August 15, 2011

የማ/ቅዱሳን መልእክት ምን ያስተምረናል?


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 15/2011/ READ IN PDF)፦ ከዚህ በታች የተቀመጠውና ማ/ቅዱሳን በወርሃዊ ልሳኑ በሐመር መጽሔት ላይ ባወጣው መልእክቱ ማህበሩ አጠንክሮ ለያዘው “ፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ” እንቅፋት በሆኑ ነገሮች ላይ በድጋሚ ማብራሪያ እና አቋሙን አሳይቶበታል። በተለይም “ተሐድሶ” የለም ለሚሉ አካላት መኖሩን ለማሳየት ሞክሯል በዚህ ጽሑፍ። ጽሑፉ “ተስፋ እየቆረጠ ያለው ተሐድሶመሠሪ ኃይል ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ተላላኪዎቹ በኩል ሊነዛ የፈለገው ተራ ማታለያተሐድሶ የለምተሐድሶየሚል ነገርን የፈጠረው ማኅበረ ቅዱሳን ነውየሚለውን አባባል” በጽኑ ይኮንናል። እነዚህ “ተላላኪዎች” ያላቸውን አካላት ማንነትን ግን እንድንገምት ለአንባብያን ትቶልናል። ወይም ከዚህ በፊት የተናገረውን ወደ ኋላ መለስ ብለን እንድንመለከት የቤት ሥራውን ለአንባቢው ሰጥቶታል። በተጨማሪም “በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ውስጥ ያሉ አንዳንድ አካላትተሐድሶ የለምበሚለው ሐሳብ ተስማምተው በአንዳንድ መድረኮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ይህንኑ አስተሳሰብ የሚያጸና አስተያየት ሲሰጡ መታየታቸው” እጅግ አስደንጋጭ መሆኑን ይጠቅሳል። አክሎም “እነዚሁ ወገኖች ሐሰትን ሊነግሩን እውነትንም ሊደብቁን የፈለጉበት ምክንያት በሂደት ግልጽ እየሆነ የሚሔድ ሆኖ ሁሉም አካላት ግን የእነዚህን ወገኖችና የመሰሎቻቸውን አቋም እንዲያጤኑ ማኅበረ ቅዱሳን መልእክት ለማስተላለፍ ተገዷል” ሲል ያብራራል።

ማ/ቅዱሳን የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ ተቃውሞውን በጥናት ላይ በተመሠረተ መንገድ የጀመረ እና ያስፋፋ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን ጉዳዩን የራሳቸው በማድረግ ቤተ ክርስቲያናቸውን መጠበቁን ቀጥለዋል። በቅርቡ አዲስ አበባ ሰ/ት/ቤቶች በይፋ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶን እንቅስቃሴ የተቃወሙ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትም እነርሱን ደግፎ አጋርነቱን ገልጿል።

ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ ርዕስ/ ራስ እና መሪ የሆኑት ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስ “ተሐድሶዎችን አትንኩብኝ” የሚል ይዘት ያለው ጦማር አሰራጭተዋል። በዚህም ታሪካዊ ስሕተትን በመፈጸም በእምነት በኩል ለሚጠረጥሯቸው ሰዎች ማረጋገጫ የሚሆን ትልቅ ዶኩመንት ሰጥተዋቸዋል። በደጀ ሰላም ደረጃ ከተመለከትነው ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያኒቱ አይታው ወደማታውቀው ዝቅጠት እንድትወርድ ያደረጉ መሆናቸው እርግጥ ቢሆንም በፀረ-ኦርቶዶክስነት ጠቅሰናቸው አናውቅም ነበር። አሁን ግን ፓትርያርኩ ሰልፋቸውን ከተሐድሶዎቹ ጋር በማድረጋቸው ከዚህ ጀምሮ የሚኖረን ተቃውሞ ዓይነቱ እና ይዘቱ ይለያል ማለት ነው። ጥብቅናቸው ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለአጽራረ-ተዋሕዶ ነውና። ለማንኛውም ለጊዜው ከዚህ በታች ያለውን የማ/ቅዱሳን ጽሑፍ እንመልከተው።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን     
+++++
ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህንን ጽፌላችኋለሁ 1 ዮሐ.227

ቀን፡ ነሐሴ 6/2003 ..
ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተነጣጠረው ተሐድሶዘመቻ ውጥን ብዙ ዐሥርት ዓመታት ያለፉት ቢሆንም 1992 .. የካቲት ወር ጀምሮ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ተጨባጭ በሆኑ የምስልና የድምፅ ማስረጃዎች ዘመቻውን በማጋለጥ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚያ በኋላተሐድሶስልቶቹን በመቀያየር ሃይማኖታችንን ለማጥፋትና በሌላ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን ካለፈው ነሐሴ 2002 . ጀምሮ ይፋዊ የሆነ ከእነዚህ ሴረኞች ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እንቅቃሴ ጀምሯል፡፡ የሐመር መጽሔት ልዩ እትምን በማዘጋጀት የተጀመረውን አገልግሎት በሌሎችም በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ከካህናቱ ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ፊት ለፊት በተደረጉ ውይይቶች በመታገዝ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ በዚህም ተሐድሶ ምንነት፣ መሠረት፣ ግብና ዓላማ፣ ስልት፣ ያለበትን ደረጃ፣ በሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት ፈጥሮት የነበረውን ቀውስና መዘዝ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ለማድረግ በይፋ በተለያዩ የኅትመት ውጤቶች እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡
ይህንን በማድረግ ሂደት ውስጥ ይህንን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቁን እንቅስቃሴ ለማጨናገፍ የተሐድሶአራማጅ ቡድኖች የተለያዩ ስያሜዎችንና አካላትን በመጠቀምናየተሐድሶእንደ ሸረሪት ድር ሠርቶት የነበረውን የጥፋት መረብ ሳይበጣጠስና በውስጥም በውጭም የሠራው መሠረት ሳይናድ ለማስቀጠል ባለ በሌለ ኃይሉ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ምእመን በእግዚአብሔር ረድኤት የዕለት ከዕለት ተግባሩን ከማከናወን ጋር የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ በንቃት መከታተልና መቆጣጠር በሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡

በዚህ ተስፋ እየቆረጠ ያለው ተሐድሶመሠሪ ኃይል ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ተላላኪዎቹ በኩል ሊነዛ የፈለገው ተራ ማታለያተሐድሶ የለምተሐድሶየሚል ነገርን የፈጠረው ማኅበረ ቅዱሳን ነውየሚለውን አባባል ነው፡፡ ይህን አካሔድ ተራ ማታለያ ነው የምንለው ተሐድሶመኖር ሊስተባበልበት የማይችልበት ደረጃ ላይ መሆኑን ራሱተሐድሶአለመረዳቱ ነው፡፡ መሣሪያ አድርጎ የተጠቀመባቸው መነኮሳትና ካህናት በየፕሮቴስታንቱ አዳራሽ ሲጨፍሩ እየታየ፣ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የቅዱሳንን ገድልና ድርሳን እንደልቦለድ የሚቆጥሩ ጋዜጣና መጻሕፈት እንዳሸን እየተሠራጩ፣ ዕቅድና ስልት አውጥቶ እየሠራ መሆኑን ራሱተሐድሶበሚዲያዎቹ እየገለጸልን፣ ቤተ ክርስቲያን ከዕለት ዕለት እየተፈተነችበት፣ ከጥቅመኞችና የሥነ ምግባር ችግር ካለባቸው በቤተ ክርስቲያንኒቱ አስተዳደር ውስጥ ካሉ አንዳንድ ግለሰቦች ጋር በማበር አያወካት እየታየተሐድሶ የለምየሚለው ልፈፋ የዘገየ ስልትና ተራ ማታለያ ከመሆን አይዘልም፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የታየው ሌላው አስደንጋጭ ነገር በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ውስጥ ያሉ አንዳንድ አካላትተሐድሶ የለምበሚለው ሐሳብ ተስማምተው በአንዳንድ መድረኮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ይህንኑ አስተሳሰብ የሚያጸና አስተያየት ሲሰጡ መታየታቸው ነው፡፡ እነዚህ አካላት ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ ቀደም የችግሩን መኖር አምኖ፣ አሳማኝ ማስረጃዎች ቀርበውለት ውግዘት ማስተላለፉን ዘንግተውና በተለያዩ ዘመቻዎችተሐድሶቤተ ክርስቲያን ላይ የሚወረውረውን ፍላጻ ከምንም በመቁጠር ተሐድሶሴራ ታይቶ እንዳልታየ፣ ተሰምቶ እንዳልተሰማ ሆኖ በምእመናን እንዲታለፍ በመቀስቀሳቸው ብዙዎችን ከማሳዘናቸውም ባለፈ ከፍተኛ ጥርጣሬ አሳድሯል፡፡ እነዚሁ ወገኖች ሐሰትን ሊነግሩን እውነትንም ሊደብቁን የፈለጉበት ምክንያት በሂደት ግልጽ እየሆነ የሚሔድ ሆኖ ሁሉም አካላት ግን የእነዚህን ወገኖችና የመሰሎቻቸውን አቋም እንዲያጤኑ ማኅበረቅዱሳን መልእክት ለማስተላለፍ ተገዷል፡፡

ተሐድሶ የለምእያሉ በተለያየ መንገድ ለሚነዙት ማደናገሪያዎች ማብራሪያና ማስተባበያ እንዲሰጥባቸው የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ያነሡትን ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ማኅበራችንም ያምንበታል፡፡ እነዚሁ አካላት በዚሁ አቋማቸው የመጽናት ፍላጎት ካላቸው ግንተሐድሶበአደባባይ በሠራቸው ፀረ ቤተ ክርስቲያን ዐዋጆች፣ ስድቦች፣ በጋዜጣ፣ በመጽሔትና በመጻሕፍት በሚያሠራጫቸው የተደበላለቁ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮዎች ይስማማሉ ወደሚል መደምደሚያ ሊያደርስ ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በተሐድሶ ላይ የምናደርገውን ዘመቻ የሚያደናቅፍ ለየትኛውም ፀረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በር የሚከፍት በመሆኑ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና፣ አስተምህሮ እና ሥርዐት በመቆም ችግሩን በመቅረፍ ሂደት ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የድርሻውን ለመወጣት ያለውን መንፈሳዊ ቅናት ምን ጊዜም ይገልጻል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ማኅበር ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመበት ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ነው፡፡ የአገልግሎቱ መገለጫ ደግሞ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና መጠበቅና ማስጠበቅ እንዲሁም ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ካልቻልን የምናገለግላት ቤተ ክርስቲያን ወዴት አለች? በመሆኑም የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የያዙትንብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝየሚለው የቅዱሳን መሓላ በእኛና በሁሉም አማኝ ክርስቲያን ደም ውስጥ ማደሩ የግድ ነው፡፡ ስለዚህ በዚሁ ረገድ እውነት እንዲደበቅ፣ ሐሰትም እንዲነገር የሚወዱ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን መገሰጽ፣ መምከርና ከአባቶች ጋር በመመካከር አስፈላጊውን ክርስቲያናዊ እርምጃ በየደረጃው መውሰድ የሁሉም የክርስቲያን ወገን ግዴታ ነው፡፡ በመሆኑምተሐድሶበሚል ሥያሜ በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የረጅም ጊዜ ዕቅድና ስልት የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ለመፈታተን፣ አስተምህሮዋንና ሥርዐቷን ለመናድ በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እና ዕቅድ እየተደረገ ያለው ዘመቻ ያለና ተጨባጭ እውነታ እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን ከመሬት ተነሥቶ ያወራው አለመሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን በአጽንኦት ያሳስባል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፡- ሐመር 19 ዓመት .3 ሐምሌ 2003 .

15 comments:

asbet dngl said...

የዓሣ ግማቱ ከጭንቅላቱ እንዲሉ፡ማንን ይዛችሁ ይሆን የምትታገሉት።
እግዚአብሒር ይርዳችሁ።

Anonymous said...

ለእኔ ራሱን ለዘመነ ጲላጦስ አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ ይመስለኛል። እነሱ እንዴት መክሰስ እንዳለባቸው፤ከማሕበረሰቡ ማውጣት እንዳለባቸው፤ ከመንግስት እንዴት መጋጨት እንዳለበት ሴራውን ቀጥለዋል። ምድራዊ ትጥቃቸውን ጨርሰዋል። አሁን ሰበብ ፈልጎ ለማሰወገድ የመጨረሻዋን ጥይት ለመተኮስ ተዘጋጅተዋል። ማህበሩም የመጣው ቢመጣ አንላቀቅም ያለ ይመስላል።
የእኔ ድርሻ ምን ይሆን? የህሊና ጥያቄ ነው-----------------------

አምላከ ቅዱሳን ይጠብቀን

THE DE..... said...

ተሃድሶ የሚባል ነገር የለም!!! ኦርቶዶክስ መስለው የሚንቀሳቀሱ መናፍቃን ናቸው። ይለወጥና ይሻሻል የሚሏቸው ነገሮች ሁሉ ቢሆኑ እንኳን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ውስጥ አይቀጥሉም። አላማው ለማደስና ለማሻሻል ሳይሆን ለመቀየር ነው። ላይ ላዩን ተዋህዶን የሚያምኑ የሚሰብኩ ይምሰሉ እንጂ በርግጥ አያምኑበትም። ተሃድሶ ሳይሆን መባል ያለባቸው ስውር መናፍቃን ነው። መፍትሔው ግን፦
፩. የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች/ ቅዱስ ሲኖዶስ/ ለቤተክርስቲያን ሲገዳቸውና ለቤተክርስቲያን ቅን መሪ ሲሾምና በቤተክርስትያን ስም ያለቤተክርስቲያን እውቅና የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ መቆጣጠር ሲቻል ነው። ከኢትዮጵያ ህዝብ አናሳ ቁጥር ያለው ክርስቲያን ሆኗል!!! 43% ብቻ ነው የኦርቶዶክስ አማኝ ፤ 57% የሌሎች ድርጅቶች ተከታይና ገና በክርስቶስ ያላመነ ነው። ከ30 እና 40 ዓመት በኋላ ይህ ቁጥር ወደ 25% ክርስቲያን/ኦርቶዶክስ/ እና 75% ሌሎች መሆኑ አይቀሬ ነው ከወዲሁ መላ ካልተበጀለት።
፪. ከሁሉም በላይ በምእመናን ዘንድ ትኩረት ሊሰጠው የሚገበው የተዋህዶን ትምህርት በሚገባ መማርና ማወቅ ነው። ጊዜ ላመጣቸውና ጊዜ ለሚወስዳቸው ሰዎች ሳይሆን ወገንተኝነታችን ለቤተክርስቲያን ብቻ መሆን አለበት።
፫. ማንም ቢሆን ተዋሕዶን የሚጎዳ ሥራ ሲሰራ፣ ትችትን ሲያቀርብ፣ የመንግስት ፖሊሲም ቢሆን መቃወምና እንዲታረም ማድረግ ያስፈልጋል።

Anonymous said...

የእኔ ድርሻ
1ኛ. መጸለይ መጾም መስገድ ማልቀስ መመጽወት አቅሜ የሚፈቅደውን በሙሉ በጽናት እና ከልብ ማድረግ
2ኛ. ከቅድስት ቤ\ክርስቲያናችን ስርዓት ደንብ ቀኖና ዶግማ እራሴን አስገዝቼ ጥሩ ክርስቲያን መስዬ ሳይሆን ሆኜ መኖር
3ኛ. ለክርስትናዬ ስርዓት ደንብ ቀኖና ዶግማ መከበር ከምን ጊዜውም በላይ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ማድረግ
4ኛ. ውሻውን በግ በጉን ደግሞ ውሻ ነው ለሚሉኝ ሁሉ ለእስከ አሁኑ የኑፋቄ አስተምህሮታችሁ እና እንቅስቃሴያችሁ ምንም ቦታ ስለሌለኝ እባካችሁ የጥፋት መረባችሁን ስብስቡና ጣሉት
5ኛ. ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነቴ እስከ ሞት ድረስ ልጋድል የቆረጥኩኝ መሆኔን ተሃድሶ እና አራማጆቹ እንዲሁም ደጋፊዎቹ እና ተሃድሶ እያለ የለም ብለው የማዘናጋት የእምነት ክህደታቸውን የሰጡት በሙሉ እንድያውቁት ማድረግ የኔድርሻ ነው::

አምላከ ቅዱሳን ቅድስት ቤ\ክርስትያናችንን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችንን እና ከምናውቀም ሆነ ከማናውቀው ፈተና እና ጥፋት ይጥብቅልን:: አሜን!!!
ምንዱባን ዘ ሲያትል ነኝ::

Anonymous said...

The exile Sinod is one in support of all these Tehadiso.

Anonymous said...

very bold statment.i think time is coming and every one is gonne be tested.My concern is not for the people but for the clergy.Will the bishops accept or side with aba paulos.As to me as a christin I am ready to die for my faith.No deal.there is no reason to back up this,i know for sure tehadso is inside our church.I want to tell aba paulos and co,we can not deal with our faith.period.

Anonymous said...

Way to go MK. It is time to stand up against all enemies.

እግዚአብሒር ይርዳን !

Anonymous said...

Yes, true. the exile sinod always support them. Like posting in their website whats said against Ethiopian church, legal sinod, mahibere kidusan. They also used to teach laziness in life like aba weldetensae preaching the types of meat we can eat. Are we preachers like chief who used to speak out information about meal. Many preachers these days likes posting their stle of preach in their facebook profile. They show us how stylish they are on the stage. surprising they mix the secular in the spritual or they want to be spritual in the facebook. True, besemay bet tarik silelelen ezihu midir lay ensaikemitew.

Anonymous said...

I have neither been the member nor supporter of mahiber kidusan. But this time I am supporting its idea and I want to express my solidarity with mahiber kidusan. lets stand up and join hands with mahiber kidusan, sunday schools and all fathers, brothers, mothers and sisters who are seving the church genuenly. Aba paulos has lost his credibility and no one is to hear him. he lost his credibility when he allowed gangs beat our fathers the bishops. And all the christans have never given him credibility and nevershall they give him. His woman can not lead the church.

Anonymous said...

Kezih behala Aba Pawulos yemifestmutin tifat kalakomu ke ersachewu mejemer yalebet yimesilegnal ... Yemileyibet gize eyekerebe yimesilal.

Anonymous said...

DS, did get this:-
ሰበር ዜና ፡
by Mistre Tewahedo on Monday, August 15, 2011 at 11:21pm

ሰበር ዜና ፡

መምህር ዘመድኩን በቀለና እና ዲ/ን ደስታ ጌታሁን በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ፡፡

ከክፍለ ከተማቸው ውጭ ተይዘው መወሰዳቸው ሁሉንም አስገርሟል፡፡

ዛሬ ነሐሴ 9 ቀን 2003 ዓም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር ዋና ጸሐፊ ዲ.ን ደስታ እና መምህር ዘመድኩን በቀለ በመጋቤ ሐዲስ? በጋሻው ደሳለኝ ከሳሽነት ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው በዋስ መፈታታቸው ተሰማ፡፡ ገንዘብ ካለ… እንደሚባለው ከ 4 ቀን በፊት ወ.ሮ እጅጋየሁ መምህር ዘመድኩን በሚገኝበት አራዳ ክፍለ ከተማ ዘመድኩን እና ዳንኤል ክብረት እንዲታሰሩላት ጠይቃ የነበረ ሲሆን በህጋዊ መንገድ ካልሆነ እንዲህ ያለ አሰራር እንደሌለው የመለሰላት የአራዳ ፖሊስ ጣቢያ የሚመሰገን ነበር፡፡በአንጻሩ የቦሌው ፖሊስ ጣቢያ ደግሞ አራዳ ክፍለ ከተማ የሚኖርን ግለሰብ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ መኪና ሳይሆን የነበጋሻው አዝማች የሆነው የፊደል ካፌ ባለቤት በሆነው በአቶ ኤፍሬም መኪና ታፍሰው ተወስደው ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊሰ ጣቢያ ሲታሰሩ ከሳሽ በጋሻው ደሳለኝና አቶ ኤፍሬም በወቅቱ መርማሪ ፖሊስ እንጂ ከሳሽ አይመስሉም ነበር፡፡

በስፍራው ተገኝተው የነበሩት የተከሳሾቹ ዘመዶች በሚያሳዝን ሁኔታ በፖሊስ እየተገፈተሩ ሲወጡ ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታማው ኤፍሬምና የአንጾኪያ መዝሙር ባለቤት (በጋሻው አሁን የኑፋቄ ስብከቶቹን እየለቀቀበት ያለ መዝሙር ቤት) አቶ አለማየሁ ገፍታሪዎች ነበሩ፡፡ አሳዛኙ ነገር ፖሊስ መኪና እያለው በግለሰብ መኪና ያለ ክፍለ ከተማው ገብቶ ሰውን እንደ እቃ ግለሰብ መኪና አፍሶ ጭኖ መውሰድ ከተቻለ ዲሞክራሲ ህግ መኖሩ ያጠራጥራል፡፡

ሌላኛው አሳዛኝ ዜና ደግሞ ለነበጋሻው መብት ወረቀት የሚበትነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዲ.ን ደስታን ከቦሌ በግለሰብ መኪና ከስራ ገበታው ላይ ታፍሶ ሲወሰድ ማን ናችሁ ብሎ የሚጠይቅ ሰው መጥፋቱ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ፖሊሶች የሚመጡት ከማእከላዊ ወይም መስሪያ ቤቱ ከሚገኝበት አራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን እሱንም ቢሆንበቅድሚያ ጥበቃዎችን ባለስልጣናቱን አነጋግሮ እገሌ የሚባል ሰው እንፈልጋለን ብለው ነበር፡፡ ዛሬ ግን በወይዘሮ እጅጋየሁ ሳቅ ታጅቦና በአቶ ኤፍሬም መኪና ታፍሶ ከቦሌ ድረስ በመጡ ፖሊሶች ተይዞ ሲወጣ አገሪቱ መንግስት አለባት ወይ ዲሞክራሲስ አለ ወይ? ያስብላል፡፡

የህግን ነገር ጠንቅቆ የሚያውቀው ዘመድኩን ያለ ክፍለ ከተማችን ቦሌ ድረስ የመጣንበት ምክንያት ለምንድን ነው? የሚል ጥያቄ በማንሳቱ ሲፈለጉ እንዲቀርቡ በሚል ማታ ላይ ሊፈቱ ችለዋል፡፡ እንቁ መጽሔት ላይ ለጥያቄ ሲደወልለት ፊቴን ወደ እግዚአብሔር መልሻለሁ ያለው በጋሻው በፍልሰታ ፋይል ይዞ መታየቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ማለቱ ይሆንን?

የቦሌው ፖሊስ ጣቢያ የነበጋሻው ምኩራብ ለሆነው የአቶ ኤፍሬም ሆቴል ፊደል ካፌ እና ሎቢያቸው ከሆነው ካልዲስ ካፌ ብዙም የማይርቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Anonymous said...

እኔ ከማህበረ ቅዱሳን መልዕክት ባሻገር፤ በቤተክርስቲያን ዙሪያ እየተሽከረከረ ያለው ንፋስ ብዙ ጥያቄዎችን እንዳነሳ አድርጎኛል። በ16ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተከሰተውን ነገር እያስታወሰኝ ነው። የቁርጥ ቀን ልጆች፤ አባቶች፤እናቶች የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። አውሬው ምን ያሕል ደም እንደሚያስፈልገው አላውቅም እንጅ በዙሪያዋ እያገሳ ነው። ብዙ ፈሪዎችን በዙሪያዋ አሰልፋል። ራሷ ያሳደገቻቸውን ልጆች አስታጥቆ ልኮባታል። እርግጠኛ ነኝ አያሸንፏትም ፤ ግን ማድረግ ስላለባቸው በደም ለመጨማለቅ ይቅበዘበዛሉ። ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ ለማነካከስ ራቸውን ጠፍጥፈው ያዘጋጁአቸውን አስመሳዮች በእየ ደረጃው መድበው ጨርሰውልናል። በአባቶቹ ስራ የሚያፍር ትውልድ አዘጋጅተውልናል። ያባቶቹን ስራ ማንጓጠጥ፤ማጣጣል፤ ጭቃ መቀባት አዋቂነት መስሎ የሚሰማው ሰው ልከውልናል። በሐሳባቸው በጀርባ ሆነው ፍልሚያውን ለማየት እየቋመጡ ይገኛሉ። ትናንት የጠበቃት አምላክ ዛሬም እንዳለ የዘነጉ ይመስላል። ሰልፉ ከማን ጋር እንደሆነ ከሕሊናቸው የተሰወረ ይመስላል። ቤቱን ሁሌም ይጠብቃል። ነገር ግን የሚጸኑትን ለማየት ለጊዜም ዝም ያለ ይመስላል። መንበሩ ላይ መቀመጥ፤ ስለፈቀደ የመሰላቸው ወዮላቸው። የንጽሑን ደም አፍሳሾች ወዮላቸው። የሕዝበ ክርስቲያኑ ደረቅ እንባ በደከመ ሰውነት ላይ ፈሶ አይቀርም። አምላክ በቅርቡ ያብሰዋል።
አምላክ ሆይ ለኔም ጽናቱን ስጠኝ፣ በቤትህ እኖር ዘንድ?

asbet dngl said...

ይህ የመጤ ሃይማኖት ሰርጎ ገብነት ችግር ለተዋህዶ ሃይማኖታችን የመጀመሪያ ግዚ ችግርዋ አይደለም። በኛ እድሜ ዘመን ልዩ ያደረገው ግን ለሃይማኖታቸው የሜሰየፎ ቆራጥ ጥቁር ለባሽ አባቶች ጥቂት ሆኖ የመገኝቱ ጉዳይ ነው።ስለዚህ ወንድሞቸ ሆይ ትግላችሁ
ቀላል አይመስለኝም ስለዚህ መላና እቅድ አክሉበት። የኣርተዶክስ ሃይማኖት ጠባቂዋ ጸሎት ነው።ምመናን በያለንበት ሆነን በጾለት እንበርታ።አምናለሁ ጊታ ከኛ ጋር ሁኖ ይዋጋልናል። አሜን

lelr said...

ebakachohe deje selam samen america yalo SANEBATE TEMEHERTE BATOCHE ega anede enedenehone selameradan hasbbe enedakafelone betarago?EMABATACHEN aserate agareshen tabekate

ኤልሮኢ ዘ ገቺ said...

ከ አዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶችና ከቆራጥ የሃዋሳ ምዕመናን ብዙ መማር ስቻል አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን የነሱ አጫፋሪዎችና ካሴት ገላጻ ሰጪዎች አልታጡም ለምሳሌ ጅማ ና አከባቢዋን ብትመለከቱ በጣም ያሳዝናል በሐምሌ ገብረኤል ዕለት የበጋሻው ምላሽ ነው ተብሎ የወጣ ካሴት የሚሸጥ ግሩፕ ከሰ/ት/ቤት አስተባባሪው ጅምሮ ሲሸጡ ነበር በጣም ከሚያስደስተው የምዕመናን ጥያቄ ና ከተራው ምዕመን ያልተሻሉ አሰተባባሪና አሻሻጮች የምዕመኑ ንቃተ ህሊና ምን ያህል እንደጨመረ ለማየት ችያለሁ:: በየክፍለ ሀገራቱ ባሉ ሰ/ት/ቤቶች ብዙ መስራት ይጠበቃል ከህዘቡ ወገን ግን በጣም ተነሳሽነቱ በጣም ጥሩ ነው "ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሄር መታዘዝ ይበልጣል" የቅዱሳን አምላክ ለሁላችንም ፅናትን ይስጠን፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)