September 16, 2011

“አቡነ ጳውሎስን እና አቡነ መርቆሬዎስን የማስታረቁ ጥረት ቀጥሏል” (ነጋድራስ ጋዜጣ)


(ነጋድራስ፤ ቅጽ 08 ቁጥር 296 ዓርብ፣ መስከረም 05 2004 .)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሥርዐተ ጵጵስና በምትመራበት ፍትሐ ነገሥት፣ በአንድ መንበርና ዘመን ሁለት ፓትርያሪክ መሾም እንደማይቻል መደንገጉን የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ ይህ ድንጋጌ በ1984 ዓ.ም ላይ አክባሪም አስከባሪም አልነበረውም፡፡ ስለዚህም በወቅቱ የቤተ ክርስቲያኗ አራተኛ ፓትርያሪክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወት እያሉ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተመርጠው መንበረ ፓትርያሪኩን እንደተረከቡ ይታወሳል፡፡


“በጤና ምክንያት ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቅቀዋል” የጠባሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አሜሪካ ከገቡ በኋላ፣ ‹ሕጋዊ የቤተ ክርስቲያኗ ፓትርያሪክ ነኝ› የሚል አቋም በመያዝ የራሳቸውን ሲኖዶስ አቋቁመዋል፡፡ ለበርካታ አባቶችም የጵጵስና ማዕርግ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

ሁለቱን አባቶች ለማቀራረብና ለማስማማት ተደጋጋሚ ሙከራዎች ሲደረጉ የቆዩ ቢሆንም ጎላ ብሎ የሚጠቀሰው ባለፈው ዓመት በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሥሐቅ የተጀመረው ድርድር እንደሆነ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ አትናቴዎስ፣ አቡነ ቀውስጦስ በአባልነት፣ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በጸሐፊነት የሚገኙበት የመንበረ ፓትርያሪክ ተወካዮች ሆነው እንዲደራደሩ ሲደረግ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም በዋና አስታራቂነት ከተመረጡት ሰዎች አንዱ ነበሩ፡፡

በአሜሪካ ከሚገኙት የሃይማኖት አባቶች በኩል በሽማግሌነት የተመረጡት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሥሐቅ ድርድሩ እንደቀጠለ መሆኑንና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አለመኖሩን ለነጋድራስ ገልጸዋል፡፡. . . “በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ብሔረሰቦች ዘንድ ሰው የገደለ ሳይቀር በሽማግሌ ታርቆ ሰላማዊ ኑሮ ይኖራል፡፡ ነገሥታት ተዋግተው በሽምግልና ተቀምጠው ይቅር ለእግዜር ተባብለው በሰላም መኖራቸው ታሪክ ይገልጣል፡፡ የዚህ ዘመን የፖሊቲካ መሪዎች በባህላዊው መንገድ ችግራቸውን ለምን መፍታት አልቻሉም? የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን ምን ድረስ የተሳካ ሥራ እየሠራ ነው?” በማለት ነጋድራስ ጠይቋል፡፡ “ይህ ባህል አልተለወጠም ብዬ አምናለሁ፤ የተለመደው ባህላችን እንዲቀጥል በሁሉም በኩል እየሞከርን ነው፤” በማለት መልስ የሰጡት ፕ/ር ኤፍሬም ወደ ዝርዝር ጉዳዮች ለመግባት ዝግጁ አለመሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡

14 comments:

sharew said...

GOOD JOB GOD BLESS ETHIOPIA////

Kinfe-Michael said...

This is what happens when politics grips the church. The saying "Mech telemedena ketekula zimidina" works here. Abune Paulos should be left to God to receive his punishment. As Aleka Ayalew said, he is a guy who is trying to ruin the church and no one should work with him. This issue should be handled by the rules and regulations of the synod, not by a bunch of "elders" who try to calm down the current turmoil in the church. This smells like the work of a frightened government who is trying to avert any potential areas of unrest. The point is: "Yewishon neger yanessa wisho new." "Ke Paulos gar yabere yebetekirstiyan telat new."

Anonymous said...

ምን ይላሉ አባቶች

ምን ተይዞ ጉዞ !

lele said...

laabatochachen lebe yestelen AMELAKACHEN.amen

Anonymous said...

“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን/ጭነቱን”

ሁለቱ ጳጳሶች እንታረቅ ቢሉም እኮ ፡ ፈቃድ ካላገኙ የማይተሰብ ህልም ነው ነገሩ ።
አባ ጳውሎስ እኮ : ወያኔ ጫካ እያለ መርጦ ያቆያቸውና በትረ ሥልጣኑን ሲይዝ በሃይል አምጥቶ ያስቀመጣቸው የፖለቲካ ሹመኛ ናቸው ። ታዲያ ፡ የእነ አይተ መለስ አረንጓንዴ መብራት ካልበራ ፡ ማን ወንድ ነው የሚሞክረው ?
ብዙ አትድከሙ ፤ መለስ ከፈቀደ በሆነ መንገድ በአጭሩ እንዲያልቅ ያደርጋል ፡ ካልፈቀደ ግን አይፈቀድም ማለት ነው በቃ ። አርፎ መቀመጥ ነው ፡ አባ ጳውሎስ ከመለስ ትእዛዝ አንዲት ስንዝር ንቅንቅ እንደማይሉ የተረዳ ነገር ከሆነ ሰነበተ ።

Close source said...

It is all possible if EPRDF changes its most detasted politics of ethnic division. The main thing here is that our Church does not support such kind of politics and thus EPRDF wants someone who does not oppose it but work as instructed and keeps an eye on those who may be threat to its ugly policies in the Church; and Aba Paulos fits for this. In addition, he himself is helping these policies of divide and rule by weakening the Church in many ways such as giving protection to heretic movements in the church, embezzelement of the Church's treasure, expansion of other 'religious' organizations, suppressing the activities of Church organizations like MK, etc. Therefore, it is highly unlikely to come to terms with opposing forces of all the aforementioned points unless the party in power changes its BASIC policy of ethnic politics which has its right leg firmly stands in the Church. This is so because, practically, the reconciliation should ultimately be with opposing forces behind these two fathers, not just the two of them. I am eager to see the problems in our church and also in our country resolved by peaceful means or by negotiation. However, the big obstacle is the stubborness of the people in power who adopt this politics of ethnicity knowning full well that the Ethiopian people did not support or want this one policy from the beggining. Even if Aba Paulos quit today, Aba Markorios will not work with the present 'government' persuing this dirty politics of ethinicity that benefitted only Ethiopia's historical enemies. In short, the problems in our Church /the divisions/ have got political faces.

Anonymous said...

sham on us,
two highest priests are can not forgive each other, they teach us about our lord becoming human (Betewahdo) and and forgave us our sin even though we were the sinners. What kind of bible they are holding. For the sake of their Lord and for the love of Tewhado they should have abandon their "patriach" post, lower their ego, obey God and forgive eachother. Now a professor is going to try to make peace between them, shame on us, this is a shame for our church.

Anonymous said...

If the Issue were relegious,the recoinciaclation would have been so difficult for such highly spritual position fathers. As the result I have little hope there will be a peace between them. It is up the will of the people behind these fathers to make a real reconcilation. The case have a mix political,recial and religious issues. At the end of the day it is upto Melese Zenawi's government who can make the process easy or difficul even not unresolved since he has part on our church not to move in the right way from the begining of his power.

Anonymous said...

I hope this reconcilation will happen soon on the will of GOD.On the other hand there are few Bishops doing wrong things.Like "Abune Phanuel"He Ordained a deacon in charlotte St.Trinity Church (GELELETNGA)two weeks ago.That little boy (Who recieved this high responsibility) doesn't know any thing even to talk to in Amharic.That arch diocess area is belongs to Abune Abrham & he is doing such kind of things for the Second time with out Abune Abraham's knowledge.
Very upsetting activity!!!!!!

Yenoah Merkeb said...

እኔ ያልገባኝ ጳጳስ በሕይወት እያለ ሌላ ጳጳስ የመሾሙ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፡ አንድ ጳጳስ እንደ ፖለቲካ ስልጣን በሕይወት እያለ ስልጣኔን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ ማለት ይችላል እንዴ? እኔ ግን ወጣም ወረደ ለስንቱ ይተርፋሉ ስንቱን ያስተምራሉ፣ ይመክራሉ ተብለው የሚጠበቁ አባቶች እንኳን በአለማዊ አባቶች በመንፈሳዊም አባቶች ይቅር እንዲባባሉና ችግራቸውን እንዲፈቱ መጋበዛቸው እንደእኔ እምነት በጣም አሳዛኝ ነው። ምክነያቱም እንኳን ጳጳሳቱ ካህናቱና ዲያቆናቱም ሳይቀሩ ሁልጊዜ ስለ ፍቅር፣ ስለ ይቅር ባይነትና ስለሌሎች መልካም ነገር እየሰበኩ እነሱ ግን ይህንን መተግበር ሲያቅታቸው በግሌ የእውነት አንጀቴ ይቃጠላል። ይህ ደግሞ ለጠላትም በር የከፈተ ጉዳይ ነው።
ይቅር ባይ አምላክ እርሱ ይታረቀን። አሜን!!
የኖኀ መርከብ ከአ.አ.c

Dan said...

One American diplomat sometimes ago said, "Why can't Arabs and Israelis behave like good Christians?"

ምነው አረቦችና እስራኤሎች ለምን እንደ ጥሩ ክርስቲያን ችግራቸውን አይፈቱም አለ ይባላል::

ታድያ ዛሬም የኛዎቹ መርቆሬዎስ ና ጳውሎስ አይሁድ አስታራቂ (ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሥሐቅ) ፈለጉ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልም ምን እንደሚያስተምርም አልገባቸውምና

Anonymous said...

ነውር ኩራት የሆነበት ዘመን ላይ ደረስን እግዚኦ ነው
ይህን ሳያዮ ያለፉ አባቶቻችን ምንኛ የታደሉ ናቸው
እኔን የሚገርመኝ የዘመናችን "አባቶች" የልባቸው ጥንካሬ
ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ሁሉም በጊዜው ይስተካክላል ሰውም ያልፋል ሀውልትም ይፈርሳል እንደነ ሌኒንና ሳዳም ሁሴን እነሱም አልፈዋል ጣኦታቸውም ፈራርሶ ወድቁዋል
ሁሉም ሀላፊና ከንቱ መሆኑ ደግሞ በጣም ያስደስታል

Anonymous said...

ነውር ኩራት የሆነበት ዘመን ላይ ደረስን እግዚኦ ነው
ይህን ሳያዮ ያለፉ አባቶቻችን ምንኛ የታደሉ ናቸው
እኔን የሚገርመኝ የዘመናችን "አባቶች" የልባቸው ጥንካሬ
ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ሁሉም በጊዜው ይስተካክላል ሰውም ያልፋል ሀውልትም ይፈርሳል እንደነ ሌኒንና ሳዳም ሁሴን እነሱም አልፈዋል ጣኦታቸውም ፈራርሶ ወድቁዋል
ሁሉም ሀላፊና ከንቱ መሆኑ ደግሞ በጣም ያስደስታል

Anonymous said...

take their cross from their hand and give the a stick. It belongs to the holy. The cross represents salvation, forgiveness, love your neighbor, care, interception,life, humbleness, rssuraction, payment, "beza" etc

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)