September 10, 2011

ደጀ ሰላም፦ ከመስከረም 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም 2004 ዓ.ም


እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ።
(ደጀ ሰላም፤ ጳጉሜን 5/2004 ዓመተ ምሕረት፤ ሰፕቴምበር 10/2011 ዓመተ እግዚእ)፦ እንኳን አደረሳችሁ። መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ። ያድርግልን። እነሆ ባለፈው ዓመትም መልካም የጡመራ ዓመት አሳለፍን። በዚህም 304 (Articles) ዜናዎች፣ ሐተታዎች፣ ርዕሰ አንቀጾች፣ ምልከታዎች ወይም ማስተዋወቂያዎች  ወጥተዋል። ዝርዝራቸው እና የወጡበት ወር (በፈረንጅኛው) ከታች ተዘርዝሮ ቀርቧል።


እዚህ ላይ መጠቀስ ያለባቸው ሁለት ቁጥሮች ስንት ደጀ ሰላማውያን የጡመራ መድረካችንን እንደጎበኟት እና ስንት ጊዜ እንደጎበኟት የሚያሳዩት ቁጥሮች ናቸው። (አንዳንድ ድረ ገጾች እና ጦማሪዎች ብሎጋቸው የተከፈተበትን ቁጥር ብዛት (Pageviews) ከሰው ቁጥር (Visits) ጋር እያምታቱ “ይኼንን ያህል ሚሊዮን ሕዝብ ጎበኘን” የሚል ሐሰት ሲጽፉ ብዙ ጊዜ እናነባለን። “A pageview is each time a visitor views a page on your website, regardless of how many hits are generated. hits are not a reliable way to measure website traffic.” ይሏል።)

በዚህ ዓመት የነበረው የደጀ ሰላም ቁጥር የሚከተለውን ይመስላል። የጎብኚዎች ቁጥር 971,005 ሲሆን፣ የጡመራ መድረካችን የታየችበት ብዛት (Pageviews) ደግሞ 2,500,984 ነው። ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ደጀ-ሰላማውያን (በቀጥታ በኢንተርኔት ያነበቡ ሰዎች ቁጥር (Ethiopia Visits) 249,618 ነው። (ኢትዮጵያ አንባብያን በቀጥታ የማንበባቸው ሒደት ላይ ማዕቀብ በመጣሉ እንጂ ቁጥራቸው ከዚህ በላይ ነው።) ከዚያ ውጪ ያለው ደግሞ ከመላው ዓለም የመጣ አንባቢ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በኢትዮጵያ ያለው የጡመራ መድረካችን ተነባቢነት በር በመዘጋቱ የአገር ውስጥ አንባብያን ቀጥታ ንባብ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድሯል። ነገር ግን አንባብያን በሌላም መንገድ ቢሆን “ደጀ ሰላም”ን በመረጃ ምንጭነቷ የመጠቀማቸውን ጉጉት ጨመሩት እንጂ ተነባቢነቱን አላቆሙትም። አሁንም ግን እኛን ግር የሚለን “ደጀ ሰላምን ለመዝጋት ለምን አስፈለገ?” የሚለው ጥያቄ ነው። በትክክል መንግሥት ነው የዘጋው ለማለት ማስረጃ ባናገኝም፤ በአገሪቱ ያለው አንድለናቱ የኢንተርኔት አቅራቢ የመንግሥት ከመሆኑ አንጻር በቦታው አሉ ሰዎች መስኮቱን ለመዝጋት እየሞከሩ መሆናቸውን እርግጠኞች ነን። ግን ለምን? ግብር ከፍለን በተቋቋመ መሥሪያ ቤት የግል ጥቅም ሲራመድ ግን አይተናል፤ ሥራችንን ግን አልገታውም። የበለጠ ተነባቢ እንድንሆን አደረገን እንጂ።    
   
ምንም እንኳን ደጀ ሰላምን ለማቆም ሙከራው የቀጠለ ቢሆንም የደጀ ሰላምን ፈለገ ተከተሉ የጡመራ መድረኮች በብዛት እየመጡ መሆናቸው ያጽናናናል። አወም ጡመራ በአማርኛ። ደጀ ሰላም በዚህ በኩል ቅድሚያውን በመያዟ ደስተኛ ናት። “ብሎግ” የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል “ጡመራ”፣ የጡመራ መድረክ፣ ብሎገሮችን ደግሞ “ጦማሪያን” የሚለው ስያሜ የሰጠችው “ደጀ ሰላም” ናት። ቃሉ አሁን ተቀባይነት አግኝቶ ከሚያግባባ ደረጃ በመድረሱም ደስ ይለናል።

ጡመራ ብቻ ሳይሆን “ደጀ” የሚለው ቃልም የብዙ ጦማሪዎች ተመራጭ የጡመራ ስም ሆኗል። አንድ ሰሞን ብቅ ብሎ የጠፋው “ደጀ-ብርሃን”፣ የእስልምናው “ደጀ-ኢስላም”፣ የተሐድሶው “ደጀ-ሰማይ” ተጠቃሾች ናቸው። በፌስቡክ ላይም “ደጀ ሰላም” ተመራጭ ነው። የሚያሳዝነው ግን “ደጀ ሰላም” ብሎ ሰዎችን ለማጭበርበር የሚሞክር ተሐድሶ ቡድንም መኖሩ ነው። ቢሆንም ሥራው ስለገለጠው ብዙም አላስደነቀንም። ደጀ ሰላማዊውም እነዚህን አስመሳዮች ማወቁ ላይ ጠንቀቅ እንዲል ከወዲሁ በድጋሚ እናሳስበዋለን።

ከመጀመሪያው ስንነሣ “በአማርኛ ለመጦመር” ቆርጠን ነው። ይህም ብዙ የአማርኛ ጦማሪዎችን አስገኝቶልናል፤ ወይም ፈር ቀዶልናል። በኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ዙሪያ ብቻ ከአስር በላይ የጡመራ መድረኮች አሉ። ብዙዎቹም ከዜና አጻጻፋቸው፣ ከሐተታ አቀራረባቸው እና ከርዕስ አወጣጣቸው ጀምሮ “ደጀ ሰላምን አርአያ” አድርገው ይጠቀሙበታል። በሒደት መቃናት የሚገባቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሯቸም ለጊዜው ግን መጀመራቸው ደስ ያሰኛል። ይህንንም እንደ 2003 ዓ.ም የሥራችን ፍሬ እንመለከተዋለን። ከልምድ፣ በጡመራው ከመቆየትም እያሻሻሉ ኢሄዳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ያየሁት አይቅርብኝ ብለው የጀመሩም ካሉ ብዙም ሳይገፉ ይተዉታል። ልክ እንደከዚህ በፊቶቹ።

ወደ ደጀ ሰላም ስንመለስ፤ ካለው የሥራው ስፋት፣ የፈተናው ብዛት አንጻር አገልግሎታችን በጣም ትንሽ ያውም ብዙ እንቅፋት የበዛበት ነው። ይቺም በዛች ብለው አፋችንን ለማፈን፣ መታየታችንን ለማጨለም ትልቅ ዘመቻ ተከፍቶብናል። ካለብን የጊዜ እና የአቅም ውሱንነት እንደተጠበቀ ሆኖ በቴሌ ያለው እጅ ደጀ ሰላምን ከኮምፒውተር ዕይታ ለማጥፋት የአቅሙን ሁሉ እየሞከረ ነው። ያላወቀው ነገር ግን ቻይናንን በመሳሰሉ አፋኝ አገሮች ሳይቀር “ጦማሪዎች” የአቅማቸውን እያደረጉ መሆኑን፣ ድምጻቸውን ማሰማት መቀጠላቸውን ነው። ስለዚህም መታየታችን ይቀጥላል፤ ከምእመኑ እና ከአባቶቻችን ጋር መገናኘታችን ይቀጥላል። ጡመራችን ይቀጥላል። በእግዚአብሔር ቸርነት።

ጥሪያችንን በማስተላለፍ እናብቃ። ያነበባችሁ ላላነበቡ ወይም የማንበብ ዕድሉን ላላገኙ አስተላልፉ። “ፕሪንት” አድርጋችሁም ይሁን በፎቶ ኮፒ አሰራጩ። ኢሜይሎችን ተጠቀሙ። የደጀሰላም ድምጽ ይስፋፋ። በቻላችሁት ሁሉ እርዱን። በጸሎታችሁ አትርሱን። ባጠፋን፣ ማሩን፣ የተጣመመውን በማቃናት አግዙን። ቤተ ክርስቲአናችንን ከገባችበት ችግር ለማላቀቅ ምእመናችንን ከመረጃ እጦት ጨለማ በማውጣት አግዙን።

የደጀ ሰላም የአንድ ዓመት ስታቲስትክስ በየወራቱ፦
  2010
          December (15)
          November (32)
          October (64)
          September (32)

    2011
          September (4)
          August (21)
          July (19)
          June (28)
          May (25)
          April (22)
          March (20)
          February (4)
          January (18)
·         Articles= 304
·          971,005   Visits
·         2,500,984   Pageviews
·         Ethiopia Visits 249,618

Compare: March 26/2010 to Septermber 2010
·             195,876     Visits
·             535,426     Pageviews
·             Ethiopia visits: Visits 35,155

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።

6 comments:

lele said...

ENKONE ADARASACHOHE DEJE SELAMOCH.ENA YAMETAWATOTEN LAMADARASE EMOKRALAHO.ENANETAME BARETOLEGE.
AMELAKE HOLEM BACHARENATO YEGOBEGACHOHE.

Gebre Z Cape said...

Well Done DejeSelam, the main source of information for myself and others regarding church progress and all other issues.

I wish you happy new year. Hope you guys work not for a group or somebody else rather for GOD.

Melkam melkamu yaseman. Eroro, chikichiki minamin betam meronan.

Anonymous said...

Happy New Year. We are glad to hear you.

Anonymous said...

EGZIABHER YABERTACHU.
Melkam Amet!!!

Anonymous said...

+++
Thank you so much, DJ.

Believe it or not DJ has been the first thing every morning to do for me for some time now and will continue to be. That has mainly been because in many ways I’ve found DJ to be credible. To be honest it is also the kind of blog where I could have found perspectives matching mine or those not difficult to accept except that crazy one from DDK. (BTW- I’m not an MK member though there is nothing wrong with being one.)

Yes, it is in Addis do I do all that no matter how/what INSA does with DJ. Here is the secret. I use a great proxy called Ultrasurf. Ultrasurf has been made so robust that no one could have stopped it including the Chinese. I can be a witness. Forgive my belated sharing of such an important info.

There is just a small client to download and install. Follow the link below for Ultrasurf:

http://www.ultrareach.com/

Spread the word and let us have many more people in Ethiopia accessing DJ, among other sites of course.

Cher yigtemen

Anonymous said...

Melkam Addis amet. Yebrlete lemesrat Egziabiher gulbetun ewqetunina tibebun yistachihu. amen.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)