August 9, 2011

የሚዲያዎች ትኩረት ማ/ቅዱሳንን ይጎዳዋል ወይስ ይጠቅመዋል?

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 9/2011/ TO READ IN PDF, CLICK HERE)፦ ማ/ቅዱሳን ላለፉት 19 ዓመታት ድምፁን አጥፍቶ እና አንገቱን ሰበር አድርጎ አገልግሎቱ ላይ ብቻ በማተኮር የዘለቀ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘሩ ትችቶች እና ስም ማጥፋቶች በጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ መጻሕፍት እና ድረ ገጾች በማስተናገድ ላይ ያለ ማኅበር ነው። የሚዲያ ሽፋኑ በፊትም የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው መልክ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ ግን አያውቅም ነበር። አገር ውስጥ በሚታተሙ ጋዜጦች እና መጽሔቶች እንዲሁም ድረ ገጾች በሰፊው ስማቸው ከሚነሣው መካከል፣ ምናልባት ከመንግሥት ቀጥሎ፣ ማ/ቅዱሳን የመሪነቱን ቦታ ይዟል።

ይህ የሚዲያ ሽፋን በማኅበሩ ወዳጆች ዘንድ የተቀላለቀ ስሜት ፈጥሯል። ግማሾቹ “የሰው ዓይን ውስጥ ገባን” ዓይነት ስሜት ሲሰማቸው ሌሎቹ ደግሞ “ሚዲያ ላይ መውጣት ራስንም ለመገምገም እና ተጠንቅቆ ለመሥራት ይጠቅማል እንጂ እንደ ክፉ ንግርት (bad omen) መታየት የለበትም” ይላሉ። ትናንት በ“ኢትዮ ሚዲያ” ድረ ገጽ ከተለጠፈው (“ማህበረ ቅዱሳን፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስቤተ ክርስቲያን እና ኢትዮጵያ”) ከሚለው ጽሑፍ ጀምሮ በየጋዜጦቹ እና መጽሔቶቹ የተጻፈው ብዙ ነው። ለጊዜው በኢትዮ-ሚዲያ ላይ የወጣውን እንድታነቡ እንጋብዛለን።

ጽሑፉ ላነሣቸው ሐሳቦች ተመስጋኙም ሆነ ተወቃሹ ጽሑፉን ያዘጋጀው አካል ነው። የደጀ ሰላም አቋም ጽሑፉ ውስጥ እንደሌለበት እያስታወስን እንድታነቡት የምናደርገውም ጽሑፉን በመደገፍ/ በመቃወም ሳይሆን ከላይ ላነሳነው እና እናንተ ደጀ ሰላማውያን ሐሳባችሁን እንድትሰጡበት ከምንፈልገው ጉዳይ ጋር በመገናኘቱ መሆኑን እንጠቁማለን። በዚህ አጋጣሚም እጃችሁ ከሚገቡ ጋዜጦች እና መጽሔቶች መካከል የቻላችሁትን “ስካን” በማድረግ ለመላክ ለምትችሉ በሙሉ የትብብር ጥያቄያችንን እናቀርባለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን

18 comments:

Anonymous said...

Not bad. Lacks Biblical support to make it more meaningful.
As individual view can help accomodate in discussions but cant be a way of life.


Because the writers, in some points, is short sighted.

Berta.

ሰናይ said...

ደጀ ሰላሞች ወቅታዊ ዜናዎችን ለማቅረብ የምታደርጉት ጥረት የሚመሰገን ነው። እግዚአብሔር ያበርታችሁ።

ጥያቄያችሁ እንዴት ነው? ሚዲያዎች ማቅ ላይ ትኩረት አድርገው ቢዘግቡ ማኅበሩ ይጠቀማል ወይንስ ይጎዳል ነው ወይንስ ማቅ ሚዲያዎችን ተጠቅሞ ራሱን ቢያስተዋውቅ ይጎዳል ወይንስ ይጠቀማል ነው?

ሚዲያዎች አንድን ተቋም ትኩረት የሚያደርጉበት የተለያየ አላማ ይኖራቸዋል።

1. የተቋሙን እቅውና እና መልካም ስም ተጠቅሞ ገበያ ወይም ትኩረት ለማግኘት።በሀገራችን ይህ በዝቶ እየታየ ይመስለኛል።ለኢ/ያ ድህነት እና ኋላቀርነት ቤንን ተጠያቂ ካላረገ የተናገረ ወይም የጻፈ የማይመስለው ትውልድ እየበዛ ነውና ከዚህ አንጻር ግለሰቦች ወይም ተቋማት ማቅን በተመለከተ አሰሱንም ገሰሱንም ሊዘግቡ ይችላሉ። ይህ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ማኅበሩም ሊያቆመው ወይም ሊያግደው አይችልም።
2. የራስን የቤት ሥራ ሌላ እንዲሰራ የሚፈልግ ቡድን ቤንንም ሆነ ማኅበሩን እንደማማሰያ ለመጠቀም ካለው ፍላጎት አንጻር አብዝቶ ሊዘግብ ይችላል።ለምሳሌ መንግስት በ1997 በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ በአንዳንድ ቦታዎች ሽንፈት የደረሰብኝ በማቅ ምክንያት ነው ብሏል። የራሳቸውን የቤት ሥራ በአንድም በሌላም መወጣት ያቃታቸው ተቃዋሚዎች ቤን እንዲህ ባታደርግ ኖሮ፤ማኅበሩ እንዲህ ቢያደርግ ኖሮ እያሉ መክሰሳቸው የተለመደ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ማኅበሩ ነቅ እንዳይገኝበት ጠንቅቆ መስራት ነው ያለበት። ሁለት ማሌያ እየቀያየሩ የሚጫወቱ የማኅበሩ አብላት ራሳቸውን ማጥራት አለባቸው። ማኅበሩም መንግስትን ለማስደሰት ያልሆነውን ሆኛለው ማለት የለበትም። ከትውልድ እና ታሪክ ተጠያቂነትም ለመዳን ከተቋቋመለት አላማ አንጻር ድርሻውን መወጣት አለበት።
3. አጽራረ ቤ/ን እና ቤ/ን ከችግሮቿ ተላቃ የማይፈልጉ ቡድኖች ስለማቅ ብዙ ሊዘግቡ ይችላሉ። እነዚህ ቡድኖች አላማቸው ዘርፈ ብዙ ነው። ማኅበሩን ማዳከም፤ መልካም ስሙን ማጉደፍ እና በአባላቱን እና በምዕመናን ጥርጣሬን መፍጠር ትኩረታቸ ነው።ሌላው እና ትኩረት እያገኘ ያለው አላማቸው ለማኅበሩ የቤት ስራዎችን መስጠት። ማኅበሩ ያንን ሲሰራ እነሱ ሩጫቸውን በድል ማጠናቀቅ።ተሃድሶዎች የቤንን መዋቅር መቆጣጠር፤ እነ አባሰረቀ ጵጵስና እነ በጋሻው ደግሞ ገንዘብ ማግኘት....
4. የተወሰኑ ቡድኖች ማኅበሩን በደንብ ካለማወቅ የተነሳ እንደጠላት የሚያዩት አሉ።በዚህ ዙሪያ ማኅበሩ ራሱን በሚገባ ቢያስተዋውቅ እና ጠላትን ቢቀንስ!

ማኅበሩ የሚገኘውን የሚዲያ ሽፋን ተጠቀሞ ራሱን ቢያስተዋውቅ ችግር ያለው አይመስለኝም። ይህ ግን ሲደረግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የሆነን ቡድን ለማስደሰት ተብሎ መዘላበድ እና የራስን ሀሳብ የማኅበር አድርጎ መቅረት አለበት።

ሰናይ ነኝ።

123... said...

ማህበረ ቅዱሳን ከያዘው የ ሰው ሃይል ስብጥር ሁሉንም ብሄረሰቦች የያዘ መሆኑ ብስለቱ እና ለ ሃገር ካለው ታማኝነት አኳያ ቤተክርስቲያንንም ሆነ ሃገርን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ መነሳት ያለበት አሁን ነው::ችግሩን ከመፍትሂ ጋር ማፈላለግ ያስፈልጋል::ሁሉም ደግሞ አንድ ሃሳብ ሊሆን አይችልም::ድሮም አለም የዳነችው በ ትንሽ እውነት በሚናገሩ ሰዎች መሪነት ነውና

Anonymous said...

ግሩም ጽሑፍ ነው።ቃለ ሕይወት ያሰማልን።ጸሐፊ ተጨማሪ ጥቆማዎችን እንደዚህ ቢያቀርቡ ማኅበሩ በደስታ የሚቀበል ይመስለኛል።ችግሩ አቡነ ጳዉሎስንና መንግስትን የሚቃወም ዉሳነ ለመስጠት ይቸገራል።ቢሰጥ እንዳሉት የሚከፈለዉን መስዋዕት ከፍለው ያለጊዘው ያጠፉታል።ስለዚህ ለሁሉም ጊዘ አለውና ጊዘ እየጠበቁ ይመስለኛል እንጂ ችግሩ ግልፅ ነው፡

Seifu said...

የጽሑፉ ባለቤት የሆንክ ወንድሜ የችግሩ መንስኤ የሆነው ራስ መታመሙ ነው ባልከውና ከታች ያለነው እኛ ራሳችንም የታመምን መሆናችን እስማማለሁ። ስራችን ተቀራርቦና ተመሳስሎ ከመስራት ይልቅ ተራርቆና ተለያይቶ ሆኖአል፤ እውነቱን ለመናገር ከተፈለገ ማህበሩ የኣካሄድ ችግር አለበት ባልከው ላይ 100% እስማማለሁ። ይኸውን፡
በተለይ “እገሌ ተሐድሶ ነው” የሚል ወሬ ሲሰማ እንደምን ብሎ ከወደቀበት ጉድጓድ ከማንሳት ይልቅ መቅበር ይበዛበታል፣ ጅምላ አስተሳሰብንም ይዞ መጓዝ እንደ መጥፎ ልማድ አይቼበታለሁ። አንድ ያልተማረ ሰው ከወደቀ ብቻውን ይሞታል፤ አንድ ምሁር ሲወድቅ ግን አእላፍን ይዞ እንደሚጠፋ አርዮስ፣ ሉተር፣መሐመድ… ምሳሌዎች ሲሆኑ በቅርቡ ተሐድሶዎች ናቸው ብለን ያባረርናቸው ወንድሞቻችን ደግሞ መምሰል ጀምረዋል። አባባሌ በቤታችን መናፍቅ ይኑር ማለቴ ሳይሆን “ጉድ-ባይ” ለማለት ጥበብ ይኑርበት ነው ምክንያቱ ተጣልተህ መለያየትና ተስማምተህ መለያየት ከፍተኛ ርቀት አላቸው።
ስለዚህ የሆነውንና ያልሆነውን ተሐድሶ እያል ብዙ ጠላቶች ከማምረት ይልቅ አካሄዳችንን በማስተካከል ቤተ ከርስቲያናችን ማልማትና መጠበቅ ይኖርባናል፤ የታመመውን ራስ ለማከም ደግሞ መጀመርያ ከታች ካሉት አካላት ጥምረት ያስፈልጋል እላለሁ። አለበዚያ አጥሩን ዘለህ መግባት የሚቻል አይመስለኝም፤ ይልቁንም ሞትን መጋበዝ ይመጣል፡>፡

lele said...

mahabro malse lamasetatte akemo kalawe tero nawe ena yameiasagage lamedia geza masetato lalawen sera yagotetale ena demesone atefeto manefasawe sera besara elalaho kawedase kentome yadenale

EHETE MICHEAL said...

ደጀ ሰላሞች አመሰግናለሁ ስለ ማህበሩ በሌሎች የተጻፈውን ስላስነበባችሁኝ። በውጭ ሀገር ያሉ የማህበሩ አባለት ሁሉም ወያኔ ወይም ወያኔ ደጋፊዎች አይደሉም ግን በትምህርት እየተባለ የሚመጡት ግን ብዙዎቹ ወያኔና ደጋፊዎቹ ናቸው። ይሄንንም በተግባር ያረጋገጥኩበት አጋጣሚ አሁን በቅርብ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ከተለያዩ የማህበሩ ትልልቅ ወንድሞች ጋር የመወያየት የመጠየቅ እድሉ ነበረኝ እንደነሱ አይነት ሰዎች ማህበሩን በዚህ በስደት ዓለም ለወንጌል ከመገዛት ይልቅ የመንግስትን ጉዳይ ለማስፈፀም የሚሰሩ እስኪመሰለኝ ድረስ ታዝቢያቸዋለሁ ስለዚህ ያ የምናውቀው በእሳት ውስጥ እየተፈተና በአገልግሎት ያለውን ማህበረ ቅዱሳን በውጪ ያሉ አባላትን መልሶ መልሶ ቢገመግማቸው ጥሩ ነው። ማህበሩን እግዚአብሄር ይጠብቅ።

Anonymous said...

Senay, Your oppinions were fine. However, excessive abreviation for the name (Mahibere Kidusan) and unknown name(Ben) look irritative. If you did that purposely, I think you are self conservative in the name of the country and religion.

Anonymous said...

betam betam diniq teshafi egiziabher yistilin

ሰናይ said...

Dear last anony,

Thanks for the comments and sorry for the confusion! ማቅ=ማኅበረ ቅዱሳን ቤን=ቤተክርስቲያን

Senay

Anonymous said...

"ማ/ቅዱሳን እና የሚዲያዎች ትኩረት፤ ይጎዳዋል ወይስ ይጠቅመዋል"" በማለት ያነሳችሁት ጥያቄ በጣም ወቅታዊ እና አስፈላጊም ነው:: ባልጽፍበትም ሳስበው የነበረ ነገር ነው::

በኢትዮሜዲያ የወጣውን ጽሁፍ በጥሞና አነበብኩት:: ጠቃሚ ትንተናዎች ተሰጥተውበታል:: ከተቆርቋሪነት ስሜትም የተጻፈም ይመስላል:: በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያለውንም ችግር ለመዳሰስ ሞክሯል:: ነገር ግን በቤተ-ክርስቲያን እየተደረገ ያለውን ነገር ለሕዝብ ማውጣት የሚለውን ነገር ጠቃሚነቱ እና ብልህ አካሄድ መሆኑ ብዙም አልታየኝም:: አንደኛው ምክንያት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ተቆርቋሪ አይድለም:: ስለሆነም ዜናዊ ባልሆነ መልኩ ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ ወገኖች በመኖራቸው ነው:: ሁለተኛው ምክንያቴ ደሞ የህወሀት መንግስት በማህበረ ቅዱሳን ላይ ጥርስ እንደነከሰ አና ለማዳከም ወይ ለመበታተን የተለያዮ ድንጋዮችን ለመፈንቀል ማሰብ ላይ እንደሆነ መገመት አያስቸግርም:: የቤተ-ክርስቲያን ችግሮችን ወደ ውጪ ወጥተው ወደ ቁጣ የሚያመራ ግርግር ቢጤ ቢፈጠር ህወሀት ነገሩን በማጣመም ፖለቲካዊ መልክ በመስጠት (ስብሀት ነጋ እንደተናገረው) እነሱ ""ህጋዊ"" ወደሚሉት ርምጃ እንዲሄዱ ያን ማድረግ ካልቻሉም የተወሰኑ ያይናቸው ቀለም ያላማራቸውን እና በጠላትነት የሚያስቡአቸውን መርጠው የማሰር ርምጃ ሁሉ ሊወስዱ ይችላሉ:: ያ ደሞ ለማህበሩ ሌላ ስራ ነው የሚሆነው:: በዚህ አጋጣሚም ቤተ-ክርስቲያናችንን ሊያዘምኑ የሚፈልጉ ወገኖች በአባ ጳውሎስ እገዛ የበለጠ ሊጠናከሩ ይችላሉ:: መተንፈሻ እና ማመዛዘኛ ጊዜ ስለሚያገኙ በቤተክርስቲያን ላይ ተጨማሪ ጥቃት ለመውሰድ ጊዜ ያገኛሉ:: ከህውሀት መንግስት ጋርም የጥቀመኝ ልጥቀምህ ነገር ሊኖርም ይችላል:: ስለዚህ በዚህ ሰዕት እንዲህ ያለ ነገርን ወደ ህዝብ መውሰዱ ጠቃሚ አይመስለኝም::

ይልቅ በቤተ-ክርስቲያናችን አመራር በተለይም በአባ ጳውሎስ ይሁንታ እና ትጋት በቤተ-ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረስ ያለውን ጥፋት በዘዴ እና በብልህነት የቤተክርስቲያን አባቶችን ጳጳሳትን እና ምዕመናንን በማስተባበር በዚያው በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ እነዚህን ሀይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የማድረግ ጠንከር ያሉ ርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል:: ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ቀናዒ የሆኑ እምነታቸውን የሚወዱ ወጣቶችን በትጋት እና በቁርጠኝነት ቤተ-ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ በብልሀት መስራት ይቻላል::ቤተ-ክርስቲያን በጥቃት ጊዜ የሚያስረሩ ልጆችም አሏት የሚል ስሜት መፈጠር መቻል አለበት:: በነ አባ ጳውሎስ ዙሪያ አድራጊ ፈጣሪ ሆነው ቤተ-ክርስቲያንን እያመሱ ያሉ ወገኖች ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የሆነ ርምጃ መወሰድ አለበት:: ማህበሩ ይዘዝ ማለቴ አይደለም:: ማህበሩ የእምነት ማስፋፋት ስራውን ይስራ:: በቤተ-ክርስቲያን ላይ የተደቀነውን ፈተና ለምዕመናን ያስረዳ ያሳውቅ ያስተምር:: ያኔ ቤተ-ክርስቲያናችን ተጠቃች የሚል ስሜት የሚሰማው ምዕመን ድንግት ብድግ ብሎ የሚያደርገውን ያደርጋል:: ከዚሁ ጋር ማህበሩን የመንግስት መገልገያ ለማድረግ በግለሰቦችም ይሁን በቡድኖች ሙከራ ሊደረግ ስለሚችል እሱንም በንቃት በመከታተል በማህበሩ አሰራር እርምት እንዲያገኝ ያስፈልጋል:: ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ትንተና በሰጡብት አንድ ዶክመታሪ መሰል ዝግጂት ላይ ዲያቆን ዳንኤል ተካቶ ስለ ላሊበላ ትንተና ሲሰጥ ይስተዋላል:: ስለ ላሊበላ ውቅር ቤተ-ክርስቲያን ያለው ምንም ችግር የለበትም:: ነገር ግን የዶክመንታሪው አላም ፕሮፓጋንዳ እንደመሆኑ(እኔ እንደዛ በየ ነው የማምነው) በእንደዛ አይነት ቅንብር ውስጥ የዳኔል መኖር ምዕመናኑን ሊያወናብድ ይችላል::

ከዛ በተረፈ በደጀ ሰላም ላይ ስለተነሳው ጥያቄ ማህበረ ቅዱሳን የሜድያ ሽፋን ማግኘቱ ይጠቅመዋል ወይ ለሚለው ጥያቄ በዚህ ሰዐት የሚጠቅመው አይመስለኝም:: ምናልባት እንደዛ ማድረግ የሚያስፈልግበት ጊዜ ይመጣ ይሆናል:: አሁን ግን የሚጠቅመው ማህበረ ቅዱሳን ድምጹን አጥፍቶ በራሱ መገናኛ ብዙሀን እየተጠቀመ ከውጥ ያሉትን ችግሮች በመቅረፍ ላይ ቢያተኩር እና እምነትን በማስፋፋት እና ምዕመናንን በመድረስ በተለይም አግልግሎት በደንብ ባልተስፋፋባቸው አካባቢ ቢያተኩር ይሻል ይመስለኛል:: የተጠናከረ አገልግሎት ያለባቸውንም የበለጠ አጠንክሮ መያዝ ያስፈልጋል:: አመሰግናለሁ::

Miskin girl said...

selifu.......አንድ ያልተማረ ሰው ከወደቀ ብቻውን ይሞታል፤ አንድ ምሁር ሲወድቅ ግን አእላፍን ይዞ እንደሚጠፋ አርዮስ፣ ሉተር፣መሐመድ… ምሳሌዎች ሲሆኑ በቅርቡ ተሐድሶዎች ናቸው ብለን ያባረርናቸው ወንድሞቻችን ደግሞ መምሰል ጀምረዋል። አባባሌ በቤታችን መናፍቅ ይኑር ማለቴ ሳይሆን “ጉድ-ባይ” ለማለት ጥበብ ይኑርበት ነው ምክንያቱ ተጣልተህ መለያየትና ተስማምተህ መለያየት ከፍተኛ ርቀት አላቸው። good point but Menafik Menafik new lensu fit mestet tiru aydlewm teqelaqelew Emnet ybelaslahu Lhulum Geta yerdan WELDIT AMELAK TERDAN Mk bertu

solomon said...

እነደእኔ ሃሳብ የማህበሩን ስራ ያጎላዋል የበለጠ እንዲሰራ ያበረታታዋል እንጂ ጉዳት ያለው አይመስለኝም
ስህተት ካለም ሊታረም ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ በእግዚአብሄር ፈቃድ ጥሩ ስራ ይሰራል ብየ አምናልሁ

tad said...

After analysing all recent articles on MK, Mulugeta Hailemariam's interview, Sibhat Nega's comment, Mesfin Negash'e analysis, Daniel's article and the one on ethiomedia, I honestly pray for the wellbeing of senior MK founders.
Additionally MK will not be the same from this time on as it was different fifteen yrs ago.
It is time to read Abune Gorgorious' books line by line.

Anonymous said...

ሰላም ለሁሉም !

እንደ እኔ አመለካከት /እምነት:ማኅበረ ቅዱሳን በሚዲያ ላይ መውጣቱ ጠቃሚም ጎጂ ጎን ይኖረዋል:: ጥቅሙ ሥራውን ማገዝ በአገልግሎቱም መሣተፍ ለሚፈልጉ በር ሊከፍት ይችላል:: ሌላው ጎን ደግሞ ከሚገባው በላይ "ትኩረት" ሊስብ ይችላል:: የማይገባና የተጋነነ "ግምት"/ expectation ጥሩ አይደለም:: ይህም ማኅበሩና አባላቱ ይዘውት ከተነሱት : አሁንም እየሄዱበት ካለው የሃይማኖት መንገድ :ጥንታዊት: ታሪካዊትና ብሔራዊት : ሐዋርያዊት ተዋሕዶ ቤ/ክንን የማገልገል: ወንጌል የማስፋፋት ተግባር እንዲዛነፉ/ እንዲዘናጉ/ ሊያደርግ ይችላል::
ትልቁና መሰመር ያለበት መስመር ግን የፖለቲካ ወይም ሌላ አጀንዳ ያላቸው አካላት (ገዢው መንግስትም ሆነ ተቃዋሚዎቹ) ይህንን ማኅበር "ለቀቅ" እንዲያደርጉት ነው:: የማኅበሩ አባላት ሰዎች እንደመሆናቸው መጠን የሚሰሩት ሥህተት ሊኖር እንደሚችል መታወቅ አለበት:: አጥፊዎች ካሉ በግል በሚፈጽሙት ሥህተት/ "ጥፋት" በግል ሊጠየቁ ይችላሉ :: ከዚያ ውጭ ጅምላ ፍረጃ ተገቢ አይደለም::
ማኅበሩ አሰራሩን ለሁሉም ግልጽ በሆነ መንገድ ከቤተክርስቲያን አባቶች ጋር በመሆን ይሥራ :: የማኅበሩ አባላትና ምዕመናንም ሥራዎችን በመንፈሳዊ ሚዛን ብቻ እየመዘናችሁ ማለትም: በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት :እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ : ለሀገር ለወገን በሚጠቅም : ቤ/ክን በሚያሳድግ : ፍቅርና አንድነትን በሚያመጣ መልኩ ... እንድትሠሩ እማጸናለሁ::
ኃ/ገ

gonderew said...

I WANT TO SAY SOME FOR MY ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO CHERCH FAMILIES AND MEMBERS OF M.K.
1. DON'T SCARE FOR WHAT YOU ARE DOING BECAUSE GOD IS WITH US.
2.PLEASE READ MATT;5:11-16.
3.I KNOW IF SOMEBODY GET MEDIA COVER FRIQUINTLY,THAT MEANS MORE PEOPLE GIVE ATTENTION.HERE THERE ARE THINGS:
A.EVERYBODY KNOWS YOU AND YOUR JOB.
B.YOUR OBJECTIVE WILL GET TIME TO REACH WHERE YOU WANT TO REACH.
C.IN THE CASE OF ETHIOPIA OUR ENEMIES WANT TO USE THIS OPPORTUNITE TO MAKE CONFLICT WITH THE GOVERNMENT.BUT DON'T WORRY THERE IS A TRANSPIRENECY IN OUR JOB.ARYONE AND ANYTIME CAN COME AND SEE WHAT WE ARE DOING.IF THEY HAVE ESSUE ABOUT WHAT WE ARE DOING.
4. WE HAVE TO PRAY.THIS KIND OF SITUATION WILL LEAD US TO BAD CONDITIONS,BECAUSE I SAW HIDEN HANDS OF GOVERNMENT IN OUR WAYS.
I WANT TO UNDERLINE 'MK IS THE ONE WHO PROTECT ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH,AND ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH MEANS THE BASE OF ETHIOPIA . THERE FOR THIS THREE FIGURES HAVE STRONG BOND TO EACH OTHER.OUR ENEMIES KNOWS THIS BOND,THAT IS WHY THEY ARE IN MARATON TO BREAK THIS STRONG BOND.BUT THEY CANN'T. BECAUSE OUR BOND COMES FROM GOD NOT FROM HUMAN.
5.WE HAVE TO KEEP WHAT GOD TELL US/M. MISALE 7:1-3/.
IN GENERAL WHOEVER AND WHATEVER SAID ALWAYS WE ARE THE MEMBER OF ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH AND EVERYBODY KNOWS WHAT ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO CHURH MEANS.
GOB BLESS OUR GREAT COUNTRY ETHIOPIA AND OUR RELIGION ORTHODOX TEWAHIDO.
AMEN

Ye Tewahedo said...

Dear EHETE MICHEAL, selam le anchi yihun!

I felt so sorry when I read your comment. You are doing similar mistakes like many others who are trying to categorise members of MK based on their political involvement. You have no enough evidence for your judgement. With how many of them have you discussed? Hope you will not say that you have discussed with "senior" members in all the continents (USA, AFRICA, EUROPE, CANADA, ...). It is always a problem when we judge just from a very little observation.

As you have done, I had also the chance to talk to brothers and sisters including founders of MK who are living in the diaspora. I also know many of the Executive Committee members in MK's foreign branches. Based on my observation, your allegation is not acceptable.

Also don't forget that members have the right to support any political party except those who are chairs of MKs branches (centers), as can be read here:-
http://mahiberekidusan.org/portals/0/mk/PressRelease.pdf

As christians, we should care for the spirituals lives of any one...whichever party he/she supports...from any part of the country, or if possible from any part of the world at large.

Our target shall be to safe guard our Holly Church from any sort of attacks. We should stop writing divisive comments. That will benefit no one ... but those who are waiting to see the bad days of our church.

Pray for the welbeing of our Church!

Katefahu yikrta adrgilign/adrgulign!

Tanash yemhon wendimachihu!

Orthodoxawi said...

Thanks MK!
Well done!

http://www.eotc-mkidusan.org/site/images/stories/pdfs/Release.pdf

Des sitlu!

Telatachihu diablos ena esu yaderebachewu hulu yiferu!

Egziabher ketemesasay fetenawoch hulu yitebkachihu!

Misgana Le Amlakachin!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)