August 16, 2011

ስለ ተሐድሶ እና ተያያዥ ጉዳዮች የዘሪሁን ሙላቱ ቃለ ምልልስ


“የሃይማኖታችን ጉዳይ የፓትርያርኩ ብቻ አይደለም” የሚለው ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ከቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ  የመጀመሪያ ዲግሪውን በሥነ መለኮት፣ ሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር በፊሎሎጂ ትምህርት ተመርቋል። በአሁኑ ወቅትም ደግሞ የዶክትሬት (ፒ.ኤች.ዲ) ጥናቱን በማገባደድ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ወቅታዊ ሁኔታ እና ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከተለው አስተምህሮ ዙሪያ ከዕንቁ መጽሔት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።  TO READ IN PDF, CLICK HERE.

54 comments:

Anonymous said...

Those Christians who are really concerned about our faith have to be careful on what we put forward. Sometimes I notice the inclination that push we Tewahido Christians to the other extreme. Which is in my view equally wrong. We have to base all our discussion on the teachings of Jesus and his apostles. Just to counter attack the teachings of others such as protestants we don't have to teach the exact opposite of it. We have to always take our faith first. Christianity is not just a religion. We have to always speak truth according to the word of God. Even if others use it as long as it is true we don't have to be refrained from using it or we don't have to label those who use it as tehadiso. I appreciate the concern but we have to do it cautiously so that not to stand against the word of God. God bless us all.

T... said...

ቃለ ሂይወት ያሰማልን:: ግሩን ትምህርት የሚመስጥ ሚስጥር ነው:: እግዚአብሄር እውቀቱን ያብዛልህ::

Anonymous said...

woow nice interview ...esti bezi yazelekelek ..

Anonymous said...

ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

“ሁለት ወፍ ባንድ ድንጋይ” ማለት እንዲህ ነው።
ጥልቅ የሚስጥር ትምህርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች
ላይ ፋና ወጊ ምላሽ ሁኖ አግኝቼዋለሁ። መልስ ሰጪውንም
ደጀ ሰላሞችንም እናመሰግናልን፤ በርቱ።

እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።

Anonymous said...

I knew this guy who wrotte a book to blame Abune Samuel.

Anonymous said...

ቃለ ሂዎት ያሰማህ። ጥሩ ትምርት ነው። እንዲያ ንግርልን።

Anonymous said...

ኧረ ጎበዝ እኘህ ሰውዬ የፓትርያርኩና የማፍያው ቡድን "ስውር ፀሐፊ" ተብለው በደጀ ሰላም (JULY 15.2010) ላይ የወጡት አይደሉም?! ወይንስ እኔ ተምታቶብኝ ነው? እንደው እኮ ዘመኑ ግራ የሚያጋባ ሆነ አያ !!!

Anonymous said...

ኧረ ጎበዝ እኘህ ሰውዬ የፓትርያርኩና የማፍያው ቡድን "ስውር ፀሐፊ" ተብለው በደጀ ሰላም (JULY 15.2010) ላይ የወጡት አይደሉም?! ወይንስ እኔ ተምታቶብኝ ነው? እንደው እኮ ዘመኑ ግራ የሚያጋባ ሆነ አያ !!!

Lik Bilhan Anony... Ahunis Dejeselamm Yemitawotawun bitawuk tiru new bay negn. This Guy was there for years and had conflict with Abune Paulos... He now is blaming him not because he saw the issue now, but because he could not get benefit from Abune Paulos...
Min Ayinet neger new ebakachihu.

Anonymous said...

What are you doing Dejeselam? This guy is one of the right hand of Tehadiso!!!!!!! He is not fasting at all. He is money lover....

You Dejeselam do not cheat us by bringing this naughty boy.

Kindly

Anonymous said...

Is zerihun mulat christian or magician ?

Anonymous said...

To Dejeselam.

ስለዚህ ሰው በጣም እኩይ ተግባር ላይ ተሠማርቶ እንደነበረ አድርጋችሁ በተከታታይ ስትዘግቡ አልነበረም እንዴ? እኔ ሰውየው አሁን ጥሩ መናገሩ አይደለም ያሳሰበኝ ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ገብቶ ተመልሶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እናንተ ያን ሁሉ መዓት ስታወርዱ ከርማችሁ ስለዚያ ማብራሪያ ሳትሰጡ ዛሬ የትምህርት ደረጃውን ደርድሮ ማቅረብ ምን የሚሉት ነው? ያኔ እኮ ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ውሻ በጨው እንዳትልሰው አድርጋችሁ ነበር ያቀረባችሁት:: ትንሽ ቆይታችሁ ደግሞ ወ/ሮ እጅጋየሁ ገዳም ገብተው መነኮሱ ብላችሁ እንዳታቀርቡ ሰጋሁ:: አትፍሩ ይህንን የኔን አስተያየት አውጥታችሁ ለጥፉና እስቲ ሰው የሚላችሁን ስሙ:: ችኮላና ነቀፋ ገዝፎ እየወጣባችሁ ስለመሰለኝ ይህንን አስተያየት ከመስጠት አልተቆጠብኩም በጎ ሥራችሁ ግን ሁልጊዜም ዋጋ ያለው ነው::

Anonymous said...

JULY 15, 2010 ዘሪሁን ሙላቱ፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer)

asbet dngl said...

ሰው ሰው ነው:: ወንድም ግራ እንዳንጋባ ጠንክረን መጽሐፍ ቅዱሳችንን እናንብብ።በተጨማሪ አባቶችንም ሆነ መምህሮችን እንውደድ እናክብር ግን ሰው መሆናቸውን አንዘንጋ።ቃለ ምልልሱ በጣም ያረካል ብሎም ትምህርት ሰጭ ነው:: ወንድሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን:: ለአባታችንም ብሩህ ልቦና ይስጥልን:: አሚን

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች፤
እንዴት ነው? ጸሓፊው አይተቹም እንዴ? ምነው ትችቴን አላወጣችሁትም?

Anonymous said...

ደጀሰላሞች ይህ ሰው ባለፈው ተፈረደበት ብላችሁ ያወራቹልን ሰው አይደለም አንዴ? አስኪ ማብራሪያ ስጡን።

Anonymous said...

to Deje Selam i read the article posted on July 15 2011
ዘሪሁን ሙላቱ፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer)--- u guys i don't understand what is you're idea can u explain----- in deje selam opinion this gay is innocent from "mafeya buden"?? we need u r explanation about this????

Anonymous said...

Deje selamwiyan
you use bad persons writing when it supports your opinion. You may use the deviel quate if it is important for you. This guy wrote a book insulting abune Samual but today you put his message as a good thing. What the hell is going on with you?

Anonymous said...

First of all I am amazed that a PHD student like him does not have an open, logical mind and kind heart to see what the speaker meant to say, when he said the phrase that is now used against him. It is so FERISAWINET to pick one phrase and run like a child to spread among innocent believers. Weather we like it or not God used BEGASHAW to comfort so many broken hearts among our Tewahdo Members. Let us assume he made a mistake, putting his name in earthly magazine is not a biblical way of saving a brother. You know who is reading it? Believers, non-believers, and those who are tired of sin and want to come to the MOTHER church to confess. Do you think they will be encouraged to come reading this and all the fight that is going on between brothers, fathers, etc...? Just because he is popular and you guys are filled with jealousy and envy, you want to raise up on top his downward spiral, or his grave. You will never be like him. Be aware that the loving and understanding Lord Jesus Christ is watching and he will preside to Judge all of us according to our deed. Please take a moment and see what you are doing to a fellow human being. Your negative and baseless accusation and labeling has a real consequences from God. If you realy care try to save him and others.

Anonymous said...

"ኧረ ጎበዝ እኘህ ሰውዬ የፓትርያርኩና የማፍያው ቡድን "ስውር ፀሐፊ" ተብለው በደጀ ሰላም (JULY 15.2010) ላይ የወጡት አይደሉም?! ወይንስ እኔ ተምታቶብኝ ነው? እንደው እኮ ዘመኑ ግራ የሚያጋባ ሆነ አያ !!!"

yes he is the one interesting haaaa lol

Anonymous said...

gra eyagaban yalew Dejeselam enji leloch aidelum. Dejeselamoch lerasachew yemimechachewin bewerq qebtew saimechachew siqer degmo kesel qebtew atqurew yaqerbulinal.
There fore we need to have our own judgement. Let us not be judgemental with what we read from Dejeselamawian. They do things for their purpose, not for the church.

Son of Church said...

የተወደዳችሁ የደጀ ሰላም ጦማር አዘጋጆች አንድ ያስገረመኝ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡
1) ለመሆኑ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ያላችሁት ሙሁር ነኝ ባይ ከነገረ መለኮት ትምህርት ቀርቶ ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጥቷል ብላችሁ ትገምታላችሁ? ነገሩ ከጥላቻ የተነሳ አይደለም፤ ሰውዬውም አላውቀውም ነገርግን ከበጋሻው የባሰ ያልተማረ ደፋር ሆኖ ስላገኘሁት ነው። ያቀረባቸው ሐሳቦች ከትምህርተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ናቸው ለምሳሌ፦
ሀ) “ማርያም ስላሴ ነው የወለደችው ወይስ ኢየሱስ” ብለህ ጥያቄ ማንሳት በራሱ ያስወግዛል ማለቱ የድፍን-ቂል አስተሳሰብ እንጂ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መርህ የፈልግኸውን መጠየቅ ትችላለህ፣ ግልጽ ያልሆነውን ፈትፍታ ማስረዳት እችላለሁ ነው የምትለን። ስለዚህ መጠየቅና መካድ ፍጹም አይገናኙም
ለ) ‘ኢየሱስ’፤ “ኢ= እግዚአብሔር፤ የሱስ=ያድናል” ብሎናል ወንድማችን ሙሁር ነኝ ባዩ። እኔ በጣም ከገረመኝ ደግሞ ይህን የግል ተውሳክ እንደ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት አድርጎ ማቅረቡ ነው፤ ከየትኛው ዘር ወይም ጥሬ ዘር ነው ያዋለደው?ከመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት እንዳንለውም የነሱ አተረጓጎም የተለየ ነው:: በመሰረቱ “ኢየሱሰ” ማለት ከግእዝ የወጣም አይደለም ተጣምሮ እንጂ ተበታትኖ የሚነበብና የሚተረጎምም አይደለም::
ከዕብራይስጥ ‘ዮሽዋህ ወይም የሹ-יהשוה’ ወይም ከግሪክ-Iησοῦς ‘ኢሱስ’ ትርጓሜውም መድሐኒት፣ አዳኝ፣ ድሕነት
ሐ) ትምህርተ ስላሴ በፍልስፍና አስተዋጽኦ በሚለው የሰጠው ትንተና ለመሆኑ የነ ፕላቶ፤ፓይታጎራስ እና የስነ ልቡና ሊቃውንት ስላሴን በተመለከተ የዶግማ ትምህርት እኛ እንደምናምነው ቀርቶ ግርድፍ ነገር ይናገራሉ?

አረ እንዲያው ደጀሰላሞች ሆን ብላችሁ የሰውዬውን ድንቁርና በአደባባይ ለመመስከር ያወጣችሁት ይመስለኛል እንጂ ሁሉም አረም ስለሆነ የሚታረም የለውም

Anonymous said...

ይህ ሰው ተፈርዶበት ወደ ወህኒ እንደወረደ አንብቤ ነበር። እንዴት እና መቼ እንደተፈታ ባላውቅም ለዕንቁ መጽሔት የሰጠውን ቃለምልልስ በማቅረባችሁ አመሰግናለሁ። አንዳንድ አንባቢዎች በዚህ ደጀሰላምን ሲወቅሱ ገርሞኛል። ደጀሰላም አይደለችም ለቃለምልልስ የጠራችው። በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠውን ቃለምልልስ ነው ያካፈለችን።የአቡነ ገብርኤልን፤መጋቤ ሀዲስ እሸቱን እና የሌሎችን እንዳስነበበችን ሁሉ።ልጁ ክርስትናን በመጻፍ እና በማውራት ብቻ የሚኖር እና ምግባር የጎደለው መሆኑን በቅርበት ባውቅም በሰጠው ቃለምልልስ በአብዛኛው ረክቻለሁ፡፡ይህ የሃይማኖች ጉዳይ በመሆኑ ትላንት መጥፎ ያልናቸው ስለሃይማኖት ይገደናል ቢሉ አናርቃቸው። የቤተክርስቲያንን ገንዘቧን የሚወድ ሁሉ ተሃድሶ ነው ማለት አይደለም።

Anonymous said...

Ene yemilew: Zerihun ke-esir tefeta ende?

Anonymous said...

Betam Des Yalegn abzagnawu anbabi ewunetun yakal... deje selam tenagariwunim nigigirunim eyayachihu enji...melkam yemimesil nigigir siletenagere bich yihen yemesele sewu mawutat tikikil ayidelem. kalefewu tifatu temiro kehonem ersu mekidem alebet. Alebeleziya dejeselam tifatin eyegabezech newu...christina nigigirin sayihon mejemeriya tenageriwu manewu yemilewun yaskedimal...Ke minchu yitayal. Asibubet

Anonymous said...

this guy has bad characters like any one of us but he has a good faith.his interview has some flaws
But,deje selam should add his previous realtion with aba paulos.Moreover,he commited crime and he was sent to jail for that.In my opnion he is not a trusted son of our church.If he got the option he will sell us for money.caution yoo.we do not need a man whoonly belive in trinity but we need teachers who care about the church.

Anonymous said...

I do not belive many of his expressions are Orthodox theachings. Do not rush to say the expressions are truly our church's teaching. for me it seems other way of war from the same source. To present Trinity as phylosophy....

kuku from eri bekentu

Anonymous said...

ለደጀ ሰላሞች፡-
በስመ ሞክሼ ካልተሳሳትሁ፤ስለማንነቱ ሰፋ ያለ ከእናንተ አንቤባለሁ። ለደጀሰላማውን ግልጽ እንዲሆን፡-መግቢያ ነገር መስጠት ነበረባችሁ። ለምሳሌ፡-“በዚህ ወቅት (ቀኑን ገልጣችሁ) እንዲህ የሰራው፤እኛ ስለ ማንነቱ ያስነበብናችሁ በዕንቁ መጽሔት ላይ ቃለ ምልልስ አድርጓል። እኛም ምን ያህን ተገለባባጭ እንደሆነ ና ምን እንማርበታለን የሚለውን እንድታውቁት በዚህ አወጣነው:፡“ ምንኛ ባማረ ነበር። አሁን ያየሁት፤ ይህን ተምሮ፤ያን አድርጎ፤እዚህ ደርሶ------ምን ይሰራልኛል። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ልጁ ገንዘብ ካገኘ እንኳን ቤተክርስቲያኒቱን፤እንደ ይሁዳ ኢየሱስ ክርስቶስን በአካል ቢያገኘው የሚሸጥ ይመስለኛል። ምን አልባት በስመ ሞክሼ በስህተት እየወቀስኩ ከሆነ ይቅርታ። ለማንኛውም ከደጀ ሰላም ማብራሪያ አገኛለሁ ብዬ እጠብቃለሁ።

Anonymous said...

ከአስተያየት ሰጪዎች አንድ ቁምነገር ተገንዝብያለሁ እሱም አንዳንዶቻችን እኔንም ጨምሮ ጠለቅ ብለን ሳናውቅ የምስጋና ሐሳብ እንሰጣለን። አንዳንዶቹ የተማሩ ሰዎች እንደ son of churchየመሰሉ ደግሞ የጎደለውን ነቅሰው በማውጣት አንባቢዎች እንድናስተውል አድርገውናል።
ጎበዝ እናስተውል!

ዳንኤል said...

እኔ እንደሚመስለኝ ልጁ ዕውቀት ኖሮት ሳይሆን ፕኤች ዲ እያጠናቀቅሁ ነኝና ስራ ፈልጉልኝ ማለቱ ስለሆነ በእንቁ መጽሔት ማስተዋወቅ የጀመረው

Temelkach said...

To ananymous #1: Could you please be more specific? What if what we believe is the exact opposite of what protestants belief and it is. I don't think it is done to counter attack the teaching of others. It is because they believe to the opposite of what we believe. It could be more clear if you can clearly tell us Which word of God we orthodox refrained to use?
Who is labled as tehadiso just because he/she used the word of God? That guy is tehadiso because his teaching is not according to Tewahido. For that matter he doesn't even know Jesus Christ is God. That must be why he instructed people to use Jessus name not Sellasie. If he is an orthodox he should be able to know that AB, WOLD, MENFESKIDUS=1GOD not 3. He is so confused!!!

Anonymous said...

ይህ ሁሉ ግርግር እኮ በጋሻውን በሕዝብ ለማስጠላት መሆኑ ግልጽ እየሆነባችሁ ነው ።
በጋሻው ያለው እኮ “ድንግል ማርያም ሥላሴን ወለደች አትበሉ ፤ ኢየሱስን ወለደች በሉ ነው”

እርግጥ ነው “ድንግል ማርያም ሥላሴን ወለደች የሚል አስተምሕሮ የለንም ። ወልድ በተለየ አካሉ ፡ በተለየ ስሙ ፡ በተለየ ግብሩ ከድንግል ተወለደ ነው ፡ ትምሕርቱ ።
አብ መረጣት ፡ መንፍስ ቅዱስ አነጻት ፡ (ይህ ከማህጸን ጀምሮ ያለውን መናገር ሲሆን) ወልድ አደረባት ወይም ከሷ ተወለደ ፤ ብለን ነው የምናምነው ።

ዘሪሁን ካለው ውስጥ ብዙ ጠቃሚ ትንተናዎች መኖራቸው አይካድም ፡ ነገር ግን ዘሪሁንም ይሁን በጋሻው ፡ አያውቅም ላለመባልና ሊቅ ለመምሰል ይጣጣራሉ እንጅ ፡ በነገረ መለኮት ትምሕርት ጥልቅ ዕውቀት እንደሌላቸው እና የነገረ መለኮት ዕውቀት ማነስ ችግር እንዳለባቸው ከንግግራቸውና ከአገላለጻቸው ይታወቅባቸዋል ።

ስለዚህ ፡ የዓይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ ፡ እርስ በርስ ከማናከስ፣ ማዶ ለማዶ ሆኖ ከመጠዛጠዝ እና በተናጠል እያንዳንዱን ግለሰብ ቃለ መጠይቅ ከማድረግ ይልቅ ፤ ሊቃውንት የሚሳተፉበት መድረክ እያዘጋጁ ፡ ጠለቅ ባሉ ትምሕርቶች ላይ ሰፋ ያለና ጥርት ያለ ውይይተ፤ ትንታኔ ፤ ክርክርና እና የጋራ የሆነ መልስ ለአንባቢዎች እንዲደርስ የሚደረግበት ሁኔታ ቢኖር ፡ እርስ በርስ ከመባላትና ፡ አማኙንም ግራ ከማጋባት እንጠበቃለን ።

Anonymous said...

Hello Deje Selam

why you didn't post my comment? I sent you many messages, but you didn't post any one. I dno't why?

Anonymous said...

ክርስትና የሚገለጸው በጣፈጠና በቆነጀ ቃል ከሆነ ዘሪሁንን የሚቀድመው የለም። በሥነ ምግባርና በታወቀ እምነት ከሆነ ዘሪሁን ባልዋለበት ቦታ ማስቀመጥ ይሆናል። ዘሪሁን እኮ ከእጅጋየሁ ጋር ከመጣላቱ በፊት እንዳልጎርስሽ ጫማሽ ይንጠለጠልብኛል የሚል የአቡነ ጳውሎስ ጋሻ ጃግሬና ስውር ጸሐፊ ሆኖ ከጌታቸው ዶኒ ጋር የሚሰራውን ያሳጣው ሰው መሆኑን እናውቃለን። አቡነ ሳሙኤልን ለማዋረድ ያላፈረ እንኳን ያላደረጉትን ቀርቶ ቢያደርጉ እንኳን ስልጣኑና አቅሙ ባልሆነ ሁኔታ የቤተክርስቲያንን ክብር ከማህሙድ ሚስት ጋር የደፈረ ሰው እኮ ነው። በህይወት የክብርሐውልት ከአውደ ምህረት ማቆም የነበረ ስርዓት ነው ሲል የተከራከረ አመጸኛም መሆኑ እንዴት ይረሳል?
ንስሃ ገብቶ ቤተክርስቲያንን ለበደለው ሁሉ ተጸጽቶ ነው? ዛሬ ምስጢረ ሥላሴ አስተማሪ የሆነልን? እንደማያደርገው አውቃለሁ። ዘሪሁን እኮ ከተማረውና ከሚያነበንበው ትምህርት ውጪ እኮ ክርስቲያናዊ ስነ ምግባርና የሚመሰከርለት እምነት የሌለው ሰው ነው። ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ጉያ ለመከለልና እነበጋሻው በእምነት ህጸጽ ሲገፈተሩ እሱ ቦታውን ለመረከብና ለመነገድ ካልሆነ በስተቀር በልቡ አምኖ የማኅበረ ቅዱሳንን ስም ለመጥቀስ እንደማይሞክር ይታወቃል። ስለኦርቶዶክስ ያነበነበ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም። ይልቁንም በታወቀና በተረዳ ማንነት የተመሰረለት ጥቂት ንግግር ያለው ምሁር ህይወትን የሚለውጥ ሆኖ ሳለ ደጀሰላሞች ግን ረጅምና የተሰካካ ቃል ስለሰጠው የዘሪሁን ኦርቶዶክሳዊ ማንነት ውስጥ የምግባር፤ የእምነትና የታወቀ መልካም ጠባያት መገለጫዎቹ ምን እንደምትመሰክሩ እስኪ ንገሩን!!!

Anonymous said...

Dear Dejeselam
After I read the article of Zerihun,I got some confusion about the teaching of Trinity. Is it our church teaching about Trinity or Zerihun's philosophy? For me, he brought a new teaching which contradicts with the real Church teachings. I think Begashaw sayings is more related with the Church than Zerihun. Why don't you ask the teachings of Ethiopian Orthodox intellectuals (Liqawent Gubaye) and give us more details. When you say Begashaw teaching is the tehadeso one I was thinking the current Tehadesos who believes in Trinity too. Now, I understood that Begashaw is free from any kinds of irrilivant teaching other than lack of knowlege. Please don't attack anybody for your sake. Think about the church and the followers.

Anonymous said...

1 John 9:1 " If we confess our sins, he is faithful and just and will forgive us our sins and purify us from all unrighteousness."

Anonymous said...

መጋቢ ሐዲስ ዲያቆን በጋሻው አይዞህ ፈተና ነውና ፅና። ሠይጣን ክርስትናህንና ቤተክርስቲያንህን ለማስጣል
ብዙ የሐሰት ምስክሮቹን ቢደረድር አንተ ግን ከመምህራችን ከኢየሱስ ክርስቶስና ከቀደሙ አባቶቻችን የተማርከውን
ታውቃለህ። -እስከ መጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናል- ነውና። የከሳሽህን ድርጅት የወንድሞች ከሳሽ የሆነውን
ጠላት ዲያብሎስ እግዚአብሔር ያሳፍርልህ ዘንድ የተዋህዶ ልጆች የዘወትር ፀሎታችን ነው።

የእመቤታችን ምልጃና ፀሎት፣ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳይነት አይለይህ።

Anonymous said...

Gena beenante Maninet layi bezu masrejawochin inagegnalen

Gin Zerihun Niseha Gebto New woyis Yawu wegenachihu silehone besefer Agegnachihut

Asiqigne sewoch

Anonymous said...

የምሥጢረ ሥላሴና የምሥጢረ ሥጋዌ ትምሕርት በቤተ ክርስቲያናችን

1. ምሥጢረ ሥላሴ ፡ ቃል በቃል ትርጉሙ፣ የሶስትነት ምሥጢር ማለት ፡ አምላክ በሥም, በአካል, በግብር, ሶስትነት እንዳለው ያስረዳል ፡

እነዚሁም፣
1.1. የስም ሶስትነት, አብ, ወልድ, መንፈስ ቅዱስ ።

አብ ይባላል እንጅ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ሥም አይጠራም ፡ ወልድም መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ በየራሳቸው ሥም ይጠራሉ ። ስመ ተፋልሶ (የሥም መቀያየር) የለም ።

1.2. የአካል ሶስትነ ፤ ለሶስቱም ለየራሳቸው ፈጹም ገጽ, ፍጹም መልክ, ፍጹም አካል (ሙሉ አካል,አላቸው ። ነገር ግን ሶስቱንም ለየብቻ (ይህ አብ ነው ፡ ያኛው ወልድ ነው …ብሎ) መለያየት አይቻልም ። ምክንያቱም ፡ አንዱ በሌላው አካል ህልው ሆኖ ስለሚገለጥ ነው ። ዮሐንስ 14 ፡ 9-11 ፡ …..እኔና አብ አንድ ነን ፤ እኔን ያየ አብን አየ…።

በዮርዳኖስ (አብ በደመና, ወልድ በለበሰው ሥጋ, መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል, ቢገለጡም ፡ ለሰው በሚረዳ ነገር ፡ በተጨማሪም ርግብም ፣ ነጭ ደመናም ፣ የየራሳቸውን ምሥጢራዊ ትርጉም ለመግለጥ እንጅ ፡ እግዚአብሐርን በመለኮታዊ ባሕርዩ ከቶ ያየው የለም ፡ ዮሐ 1 ፡ 19 ።

1.3. የግብር ሶትነት ፤ አብ አባት ወልድን የወለደ ፤ ሰራጺ/አስገኝ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ/ያስገኘ ፤
ወልድ ልጅ ከአብ የተወለደ ፤
መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ከአብ የሰረጸ/የተገኘ ፡ ዮሐ 15 ፡ 26 ፤ ማለት ነው ።

ይህ ማለት ግን ፡ እንደ ፈጡራን ሥርዓት አብ አባት አስገኝ በመሆኑ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስም አይቀድምም ፤ አይበለጥም ፡
ወልድና መንፈስ ቅዱስም ከአብ ጋር አይቀዳደሙም፡ አይበላለጡም ፡ እኩል /ዕሩያን ናቸው ።

ከዚህ በላይ የተገለጸው የሶስትነትን ትምሕርት በአጭሩ የሚያብራራ ሲሆን ፤ ከነዚህ ከሰሶስቱ (ከስም ፡ ከአካልና ከግብር)በቀር በሌላው ሁሉ (በህልውና/በመኖር ፣ በባህርይ/መለኮቱ ፣ በፈቃድ ፣ በመፍጠር ፣ በመግዛት ፤ እና በመሳሰለው ሁሉ አንድ ናቸው ።

በሌላ በኩል አንድነትንና ሶሰትነትን የሚያገናዝብ ትምሕርት አለ ፤ ይኸውም ኩነት/መሆን : ወይም ከዊን/ሁኔታ ፡ ይባላል ።

ይህም ፡ በሰው ነፍስ ምሳሌነት ይብራራል ፡ የሰዎች ነፍስ ፡ ለባዊት ፡ የምታስብ ፤ ነባቢት ፤ የምትናገር ፤ ሕያዊት ለዘለዓለም ሕያዊት ሆና የምትኖር ናት ። ከሥጋ ጋር እያለችም ለሥጋ የሌሉትን እኒዚህን አገልግሎቶች ስትሰጥ ትኖራለች ፤ ከሥጋ ስትለይም ፡ ሶሰቱንም ይዛ ለጊዜው በገነት/በሲዖል ትቆያለች ፤ ከምጽአት በሃላም ከሥጋ ጋር ተዋሕዳ ለዘለዓለም ትኖራለች ።

አብ ልብ (ለራሱ ልብ ሆኖ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው) ነው ፤ ወልድ ቃል (ለራሱ ቃል ሆኖ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው) ነው ፤ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት (ለራሱ ሕይወት ሆኖ ለአብና ለወልድ) ሕይወታቸው ነው ።
ስለዚህ ፡ ለእግዚአብሔር/ለሥላሴ ፡ አንድ ልብ ፤ አንድ ቃል ፤ አንድ ሕይወት አለ ማለት ነው ፡

ይህ ከላይ የተገለጸው ምሳሌ ለማሳያነት የቀረበ ነው እንጅ ፡ የፍጡር ባሕርይ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ሙሉ በሙሉ መግለጥ አይችልም/ምሳሌ ዘየሐጽጽ ነው ።

ለማጠቃለልም ፤ አብ ፤ ወልድ ፤ መንፈስ ቅዱስ ፤ በሚባሉ ስሞች ብቻ ሶስት ይሁኑ እንጅ ፤ ሌሎቹ (እግዚአብሔር ፣ አምላክ ፣ ፈጣሪ ፣ እና የመሳሰሉት)ስሞች ግን የአንድነት ስሞች ናቸው ።
እግዚአብሔር ወይም አምላክ…..ባልን ጊዜ ፤ በእንድነት ውስጥ ሁልጊዜ ሶሰትነት እንዳለ እናውቃለን ማለት ነው።

አብ እግዚአብሔር/አምላክ… ፤ ወልድ እግዚአብሔር/አምላክ…፤ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር /አምላክ… ብንልም ሶሰትነትን ለመግለጽ እንጅ ፤ ሶስት አማልክት ማለታችን አይደለምና ማስተዋል ይገባል ።

እርግጥ ነው ፡ ወልድ በተለየ አካሉ ፡ በተለየ ስሙ እና በተለየ ግብሩ ሰው ከሆነ በሃላ የተጠራባቸው ስሞች (ኢየሱስ ፣ ክርስቶስ ፣ አማኑኤል ፣ መድሃኔ ዓለም…..)የሚባሉ ስሞች አሉት ። ነገር ግን ፡ ሥሞቹ ፡ በወልድ ስምነት ይታወቁ እንጅ ፡ በሥራው ሁሉም አሉበት ። ማለትም ፡
እግዚአብሔር ፡ በአብነቱ ፡ በወልድነቱ ፣ በመንፈስ ቅዱስነቱ ፤ሥም ተጠርቶ ፡ አንድ ሥራ ቢሠራም ሥራው ግን የሁሉም ነው ፡ ምክንያቱም ፡ በፈቃድ ፣ በመሥራት እና በመሳሰለው ሁሉ አምላክ አንድ ነውና ።
======================================================================

2. ምሥጢረ ሥጋዌ ፤ የአምላክ ሰው መሆን ትምሕርት ማለት ሲሆን ፤
ከላይ በትንሹ እንደገለጥነው ፡ አግዚአብሔር ወልድ ፡ በተለየ አካሉ ፡ በተለየ ስሙ ፡ በተለየ ግብሩ ፤ ከድንግል ተወለደ/ሰው ሆነ ፡ ስንል ፤ ፍጹም አምላክነቱን ሳይተው ፡ (ልብ በሉ የአብም መንፈስ ቅዱስም ጭምር የሆነውን ፡ ሁሉ ይዞ) ማለታችን ነው ። አምላክነቱ ፣ ፈጣሪነቱ ፡ ህልውነቱ…. ሁሉ ከሱ ጋር ነው ትቶ የመጣው ነገር የለምና ፡ ፍጹም አምላክ ፡ ፍጹም ሰው ሆነ ብለን እናምናለን ።
ፍጹም ሰው ማለትም ፡ ምንም እንኳን፡ በሰው ልማድ ከታወቀው ሥርዓት በተለየ ሁኔታ ከእመቤታችን ብቻ (ያለ ወንድ ዘር) በድንግልና ቢወለድም ፤ የተወለደው ግን ፡ ነፍስንም ሥጋንም ተዋሕዶ ነው ፡ ስለዚህም ነው ፍጹም ሰው የምንለው ፡ ሥጋን ብቻ ወይም ነፍስን ብቻ ሳይሆን ፤ ነፍስንም ሥጋንም ከመለኮቱ ጋር አዋሕዶ ፡ ፍጹም ሰው ፣ ፍጹም አምላክ ሆኖ ተወለደ ፡ ""ሆኖ ተወለደ"" ስንልም ፤በፊት ያልነበረውን ሆነ እያልን ሳይሆን ፤ ከነበረው ምንም ሳይቀንስ ሳይጨምር ተወለደ ማለታችን ነው ።

በሚዋሐድበት/ሰው በሚሆንበት ጊዜም ፡ መለኮቱ የሰውነትን ባሕርይ ሳያጠፋው ፤ ሰውነቱም የመለኮትን ባሕርይ ሳይለውጠው ፤ የሁለቱም (የሰውነትም ፡ የመለኮትም ባሕርይ ሳይለወጥ)፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ፤ ሆኖ ተዋሕዶ ተወለደ ።

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን አንድ ነጥብ ፡ አመቤታችን ገና ከማህፀን ጀምሮ በሰው ልጆች ላይ ሁሉ ይተላለፍ ከነበረው የመጀመሪያ በደል/ጥንተ አብሶ ንጹህ ሆና እንድትወለድ ስላደረገ ፡ አምላክ ከድንግል የተዋሐደው ሥጋና ነፍስ/ሰውነት ከመጀመሪያው በደል ንጹህ ነው ።


ማሳሰቢያ ፤ ይህ የአምላክ ወይም የሥላሴ ፡ አንድነትና ሶስትነት ፡ ልዩ አንድነትና ልዩ ሶስትነት ስለሆነ ፡ በእኛ የሒሳብ ቀመር ለመረዳትም ለማስረዳት አይቻልም ፡

የምሥጢረ ሥጋዌ ትምሕርትም በሰው ሥርዓት ሳይሆን ፤ ያለወንድ ከእመቤታችን ብቻ በድንግልና መወለዱን በሰው ሰውኛ (በሥጋዊና ደማዊ)ዕውቀት መረዳት አይቻልም ።

ምናልባት በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ ያልሆነልን ነገር ካለ ፡ በቂ የነገረ መለኮት ዕውቀት ወዳላቸው ካሕናት አባቶችም ይሁን ወንድሞች ቀረብ ብለን መማር ይገባል እንጅ ፡ በመሰለን አስተያት ብቻ ወደ ስህተት እንዳንገባ ማስተዋል ይገባል ።

ዛሬ በዓለማችን የበዙ ሃይማኖች የሁሉም መነሻቸው ፡ በራሳቸው ቁንጽል ዕቀውቀት ብቻ ተደግፈው የተሳሳቱና ፡ ሌሎችም መንፈሳዊዉን ትምሕርት በዓለማዊ ዕውቀት እንረዳለን ያሉ ግለሰቦች የፈጠሯቸው ችግሮች ናቸው ።

Anonymous said...

የምሥጢረ ሥላሴና የምሥጢረ ሥጋዌ ትምሕርት በቤተ ክርስቲያናችን

1. ምሥጢረ ሥላሴ ፡ ቃል በቃል ትርጉሙ፣ የሶስትነት ምሥጢር ማለት ነው ።ይኸውም ፡ አምላክ ፤ በሥም, በአካል, በግብር, ሶስትነት እንዳለው ያስረዳል ፡

እነዚሁም፣
1.1. የስም ሶስትነት, አብ, ወልድ, መንፈስ ቅዱስ ።

አብ ይባላል እንጅ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ሥም አይጠራም ፤ ወልድም መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ በየራሳቸው ሥም ይጠራሉ ። ስመ ተፋልሶ (የሥም መቀያየር) የለም ።

1.2. የአካል ሶስትነት ፤
ለሶስቱም ለየራሳቸው ፈጹም ገጽ, ፍጹም መልክ, ፍጹም አካል (ሙሉ አካል) አላቸው ። ነገር ግን ሶስቱንም ለየብቻ (ይህ አብ ነው ፡ ያኛው ወልድ ነው …ብሎ) መለያየት አይቻልም ።
ምክንያቱም ፡ አንዱ በሌላው አካል ህልው ሆኖ ስለሚገለጥ ነው ። ዮሐንስ 14 ፡ 9-11 ፡ …..እኔና አብ አንድ ነን ፤ እኔን ያየ አብን አየ…።

በዮርዳኖስ (አብ በደመና, ወልድ በለበሰው ሥጋ, መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል, ቢገለጡም ፡ ለሰው በሚረዳ ነገር ፤ በተጨማሪም ርግብና ፣ ነጭ ደመናም ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚያገናኛቸውን የየራሳቸውን ምሥጢራዊ ትርጉም ለመግለጥ እንጅ ፡ እግዚአብሐርን በመለኮታዊ ባሕርዩ ከቶ ያየው ማንም የለም ፡ ዮሐ 1 ፡ 19 ።

1.3. የግብር ሶትነት ፤
አብ አባት ወልድን የወለደ ፤ ሰራጺ/አስገኝ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ/ያስገኘ ፤
ወልድ ልጅ ከአብ የተወለደ ፤
መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ከአብ የሰረጸ/የተገኘ ፡ ዮሐ 15 ፡ 26 ።

ይህ ማለት ግን ፡ እንደ ፍጡራን ሥርዓት አብ የወልድ አባትና ፡ የመንፈስ ቅዱስ የአስገኝ በመሆኑ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስም አይቀድምም ፤ አይበልጥም ፡
ወልድና መንፈስ ቅዱስም ከአብ ጋር አይቀዳደሙም፡ አይበላለጡም ፡ እኩል /ዕሩያን ናቸው ።

ከዚህ በላይ የተገለጸው የሶስትነትን ትምሕርት በአጭሩ የሚያብራራ ሲሆን ፤ ከነዚህ ከሰሶስቱ (ከስም ፡ ከአካልና ከግብር) በቀር በሌላው ሁሉ ፡ (በህልውና/በመኖር ፣ በባህርይ/መለኮቱ ፣ በፈቃድ ፣ በመፍጠር ፣ በመግዛት ፤ እና በመሳሰለው ሁሉ አንድ ናቸው ።

በሌላ በኩል አንድነትንና ሶሰትነትን የሚያገናዝብ ትምሕርት አለ ፤ ይኸውም ኩነት/መሆን : ወይም ከዊን/ሁኔታ ፡ ይባላል ።

ይህም ፡ በሰው ነፍስ ምሳሌነት ይብራራል ፡ የሰዎች ነፍስ ፡ ለባዊት- የምታስብ ፤ ነባቢት- የምትናገር ፤ ሕያዊት - ለዘለዓለም ሕያዊት ሆና የምትኖር ናት ።
ከሥጋ ጋር እያለችም ፤ ለሥጋ የሌሉትን እኒዚህን አገልግሎቶች ስትሰጥ ትኖራለች ፤ ከሥጋ ስትለይም ፡ ሶሰቱንም ይዛ ለጊዜው በገነት ወይም በሲዖል ትቆይና ከምጽአት በሃላም ከሥጋ ጋር ተዋሕዳ ለዘለዓለም ትኖራለች ።

የሥላሴ አንድነትና ሶስትነት በሰው ነፍስ ምሳሌ (ኩነት-ከዊን)

አብ ልብ ፤ (ለራሱ ልብ ሆኖ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው) ነው ፤
ወልድ ቃል (ለራሱ ቃል ሆኖ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው) ነው ፤
መንፈስ ቅዱስ ሕይወት (ለራሱ ሕይወት ሆኖ ለአብና ለወልድ) ሕይወታቸው ነው ።
ስለዚህ ፡ ለእግዚአብሔር/ለሥላሴ ፡ አንድ ልብ ፤ አንድ ቃል ፤ አንድ ሕይወት አለ ማለት ነው ፡

ይህ ከላይ የተገለጸው ምሳሌ ለማሳያነት ቀረበ እንጅ ፡ የፍጡር ባሕርይ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ሙሉ በሙሉ መግለጥ አይችልም (ምሳሌ ዘየሐጽጽ ነው) ።

ለማጠቃለልም ፤ አብ ፤ ወልድ ፤ መንፈስ ቅዱስ ፤ በሚባሉ ስሞች ብቻ ሶስት ይሁኑ እንጅ ፤ ሌሎቹ (እግዚአብሔር ፣ አምላክ ፣ ፈጣሪ ፣ እና የመሳሰሉት) ስሞች ግን ፡ እግዚአብሔር በአንድነቱ የሚጠራባቸው የአንድነት ስሞች ናቸው ።
እግዚአብሔር ወይም አምላክ…..በምንበት ጊዜ ፤ በህሊናችን ውስጠ ፡ ሁልጊዜ በእንድነት ውስጥ ሶሰትነት እንዳለ እናውቃለን ።

አብ እግዚአብሔር/አምላክ… ፤ ወልድ እግዚአብሔር/አምላክ…፤ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር /አምላክ… ብንልም ሶሰትነትን ለመግለጽ እንጅ ፤ ሶስት አማልክት ወይም ሶስት እግዚአብሔሮች አሉ ማለታችን አይደለምና ማስተዋል ይገባል ።

እርግጥ ነው ፡ ወልድ በተለየ አካሉ ፡ በተለየ ስሙ እና በተለየ ግብሩ ሰው ከሆነ በሃላ የተጠራባቸው (ኢየሱስ ፣ ክርስቶስ ፣ አማኑኤል ፣ መድሃኔ ዓለም…..) የሚባሉ የሥጋዌ ስሞች አሉት ። ነገር ግን ፡ ሥሞቹ ፡ በወልድ ስምነት ይታወቁ እንጅ ፡ ወልድ በሰራው ሁሉ አብና መንፈስ ቅዱስም አሉበት ።
እግዚአብሔር ፡ በአብነቱ ፡ በወልድነቱ ፣ በመንፈስ ቅዱስነቱ ፤ሥም ተጠርቶ ፡ አንድን ሥራ ቢሠራም ሥራው ግን የሁሉም ነው ፡ ምክንያቱም ፡ በፈቃድ ፣ በመሥራት እና በመሳሰለው ሁሉ አምላክ አንድ ነውና ።
======================================================================

2. ምሥጢረ ሥጋዌ ፤ የአምላክ ሰው መሆን ትምሕርት
ከላይ በትንሹ እንደገለጥነው ፡ አግዚአብሔር ወልድ ፡ በተለየ አካሉ ፡ በተለየ ስሙ ፡ በተለየ ግብሩ ፤ ከድንግል ተወለደ/ሰው ሆነ ፡ ስንል ፤ ፍጹም አምላክነቱን ሳይተው ፡ (ልብ በሉ የአብም የመንፈስ ቅዱስም ጭምር የሆነውን ፡ ሁሉ ይዞ) ማለታችን ነው ።
አምላክነቱ ፣ ፈጣሪነቱ ፡ ህልውነቱ…. ሁሉ ከሱ ጋር ነው ። ትቶ የመጣው ነገር የለምና ፡ ፍጹም አምላክ ፡ ማለታችን ለዚህ ነው ።
ፍጹም ሰው ማለታችንም ፡ ምንም እንኳን፡ በሰው ልማድ ከታወቀው ሥርዓት በተለየ ሁኔታ ከእመቤታችን ብቻ (ያለ ወንድ ዘር) በድንግልና ቢወለድም ፤ የተወለደው ግን ፡ ነፍስንም ሥጋንም ተዋሕዶ ነው ፡ ስለዚህም ነው ፍጹም ሰው የምንለው ፡ ሥጋን ብቻ ወይም ነፍስን ብቻ ሳይሆን ፤ ነፍስንም ሥጋንም ከመለኮቱ ጋር አዋሕዶ ፡ ፍጹም ሰው ፣ ፍጹም አምላክ ሆኖ ተወለደ ለማለት ፡ ""ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ሆኖ ተወለደ"" ስንልም ፤ አምላከ፤ በፊት ያልነበረውን የሱ ያልነበረውን የሰው ባህርይ ፤ ሰውም የሱ ያልነበረውን የአምላክ ባህርይ ተዋሐድ -አምላክ ሰው ሆነ ፤ ሰው አምላክ ሆነ ፤ ከነበረው ምንም ሳይቀንስ ሳይጨምር ተወለደ ማለታችን ነው ።

በሚዋሐድበት/ሰው በሚሆንበት ጊዜም ፡ መለኮቱ የሰውነትን ባሕርይ ሳያጠፋው ፤ ሰውነቱም የመለኮትን ባሕርይ ሳይለውጠው ፤ የሁለቱም (የሰውነትም ፡ የመለኮትም ባሕርይ ሳይለወጥ)፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ፤ ሆኖ ተዋሕዶ ተወለደ ።

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን አንድ ነጥብ ፡ አመቤታችን ገና ከማህፀን ጀምሮ በሰው ልጆች ላይ ሁሉ ይተላለፍ ከነበረው የመጀመሪያ በደል/ጥንተ አብሶ ንጹህ ሆና እንድትወለድ ስላደረገ ፡ አምላክ ከድንግል የተዋሐደው ሥጋና ነፍስ/ሰውነት ከመጀመሪያው በደል ንጹህ ነው ።


ማሳሰቢያ ፤ ይህ የአምላክ ወይም የሥላሴ ፡ አንድነትና ሶስትነት ፡ ልዩ አንድነትና ልዩ ሶስትነት ስለሆነ ፡ በእኛ የሒሳብ ቀመር ለመረዳትም ለማስረዳት አይቻልም ፡

የምሥጢረ ሥጋዌ ትምሕርትም በሰው ሥርዓት ሳይሆን ፤ ያለወንድ በድንግልና ከእመቤታችን ብቻ መወለዱን በሰው ሰውኛ (በሥጋዊና ደማዊ) ዕውቀት መረዳት አይቻልም ።

ምናልባት በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ ያልሆነልን ነገር ካለ ፡ በቂ የነገረ መለኮት ዕውቀት ወዳላቸው ካሕናት አባቶችም ይሁን ወንድሞች ቀረብ ብለን መማር ይገባል እንጅ ፡ በመሰለን አስተያት ብቻ ወደ ስህተት እንዳንገባ ማስተዋል ይገባል ።

Anonymous said...

How come you did no post Deacon Daniel's article about :YIKERTA??

https://docs.google.com/viewer?a=v&pid=explorer&chrome=true&srcid=12qs9ytXQ-A4m4g1la4WRtpj_9-ukZD2X4RzL4DNdsMKv0h4aEfFodtQcTI8_&hl=en_US

Anonymous said...

https://docs.google.com/viewer?a=v&pid=explorer&chrome=true&srcid=12qs9ytXQ-A4m4g1la4WRtpj_9-ukZD2X4RzL4DNdsMKv0h4aEfFodtQcTI8_&hl=en_US

Anonymous said...

correction

1.3. የግብር ሶትነት ፤
አብ አባት ወልድን የወለደ ፤ ሰራጺ/አስገኝ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ/ያስገኘ ፤

should read

አሰራጺ/አስገኝ

Anonymous said...

"እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን አንድ ነጥብ ፡ አመቤታችን ገና ከማህፀን ጀምሮ በሰው ልጆች ላይ ሁሉ ይተላለፍ ከነበረው የመጀመሪያ በደል/ጥንተ አብሶ ንጹህ ሆና እንድትወለድ ስላደረገ" is catholicism.

Orthodox Tewahdo belives "ANTSEHO SEGAHA HADERE LA ELEHA"

"The Orthodox Church, whose love towards St. Mary is
deeprooted, considers her more holy than all the heavenly
creatures, whilst a natural member of the human race. We do not
however, set her apart from the human race by assuming that she
was born without original sin, as if she was born not of human
seed" source Coptic orthodox church which we call them AS MARKOS ABATACHEN ESCNDRIA ENATACHIN

Anonymous said...

ጎበዝ ይህ ዘሪሁን የሚባል ግለሰብ እኮ አደገኛ ወሮበላ ሞላጫ ነገር ነው ።
ለመጀረመሪያ ጊዜ ዲ በጋሻው “የመስቀሉ ስር ቁማረተኞች ብሎ አንድ መጽሐፍ ባሳተመ ጊዜ “የስድብ አፍ” በሚል ርእስ ለበጋሻው መልስ በመስጠቱ ነው ያወቅነው ፡ ለዚህ መጽሐፉም ከአባ ጳውሎስ ስልሳ ሺህ ብር ተቀብሏል እየተባለ ይወራ ነበር ፡ የብሩ መጠን ልዩነት ይኖር ይሆናል እንጅ ብር መቀበሉ የታወቀ ጉዳይ ነው ።
ለሁለተኛ ጊዜ እጅግ የቅርብ ወዳጁ የነበሩትን አቡነ ሳሙኤልን ለሚሊኒዬም በዓል ዝግጅት ተብሎ በተለቀቀው ብዙ ሚሊዮን ብር ክፍፍል ላይ እሱም የበአሉ ዝግጅት ኮሚቴ ጸሀፊ ነበርና የድርሻውን ስለከለከሉትና በዚያ ስለተጣላቸው ከፓትርያርኩ ጋር የመጣላቸውን አጋጣሚ ተጠቅሞ እንደዚያ የአባቶችንም ሆነ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር የሚያዋርድ ተራ ጽሑፍ ጻፈና ተገቢውን የካም ዋጋ ተቀበለ ።

ከዛ በማስከተል ደግሞ የአባ ጳውሎስ ሐውልት ሲገነባ ከተለቀቀው ገንዘብ ላይ ወፍራሙን ድርሻ ካላገኘሁ ብሎ በፋንታሁን ሙጨ በበጋሻውና በእጅጋየሁ ላይ የስድብ መጸሐፍ ጽፎ ነበር በዚህኛው ትንሽ ዋጋ የከፈለበት ይመስለኛል ።
አሁን ደግሞ ድመጹን አጥፍቶ ቆይቶ ይህችን የተሃድሶ ግርግር ጠቅሞ ዳቦዉን ለመጋገር ዳር ዳር እያለ ነው ። ማህበረ ቅዱሳን እንዲህ ዓይነቱ ወሮበላ ከሃዲ ተሃድሶ እያለ ስለተሳደበ አምናችሁት ወደ ውስጣችሁ ማስገባት የለባችሁም ፡ ይህ ግለሰብ አጓጉል ቦታ ላይ ካገኛችሁ እንደማይምራችሁ መገመት አለባችሁ ።

Anonymous said...

deja selamwoche lamen lamettetayakote malse atesatome?yeha nekate nawe yakabarachehone anebabe.who is he????????????????????????????????????????????

Anonymous said...

kala heiwate yasamahe.

ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል ከደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሰ/ት/ቤት said...

የተወዳዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶክሳውያን :-
እስካሁን ከበጋሻ የስህተት ትምህርቶች ጎልቶ የወጣውና መልስም እየተሰጠበት ያለው ምሥጢረ ሥላሴን በተመለከተ ባስተመረው ላይ ነው:: ይህም ምሥጢረ ሥላሴ ከአዕማደ ምሥጢርና ከክርስትና ሃይማኖት መሠረታዊ ትምህርቶች አንዱ እንደ መሆኑ ተገቢ ነው ::
ነገር ግን በዚህ ሁኔታ መልስ ስሰጥ በጋሻው ባለማወቅ ብቻ በየዋህነት የተሳሳተ ልመስለን ይችላል ::
የባጋሻውን የተለያዩ ትምህርቶች ስናይ ግን ነገሩ ከዚህ የዘለለ ሆኖ እናገኘዋለን ::በትንሹ 2ቱንም በአዋሳ ምዕመናን የተዘጋጁ ሲዲዎችን ብናይ በጋሻው ቤተክርስቲያኒቱን እንደሚጠላ አባቶችንም እንደምንቅ የቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ እንደሚያጥላላ ይልቁንም በቤተክርስቲያን ስም ብቻ የነበረ የለየለት መናፈቅ መሆኑን ነው::
ለምሳሌ
1. አሮጊቱዋ ሣራ
2. ይህ ሃይማኖት ከዛሬ 20 ዓመታት በፊት ድኅነት የማይገኝበት የኦሪቱ ሥርዓት የጨለማ ሕይወት
3. ጸበል ያድናል እምነት ያድናል ይህ ያድናል ያ ያድናል አትበል ሲያድን አየሀው እንዴ በመጽሐፍ ቅዱስ
4. እስካሁ በእድር ሥርዓት ነው ያለው ወንጌል አልገባውም
5. ቦታ አትለውጥ ራስህን ለውጥ
6.አባ አባ ዲያቆን ዲያቆን ኤገለ ኤገለ መባባል ይቀራል
የሚሉትን ከብዙ በጥቅቱ የበጋሻውን የኑፋቄ ትምህርቶች ሲናይ ሰውዬው የለየለት መናፍቅ የ"ተሐዲሶ "ፊተአዋራሪ ከመሆኑም በሻገር ደፋር በንቀት በሃይማኖታችን አደባባይ የመናፍቃንን አስተምህሮ ያስተማረ ሆኖ እናገኘዋለን::
7."ስለ ማርያም ሳወራ ሰዎች ይህ ልጅ ምን ነካው ስለ ድኅነት ስለ ኢየሱስ አያወራም እንዴ ........."የሚል ዓይነት የኑፋቄውን ትምህርት ከነዛ በኁላ "ሰዎች ሰው ወዘተርፈ" እያለ በሰዎች የሚያላክካቸውና መጨረሻ ለይ የሚጨምራቸው ቃላት አጉል ብልጣብልጥነቱንና ከተጠያቂነትም ለመደን የዘየደው መሆኑን ከመግለጡም ባሻገር ሆን ብሎ የኑፋቄ ትምህርቱን በዝግጅት እንደሚነዛ ያሰውቁበታል::
የእነ በጋሻው ማኅበር ሰብሳቢ ፍጹም ታደሰ የሚባለው የ"ተሐዲሶ "መናፍቃንን ሤራ ማጋለጥ ስጀመር በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ዐውደ ምሕረት ላይ "ጣላት ነው የሚያስወራው በ EBS የሚተላለፈውን ታዖሎጎስ መርሐ ግብር ተከታተሉ" በማለቱ በራሱ ጊዜ የ"ተሐዲሶ "አቀንቃኝ መሆኑን በማጋለጡ እንደ ቃየን ግብሩ አባሮት ዱባይ ሚካኤል ስቆይ ከደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ በራሱ ጊዜ ሥራ እንደለቀቀ ተብሎ ማስታወቂያ ሲወጣበት አሁን ደግሞ "ወንድሜ ስለሞተ ነው የጠፋሁት" በማለት ወደ ቢሮ እየገባ ነው ::
እነዚህን ሰዎች አቡነ ፓውሎስ ለመቅጣር ደብዳቤ መጻፋቸው በቅርቡም በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም በተደረገው የደቀ መዛሙርት የምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ "የሰው መብት በተጠበቀበት ዘመን ምንድን ነው ሰውን ኤገሌ ተሐዲሶ ነው ኤገሌ ይህ ነው እያሉ መወንጀል " በማለት ንግግር ማድረጋቸው በጽሑፍም ማረጋገጣቸው ጸረ ቤተክርስቲያን መሆናቸውን አረጋግጦ የ"ተሐዲሶ" ጉዳይ ምን ያህል አሳሳቢ እንደ ሆነና በጸረ -"ተሐዲሶ "የሚናደርገው እንቅስቃሴ ምን ያህል ጥንቃቄና ትኩረት እንደሚያስፈልገው ያሳየናል::
የቤተክርስቲያን አምላክ አንድነቱዋን ያጽናልን::

Anonymous said...

Dn Haile Michael kala heiwot yasamahe.Dn Bagashawe protestanto yega nawe enedamelo sametanale gene sela sawe bamawerate geza kamenatafa yarasachenen enewake yane holome yegabachehole.

Anonymous said...

ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል

I feel so sorry for you that you have one of the best title "ዲ/ን" "am assuming that you meant to say "ዲያቆን". You know one of our church pillars st. Stephanos has this title. As you know he died preaching Jesus Christ. ዲያቆን should know his religion very well. From your comments I doubt that you have a clue about the teachings of Tewahdo. Am afraid that your are one of those people with the highest title, but no sprituality and knowledge about a heavenly institution like Tewhado. Could you please categorize the following accordingly so that me and others would know the persons ኑፋቄ


የለየለት መናፈቅ መሆኑን ነው::
ለምሳሌ
1. አሮጊቱዋ ሣራ
2. ይህ ሃይማኖት ከዛሬ 20 ዓመታት በፊት ድኅነት የማይገኝበት የኦሪቱ ሥርዓት የጨለማ ሕይወት
3. ጸበል ያድናል እምነት ያድናል ይህ ያድናል ያ ያድናል አትበል ሲያድን አየሀው እንዴ በመጽሐፍ ቅዱስ
4. እስካሁ በእድር ሥርዓት ነው ያለው ወንጌል አልገባውም
5. ቦታ አትለውጥ ራስህን ለውጥ
6.አባ አባ ዲያቆን ዲያቆን ኤገለ ኤገለ መባባል ይቀራል
የሚሉትን ከብዙ በጥቅቱ የበጋሻውን የኑፋቄ ትምህርቶች
If you get a chance please read them well before you write

Anonymous said...

ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማስቀደም አስፈላጊ መስሎ አይታያችሁምን?
ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባረርህ እርስዋንም ተከልህ። በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ፥ ሥሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች። ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ። ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች። አጥርዋን ለምን አፈረስህ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይቀጥፋታል መዝ 80፥8-12
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረ ሰቦች ሐገር ናት ይህ አባባል የብዙ ሰዎችን ልብ ያደከመ ይመስላል ሆኖም እውነቱ ግልጽ ነው በሃይማኖትም ደረጃ ቢሆን ብዙ የተለያዩ ሃይማኖቶች አሉ ሁሉም ሃይማኖት ለራሱ እንደክብሩ ነውና። በዚህ ጽሑፍ ግን ሃይማኖት ማለት “እምነት” ማለት እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።

በሀገራችን ክርስትና ተጀመረ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ለክርስትና መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽዖ ያደረገችው ጥንታዊትና ወንጌላዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በየዝመናቱ ያለፈችበት ታሪክ ቀላል አይደለም። ይህ የወንጌል ዘር በአፍሪካ በወንጌላዊዊ ፊልጶስ ከዚያም በአባ ሰላማ ወደ ዚህች አገር ከገባ ቆይቷል። ከዚያው ጊዜ ጀምሮ የገጠማት ፈተና ከባድ ነበር። ለምድሪቱ ዘር የተሸከመችው ይህችው ቤተ ክርስቲያን በትክክል የተዘራው ዘር በትክክል እንዳይበቅል ጠላት በሚገባ ተፈታትኖታል ብንል ታሪክ በምሥክርነት ይቆምልናል።
ዓላማዋን እንዳታሳካ መሣሪያውን እየቀያየረ ደብድቧታል። ክርስትና ከመካከለኛው ምሥራቅ ቀጥሎ የገባው ወደ ኢትዮጵያ ነው፤ ለመቶ አመታት ከአረማዊና ኦሪታዊ አምልኮ ጋር ሲታገል የነበረው ክርስትና ከመቶ አመታት በኋላ ግን እራሱን በጥረት ማቆም አቅቶት ከባህልና ከልማድ ጋር እንዲሁም ከሐሰት ትምሕርቶች ጋር እየተቀላቀለ ነገሮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ጋር ማገናዘብ አቅቶት እየተጨነቀ መጓዝ ከጀመረ ሰንብቷል።
ዛሬ አንዳድ የሃይማኖት ድርጅቶች ኦርቶዶክስ ማን ናት? ማለት ከጀመሩ ቆይተዋል። ውለታን ቆጥሮ ማመስገን እና መብትን መጠየቅ ሌላ ነገር ሆኖ ሳለ ማን ነው? ማን ናት? እንዲያውም ነጻነቴን ነፍጋኛለች፤ ማለትና ማወጅ “ባጎረስኩኝ ተነከስኩኝ” የሚለውን የአበው ብሂል እንድናስታውስ ያደርገናል።

Anonymous said...

ወጣም ወረደ ሕዝባችን ሃይማኖቱ ተጽእኖ እንዳደረገበት ካለው የስነ ምግባር አራያነትና ካለው ፈሪሃ እግዚአብሔር መረዳት ይችላል። ሆድ ብሶት ገፍቶ ካልወጣ በስተቀር እግዚአብሔርን በመለመን የሚያምን፤ የርስበርስ እልቂትን የሚጠላ፤ በተለያየ የታሪክ አጋጣሚ ተጋብቶና ተዛምዶ በሰላም የሚኖር መሆኑ ያስደንቃል። የውጭ አገር ዜጎች ወርቅ ፒያሳ ላይ በየመስኮቱ ተንጠልጥሎ ሲሸጥ ሲያዩ “እዚህ አገር ሌባ የለም ወይ” ሲሉ ይጠይቃሉ። ምክንያቱን ብናጠናው ግን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፈሪሃ እግዚአብሔርን በማስተማሯ ነው። ሕዝቡም ሃይማኖታዊ ስራት ማለት የማዘዝ እና የመታዘዝ ሥራት እንዲኖረው አድርጋለች። በነበሩት ውስብስብ ሁኔታዎች ቤ/ክ/ ለተለያዩ ነገሥታት መጠቀሚያ የሆነችው የሕዝቡ የመገዛት ጠባይ መሠረት ተደርጎ ነው። እንግዲህ ይህ ሁሉ ያሳደረባትን ተጽእኖ ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ቤተ ክርስቲያኒቱን መውቀሱ አመጽ ነው እንላለን።
በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሚሲዮናውያን የኦርቶዶክስን ቤተ ክርስቲያን ተተግነው ከገቡ በኋላ ምእመኖቹ እነሱ የሚሉትን እንዲሉ በማድረግና ካሉበት ቦታ በማስኮብለል የጀመሩት ሥራ ቤተ ክርስቲያንን አስከፍቷል። ጠባሳውም እስከ ዛሬ በመኖሩ በሀገሪቱ ያለው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የሚፈለገውን ያህል እያደረገ እንዳልተራመደ ብዙ ምሁራን ይናገራሉ። የሥነ መለኮት ተማሪዎችም አፍሪካን በሚመለከት በሃይማኖት ስም የተደረገውን ቅርመታ በስፋት ዘግበውታል።
አባቶቻችን መሬታችንን አናስነካም እያሉና በሃይማኖት አንድ በማድረግ አንድነታችንን እና ሀገራችንን በሚችሉት ሁሉ በማስተባበር ያደረጉትን ተጋድሎ መርሳት ከኛ ከልጆቻቸው አይጠበቅም።
ከዚህም ሁሉ ጋር ቤተ ክርስቲያን አንድነታችንን እና የሀገራችንን ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት፤ የክርስቶስን በሥጋ መወለድ የአምስቱን ምሥጢራት ትምህርት ከሕጻንነታችን ጀምረን እንድናውቀው በማድረግ ዛሬ ለደረስንበት ሁኔታ አስታዋጽዖ አድርጋልናለች ብለን የምናምን ጥቂቶች አይደለንም።
ዛሬ አገሪቱ ካለችበት የሃይማኖት እንቃሥቃሴ አንጻር ከግራና ከቀኝ የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን መሸራረፍ የዘሩትን ማጨድ እንዳለ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መርሳት ነው። ለዚህ እንዲያመች ተብሎ ቤተ ክርስቲያኒቱን “ቤተ ክርስቲያን አይደለችም” ማለት ሌላ ጥፋት ነው።
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በ1600 ዓመታት ውስጥ ያለፈችበት ጎዳና ዛሬ በምድራችን ያሉና የክርስትናን ስም ይዘው ከወራት እስከ እስከ 100 አመት የሆናቸው ቤተ እምነታት አሁን የደረሰባቸውን ቀውስ በመመልከት ነገ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ አስቀድሞ ማየት አስፈላጊ ነው።
በቅርብ የወጣ አንድ መንፈሳዊ መጽሔት ባለፉት ዓመታት ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት “አስቸግረውናል” በማለት በተለያየ ነገር ሲከሷቸው የነበሩና እንግሊዝ ሐገር ኑረው በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የመጡ አንድ ሰው በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ ተገኝተው መናገራቸውን ዘግቦ ነበር። እኒህ ሰው እንዲህ ብለው ነበር “ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን ከዓለም እንጂ ከቤተ ክርስቲያን አናወጣም ወደ ጤናማነት እንመለሳለን እንጂ ወደ እብደት አንሄድም። ብልጽግና ብልጽግና አትበል ብልጽግናህ እግዚአብሔር ነው እንደ ጭልፊትና ንሥር ባለጠጋን መናጠቅህን አቁም ከሌላው የተነጠቁ ምእመናን ሁሌም የናንተ አይደሉም የዚህ ሰው ፈውስ ያለው በቤተ ክርስቲያኑ ነው። ስለዚህ ሙሉ ወንጌል የሆነውን ወደ ሙሉ ወንጌል መልሱ መሠረተ ክርስቶስ የሆነውን ወደ መሠረተ ክርስቶስ መልሱ ኦርቶዶክስ የሆነውን ወደ ኦርቶዶክስ መልሱ ካቶሊክ የሆነውን ወደ ካቶሊክ መልሱ አዎን የክርስቶስን ሥራ በዚያው በሥፋራቸው ሆነው ያቀጣጥሉ... ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሥር እየሄድህ ሰው አትሥረቅ ወደ አደባባይ ውጣ ከአደባባይ አምጣ ብለዋል...” ይህን ካሉ በኋላ ሪፖርት አቅራቢው የራሳቸውን ሐሳብ ለማንጸባረቅ እንዲህ በለዋል “ ወንጌል እሰብካለሁ እያላችሁ በየቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ እየሄዳችሁ ሰው አትስረቁ” ማለታቸው ብቻ ሳይሆን ይባስ ብለው ይላል ዘጋቢው “ከአብያተ ክርስቲያናት የሠረቃችኋቸውን ምእመናን ወደየቤታቸው መልሱ” ማለታቸው ለኔ ያስረዳኝ ነገር ቢኖር በርሳቸው የመጣው ኃይል እጅግ ብርቱ ስለመሆኑ ዘጋቢው አበክረው ገልጠዋል።
የእርሳቸውን ሁኔታ ንግግር የተረዱ ሌላው እዚያው ያሉ አገልጋይ “በምድር ያሉት የቤተ ክርስቲያን አባሎች ሁሉ የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች ናቸው። ስለዚህ በወንድሜ ቦታ ለመቀመጥ መፈለግ ትልቅ አመጽ ነው። እኛ ግን ሁሌም ስናየው የማንወደውን ልንለውጠው እንፈልጋለን ሰይጣንም ያደረገው እንዲህ ነው ለምን እግዚአብሔር ዙፋን ላይ አልቀመጥም ያለው እንዲሁ ነው። ለምን ? እግዚአብሔር ትንሽ ስጦታ ሲሰጠን ሊገለገልብን ሲጀምር ሁሉም ነገር እኛ ላይ ያረፈ ይመስለናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል

ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል ከደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሰ/ት/ቤት said...

@The second Anonymous who criticised my comment:
ስለ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስን በመጥቀስ የዲቁና ማዕረግ ታላቅነትን ስለገለጹ ላመሰግኖት እወዳለሁ::
ነገር ግን ከሰጠሁት አስተያየት ብቻ ተነስተው ስለ ሃይማኖቴ ምንም እንደማለውቅ አድርገው ለመናገርና ለመደምደም እንዴት እንደ ቻሉ ግልጽ አይደለም::
ምንአልባት ከበጋሻው የስህተት ትምህርቶች የጠቀስኩአቸው ነጥቦች የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ናቸው እንጂ ስህተት አይደሉም የሚል አቁዋም ካሎት በግልጽ መነጋገር እንችላለን ::
እርሶም የቤተክርስቲያን ልጅ መስለው ከማደናገር ጎራዎን ለመለየት ለአንባብያንም ግልጽ ይሆናል::
እስኪ እርሶ ያነሱትን ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስን እንይ:-
ቅዱስ እስጢፋኖስ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን መርጦ ሊያድናቸው ወዶ ብዙ ጊዜ ነቢያትን ልኮላቸው እንደ ነበረ ተርኮ እነርሱ ግን ልበ ዳንዳኖች መሆናቸውን በግልጽ ማንነታቸውን በመናገሩ አይደል የተወገረው?
"......እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁ ያልተገረዘ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ......."እንዲል::ሐዋ7:51
ይህ መቼም ለቅዱስ እስጢፋኖስ ኃጢአት ሆኖ እንዳልተቆጠረበት ይልቁን በሃይማኖት ጸንቶ በመመስከሩ ሰማያት ተከፍተው እስከማየት እንደደረሰ የሚያስተባብሉ አይመስለኝም::
ዮሐንስ መጥምቅ የእፉኝት ልጆች ብሎ መናገሩ ስድብ ይሆን ?
ስድብ ብሆንማ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከሴቶች ከተወለዱት ዮሐንስን የሚበልጠው እንደሌለ በልተመሰከረለት ነበረ::
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድን የዲያብሎስ ልጆች ማለቱ ስህተት ይሆን? ሎቱ ስብሐት ::ክብር ይግበውና እንዲህም አይነገርለትም ::እርሱ መእምረ ኅቡኣት ከኀለ ኩሉ ነውና::
እንግድህ እነዚህ ሁሉ የሚያስገነዝቡን በሃይማኖት ለተለየን ነገር ግን በሃይማኖት ለሚመጣብን ምንም ይሉኝታ ሳያስፈልግ ማንነቱን መናገር ተገቢ መሆኑን አይደለምን?

Anonymous said...

ዘሪሁን:-ኢየሱስ ስንል የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተገለጸበት ነው የእግዚአብሄር ስም በአብ በወልድ በምንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቁ ሲባሉ ሃዋርያት በኢየሱስ ስም አጥምቀዋል ይሄ ማለት ሃዋርያት ተሳስተዋል አያሰኝም::የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተገለጸበት የእግዚአብሄር ስም ኢየሱስ ስለሆነ በስሙ አጠመቁ::ልክ እግዚአብሄር የሚለው ስም በውስጡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን እንደያዘ ኢየሱስ የሚለው ስም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ይዟል
...
ወዴት ወዴት ጥምቀት በኢየሱስ ስም?

Anonymous said...

ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል ከደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሰ/ት/ቤት you said
"ቅዱስ እስጢፋኖስ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን መርጦ ሊያድናቸው ወዶ ብዙ ጊዜ ነቢያትን ልኮላቸው እንደ ነበረ ተርኮ እነርሱ ግን ልበ ዳንዳኖች መሆናቸውን በግልጽ ማንነታቸውን በመናገሩ አይደል የተወገረው?
"......እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁ ያልተገረዘ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ......."እንዲል::ሐዋ7:51
ይህ መቼም ለቅዱስ እስጢፋኖስ ኃጢአት ሆኖ እንዳልተቆጠረበት ይልቁን በሃይማኖት ጸንቶ በመመስከሩ ሰማያት ተከፍተው እስከማየት እንደደረሰ የሚያስተባብሉ አይመስለኝም::
ዮሐንስ መጥምቅ የእፉኝት ልጆች ብሎ መናገሩ ስድብ ይሆን ?
ስድብ ብሆንማ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከሴቶች ከተወለዱት ዮሐንስን የሚበልጠው እንደሌለ በልተመሰከረለት ነበረ::
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድን የዲያብሎስ ልጆች ማለቱ ስህተት ይሆን?"

those who are called አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁ ያልተገረዘ,የእፉኝት ልጆች,የዲያብሎስ ልጆች" የተባሉት, የጌታችን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት የማያምኑ ናቸው

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)