September 30, 2011

ቤተ ክርስቲያን በ20ኛውና 21ኛው መቶ ክ/ዘመን

ቤተ ክርስቲያን
 በሃያኛውና ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን

(በመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን)

4 comments:

Anonymous said...

ተሐድሶ›› በግልጽ መነጋገርና የጭፍን ተቃውሞን ወይም የጭፍን ድጋፍን ችግር ማስቀረትና የጋራ መግባባትንና ግንዛቤን ማግኘት ለችግሩም መፍትሔ መፈለግ ይቻላል፡፡ ይህም ለቤተ ክርስቲያናችን ከምንም በላያ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡
አንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ወይም በአንድ ዓይነት ስያሜ የምትጠራ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት መስመር ልትወጣ የምትችልባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ ብዙ ሳንርቅ በሐዋርያት የመጨረሻው ዘመን ላይ የነበሩትን በራእይ ዮሐንስ ምዕራፍ 2 እና ምዕራፍ 3 የተጠቀሱትን አብያተ ክርስቲያናት መጥቀስ እንችላለን፡፡በነዚህ ምዕራፎች የተጠቀሱት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ክርስቶስ ገንዘቡ ያደረጋቸው ናቸው፡፡ ከነዚህ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት አምስቱ ድካም ተገኝቶባቸው ንስሓ እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው÷ ሁለቱ ብቻ ናቸው ማበረታቻ የተሰጣቸው፡፡ በሐዋርያት ዘመን የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ሁኔታ እንዲህ ከሆነ ይልቁንስ በብዙ ዘመን ርቀት የሚኙት የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት እንዴት የሕይወት ለውጥ ወይም ተሐድሶ አያስፈልጋቸውም)
እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት መንገድ የሳተችበትን ወይም የደከመችበትን ሁኔታ በንስሐ አስተካክላ የሕይወት ጉዞዋን በብርታት የምትቀጥልበት የእርማት ድርጊት ማለት ነው፡፡ በአጭሩም የቤተ ክርስቲያን የሕይወት መስተካከል ማለት ነው፡፡ አንዳንዶች የተሐድሶን ሓሳብ አፍራሽ አድርገው እንደሚያቀርቡት ያልነበረ አዲስ ሃይማኖት መመሥረት አይደለም፡፡በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መደረግ ያለበት ተሐድሶ በሕዝቡ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ የሚያተኩር መጽሐፍ ቅዱስንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥንታዊ ዶግማ ወይም ትምህርተ ሃይማኖት መሠረት አድርጎ የሚከናወን ነው፡፡
የዚች ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ የሌሎችን ባህል÷አስተምህሮ÷የአምልኮ ሥርዐት መቅዳት ሊሆን አይገባም÷ ወይም አንዳንዶች እንደሚናገሩት ቤተ ክርስቲያኒቱን 'ፕሮቴስታንት' ማድረግ ሊሆን አይችልም፡፡የፕሮቴስታንቱ ክፍል ራሱ በችግር ውስጥ የተዘፈቀና የእግዚአብሔርን እጅ የሚፈልግ ነው፡፡

memeru said...

my brother anonymus , you said very good idea , that is why we are saying the church should be reform , but most of the people do not understand we what we are saying . No body say the dogma but those which are obstacle fron the Gospel .God bless you

Anonymous said...

Memru, I like your understanding about 'reformation' God bless you too. I wish for others, this Idia
cristal clear too, God Help them to better knology.

ኅይለ ገብርኤል said...

ወገኖች !
ማስተዋል የሚገባን ነገር አለ:: ድካም እርጅና የሰው ልጅና የሰው ልጅ ለፈጠራቸው ነገሮች የሚሰጡ ገላጭ ባህርያት ናቸው : ሃይማኖት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ/ የጠፋውን አዳም ፍለጋ ያደረገው ጉዞ ነው - ፍኖተ እግዚአብሔር ነው:: ይህንን መንገድ አውቆ መሄድ ያስፈልጋል እንጂ አዲስ መንገድ መቀየስ ሰው ሰራሽ ሃሳብ መጨመር ወደ ጥፋት መንገድ መሄድ ነው:: በዚህ ምክንያት የምዕራቡ አለም ክርስትና የደረሰበትን ክስረት / " የወረደበትን ደረጃ " ማየት ይቻላል ::
በራስ ሕይወት ውስጥ ያለ ዝለትን ብልየት / እርጅናን በንስሐ በቃለ እግዚአብሔር "ማደስ" ያስፈልጋል:: በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት መሰረት "አዲስ ሰው" መሆን ያስፈልጋል :: የኢትዮጵያ ቤ/ክን ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዓት ተጠብቆ መቆየት መስፋፋት ይገባዋል :: ዘመኑን ያልዋጀ አሠራር አስተዳደር ደግሞ እየተስተካከለ እየተቃና እየተሳለጠ እንዲሄድ ማድረግ ያስፈልጋል : ስለዚህ ቅድስት ቤ/ክናችን የሚያስፈልጋትን ነገር ለይቶ ማወቅ ግድ ነው::ዘመናዊ አስተዳደር ዘመናዊ አሰራር እንጂ "ዘመናዊ ሃይማኖት " አይደለም :: የቅዱሳን አባቶቻችንን ርስት እንደ ናቡቴ መስጠት የለብንም:: እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ የተዋህዶ ሃይማኖታችንን መጎናጸፊያ የቀደሙ አበው በረከት ጠብቀን ልንይዝ ይገባናል : እግዚአብሔር ይርዳን::

ኅ/ገ ከሲያትል:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)