September 1, 2011

እነ መ/ር ዘመድኩን በቀለ ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 1/2011)፦ በበጋሻው ደሳለኝ ‹የስም ማጥፋት ወንጀል› ክስ የቀረበባቸው ዲያቆን ደስታ ጌታሁን፣ መ/ር ዘመድኩን በቀለ እና መ/ር ሣህሉ አድማሱ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ዛሬ፣ ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓ.ም ጠዋት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የቀረቡት ሦስቱም ተከሳሾች በበጋሻው ደሳለኝ የቀረበባቸውን ክስ እንደማይቃወሙት፣ ነገር ግን የስም ማጥፋት ድርጊት ፈጽመናል ብለው እንደማያማኑ ለችሎቱ ተናግረዋል፡፡ ከእነርሱም መካከል አንደኛ ተከሳሽ ዲያቆን ደስታ ጌታሁን ከከሳሽ ጋራ ያላቸው ልዩነት ሃይማኖታዊ በመሆኑ ክሱ በፍትሕ መንፈሳዊ መሠረት ይታይ ዘንድ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መንፈሳዊ ፍ/ቤት እንዲመራላቸው መጠየቃቸው ተገልጧል፡፡


ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ጉዳይ በጽሑፍ እንዳልደረሳቸው ለችሎቱ በማስረዳታቸው ዐቃቤ ሕግ የክሳቸውን ጽሕፈት ለሁሉም ተከሳሾች እንዲሰጥ ታዝዟል፡፡ በመጨረሻም ዳኛው ዐቃቤ ሕግ ክሱን ያስረዱልኛል የሚላቸውን ማስረጃዎች እንዲያቀርብ፣ ሦስቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው የብር 5000 ዋስ ጠርተው እንዲወጡና የሕግ ባለሙያ አማክረው ከጠበቃ ጋራ እንዲቀርቡ ለጳጉሜን ሦስት ቀን 2003 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የገዳማት መምሪያ ጸሐፊ የሆኑት ዲያቆን ደስታ ጌታሁን ‹‹የሰባኪው ሕጸጽ››፣ መ/ር ሣህሉ አሰግድ ‹‹በጋሻው ኦርቶዶክሳዊ ነውን?›› በሚሉ ርእሶች ባሳተሟቸው መጻሕፍት የበጋሻው ደሳለኝን ማንነትና በስሕተት የተሞሉ ስብከቶች ነቅሰዋል፤ አደባባይ ከመውጣት ተወግዶ ተቀምጦ እንዲማርና ለፈጸመው ስሕተቱ ንስሐ እንዲገባ መክረዋል፤ ‹‹ራሱ ሕጋዊ ሳይሆን ስሜን የሚያጠፉትን በሕግ እጠይቃለሁ፤ ሓላፊነቱን የሚወስድ ሰው አጣሁ›› በማለት ለሚናገረውም ‹‹ፈረሱም ያው! ሜዳውም ያው›› ብለውታል - በመጽሐፎቻቸው፡፡ መ/ር ዘመድኩን በቀለም በቅርቡ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን አስመልክቶ በተለያዩ መጽሔቶች ላይ በሰጣቸው ቃለ ምልልሶቹ ነው የተከሰሰው፡፡ የበጋሻው ክስ ጠቅላላ ይዘትም ‹‹ሕገ ወጥ ሰባኪ በመባሉ ከኅብረተሰቡ እና ከቤተሰቡ የመለየትና የመገለል በደል እንደተፈጸመበት›› የሚያመለክት ነው ተብሏል፡፡

ፍ/ቤቶች እስከ መጪው ዓመት ጥቅምት ወር ድረስ በሥራ ላይ የማይሆኑበት ሁኔታ በመኖሩ ተከሳሾቹን በእስር ለማሰንበት ቋምጠው በችሎቱ ቅጽር የተገኙ የሚመስሉት ከሳሽ እና ግብረ አበሮቹ (አሰግድ ሣህሉ፣ ትዝታው ሳሙኤል እና የጥቅም አጋራቸው ነው የሚባለው ኤፍሬም ኤርሚያስ) ተከሳሾች የዋስ መብታቸው ተጠብቆላቸው በመውጣቸው ከፍተኛ መከፋት አድሮባቸው ታይተዋል፡፡ በአንጻሩ እንደ ዐቃቤ ሕግ አነጋገር ተከሳሾች የተጠየቁትን ‹‹ጠበቅ ያለ ዋስትና›› ለማቅረብ በችሎቱ እና ከችሎቱ ውጭ በፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ እንቅስቃሴው ዙሪያ ግንባር የፈጠሩ አካላት እና አባላት ከፍተኛ መረባረብ እና መደጋገፍ አሳይተዋል፡፡

12 comments:

Ben said...

Truth will always come out. Zemedkun falsely accused Begashaw and his friends of being Tehadiso. He should have been sent to jail for a very long time and should apologize on public for misleading the media.

Anonymous said...

as we all know we have big problem from top leader of church those who support tehadiso hakenkagn people we should stand with those who told us the truth help them in any ways to get out this. as we all know we don't have rule of law in the country they will take that advantage by giving corruption money. pls everyone do everything u can to help our brothers from those tehadiso evils?

123... said...

እነ ዘመድኩንን ፍርድቤት ማንገላታት መዘዙ ብዙ እንደሆነ መንግስት ቢረዳው ደስ ይላል::
መንግስት ቤ/ክርስቲያንን መርዳት ሲገባው ለ ባንዳ ከሳሾች አሳልፎ መስጠቱ ያሳዝናል:: የበፊት መንግስታት ደርግ እንኩዋን ቤ/ክርስቲያንን ከ ባንዳ ተሃድሶ እና መናፍቅ ለመታደግ ሞክሩዋል:: አሁን ግን የተዋህዶ ልጆች ፍርድ ቀረቡ:: በ ኢትዮዽያ ታሪክ የ ቤ/ክርስቲያንን ችርግ ችላ ያለ ከ ደርግም በባሰ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ የ አቦይ ስብሃት መንግስት ብቻ ነው::ታሪክ በ ዝርዝር ይፅፈዋል::ቤ/ክርስቲያን ደግሞ በ ታሪክ አጻጻፍ አትታማም እናም የ አቦይ ስብሃትም ሆነ የመንግስታቸውን አቀላለድ በደንብ አርጋ ትዘግበዋለች::ከ እዛ በፊት ግን እግዝያብሔር ሁሉን ይቀድማል::

lele said...

yahege yabalayenate kala kasaheo yetaserale.kalela gene yekoye enje yaewenate amelake kaenaneta gara nawe..batsalote enebareta

d/n haile michael zedebre tsige said...

"ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል" አሉ::
አንድ ሰው ስለ ሃይማኖቱ መመስከር አይችልም ነው ነገሩ?ለዘውም ስለ ተሰደበው ሃይማኖቱ መናገር አይችልም ነው?
አሁን የፍርድ ቤት ውሳኔ ስላልሰማን ምንም ማለት አንችልም::
ግን ለፍርድ ቤት አንድ መልእክት ማስተላለፍ እንወዳለን::
ገና ብዙ ዘመድኩኖች አለን ::በጋሻውንም በቤተክርስቲያናችን አደባባይ የመናፍቃንን ጩሀት በንቀትና በድፍረት ለምን እንደ ጮሀ በአግባቡ ለመጠየቅ ዝግጅት ላይ ነን::
የንፍሮ ቀቀይ ልጅ ተብለን የተሰደብን ኦርቶዶክሳውን ትዕግሥታችን ፍርሃት ከመሰላችሁ:-
እየጠበቅን ያለው ምዕምኑ ሁሉ መረጃ እስክ ደርሰው ስለ ቤተክርስቲያን ችግር አንድ ዓይነት ግንዘቤ እስክኖረውና አንድ እስክሆን ነው::
መረጀውም እንዲዳረስ ጠንክረን እንሠራለን ::

መንግሥት የደኅንነት ኃይሉን በእጅጋየሁ አማካይነት በቤተክርስቲያናችን ላይ ያለ አግባብ የሚጠቀመውን አካሄድ ካላቆመ ስለ ሃይማኖታችን ለመሞት እንደ ተዘጋጀን ልንገልጽላችሁ እንወዳለን::
ቤተክርስቲያናችንና አባቶቻችን በማንም የመንግሥትን ኃይል ተገን በደረገ ፈት አትመራም::
ይህ ለኛ ለልጆቻችንም ትልቅ ኃፍረት ነው::የአባቶቻችን የአጽማቸው ወቀሳ ይህን ዝም እንዲንል ዕረፍት አይሰጠንም::
አቡነ ፓውሎስንም ፕትርክናቸውን የሚንቅበለው የቤተክርስቲያኒቱን ሕግና ሥርዓት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ እስከ ሆነ ብቻ ነው::
ለተሐዲሶዎችና ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ለተሰለፉ ኃይሎች [ወፎች] ማረፊያ ዛፍ መሆናቸውን ካላቆሙ ከዚህ በፊት የቤተክርስቲያኒቱን ሀብት ሲያባክኑ ሊቃውንቱን ሲያስፈራሩ በቤተክርስቲያን ዘረኝነትና ሙስና ሲያንሰራፉ ዝም እንዳልን ዝም ማለት አንችልም::ወፎቹ እንዲበተኑ የዘፉ መቆረጥ ግድ ይሆናል::

Anonymous said...

Begasha had written a book insulting the patriarch and other bishops some years ago. He has been also insulting the priests and other church fathers through all his preachings. No one accused him of by then. Why he wanted to accuse these true brothers now? Now, he should also be put in trial for all his insults, causing conflicts in Awassa, St. Yosef churche (AA) and many other places. If he is not going to stop this, please brothers, let us collect all the relevant evidences and let's bring him trial. He is always aiming to disturb the church. When he could not continuing doing the mess inside, he wanted now from outside. If he were a real christian, he would have gone to them ask excuse or confess. All what he does is not christianity. Egziabher libona yistew

Anonymous said...

Please donot mix politics and religion. We are striving for the development of our church and dissemination of the holy Gospel. This government has also done a lot of supports to our church including returning its lands and houses which were taken by the previous regime. We have also a better fredom of belief, at least better than the previous regime again. Ejigayehu (Yodit gudit) and her fellow wanted to utilise their support from the government officials as a tool to silence those true fathers and brothers so that they can loot the church and become rich. She assumed herself as a spy and big government official. This is a religion which is completely different from politics. In my opinion, the government is not barely supporting these people. If so they know that it will be a mess up. Donot blame the government with out enough evidence. I strongly beilieve that the government knows the importance of the church for the country. Egigayehu can not represent the government. Rather, we have to continue our efforts to make the government know the reality as much as possible. God bless Ethiopia

Anonymous said...

This message is to Ben, the first comment..
What do you mean by falsely accused? Did zemedkun forced Begashaw to say what he said? Everything is on a record brother. No one is accusing nobody. Whatever they said is kept as proof, so don't waste your time. For those real Tewahidos, don't worry the message is spreading in Ethiopia like a wild fire, and people couldn't even believe what they heard when Begashaw insulting the church. Let GOD help you all. Atlanta.

Ye dingil baria said...

Am sorry for Mr."Anonymous", u seem a confused cadre of the regime and an orthodox follower, how ever your efforts to cover up things and defend the govr't seems to be ridiculous. To tell u frankly from z very begging it's the so called government)who does n't represent z real Ethiopia)brought such a mess in our church and never wants to see our church and her followers organized and stabilized so as to make sure it's divide and rule method of rule when we get rid of this shameful dictatorial non Ethiopian regime from our land our church problems will be solved completely. These ridiculous groups of gangs whose motto is to suck the blood of it's followers of our church in the name of preaching is now very very clear in addition to their agenda of planting suspicion and confusion with in us sent by the destructive protestant missionaries, now yoor game is over by the help of z Almighty God and our Lady St. Virgin Mary....

Temelkach said...

I don't think Begashaw believes he can win this case under normal circumstances. Deep inside him he is thinking that paulos will help him win the case somehow. But he better understand that this may not always be the case. The truth will always come out at last!!

What can these people be accused of? What they did was just defending their belief. It is all a matter of belief. He is the one who tracepassed and rediculed our belief. They told him he is wrong based on reasons. The right thing for him to do is to prove that they are wrong and he is right logicaly with enough reasons and references. Going to court is not the answer. Proving himsel as true Orthodox Tewahido belier is the answer people are looking for!! Begashaw: You can't confuse as again and again. Enough is enough!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

atfru ke-egna gar Egziabher ale ewnetinim hule tenageru.Yetesasatut kesashm sihtetachewn bekis sayhon benisiha biyatbut.besew fit netsa lemebel kehone keEGZIABHER zend netsanet aysetimina.(Ene Zemedkun Egziabher Yiredanal tseliyu)

Anonymous said...

I'm so thankfull for these kind of brothers, like Dn. Zemedkun. If GOD hasn't given us some real ones like them, the church would have been in the hands of Ethiopia hater protestants. So i would keep praying to GOD to give them strength until we, DIASPORA, have the chance to go and join them. Until then, I personaly do anything, including financial help to support this coause. May our Lord and his mother be with us.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)