August 11, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁለት መግለጫዎች ሰጠ


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 10/2011)፦ ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ እና አንገብጋቢ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁለት መግለጫዎች ሰጠ። ቀደም ሲል በዕቅድ ከተያዘለት ጊዜ (ነሐሴ 23 - 24 ቀን 2003 ዓ.ም) ቀደም ብሎ ሐምሌ 30 እና ነሐሴ1/2003 ዓ.ም በተጠራ ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አስቸኳይ ጉባኤ ውጤት እና......
ውሳኔዎች ዙሪያ እንዲሁም አባ ሰረቀ ብርሃን በሚመሩት ድረ ገጽ ላይ ስለሚወጡ “የሐሰት ማስረጃዎች” ጉዳይ የሚያትቱት እነዚህ መግለጫዎች በማኅበሩ ድረ ገጽ ላይ የተስተናገዱ ናቸው።
  • የሥራ አመራር አስቸኳይ ጉባኤ ውሳኔዎችን በተመለከተ ያለውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ፤
  • ከማኅበሩ እንደተገኙ ተደርገው የተዘጋጁትን “የሐሰት ማስረጃዎች” በተመለከተ የተዘጋጀውን ጽሑፍ ከዚህ በታች ይመልከቱ

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሠሩ የሐሰት ሰነዶችን አስመልክቶ ከማኅበሩ ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፡፡ 
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሥር ተዋቅሮ በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለቤተ ክርስቲያን በማበርከት ላይ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በመመራት ሕጋዊ በሆነ መንገድ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ የሚገኝ ማኅበር ነው፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዕድገትና ልማት የማይፈልጉ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን የማኅበሩን መልካም ስም በማጥፋት አገልግሎቱን ለማሰናከል በየጊዜው ይጥራሉ፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማኅበሩን ስም ለማጥፋት አመች ነው ብለው ያሰቡትን የሐሰት ሰነድ የማዘጋጀት ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከዚህ በፊት በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የግንቦት ወር ልዩ ዕትም “የማኅበረ ቅዱሳን የ25 ዓመት ዕቅድ” ብለው ያዘጋጁትን የሐሰት ሰነድ አስመልክተን እንደገለጽነው ሁሉ አሁንም ሁለት የሐሰት ደብዳቤዎች በማኅበሩ የመቀሌ ማዕከል ስም ተዘጋጅተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ መካነ ድር ተለቅቀዋል፡፡
 
እጅግ በጣም የሚያሳዝነው የሐሰት ሰነዶቹ መዘጋጀት ሳይሆን እነዚህ በከባድ ወንጀል ሊያስጠይቁ የሚችሉ የተጭበረበሩ ሰነዶች የቤተ ክርስቲያኒቱ መምሪያ ነኝ በሚል ተቋም መካነ ድር ላይ መለቀቃቸው ነው፡፡ ከሐሰት ሰነዶቹ መካከል አንዱ የተሐድሶ መናፍቃንን ዝርዝር የሚገልጽ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የመቀሌ ማዕከል የሒሳብ ሪፖርት አስቸጋሪ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን የሐሰት ሰነድ አስመልክቶ ድርጊቱ እንዲጣራና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለመንበረ ፓትርያርክና ለሚመለከታቸው ሁሉ የሚያቀርብ ሲሆን በሐሰት ሰነዶቹ ስማቸው የተነሱ አካላትም ድርጊቱ የማኅበሩ አለመሆኑን እንዲያውቁና ምዕመናንንም እውነቱን እንዲረዱ ይህ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መካነ ድር የተለቀቁት ሁለቱም የሐሰት ሰነዶች በቁጥር መቀጽቤ 99/2003 ዓ.ም እና መቀጽቤ 100/2003 ዓ.ም “ለማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ክፍል” በሚል አድራሻ የተላኩ ናቸው፡፡
ነገር ግን ከመቀሌ ማዕከል መዝገብ ቤት ቀሪ ሆነው የተገኙት እውነተኞቹ ደብዳቤዎች በማኅበረ ቅዱሳን የመቀሌ ማዕከል በቁጥር መቀጽቤ 99/2003 ዓ.ም እና በቁጥር መቀጽቤ 100/2003 ዓ.ም በቀን 05/09/2003 ዓ.ም በማዕከሉ የሰባኬ ወንጌልነት ተቀጥረው ሲያገለግሉ ለነበሩ /አሁን የIT ምሩቅ ናቸው/ ግለሰብ የሥራ ስንብትና የሥራ ልምድ መስጠትን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ መመልከት እንደሚቻለው የሐሰት ሰነዶቹም ሆነ  እውነተኞቹ ደብዳቤዎች ቁጥራቸው ተመሳሳይ ነው።
በቀጣይነትም በሰነዶቹ ላይ ማጭበርበሩ የተደረገው በማዕከሉ መዝገብ ቤት ከተገኙት ደብዳቤዎች ሳይሆን ምን አልባትም ከባለጉዳዩ እጅ ከወጡት ደብዳቤዎች ሊሆን እንደሚችልም አንባቢ ያስተውል፡፡ ምክንያቱም የማኅተሞቹና የፊርማዎቹ አቀማመጥ ተመሳሳይነት የላቸውምና አልተጭበረበሩም ብለን እንዳናስብ ያደርገናልና፡፡ ወደ ዝርዝር ጉዳዮቹ ስንገባ ደግሞ፣
1. በአድራሻው ላይ የተጠቀሰው የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት እንደ ክፍል ያልተዋቀረ እንደሆነ ይታወቃል። በአድራሻው የሚመጡለት ደንዳቤዎችም “ለማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ አገልግሎት” ተብለው ይደርሱታል እንጅ “ለማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ክፍል” ተብሎ በአድራሻ አይጠራም። ከዚህ በፊት በመካነ ድራችን የተለቀቁትንና በአገልግሎቱ እየወጡ የሚታተሙትን የመጽሔተ ተልዕኮ መጽሔቶችንም መመልከት ይቻላል።

2. በቁጥር መቀጽቤ 99/2003 ዓ.ም የተጻፈው የሐሰት ሰነድ “በቀን 17/07/2003 ዓ.ም በቁጥር አአ/ልዩ/05/2003 ዓ.ም 11 ገጽ አባሪ አድርጋችሁ በጻፋችሁልን ደብዳቤ ተንተርሰን የሰራነው ሥራ…” ብሎ ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ጽ/ቤት ለመቀሌ ማዕከል የተላከ ለማስመሰል ይሞክራል፡፡ ነገር ግን በማኅበረ ቅዱሳን ስም የሚወጡት ማናቸውም ደብዳቤዎች ቁጥራቸው ማቅ በማለት የሚጀመሩ ናቸው። በተጨማሪም የማኅበሩ ዋናው ማዕከል ጽ/ቤት ለመቀሌ ማዕከል ልኮታል ተብሎ የተጠቀሰው ደብዳቤ የተጻፈበትን ቀን ስንመለከት፤ 17/07/2003 ዓ.ም የዋለው ቅዳሜ ዕለት ሲሆን በዚህ ቀን የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልግሎት የማይኖርበት ዕለት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ምን አልባት ካላንደር ሳይዙ ጽፈውት ይሆን? የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያው በየጊዜው ከማኅበሩ ደብዳቤዎች ይደርሱታል። አአ/ልዩ/05/2003 ዓ.ም የሚለው ቁጥር አስተውሎት ውስጥ ሳይገባ በመካነ ድሩ በችኮላ መለቀቁ ማኅበሩን ለመክሰስ ካለው የግለሰቦች ጉጉት የተነሣ ይሆን?

3. በቁጥር መቀጽቤ 99/2003 ዓ.ም በተጻፈው የሐሰት ሰነድ ሒሳብ ክፍልንና ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍልን የሚመለከት ምንም ጉዳይ ሳይኖረው ወደ ሒሳብ ክፍልና የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ግልባጭ መደረጉ ለምን ይሆን? ለዚያውም በማደራጃ መምሪያው መካነ-ድር እንደተገለጠው የተደበቀ የስለላ ሥራ ከሆነ እንዴት ለእነዚህ ክፍሎች ግልባጭ ሊደረግ ይችላል? ሒሳብ ክፍልስ ከሕዝብ ግንኘነት አገልግሎቱ ጋር ምን ግንኙነት ይኖረው ይሆን? እነዚህ ጥያቄዎች በጥብቅ ሊመለሱ የሚገባቸው ናቸው።

ምን አልባት ለማጭበርበር በሚደረገው ሙከራ የአንዱ ደብዳቤ ሐሳብ ከሌላው ደብዳቤ ላይ ተቀያይሮባቸው ይሆን? የየትኛው ደብዳቤ ሃሳብ ለየትኛው ክፍል ግልባጭ መደረግ እንዳለበት ፊደል የቆጠረ የሚያስተውለው ነው።

4. በማኅበሩ የአገልግሎት ክፍሎች የሚመደቡት አባላት በሰበካ ጉባኤ ወይም በሰንበት ትምህርት ቤት የታቀፉ መሆን እንዳለባቸው በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 6/ለ ተጠቅሶ ሳለ “የሰ/ት/ቤቶችን በተመለከተ፣ የማኅበሩ አባላት በሙሉ በየሰንበት ትምህርት ቤቱ በአባልነት እንዲያገለግሉ ተደርጓል፤ እየተሰራበት ይገኛል።” የሚለው ዓረፍተ ነገር የማኅበሩ አባላት የሰ/ት/ቤትና የሰበካ ጉባኤ አባላት አይደሉም የሚለውን የአባ ሠረቀን የሐሰት የክስ ሐሳብ ለማጽናት ይሆን?
ማኅበረ ቅዱሳን በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር የሆነው በራሱ ጥያቄ አቅራቢነት ነው፡፡ ይኸውም አባላቱ በሰ/ት/ቤቶች ታቅፈው እንዲያገለግሉለት ካለው ጽኑ ፍላጎት የተነሣ እንደሆነ ግንዛቤ ውስጥ ሊገባ ያስፈልጋል፡፡
የሐሰት ሰነዶቹን አጠቃላይ ሐሳብ ለመረዳት ለሚሞክር ሰው፥ አጭበርብሮ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ እንዲሁም የፀረ ተሐድሶ መናፍቃንን ዘመቻ ለማጨናገፍ የሚደረግ ሴራ መሆኑን ማኅበሩ አያጣውም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳንና ሌሎች ማኅበራትም በሚያደርጉት የፀረ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው ከተለዩት ግለሰቦች ውጭ የማንም ስም በግልጽ ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ የተሐድሶ መናፍቃንን ምልክቶች ግን ይጠቁማል፡፡ ከተሰጡት መረጃዎች እንዲሁም ከምልክቶቹ ምእመኑ እየተረዳው እንደመጣ ይታመናል፡፡

የተሐድሶ መናፍቃኑ እንቅስቃሴ ዘርፈ ብዙ የሆነ፣ በብዙ ሚሊዮኖች በጀት ተመድቦለት፣ በዓላማ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመበርዝና ለማጥፋት እጅግ ተምረዋል ተብለው በሚገመቱ ሰዎችና በግዙፍ ድርጀቶች የሚመራና የሚታገዝ ቤተ ክርስትያኗን የሚያናጋ ነው።

ነገር ግን ትግሉ ከተጀመረ ጀምሮ አንዳንድ ግለሰቦች እንቅስቃሴውን ከግለሰቦች ጋር እያያዙት ይገኛሉ፤ የተሐድሶ ኑፋቄ ዘመቻንም እያፋጠኑት ይገኛሉ። ይህንን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማስተጓጐል ብሎም የምእመኑን ትክክለኛ ትኩረት ለማሳጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ እንደሆነ እናምናለን፡፡

ምን አልባት ማኅበረ ቅዱሳን ስም አጥፊ ነው፣ የአባቶችና የሊቃውንት ከሳሽ ነው የሚለውን የአንዳንዶችን ክስ ለማጠናከር ይሆን? አንባቢ ይመርምር።

እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያን እና ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

12 comments:

Anonymous said...

Great start MK.....

Anonymous said...

selam lekulikimuu yisebha EGZIABHER minew wegen beka sele mahebre kidusan becha hone ende negeru ere sera seru ers beres setechekachehu gezew hede menafeku bereta enanete sele mk becha hone sebketu kale egziabeher kere eko zim belachehu tselotena sera seru ahun betam techemelaleke negeruu mk ebakachehu legnam selam setun lelaw degemo abakachehu be wechi alem lalut ye mahebru abalat temehert setuu betam maheberun eyasewekesu yalu wegnoch alu betely be GERMEN maheberu teru sera eyesera nebr andand geleseboch gin mahebrun be me emenu mehakl teru amelekaket endayenor yemeyadergu aluna lezhi guday mefethe mefelg yasfelegal elalhu selamun yametalin ethiopia hagerachenn betkereseteyanachenn yitebikiln amen

Gebre Z Cape said...

This is how you remove the confusion from each and every member. Well done MK, please update us very crucial informations. I much liked the way you also admitted mistakes. This is a civilised organisation where you admit mistakes and also stand for the truth. Keep doing the good job MK.

Thanks Dejeselam, it is because of you we are update by the church informations and issues. But make sure that there is no hatredness in your reports, blogs, use polite words (show christianity to other blogs which they only know how to insult Fathers and organisations).

Incase you want to see directly from Mk website check http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_frontpage&Itemid=1

http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=721&Itemid=1

GOD is always GOD!!

Anonymous said...

Thanks be to God! Well done MK! This is the MK I know! Proud of you. May God bless you more.

Anonymous said...

Thanks be to addystGod, Anjete kibe teta!!!!!!!!!

Orthodoxawi said...

To Dejeselam:-

Thanks for the update!

But your second link points to "Emebetachin's Tinsae". Which is a very nice timely article to read.

The correct link about Abasereke's false documents is on:
http://www.eotcmk.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=720:2011-08-09-09-11-02&catid=1:-&Itemid=18

Since the MK guys are changing their website quite frequently, it will be better if you can copy and paste the second article together with the pdfs here on your blog so that everyone will know the reality.

Ewnet ena Nigat eyader yigeltal!!!


Good job MK! Egzer yitebkachihu!

We are learning from you!

Melkam said...

ምስጋና ለቸሩ እግዚአብሔር ይገባልዋል እናመስግነው
“ወድሞች በህብረት ቤኖሩ መልካምነው”
በጣም ነው የሚገርመኝ መቼም የ አባልነት ፎር ሞልቼ አባል የሆንኩባት
ቀን የ ተመሰገነች ትሁን ማን እንደ ማሕበረቅዱሳን በውነቱ ማንነው
እንደዚህአይነት አሰራር ያሳየን ?ተጣልቶም ተጨቃጭቆም በግልጽ ተወያይቶም
መፍታት ይሄ ደግሞ ከተማሩ የእግዚአብሔር ሰዎች የሜጠበቅ ነው፤
ዳ/ን ዳኒኤልም ከዜህ መንጋመለየት ፍቅር ማጣት እንደሆነ ብዙ ጌዜ ትነግረን
ነበር ፡ ባለፈው ሰሞን አንድ ወንድሜ ይህን ግርግረ ሰምቶ “ መሐበረ ቅዱሳን በደሜውስጥ
ነው “ብሎ የለወይ ለምን እንዴህያደርጋል ቤለኝ ?እንደ ትንቤት ታያለህ ወንድሞቻችን መንፈሳዌ
ናቸው ይፈቱታል ፤ደግሞም በየገዳማቱ፤ በየበረሐው የሚጸልዩለት እና የሚማልዱለት የአባቶ
የቅዱሳኑ ፀሎት አለ አይለየውም ብየውነበር ፤ሌሎቻችንም ብንሆን ይን በህይወታች ልንጠቀምበት ይገባል
በጣም የማይረሳኝ የጠቅላላ ጉባዩ ጊዜ የ መጨረሻዋ ቀን የምትሰበሰበዋ ገንዘብ የጸሉተ አጣን ተብሎ
ይሁሉ ማህበሩን ከእዲህ ያለፈተና ይጠብቀዋል ድክመት ሲኖር ችግር ሲመጣ የቤተክርስቲያን አምላክ
ይራዳዋል መንፈሳዌ አገልሎት ነውና
ደጀሰላሞችን አመሰግናለሁ

gonderew said...

GOD BLESS M.K.
THAT IS THE WAY GOD TEACH US HOW TO SOLVE PROBLEMES WHEN IT HAPPEN BETWEEN BORTHERS AND SISTERS.AND YOU SHOW WHO WE ARE /THIOPIAN ORTHODOX CHURCH MEMBERS/
FOR NEXT TIME DON'T LEAVE ANY PROBLEMS UNTIL SUNSET ACCORDING TO OUR HOLLY BOOK.WE TO PROTECT OUR CHURCH NOT OUR PERSONALITY.
I WANT TO SAY MANY THANK YOU FOR DEJE SELAM.KEEP DOING THE SAME JOB .YOU ARE THE ONE GIVE INFORMATION FOR OUR MEMBERS.
GOD PROTECT OUR CHURCH AND ETHIOPIA
AMEN

lele said...

kebere mesegana yegebawe macheam behone YaDENEELE MAREIAME melega kaga gara selahona fataname benore bacharenato enashanefalane.baamerare laye yalachohe mene endamel alawekem enbayee selamata makatale alechelem..........

tad said...

Should there be an age limit for sunday school members?
I know there is one in Ethiopian orthodox church "KALE AWADI".

Anonymous said...

Tew tenqeq bel wogen! Yalefe sihitetin lememeles fitsum wodajinetihin atiglet. ke kegnim ke giram satil qetil zim bileh! yiheninu degmo post adrigewuna gud yifla. rrrrrrrrrrrmmmm.

Anonymous said...

Thank You.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)