September 23, 2011

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የሚል መጽሐፍ አሳተሙ


  • መጽሐፉ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ ነው በሚባል ሰው የተዘጋጀ እንደሆነ ተነግሯል፤
  • በመስቀል-ደመራ በዓል ዐውደ ትርኢት የሚያቀርቡ ወጣቶች የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊን ጨምሮ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና ሕገ ወጥ ሰባክያን በበዓሉ ላይ አንዳችም ተሳትፎ እንዳይኖራቸው አስጠንቅቀዋል፤
 (ደጀ ሰላም፤ መስከረም 12/2004 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 23/2011)፦ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አቡነ ጳውሎስን ሰርፕራይዝ አድርጌበታለሁ የሚሉትንና ከብር አራት መቶ ሺ በላይ ገንዘብ እንደወጣበት ተናገሩለት ሐውልተ ስምዕ በተመለከተ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የተሰኘ መጽሐፍ ማሳተማቸው ተሰማ፡፡ ወይዘሮዋ መጽሐፉን መስከረም 16 ቀን 2004 ዓ.ም ተከብሮ በሚውለው የመስቀል-ደመራ በዓል ላይ ለማሰራጨት እንደተዘጋጁ ተነግሯል፡፡


ወይዘሮዋ
ከ100 ያላነሱ ገጾች ያሉት ይኸው መጽሐፍ የተዘጋጀው፣ በወይዘሮዋ አቅራቢነት ከአቡነ ጳውሎስ ጋ የተዋወቀውና በፓትርያኩ ልዩ ጽ/ቤት ተቀምጦ ከኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ እና ላህይ በራቀ አገላለጽ በፓትርያኩ ስም የተለያዩ የጽሑፍ መልእክቶችን ሚያሰራጨው አሸናፊ መኮንን አማካይነት እንደ ሆነ ተዘግቧል፡፡

በቤተ ዘመድ ስም በፓትርያኩ ዙሪያ ለተሰበሰቡት አንዳንድ ግለሰቦች በፕሮቴስታንቶቹ ባህል እጁን እየጫነ እስከ መጸለይ መድረሱ የሚነገርለት ይኸው ግለሰብ ባለፈው ዓመት ብቻ በሰሙነ ሕማማት፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የደቀ መዛሙርት ምረቃ በዓል እና በፓትርያኩ 19 ዓመት በዓለ ሢመት ወቅት  “አባታዊ መልእክት ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ” እና “አባታዊ መልእክት ለደቀ መዛሙርት” በሚል አርእስት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያኩ ስም የተሰራጩት ጽሑፎች ያዘጋጀ ሲሆን ጽሑፎቹ በመሠረታዊ አስተሳሰባቸው ከኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ ሃይማኖት የሚፃረሩና የእምነትን ድንበር የሚያፈልሱ እንደሆኑ ተተችዋል፡፡

በጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም የተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና የአበውን የተቀደሰ ትውፊት በመጣስ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ቅጽር የተተከለው የአቡነ ጳውሎስ ሐውልተ ስምዕ ተነሥቶ በመንበረ ፓትርያኩ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር እንዲቀመጥ ላስተላለፈው ውሳኔ ተገዥ አለመሆናቸውን በተደጋጋሚ ያሳዩት ወ/ሮ እጅጋየሁ ባለፈው ዓመት ከ”ቁም ነገር” መጽሔት ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ሐውልቱ አሁንም አለ፤ ይኖራል፤ ይቀጥላል፤ የሚፈርስ ሐውልት የለም፤ ሐውልት መሥራት በቅዱስ አባታችን ጊዜ የተጀመረ አይደለም፤ ለሀገራቸው ብዙ ለሠሩትና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ለሆኑ አባት ሐውልት ይበዛባቸዋልን?” ማለታቸው ይታወሳል፡፡

በመስቀል-ደመራ በዓል እንደሚሰራጭ የተነገረለት መጽሐፍም ወ/ሮ እጅጋየሁ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመገዳደር በቃለ ምልልሱ እንደተናገሩት፣ “ሐውልቱ እንዳለ እና እንደነበረ እንደሚቀጥል” የሚገልጹበት፣ “በልዩ ሁኔታ ለማክበር” እያሰቡበት እንደሆነ ለሚነገረው የፓትርያኩ 20 ዓመት ሢመትም መቅድም እንደሆነ ተገልጧል፡፡

በተያያዘ ዜና ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነን ጨምሮ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ የሆኑት አባ ሰረቀ፣ በጋሻው ደሳለኝ እና አሰግድ ሣህሉን የመሳሰሉ ሕገ ወጥ ሰባክያን መስከረም 16 ቀን 2003 ዓ.ም በተለይም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በሚከናወነው የመስቀል-ደመራ በዓል አከባበር ወቅት በክቡር ትሪቡኑ እና በአደባባዩ ላይ አንዳችም ተሳትፎ እንዳይኖራቸው የዕለቱን ዐውደ ትርኢት ለማቅረብ በልምምድ ላይ የሚገኙት ከአምስት ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ቁጥራቸው 5000 የሚሆን የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አስጠንቅቀዋል፡፡

የማደራጃ መምሪያው ዋና ሐላፊ ስለ ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ ባላቸው አቋም፣ ማደራጃ መምሪያው የተሰጠውን ተልእኮ በአግባቡ ባለመወጣቱ እንዲሁም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያኩ የፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን ለመመከት ስለሚደረገው ትግል ባስተላለፉት መመሪያ ሳቢያ የዘንድሮውን የመስቀል-ደመራ በዓል ወደ አደባባይ ወጥቶ በማክበር እና ወደ አደባባይ ሳይወጡ በአጥቢያ ተወስኖ በማክበር መካከል የተለያዩ አቋሞች ሲራመዱ መቆየታቸው ተነግሯል፡፡

ጉዳዩ ያሳሰባቸው የሀገረ ስብከቱ እና የመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሓላፊዎች ከአድባራት እና ገዳማት አለቆች፣ ጸሐፊዎች እና የሰንበት ት/ቤቶች ተጠሪዎች ጋራ መስከረም ዘጠኝ ቀን 2004፣ የበዓል አከባበር ኮሚቴ አባላት እና የመንግሥት ተወካዮች ደግሞ ትንት መስከረም 11 ቀን 2004 ዓ.ም መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

በዘመን መለወጫው “የእንኳን አደረዎ” በዓል እና መስከረም 10 ቀን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከበረው የተቀጸል ጽጌ በዓል ከወትሮው በተለየ ዝቅተኛ የተሳታፊዎች ቁጥር ያሳሰባቸው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያኩ ለመስቀል-ደመራው በዓል ምእመኑ በስፋት ተቀስቅሶ ወጥቶ እንዲያከብር ተማነዋል፤ መንግሥት በበኩሉ ፓትርያኩ እና አንዳንድ ሓላፊዎች ምእመኑን የሚያስቆጡና ውዝግብ ውስጥ የከተቱ ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲበጅላቸው በአጽንዖት አሳስቧል ተብሏል፡፡

በሀገረ ስብከቱ 138 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የሚገኙትን ሰንበት ት/ቤቶች የሚያስተባብረው የአንድነት አመራር በበኩሉ በአባ ሰረቀ፣ በአጥማቂ ግርማ፣ በበጋሻው ደሳለኝ እና በአሰግድ ሣህሉ ላይ የተጠናቀሩ የምስል ወድምፅ እና የጽሑፍ ማስረጃዎችን በማጠናቀር ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲሁም ለቋሚ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ማስረከቡ ተመልክቷል፤ በቀረበው ማስረጃ መሠረትም የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ማስረጃዎቹን መመርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዲያሳልፍ ተጠይቋል፡፡ ከዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ጋራ ያለንን ዜና ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡  

7 comments:

Anonymous said...

I hope they warn more, that if they try to do anything at meskel adebaby, they should act like Ye Teklehimanot church sunday school. It is not about papasat, kahenat, diacons or sebskiyan, it is about our holy mother church. You, young PEOPLE with hot power, go forward and warn more and more then we will have peace on damera day. BABATOCHISH FANTA LIJOCH TETEKULCH. ENAT BETEKIRISTIAN DES YIBELISH. AMEN.

Anonymous said...

Meskerem 10 2003 ymilw 2004 bitilut

Anonymous said...

i will say if those people participating like Begashaw, wozero Ejigayew and some others who support tehadiso and build that statue this event is the only chance to protect our church show them how we care about our church. no matter what happen in that day it is up to our church leaders problem because if have done their part we shouldn't come this far. it will be shame for those who have been manipulating our church for their interest. this is the time we show them that we no longer waiting because we already waited enough. i am sorry for some of our fathers who worked hard through their life seeing us disrespecting them in front of the world. but this is the time to do our part now. i strongly admire u all sunday school stay focus and protect our church may God bless you all and protect our church

Anonymous said...

እግዚአብሔር አምላክ ለኦ/ተዋሕዶ አዋኪዎች
ልብ ይስጥልን!!!! ምነው ወ/ሮ እጅጋየሁ 100 አመት እንክዋን ለማንኖርባት በዚህች እድሜ 2000ዘመን ያስቆጠረችን ቤተክርስቲያን የመናፍቃኖች ቀኝ እጅ ሆነሽ ጥላሸት ትቀቢያለሽ::
አንቺ እና ዘንዶ በጋሻው አባ ሰረቀ እንዲሁም ያሬድ አደመ በምትሰሩት ሥጋዊ ማሽቃበጥ: ፓትሪያርኩን እውነት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናቸውን እያሰኘሽ የበለጠ በመላዋ ኢትዮጵያ እንዲሰደቡ አደረግሻቸው እንጂ አልጠቀምሻችውም:: አንቺ በጎጥሽ እና በገንዘብ ይዘሽ ንጹሃኑን የምታስለቅሽበት ደህንነት በምድር ሃላፊ መሆናቸውን ዘንግተሽዋል በታውቂው ነው እንጂ የክፉ ትንቢት መፈጸሚያ እየሆንሽ ነው:: ቅዱስ አባታችንም የተመረጡት ሁሉ እስከ መሳት ይደርሳሉ ተብሎ የለ:: እባክዎ ቅዱስነትዎ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ታርቀው ፈጣሪ እስከ ጠራዎት ድረስ በሰላም ይኑሩ ደግሞ እግዚአብሔር ዘረኝነትን እንደማይወድ ያቁ የለ ታዲያ ምነው ? ይህ ሁሉ ግፍ!!! በዚህ ጉዳይ ከኔ ጀምሮ በርካታ
የአድዋ ተወላጆች ከልብ እያዘንን ነው:: እነዚህ ልጅ እግር ቀሚስ ለባሾች እንደ አሸን የበዙት በእርሶ ዘመን ነው:: የሁሉም አላማ አንድ ነው:: ይብቃ አባታችን ይብቃ!!! ሰው እኮ የሃይማኖት ፍሬው ያስታውቃል:: እኔ አዘንኩ ቅዱስነትዎ በእውነት አዋሳ ነዋሪ ባልሆን ይቆጨኝ ነበር:: ያ ዱርዬ ያሬድ እንኳን አቡነ ገብር ኤልን እንደሚጠሉ ማህበረ ቅዱሳን የሚባሉትን ለመምታት ዱርየውንም ጳጳስ ያደርጋሉ ከመባል ሞት አይሻልም? ይብቃ ቅዱስነትዎ !!! እባክዎ ሲሆን ሲሆን ገዳማቱን ባጀት መድቦ መርዳት የተዘጉት አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ ማድረግ የፍረሱትን ማስጠገን እድሜአቸው አንጋፋ የሆኑትን ሊቃውንተ ቤ/ክ እንዲጦሩ ማድረግ ስንቱ የገጠር ክፍል በእስላም እና በ ፕሮቴስታንት በጉ እየተነጠቀ
ባለበት በዚህ ዘመን የሃይማኖት አባቶች ተስማምታችሁ ብዙ መስራት ስትችሉ ምነው የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ሃይማኖት ሰው እንደሌላት አደረጋችሁ:: ተሳዳቢው ፓስተር ቶሎሳ ያን ሁሉ ስድብ በተሳደበበት አንደበቱ የኛን ሃሳብ የሚደግፉ አባቶች አሉ እያለ ፕሮቴስታንቶቹም የዘመኑን የልብስ መነኮሳቶች ስብከት እኝህ አባ አይደሉም አሰባበካቸው እንደ ፓስተር እከሌ ነው:: እናንት ጌታን አንቀበልም አላችሁ እንጂ ቤተክህነቱም በኛሥር ነው ቤ/ክ የሚጠብቁአት ጳጳሳቱ ሳይሆኑ የኦርቶዶክስ ህዝብ ነው እያሉ በሚደነፉበት በአሁኑ ወቅት እውነትም ሳስተውለው ፓስተሮቻቸው አንዳች ባይተነፍሱላቸው እነሱስ ከየት ይሰሙታል?? ቅዱስነትዎ እርሶ የአለም አብያተ/ክ የሰላም ፕሬዝዳንት አይደሉ እንዼ?? ታድያ ምነው? በእርሶ አስተዳደር ለቤ/ክ የሚደክመው እየተገፋ ለስደት እየተዳረገ ደግሞ አጥፊው እየተሾመ እነሆ 20 አመት ሊሆነን ነው:: እባክዎ ሰው ሆኖ የማይሞት የለም ሁሉ በፍቅር ይሁን ደግሞ ይቅርታን መሳሪያ አይደረግ የብቀላ እርሾ ልብ ውስጥ አስቀምጦ ለሰው ታይታ አሳዛኝ ይሆናል
ወ/ሮ እጅጋየሁ መንፈሳዊ ልጅዎ እንደመሆናቸው መክረው ያሳርፋቸው ዐይናችንን የሰራ አምላክ ሁሉን ያያል:: ጆሮአችንን የፈጠርም ያዳምጣል::
ይሀው እያየነው ነው::
አምላክ ሲቆጣ አርጩሜ አይቆርጥም
ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም:: ይባል የለ
ይህው ታድያ ምን የሚጥም ነገር አለ?????
ቅዱስነትዎ ደግሞ የአለም ሃያላኖች ኒው ዎርልድ ኦርደር የሚባል ኢሉምናቴ የሚባሉ የአለምን ኢኮኖሚ የሚያሽከረክሩ ሴክሪት ሶሳይቲ እንዳሉ ሳያውቁ መቸም አይቀሩም:: ታዲያ ቅዱስነትዎ
የሮሙ ጳጳስ ይህንን ሁኔታ ሲያመቻቹ የቡድሂስቱ የእስላሙ የፕሮቴስታንቱ, ብቻ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች እየመሩ ሁላችንም የምናመልከው እግዚአብሔርን ነው በሚል ጸሎት አርገው ነበር:: ይሄ ጉዳይ አለምን የተቆጣጠሩዋት በይፋ ሴክሪት ሶሳይቲ ከመባል ወተው አለም በአንድ መሪ በአንድ ገንዘብ መተዳደር አለባት እያሉ ነው:: ለመሆኑ ያ መሪ ማን ነው 666 ሉሱፈር ( ሌጌዎን አይደለም ን)
እባክዎ ቅዱስነትዎ ያንን ሁሉ ዲግሪ ይዘው እርሶን የሃይማኖቴን መሪ ር እሰ ሊቀ ጳጳስ አሸቅቤ ማስተማሬ ሳይሆን በዘመኑ መገናኛ በ ኢንተርኔትም የምዕራቡ አለም ዜና ላይ የተራገበውን አይቼ አዝኜ ነው:: ታድያ እነዚህ አደገኞች ትልቅ ባጀት እያረጉ በየዘመኑ በክርስትና ስም የሚልኳቸው አጥፊዎች:: የተሽነሽነ ክርስትናን ለብራቸው ሲሉ ተከፋፍለው ከላይ ትልቅ ገንዘብ መድቦ ለሚያንቀሳቅሳቸው አታላይ ለጥቅምም ሆነ በየዋህነት ያገለግላሉ:: ይህ ለማንም ግልጽ ነው:: ዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሐዋርያት መጀመሪያ እንደሰበኩት የነበረውን ተዋህዶ እምነት አውቀው አንድ ቢሆኑ ሉሱፈር ስለሚረታ:: እውነተኛዋን የክርስቶስ ቤ/ክ ከፍለው ካቶሊክ ያሉ + ለእስልምና መስፋፋት እንዲሁም ከካቶሊክ ደግሞ የተቸረቸሩት በክርስቶስ ስም በ መቶ ሺዎች የሚቆጠር (ከይቅርታ ጋር ሱቆች) ብለው የተሳሳትኩ አይመስለኝም::ይህ ሁሉ በ ቤ/ክ መከፋፈል ሰላም ማጣት የ ሃሳዊ መሲህ ምልክቱ ነው እና:: ልግስና ከቤት ይጀምራል ይባል የለ ሰላም ቅድሚያ ለ ኢትዮጵያ ተዋህዾ: ይደረግ:: እኛ የተዋህዶ ልጆች የሃይማኖት አባቶቻችን የሚያስተምሩንን በተግባር የሚኖሩ እንዳሉ ብናውቅም ቤ/ክ የምትታመሰው ተመሳስለው በገቡ ተኩላዎች እንደሆነ ይፋ እያየን ነው:: ስለዚህ ለማጠቃለል ያህል ወይዘሮዋ በጎጥ ደጀን ያደረገችው ታጣቂ ምድራዊ ነው እና ለኛ ለምስኪኖች የምንመካበት አምላክ ከአርያም ሆኖ የህዝቡን እንባ ያብሳል ውይዘሮዋ ያሳተሙትን ቅዥት ህዝቡ ገዝቶ ቅዱስነውዎ ባርከው በቀጣጠሉት ደመራ ላይ የድርሻዬ ይሀው እያለ ወደ እሳቱ ማበርከት አያቅተውም:: ልብ በሉ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች ህዝቡ አንብቦ ከስንት አመት በፊት ድንጋይ አስጨጦ የነበረ ዘንዶ አሁን ደግሞ በሃውልቱ ስር ቁማርተኞች ከች አለ ይብቃን !!! ቅዱስነትውዎ :: በአለም አብያተ ክርስትያን ላይ ከሃገረ እግዚአብሔር መርጦ እርሶን የሰላም ፕሬዝዳንት ያደረግዎ ፈጣሪ አምላክ ቅድሚያ በ 40 ቀን ለተጠመቁባት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሰላም እርቅ ፍቅር እንዲያደርጉ ፈጣሪ ይርዳዎ!!! አሜን!!
ተክለወልድ

Anonymous said...

wey ejigayehu!!! ere ebakachihu tewun bealun selam enasalif? silemin yetelatin eji mensha eyetebekachihu miemenun selam tinesutalachihu?ABETU GETA HOY ESKEMECHAY TITEWENALEH? EBAKHEN ATSIRARE BETECHIRSTIANEN ANTE YAZLIN...

Anonymous said...

Wow Teklewold I don't know what to say. I feel really relief knowing that there are people who really care about our church. Because this time I always say there is no one, there is no one, there is no one. Oh God please help us.
W/ro Ejigayehu you only need one goremesa's slap on your face. Ere rega bey ebakish. When people get old they become more calm. What happen to you. Mihiretun yaweridelish.

asbat dngl said...

ለትልቁ አባታችን፡ለወይዘሮዋ እንዲሁም ለአጃቢወቹዋ መድሃኒዓለም ልብ ይስጥልን።እኛም ቆም እንበልና ለጻለት እንበርታ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)