September 30, 2011

ቤተ ክርስቲያን በ20ኛውና 21ኛው መቶ ክ/ዘመን

ቤተ ክርስቲያን
 በሃያኛውና ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን

(በመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን)

September 28, 2011

ሊያዳምጡት የሚገባ ትምህርታዊ ቃለ ምልልስ

የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ አደጋ በቅኔም ሲጋለጥ

መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ

 • “በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን ስብከተ ወንጌል እንደበረታው ሁሉ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክናም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ ትምህርት ተስፋፍቶ መሰጠት ይኖርበታል፤” /መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በዘመን መለወጫ - ቅዱስ ዮሐንስ የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ላይ ቅኔያቸውን ሲያብራሩ ከተናገሩት/
 • “በቅኔው ካነሣችሁት አይቀር ስላሉት ችግሮች መናገር እፈልጋለሁ፤ የትኛው እግዚአብሔር ነው ያረጀው? የትኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት ያረጀችው? የሊቃውንቱ ዝምታ ምንድን ነው? አባቶችስ የማይገባ ትምህርት ሲሰጥ ዐውደ ምሕረታችሁን የማትጠብቁት ለምንድን ነው? ዝምድና፣ ጓደኝነት ወይስ ውለታ ይዟችኋል?. . . በ2004 ዓ.ም መሠራት የሚገባው ሥራ ይህችን ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ፣ በሚገባ ማስተዳደር ነው፤” (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቅኔውን መሠረት አድርገው ከተናገሩት)
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 17/2004 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 28/2011)፦መስከረም አንድ ቀን 2004 ዓ.ም በተከበረው የዘመን መለወጫ - ርእሰ ዐውደ ዓመት-እንቁጣጣሽ-ቅዱስ ዮሐንስ በዓል በመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያክ አቡነ ጳውሎስን እንኳን አደረ ለማለት የሚዘጋጅ ዓመታዊ መርሐ ግብር አለ። በዚሁ በዓል ላይ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆኑት መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ቀርበው ከሰጧቸው ቅኔዎች መካከል ከፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ የተነሣ ቤተ ክርስቲያናችን አደጋ እንደተጋረጠባት በመጠቆም የሐዋርያ እና ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስን ረድኤት የሚማፀነው አንዱ ቅኔ ዘመኑን የዋጀ ሆኗል።

Demera, The Finding of the True Cross

September 25, 2011

አባ ሰረቀ በመስቀል-ደመራ በዓል አከባበር ላይ በአደባባዩ እንዳይገኙ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው


 • ማስጠንቀቂያው ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነንና እነበጋሻው ደሳለኝንም ይመለከታል::
 • “እኔ ችግር [የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ] ካለብኝ ከመምሪያ ሓላፊነቴ መነሣት ብቻ ሳይሆን ከቤተ ክርስቲያንም ልወገድ ይገባኛል፤”/አባ ሰረቀ ለመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ አስተዳደር ጉባኤ፣ ለበዓል አከባበር ዐቢይ ኮሚቴ፣ ለሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና ለጸጥታ ኀይል የጋራ ስብሰባ ከተናገሩት/::
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 25/2011)፦ በሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም በመላው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች፣ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ደሴ ከተማ የ12 አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ የተቃውሞ መግለጫ የወጣባቸው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል መስከረም 16 ቀን 2004 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በሚከናወነው የመስቀል-ደመራ በዓል አከባበር ላይ እንዳይገኙ ውሳኔ ተላለፈባቸው፤

September 23, 2011

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የሚል መጽሐፍ አሳተሙ


 • መጽሐፉ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ ነው በሚባል ሰው የተዘጋጀ እንደሆነ ተነግሯል፤
 • በመስቀል-ደመራ በዓል ዐውደ ትርኢት የሚያቀርቡ ወጣቶች የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊን ጨምሮ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና ሕገ ወጥ ሰባክያን በበዓሉ ላይ አንዳችም ተሳትፎ እንዳይኖራቸው አስጠንቅቀዋል፤
 (ደጀ ሰላም፤ መስከረም 12/2004 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 23/2011)፦ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አቡነ ጳውሎስን ሰርፕራይዝ አድርጌበታለሁ የሚሉትንና ከብር አራት መቶ ሺ በላይ ገንዘብ እንደወጣበት ተናገሩለት ሐውልተ ስምዕ በተመለከተ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የተሰኘ መጽሐፍ ማሳተማቸው ተሰማ፡፡ ወይዘሮዋ መጽሐፉን መስከረም 16 ቀን 2004 ዓ.ም ተከብሮ በሚውለው የመስቀል-ደመራ በዓል ላይ ለማሰራጨት እንደተዘጋጁ ተነግሯል፡፡

September 16, 2011

“አቡነ ጳውሎስን እና አቡነ መርቆሬዎስን የማስታረቁ ጥረት ቀጥሏል” (ነጋድራስ ጋዜጣ)


(ነጋድራስ፤ ቅጽ 08 ቁጥር 296 ዓርብ፣ መስከረም 05 2004 .)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሥርዐተ ጵጵስና በምትመራበት ፍትሐ ነገሥት፣ በአንድ መንበርና ዘመን ሁለት ፓትርያሪክ መሾም እንደማይቻል መደንገጉን የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ ይህ ድንጋጌ በ1984 ዓ.ም ላይ አክባሪም አስከባሪም አልነበረውም፡፡ ስለዚህም በወቅቱ የቤተ ክርስቲያኗ አራተኛ ፓትርያሪክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወት እያሉ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተመርጠው መንበረ ፓትርያሪኩን እንደተረከቡ ይታወሳል፡፡

September 14, 2011

STEVEN Golding, Son of Jamaican Prime Minister

(Jamaica Observer):- He is Gabre Selassie, having been renamed following baptism at the Saint Gabriel Ethiopian Orthodox Church in Gondar, Ethiopia on May 15. Gondar was the political center for Ethiopia for a number of centuries. "My new name is Gabre-Selassie," he told the Sunday Observer, adding that it means servant of the trinity. The baptism, Golding explained, occurred while on a month-long tour of the African continent which also took him to Kenya and Tanzania.

September 13, 2011

ምን ዓይነት ለውጥ ለቤተ ክርስቲያን? (ለግልጽ ውይይት የቀረበ)


 • በትዕግስት አንብቡት፤ ሚዲያዎችን ጨምሮ ለአባቶችም ለምእመናንም በማድረስ ተባበሩን። .
(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 3/211 READ IN PDF)፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጨርሶ መደበቅና ማስተባበል እንኳን ከማይቻልበት ደረጃ የደረሰው የቤተ ክርስቲያናችን ውስጣዊ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል። እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ ነገሩን በተቻለን ቅርበት ስንከታተል ቆይተናል። በየሚዲያው የሚወጡትን ጽሑፎች፣ ዜናዎች እና ቃለ ምልልሶችንም ሳያመልጡን ለመረዳት ሞክረናል። ሆኖም በሚዲያ የሚቀርቡት ብዙዎቹ አስተያየቶች ችግሩን በተረዱት መጠን ወይም መልክ በማንጸባረቅ ላይ የተወሰኑ ናቸው።

September 11, 2011

አዲስ ዓመት


ከዚህ በታች ያሉት ጽሑፎች ከ“አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ያገኘነው የመምህር ያሬድ ፈንታ እና ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ የጻፉትና ለእርሳቸው መታሰቢያ ከተዘጋጀው ድረ-ገጻቸው ላይ የተገኘውም ነው። ሙሉውን ጽሑፍ ከዚያው ታገኙታላችሁ። መልካም አዲስ ዓመት፣ መልካም በዓል። (ደጀ ሰላም/ READ IN PDF.)
++++++++++++++++++++++++

የዘመን መለወጫ በዓል
(አለቃ አያሌው ታምሩ):- የዘመን መለወጫ በዓልን በተመለከተ የተለያዩ የእምነት ክፍሎች የየራሳቸው መነሻ ምክንያት አላቸው። በአይሁድ የዘመን መለወጫ ተብሎ የሚከበረው መባቻ ተብሎ ከሚጠራው ቀን የተለየ ነበረ። እነሱ የዘመን መለወጫን የሚያከብሩት በሚያዝያ ነው። ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት አባቶቻቸው ወደ ግብጽ ተሰደው ሁለት መቶ ዐሥራ ዐምስት ዓመት በግብጽ ከኖሩ በኋላ እንደገና ከግብጽ ወጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ሲገቡ እግዚአብሔር እነሱን ከግብጽ አውጥቶ፥ ባሕር ከፍሎ፥ ደመና ጋርዶ ወደ ምድረ ርስት ለማድረስ ከግብጽ ያወጣበትን ቀን ልክ ነጻነታቸውን እንዳገኙበት ቀን አድርገው በየዓመቱ የዘመን መለወጫ ብለው እንዲያከብሩትና ወሩንም የወሮች መጀመሪያ እንዲያደርጉት ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለ ተሰጣቸው በዚህ መሠረት ሚያዝያን ያከብራሉ።

September 10, 2011

ደጀ ሰላም፦ ከመስከረም 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም 2004 ዓ.ም


እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ።
(ደጀ ሰላም፤ ጳጉሜን 5/2004 ዓመተ ምሕረት፤ ሰፕቴምበር 10/2011 ዓመተ እግዚእ)፦ እንኳን አደረሳችሁ። መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ። ያድርግልን። እነሆ ባለፈው ዓመትም መልካም የጡመራ ዓመት አሳለፍን። በዚህም 304 (Articles) ዜናዎች፣ ሐተታዎች፣ ርዕሰ አንቀጾች፣ ምልከታዎች ወይም ማስተዋወቂያዎች  ወጥተዋል። ዝርዝራቸው እና የወጡበት ወር (በፈረንጅኛው) ከታች ተዘርዝሮ ቀርቧል።

September 9, 2011

መ/ር ዘመድኩን በቀለ ለጥቅምት ሦስት ተቀጠረ

 • አርማጌዴን ቁጥር 2 ቪሲዲ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ ይውላል::
 • ሁለቱ ተከሳሾች ጉዳያቸውን በዕርቅ ለመጨረስ ከበጋሻው ጋራ እየተደራደሩ ነው
 • ‹‹እርሱ የመሠረተብኝ ክስ ወኅኒ ብቻ ሳይሆን ሲዖል የሚያወርደኝ ቢሆን እንኳ ሲዖል እገባለሁ እንጅ በሃይማኖቴ አልደራደርም፤ የምፈጽመውም ዕርቅ የለኝም፤ ሕጉ ነጻ ያወጣኛል፤››(መ/ር ዘመድኩን በቀለ)
(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 9/2011):- የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት በሕገ ወጡ እና ጥቅመኛው በጋሻው ደሳለኝ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት መ/ር ዘመድኩን በቀለ ከሕግ ባለሞያ ጋራ ተማክሮ በክሱ ላይ ያለውን የእምነት-ክሕደት ሐሳብ እንዲያቀርብ ለጥቅምት ሦስት ቀን 2004 ዓ.ም ትዝዛዝ ሰጠ፡፡

September 7, 2011

ፀበል እየተፀበሉ በነበሩ ወጣቶች ላይ “በተሰነዘረ ድንገተኛ ጥቃት” 2 ወጣቶች ሞቱ


 • የወጣቱ የቀብር ሥነ ሥርዐት “ለጸጥታ” በሚል በአስቸኳይ ተፈጽሟል።
(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 8/2011)፦ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ደሴ ከተማ በተለምዶ አሬራ እየተባለ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኘው የደብረ ሣህል ቅዱስ ዐማኑኤል እና ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኝ ፀበል ተፀብለው ወደ መኖሪያ ቤታቸው እየተመለሱ በነበሩ ወጣቶች ላይ፣ ዛሬ ጳጉሜን 3 ቀን 2003 ዓ.ም ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት በደረሰ ድንገተኛ ጥቃት ሁለት ወጣቶች ሞቱ፡፡

September 6, 2011

የደሴ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች በሀ/ስብከታቸው ስላለው የሕገ ወጥ አጥማቅያን፣ ሰባክያን እና ዘማርያን ሁኔታ የሰጡት መግለጫ

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 6/2011)፦ የደሴ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች በሀ/ስብከታቸው የሕገ ወጥ አጥማቅያን፣ ሰባክያን እና ዘማርያን መስፋፋት እንደሚያሳስባቸው በመግለጽ ከአዲስ አበባ እና ከሰሜን አሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር ተቆጥረዋል። የደሴው ሰ/ት/ቤቶች መግለጫ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል።
 • በሕገ ወጥ አጥማቅያን፣ ሰባክያንና ዘማርያን ዙሪያ ለሚደረገው የመከላከል እንቅስቃሴ ከምእመናን፣ ከየአድባራቱ፣ ሰንበት ት/ቤቶችና ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲቋቋምና ጥናት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

September 1, 2011

ማስታወቂያ፦ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ በአሜሪካ

፲፩ኛው የሰ/አሜሪካ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ ከነሐሴ 27-29/2003 ዓ.ም. (September 2-4/2011) በዴንቨር ኮሎራዶ በደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል። በዚህ ጉባኤ ላይ በሰሜን አሜሪካ ያሉት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ይገኛሉ። በተጨማሪም ከኢትዮጵያና ከዚሁ ከምንኖርበትም ሀገር የቤተ ከርስቲያን ጥናት ባለሙያዎች በወቅቱ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎችና በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፎች ያቀርባሉ። ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን ቪዲዮ ይመልከቱ፤ ድረ ገጻቸውን (http://eotc-nassu.org) ይጎብኙ። ደጀ ሰላምም የቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንቶች የሆኑት የሰ/ት/ቤቶች በውጪ አገርም ጠንክረው ለቤተ ክርስቲያናችን ዋልታ መከታ ይሆኑ ዘንድ፣ ጉባኤያቸውም ፍሬያማ ይሆን ዘንድ ከልብ ትመኛለች።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን።

እነ መ/ር ዘመድኩን በቀለ ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 1/2011)፦ በበጋሻው ደሳለኝ ‹የስም ማጥፋት ወንጀል› ክስ የቀረበባቸው ዲያቆን ደስታ ጌታሁን፣ መ/ር ዘመድኩን በቀለ እና መ/ር ሣህሉ አድማሱ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ዛሬ፣ ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓ.ም ጠዋት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የቀረቡት ሦስቱም ተከሳሾች በበጋሻው ደሳለኝ የቀረበባቸውን ክስ እንደማይቃወሙት፣ ነገር ግን የስም ማጥፋት ድርጊት ፈጽመናል ብለው እንደማያማኑ ለችሎቱ ተናግረዋል፡፡ ከእነርሱም መካከል አንደኛ ተከሳሽ ዲያቆን ደስታ ጌታሁን ከከሳሽ ጋራ ያላቸው ልዩነት ሃይማኖታዊ በመሆኑ ክሱ በፍትሕ መንፈሳዊ መሠረት ይታይ ዘንድ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መንፈሳዊ ፍ/ቤት እንዲመራላቸው መጠየቃቸው ተገልጧል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)