፍ እና በምስል ወድምፅ ተጠናቅረው በሲኖዶሱ ጽ/ቤት አማካይነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡

ግልጽ እና ቅርብ እየሆነ የመጣውን አደጋ ለማየት የተከፈተ ዐይን፣ የሚሰማ ጆሮ እና የሚያስተውል አእምሮ ካለ ደግሞ ባለፈው ዓመት በተለያዩ አካላት በተደረገው የተቀናጀ ጥረት ከዐውደ ምሕረት በወሳኝ መልኩ የተመታው የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ ኀይል ከልዩ ጽ/ቤታቸው ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች፣ በሀገር ውስጥ እና በባሕር ማዶ አህጉረ ስብከት ቢሮዎች/መዋቅሮች እና በትምህርት ተቋማት ውስጥ እየተሰገሰገ፣ የአቋምም ሽግሽግ እያደረገ መሆኑን መገንዘብ በተቻለ ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ፓትርያክ አቡነ ጳውሎስ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዐቢይ አጀንዳ ሆኖ እንደሚቀርብ በሚጠበቀው የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ ጉዳይ በደብዳቤ መመሪያ እስከ መስጠት ድረስ ሲጠይቋቸው በቆዩትና ስለቀረቡላቸው የሚታዩና የሚጨበጡ ከደርዘን በላይ ማስረጃዎች ምን አቋም እንደሚይዙ በወቅቱ የምናየው ይሆናል፡፡  

ቀጣይ የፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ እንቅስቃሴ አገልግሎትም ስብከተ ወንጌሉን እና ትምህርተ ወንጌሉን በተለያዩ አገባቦች ከማጠናከር ጎን ለጎን ቢሮክራሲያዊ መልክ እየተላበሰ የመጣውን የተሐድሶ-ኑፋቄ ምንደኛ በቅዱስ ሲኖዶስ እና በየደረጃው በሚወሰዱ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ርምጃዎች በማጋለጥ ማፍለስ/ማጥራት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

7 comments:

Anonymous said...

እግዚያብሄር ተውጊ ነው። ስሙም እግዚያብሄር ነው። ግልጽ ሆኖ የሚታያወን የለም ይህ እንቀስቃሴ የለም የሚል ክፍል ካለ፤ አንድም ካለማወቅ የተነሳ ሊዎን ስለሚችል ማሳዋቅ ያለባቸው ወገኖች ቸል ሳይሉ ሊሳውቁ ይገባል። እያወቁ ግን የሚይድበሰብሱት ወይም እንቅስቃሴው እንደሌለ ሽንጣቸውን ገትረው የሚሞግቱት የበግ ለምድ የለበሱ በውስታቸው ግን ነጣቂ ተኩላ ያለባቸው ናቸው።

በቀድሞ ዘመን አይሁድ ለእግዚሃብሄር የቆሙ መስሎዋቸው.. ጌታችን ልብስ ላይ እጣ ተጣጣሉ። በዚህ ዘመን ደግሞ ፕሮቴስታንቱ ክፍልና ያሰማሩዋቸው ልጆቻቸው ፤ በቤተክርስቲያን ላይ ከአይሁድ የተማሩትን እጣ እየተጣጣሉ ይዘርፋሉ፤ ክርስቶስ የሞተለትን ክርስቲያን ይዘርፋሉ።

Anonymous said...

well done megabe mister!!!endih amargna kalteredu bekineyw asreduachew enji.endenante yalu kin agelgayochen amlak yabzalin.

lele said...

abeato laABATOCHACHEN MASETAWALE YESETELEN.

ርብቃ ከጀርመን said...

ሰላም ደጀሰላሞች እንደምን ከረማችሁ እንኩዋን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ! ደጀሰላሞች ከዚህ በመቀጠል ላካፍላችሁ የምፈልገው ነገር ቢኖር እኛባለንበት በፍራንክፈርት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን በመስቀል በአል ላይ የተፈጠረውን ድፍረትና ንቀት ነው! የሙኒክ ቅዱስገብርኤል በተክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩት ግለሰብ ካንድ ከስድስት ወር በፊት በተደረገባቸው የሂሳብ ማጣራት (ኦዲት) ከመቶ ስልሳሽብር በላይ ጉድለት ተገኝቶባቸው በምእመን ጩሀትና አቤቱታ ጉዳዩን ለበላይ አቅርበው በመከራ ዉሳኔተሰጠበት ውሳኔውም ካገልግሎት እንዲታገዱና የለውን ንወያተቅዱሳን እንዲያስረክቡ ተደረገ ገንዘቡን በተመለከተ ጉዳዩን ፍርድቤት ይዞታል በዚህመሀል ሙኒኮች ጠንካሮችናቸው ካገርቤት አባት አስመጥተው መገልገላቸውን ቀጥለዋል ይህበንዲህ እንዳለ ለመስቀል በአል በተለያየከተማ የሚኖረው ምእመን በ24 /09/ 2011 ፍራንክፈርት ገባ እንህም ባለዳ(ዘራፊ) ለበአሉ ከመጡት ውስጥ አንዱ ነበሩ እናም የጸሎት ፕሮግራም ለይ እኒሁ ሰውየ ልብሰተክህኖ አድርገው ብቅማለት ከዚያም የሙኒክ ምእመናት እርሳችው የሚያገለግሉከሆነ ወደቤታችን እንሄዳለን ስላሉ ሳያገለግሉ ይቀራሉ የቅዳሜውደመራ በዚህ አብቅቶ እሁድ ከቅዳሴበሁዋላ ታቦት ሲወጣ እንደፈራነው እኒህ ሌባ ሰውየ ታቦቱን ተሸክመው ብቅ ምንእናድርግ ለታቦቱ ክብር ሲባል አንጀታችን እያረረ አሳልፈን ምሳላይ ለምን እንዲህ እንዳደረጉ የማርያሙን መለኩሴ ስንጠይቃቸው ባሉበት ቦታ ነው እንጅ ሌላቦታ ማገልገል እንደሚችሉና ክህነታቸው መታገድ እንደማይችሉ ገለጹልን ከዚያም የተለያዮ ምእመናት በነገሩ ግራ ስለተጋቡ ለብጽእነታቸው ደውለውሲጠይቁ እንዳልፈቀዱላችውና ከእምነት ማጉደል በላይ ክህነትን የሚያሳግድ ምን አለና ብለው መለሱ ሌላውንም አገልጋይ መነኩሴ ስንጠይዋቸው እርሳቸው ታቦት እንደሚሸከሙና እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው እና እየተዘጋጁ እያሉ ሰውየው ተሸክመው ሲያዮዋችው እንደደነገጡ ነው የተናገሩት ታዲያ ደጀሰላሞች እንዲህ አይነቶችን በቤተክርስቲያን ስርሁነው ምልኩስናቸውን ከሸጡ አባቶች ጋር እንዴትነው መዝለቅ የምንችለው እስኪ ምክት ካለችሁ የሚመለከተውን ክፍል አነጋግራችሁ መልስ ስጡበት አስተያየት ያለውም አስተያየቱን ይስጥበት !የድንግል ማርያምልጅ ቤተክርስትያንን ይጠብቅልን አሜን!

ገራ

Anonymous said...

I do agree with the forst anonym. "Netaki tekulawoch nachew.."

zedebre tsige said...

pየተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶክሳውያን:-
አቡነ ጳውሎስ ተሐዲሶን በተመለከተ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ምክክር ማድረጋቸው ይታወቃል::
በምክክሩ ላይ አቡነ ጳውሎስ ማኅበሩ ያቀረበውን መረጃ ካዩ በኋላ "ይህ ሁሉ በቤተክርስቲያን ላይ ስደረግ ምን እየሠራችሁ ነው ?"በማለት እርሳቸው ማኅበሩ የ"ተሐዲሶ"ን ሤራ ማጋለጥ ሲጀምር ነገሩን ከዓረቡ ዓለም ብጥብጥ ጋር አመሳስለው ለማስቆም እንዳልጣሩ ስለ "ተሐዲሶ "መረጃ የሌላቸው ለመምሰል ሞክረዋል:: ጉዳዩ ከማንም የተደበቀ ባይሆንም::
አቡነ ጳውሎስ ይህን ምክክር ያደረጉበት ዓላማ ብዙ አንድምታ ያለው ብሆንም በጥቅቱ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል:-
1.ምናልባት ማኅበሩ በቂ መረጃ ባይኖረው ኖሮ ለማሳጣት እና ለከሳሾች አሳልፎ ለመስጠት
2.የአባ ሰረቀን ጉዳይ ለማርገብና ማኅበሩን ለማለዘብ
3.አቡነ ጳውሎስ ተሐዲሶን መደገፋቸውና አጣቃላይ ቤተክርስቲያኒቱን ለማደከም የሚያደርጉት ሴራ በምእምናን ሁሉ ዘንድ ግልጽ እየሆነ መምጣቱን ስለተገነዘቡ ምእመኑ "ፓትርያርኩ ተመልሰዋል "በማለት እንዲዘናጋና እርሳቸውም ሥራቸውን ለመሥራት[ለዚህ ማሳያ የሚሆን ፓትርያርኩ ውስጥ ለውስጥ እየሠሩ ያሉትን ቀጥለን እናያለን]
4.በአዋሳ ምዕመናን የተዘጋጀው ቁጥር 2 ቭሲዲ አቡነ ፓውሎስ ካልተመለሱ የእሳቸውን ቤተክርስቲያንን የመዳከም ሴራ በመረጃ የተደገፈውን ብቻ በመውጣት እንደሚያገልጥ ማስጠንቀቁን አቡነ ጳውሎስ ያውቁታል ::አቡነ ጳውሎስ ከዚህ ጀርባ ማኅበረ ቅዱሳን አይጠፋም የሚል እምነት ስላላችው ከማኅበሩ ጋር አብሬ የሆንኩ የመሰልኩ እንደሆነ ቪሲዲው ከመውጣት ይቀራል ብለው ስላሰቡ::
አቡነ ጳውሎስ ፊት ለፊት ይህን ለመምሰል እየጣሩ ከኋላ ግን የሚሠሩት ሌላ ነው::
የማኅበሩ አባለት የሆኑ ሰባኪያነ ወንጌል በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ብዙ ጊዜ እንደሚያስተምሩ ይታወቃል ::
የደብሩ የስብከተ ወንጌል ኃላፊም ሰባኪያነ ወንጌሉን በግላቸው ስለ ትምህርት አሰጣጣቸው ስለሚወዱአቸው ብዙ ጊዜ እንደሚጋብዙአቸው ያወቁት አቡነ ጳውሎስ የማኅበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ሰባኬ ወንጌል ድርሽ እንዳይል ብለው ለስብከተ ወንጌል ኃላፊው በቀጥታ መመሪያ መስጠታቸውንና በመመሪያውም የስብከተ ወንጌል ኃላፊው እንደተጨነቁ የንስሐ አባቴና መምህሬ ነግረውኛል::
እንግድህ አቡነ ጳውሎስ መዋቅር እንኩዋን ሳይጠብቁ በቀጥታ ለአንድ የደብር ስብከተ ወንጌል ኃላፊ በቀጥታ መመሪያ መስጣታቸው የተሐዲሶን ዓላማ ለመጽፈጸም ቁርጠኛ መሆናቸውን የሚያሳይ ካልሆነ ምን ልሆን ይችላል ?
እንዲያውም ከተሐዲሶዎቹ ጋር እየተመካከሩ የሚሠሩ ነው የሚመስለው::
የእነ በጋሻው ማኅበር ሰብሳቢና የተሐዲሶ መናፍቃን ዋነኛ አቀንቃኝ ፍጹም ታደሰም በተመሳሳይ ሁኔታ የራሱ ሥራ "ተሐዲሶነቱ"ን አጋልጦበት ከደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ከጠፋ በኋላ እንታረቅ እያለ በድጋም የአከባቢውን ምእመናን ለማግባባት ሲሞክር ነበረ ::አልተሳካለትም እንጂ::
ባጋሻውም በFM ስለማመጥ ነበረ::
ማኅበሩም ማንንም ሳይፈራ በምንም ሳይታለል ቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተጋለጠውን አደጋ በመከላከል የድርሻውንና ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ጠንክሮ መሥራት ይጠበቅበታል::
ምእመናን ሁሉ ቤተክርሰቲያናቸውን በንቃት የሚጠብቁበትና በቤተክርስቲያን ጉዳይ በቀጥታ የሚሳተፉበትን ባህል ለማደበር ሥራ መሠራት አለበት::
የቤተክርሰቲያኒቱ ገንዘብ በትክክል ለቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎት ማዋሉ ሳይረጋገጥ በየ ጉዳይ ጥላ መዘርጋት መቆም አለበት:: አቡነ ጳውሎስ የቤተክርሰቲያኒቱን ብር እየበዘበዙ ልቃውንቱና አገልጋዮቹዋ የሚመቅቁበትና ተስፋ የሚቆርጡበት አገልጋዮቹዋ የሚፈልቁበት ምንጮች የሚደርቁበት ሁኔታ መቆም አለበት::
በምቀጥለው የጥቅምት ስኖዶስ ስለ ተሐዲሶ የአቡነ ጳውሎስ ተጽእኖ ያላረፈበት ወሳኔ እንዲተላለፍና ውሳኔውም እንድተገበር የሚመለካታቸው አካላትና የምእመናን ድርሻ ምን መሆን አለበት ?

guadengash said...

ለርብቃ
ርብቃዬ!
ለስንቱን ሌባ ብለን መልስ እንሰጣለን! ደግሞ በአካባቢያችን ያሉትን ማፊያዎች ለቅመን መጨረስ ስላቃተን ይቅርታ
ብቻ ወደ እግዚአብሔር እንጩሕ፤ በተቻለ ዓቅምም ባለንበት ቦታ ሁነን ራሳችን እንዋጋ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)