August 7, 2011

(ሰበር ዜና) ማ/ቅዱሳን በይቅርታ እና በዕንባ ችግሩን ፈቷል፤

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 7/2011)፦ ቀደም ሲል በዕቅድ ከተያዘለት ጊዜ (ነሐሴ 23 - 24 ቀን 2003 ዓ.ም) ቀደም ብሎ በአስቸኳይ እንደተጠራ በተገለጠው የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አስቸኳይ ጉባኤ የቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003 ዓ.ም ስብሰባ ማበሩ በገጠሙት ውስጣዊ ችግሮች ላይ በጥልቅ ከተወያየ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በቅርቡ በደጀ ሰላም ብሎግ ቀጥሎም በተለያዩ መገናኛዎች በተሠራጨው የዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጽሑፍ ላይ እንዲሁም ያንን ተከትሎ በተጣለበት “ዕግድ” ላይ ሰፊ ውይይት ያደረገው ሥራ አመራሩ ዲ/ን ዳንኤል በአካል ቀርቦ እንዲያስረዳ ተደርጓል። ሥራ አመራሩም በበኩሉ የጣለበትን ዕግድ አንሥቷልዲ/ን ዳንኤልም በጽሑፍ ለሰጠው ሐሳብ በጽሑፍ ማስተባበያ እንደሚሰጥ ተናግሯል። የሥራ አመራሩ አባላት ዲ/ን ዳንኤልን፣ ዲ/ን ዳንኤልም የሥራ አመራር አባላቱን ይቅርታ ጠይቀዋል። 

ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ሌሊት ድረስ በተካሄደው በዚህ ረዥም እና እልህ አስጨራሽ ስብሰባ ላይ ከሁሉም ማዕከላት የተገኙ ተወካዮች፣ አባቶች እና በአገልግሎቱ ውስጥ ባላቸው የረዥም ዘመን አገልግሎት አሁን ለገጠመው ችግር መፍትሔ የሚጠቁሙ ወገኖች የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይም ዲ/ን ዳንኤልን ጨምሮ ሌሎቹ አባላትም በዕንባ ለማኅበሩ አገልግሎት መቃናት እና መሳካት የበኩላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል ተብሏል።  

113 comments:

ለውጥአየሁ said...

ተመሰገን ጌታዬ እንዲህ ነው ክርስትና። አሁንም በለጠውን ቸር ያሰማን

Mekane Eyesus said...

ይህ በእውነቱ መላካም ዜና ነው:: ደጀ ሰላሞች እናመሰግናለን!
ዲ. ዳንኤልም ይህን ማድረጉ ለሌሎች አአስተማሪ ነው : የተስተካከለና የማያወዛግብ ማብራሪያ እንዲጽፍ እግዚአብሄር ይርዳው::

Anonymous said...

ተመስገን

ወንድሞቼ ኮራሁባችሁ ። ብትጣሉ ብትከራከሩ ውስጣችሁ በፍቅራቸሁ የተሞላ እንደሆነ እውን ነው። ሁላችሁ ብትሮጡ ለተዋህዶ ነው ። እግዚአብሄር ይጠብቃችሁ። ውድድድ አደርጋችኋለሁ።

Anonymous said...

ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው፡፡ መዝ 133 ቁ. 1

ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ምሕረትና ቸርነት የባሕረዩ የኾነ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የተመሰገነ ይኹን፡፡ አኹንም የተሰወረውንና በገሃድ የመጣውን ፈተና ኹሉ በቸርነቱ አርቆ አንድነታችንን እንዲያጸናልን ቤተ ክርስቲያናችንንም ሰላም እንዲያደርግልን የእናቱ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ ከኹላችን ጋር ይኹን፡፡ እሰኪ የበለጠ ቸር እንዲያሰማን በሱባዔው ተግተን እንጸልይ ለዚኽም የፈጣሪያችን ቅዱስ ፈቃድ ይኹንልን፡፡ አሜን፡፡ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ምሕረትና ቸርነት የባሕረዩ የኾነ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የተመሰገነ ይኹን፡፡ አኹንም የተሰወረውንና በገሃድ የመጣውን ፈተና ኹሉ በቸርነቱ አርቆ አንድነታችንን እንዲያጸናልን ቤተ ክርስቲያናችንንም ሰላም እንዲያደርግልን የእናቱ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋ ከኹላችን ጋር ይኹን፡፡ እሰኪ የበለጠ ቸር እንዲያሰማን በሱባዔው ተግተን እንጸልይ ለዚኽም የፈጣሪያችን ቅዱስ ፈቃድ ይኹንልን፡፡ አሜን፡፡

Anonymous said...

እልልልልልልልልልል
እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን::

መጋጨት በሁሉም ያለ ነው:: እንዲህ ያለ ፈጣን የመነጋገር ባህል እና ስህተትን የማረም ጸጋ ግን ከላይ ካልሆነ ከዚህ ምድር አስተሳሰብ የራቀ ነው::

እንዲህ ለመወያየት እና ለመተራረም የበቁትን ወንድሞች፣ አባቶች፣ እህቶች፣ እናቶች አምላክ በጸጋ ይጠብቅልን::

አምላክ አሁንም ማህበራችንን ከፈተና ይጠብቅልን:: እንድነነቃ የሚሰጠንንም ፈተና በትዕግስት እና እንዲህ በመመካረ ለማለፍ ይርዳን::

ለመኅበሩ መሞት እና ለቤተክርስቲያን መዳከም የሚጥሩ ወገኖቻንንም ልቦና ይስጥልን::

Anonymous said...

Egziabher Yimesgen.

Anonymous said...

I am so happy to this breaking news about the solution of MK and Dn. Daniel. Dn. Daniel Egiziabehere yistilen, yeagelegilote zemenehenem yarzimlen.

Anonymous said...

sile hulum egiziabher yimesgen melikam ye filiseta tsomi yihunilin

Anonymous said...

ስላደረገልን ሁሉ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን::
ግን ወገኖቼ ጥፋትን ሁሉ በአንድ ሰው ጥፋት በመጠቅለል ቤተክርስቲያንን እና የማኅበሩን አገልግሎት መጠበቅ ይቻላልን? የሁለተኛው ጥፋት ከቀደመው እንዳይብስ መድኅኔዓለም ይርዳን::

EW said...

ሁሉ ያደረገ እ/ር ብቻ ነው የረዳንን እ/ር ኣመሰግናለሁ

EHETE MICHEAL said...

እግዚአብሔር ይመስገን ይህንን ዜና ያሰማን አሁንም በፍለሰታ በቤተክርስቲያናችን ላይ የተጋረጠው ፈተና ይቆም ዘንድ በርተተን እንትጋ። እልልልልልልልልአእልልአለልልልልልልልለእለአልአልልልል

Anonymous said...

Cher werie yasemachihu!

Anonymous said...

Elelelelelel

Ye Qidusan Amlak Egziabher Yetemesegene yihun. Wendmochachin Egziabher yitebikachihu. Endezih libachinin asarfut enji.

Anonymous said...

ደግ ዜና ነውና ደስ ቢያሰኝም እናንተ ግን ወገንተኝነት አይታይባችሁ፡፡
ማ/ቅዱሳንም ራሱን ይፈትሽ ለእናት ቤ/ክ ከሆነ የቤ/ክ ሥርዓት እያዛቡ ካሉት ገለልተኞች ራሱን ያርቅ፡፡ ደሞስ በየአጥቢያው ያሉት አባላቱ አይደል ማኅበር የሚያሰኙት ስለዚህ እምነታቸውን በስም ሳይሆን በምግባር ይግለጡት ፡፡ ለሌሎቹም አርአያነቱ በመልካም ብቻ እንዲሆን አባላትን በአገልግሎት ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸውም በያሉበት ምስክር እንዲሆኑ ጥንቃቄ ያድርግ ፍቅር ሁሉን ያሸንፍ የለ የቀደመው ፅናትና ፍቅር እንዳይቀዘቅዝ ከፊት ይልቅ ይትጋ ስራው እንጂ አፉ ይህን አድርጌአለሁ አይበል ምንም እንኳን ተቃዋሚ ቢበዛ የሚዋጋለት እግዚአብሔር ስላለ በመንፈሳዊ አይን ሁሉን ይይ

Anonymous said...

Ejig betam des yilal, engdih min enilalen negern hulu lebego yihon zend ersu akenawenew enilalen enji.

Wendimoche hoy Dn. Daniel yaneachew netiboch( ke gil negeroch wuchi sile mahiberu re'ey, alama,.....) gin wesagn mehonachew ena be enersum Mahiberu bedenb binegagerbet melkam new elalehu.

Egziabher Mahiberachinin Yibark.

Tesfahun, Arizona, N.America

Anonymous said...

ይህን ያሰማን አምላክ የተመሰገነ ይሁን።

Anonymous said...

Bravo MK. That is exactly what need to be done. You are always teaching us, even during your down times. Take the lesson and go forward. May God bless your service!

Anonymous said...

"...በዕለቱ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይም ዲ/ን ዳንኤልን ጨምሮ ሌሎቹ አባላትም በዕንባ ለማኅበሩ አገልግሎት መቃናት እና መሳካት የበኩላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል ተብሏል።"
እያነበብኩ ቆይቼ እዚህ አረፍተ ነገር ላይ ስደርስ ከአይኔ ባላወቅሁት መልኩ የማያቋርጥ እንባ ዱብ ማለት ጀመረ:: ማህበሩን እጅግ በቅርብ ርቀት የሚሰራውን በጎ ስራ ሁሉ በሚገባ አውቃለሁ ብል ማጋነን አይሆንብኝም... በተለይም በግቢ ጉባኤያት ላይና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለማጠናከር የሚያረገው ጥረት ከምንም በላይ ያስደስተኛል:: በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ከማህበሩ ጎን በመቆም የነበረኝን ጠንካራ ተሳትፎ ሳስታውስና አሁን ደግሞ ከመሳተፍ ይልቅ ከጥግ ሆኜ ስራቸውን ብቻ ማድነቅ መሆኑ እጅግ አንገበገበኝ:: አሁን ግን ከጥግ ሆኖ መከታተል ያበቃል:: ወደ ውስጥ ገብቼ የሚጠበቅብኝን ማረግ እንዳለብኝ ዛሬ ወሰንኩ:: ወንድሞቼ በርቱ ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ሁሉ በሙስና ወንጀል: ባለመተማመን: የስራ ቅልጥፍናን በማጣት: አዳዲስ አሰራሮችን ከማከናወንና ከድህነት ለመውጣት ከማሰብ ይልቅ ሁሌ ወደ ልመና በመሄድ: ያገራችን ባህል ባልሆነው እምነት በማጉደልና በመሳሰሉት ሁሉ ለተተበተቡ ተቋማት ጥሩ ምሳሌ መሆን እንችላለንና እንበርታ: ስራችንን ሁሉ በጣም ግልጽነት በተሞላበትና በመነጋገር እናከናውን:: ለወደፊቱም ቢሆን አይደለም የዳንኤልን አስተያየቶችና ስትራቴጂዎች ቀርቶ ለሰው በአይን የማይገባ አባል እንኳን ሀሳብ ቢሰነዝር ሳንንቅ በጉባኤ ተወያይታችሁ ያን ሰው በሚያሳምን መልኩ ወይ ውድቅ ማረግ ወይም ሃሳቡን መተግበር ያስፈልጋል:: አንድ ያረገን ሐይማኖት ቢሆንም በአላማ መመሳሰላችን ደግሞ የበለጠ ያጠናከረን ይመስለኛል:: ከማህበሩ አላማዎች አንዱ ወጣቱን ለሐይማኖቱና ለሐገሩ ታማኝ ዜጋ አድርጎ መቅረጹ ጠቀሜታው ለቤተክርስቲያን ብቻ አይደለም ለሐገርም ጭምር ነው:: ስለሆነም ይህን በቀና መንፈስ የሚመለከቱና ለሐገራችን እድገት ከልብ የሚመኙ የሌሎች እምነት ተቋማትና መንግስትም ጭምር ከጎናችን ሊሆኑ እንደሚችሉ መዘንጋት የለብንም ዋናውና ሀገሪቱን የሚጠቅመው አላማ ያገናኘናልና:: በማህበሩ ውስጥ እጅግ በሙያቸው አንቱ የተባሉና አሁንም ከማንኛውም ዜጋ በተሻለ ሊያበረክቱ የሚችሉ እጅግ በርካታ ሰዎች አሉ:: በፍቅር ሁሉን ማረግ ይቻላልና ብዙ ልታሰሩን ትችላላችሁ:: በዚህ ደግሞ አይደለም ለኢትዮጵያ ቀርቶ በምዕራባውያኑ ዘንድ እድገቷ ለማይፈለገው ለመላው አፍሪካ መትረፍ እንችላለን ብዬ አስባለሁ::

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ:: ከምዕራባውያኑ ለሰው በማይታይና በረቀቀ መንገድ እንዳናድግና እዛው ባለንበት አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆነን እንድንቀርና እርስ በርሳችን እየተበላላን እንድንኖር ከታሰርንበት ቁልፋቸው እግዚአብሔር በጥበቡ ኢትዮጵያንም ሆነ መላዋን አፍሪካ እንድንላቀቅ ያብቃን::

ትቢያው ወንድማችሁ ከጀርመን

Anonymous said...

"በዕለቱ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይም ዲ/ን ዳንኤልን ጨምሮ ሌሎቹ አባላትም በዕንባ ለማኅበሩ አገልግሎት መቃናት እና መሳካት የበኩላቸውን...."

ሰይጣን ለክፉ ያሰበዉ የመከፋፈያ ሴራ የፍቅር ጦርና ቀስት ሆኖ ወደራሱ ሄደበት። እንኳንም ተጣልተናል፣ ተከራክረናል፤ ባንለያይና ባንከራከር ኖሮ ይህን የመሰለ ፍቅር ሳናይ በዉስጥ ለዉስጥ መኳረፍ በየፊናችን እንቀጥል ነበርና።
ልክ አባቶች "አዳም ሆይ እንኳንም ቅጠሏን በልተሃል፣ ባትበላ ኖሮ የሰዉ ዘር የአምላክ እናት፣ የአምላክ ልጆች... አይባልም የፍቅርህን መጠንም ሳናዉቅ ለዘላለም እንኖር ነበር" እንደሚሉት ያለ። ያላስተዋልናት አረም አሁን በኪነ ጥበቡ ተነቅላለች።


መልካም ጾም ለሁላችን።

Anonymous said...

አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
እንዲህ ነው ክርስትና
በጣም ደስ ይላል::

"ዲይብሎስን ተቃወሙት:ከእናንተም ይሸሻል::
ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ:ወደ እናንተም ይቀርባል::"

ይህን የአምላክ ትዕዛዝ ለፈጸማችሁ ወንድሞችና እህቶች ታላቅ እርቅን ስላሰማችሁን ቃለ ሕይወት ያሰማልን::

Anonymous said...

ይህንን ብሎግ የማየው ሌሊት 3፡26 ወደ ቤተ ክርስቲያን ስሄድ ምን ላይ ተደርሷል ለማለት ደጀ ሰላም እንደዚህ የምሥራቹንም ስትነግሪን የተሰበረ ልባችን ይጠገናል። እንባችን ይታበሳል አሁን ጾመ ፍልሰታ ነው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ ተነስቻለሁ ሰሞኑን አምላኬን በመለመን በመወትወት ነው ያሳለፍኩት አሁን ግን በፊቱ የምቆመው ለማመስገን ነው።
ወጥመዱ ተሰበረ ሰይጣን አፈረ ክብር ለእርሱ ለአምላካችን ይሁን።

Anonymous said...

Thanks to the almighty God, we were expecting this news. This is exemplary for all Ethiopian institutions!! We are exhausted by separatist ideas and deeds!!Hope this will be an opportunity to strengthen ourself.

Thanks brothers & sisters if this is really true and from heart!!!

Anonymous said...

Thanks to the almighty God, we were expecting this news. This is exemplary for all Ethiopian institutions!! We are exhausted by separatist ideas and deeds!!Hope this will be an opportynity for us to confess and strengthen ourself.

Thanks brothers & sisters if this is really true and from heart!!!

Ruth ke SouthDakota said...

BE EWNET EGZIABIHER TALAK NEW!! BEZIH ACHER KEN WIST YIHIN MELKAM ZENA KASEMAN YE EMEBETACHININ TSOM KETSOMIN KETSELEYIN KALEKESIN YEABATOCHACHININIM LIBONA ENA ANDEBET AND YADERGILINAL ENA SEBER ZENAWIN KANEBEBKU BEWALA ENEM ALEKESIKUGN SILEWNET ENBERTA HULACHINIM BEYALENIBET SUBAEWIN KE EGZIABIHER MELS YEMINAGEGNBET KE EMBETACHIN BEREKET YEMINAGEGNBET YADIRIGILIN AMEN!!

Anonymous said...

GETA HOY TEMESGEN!

Anonymous said...

Oh this is so great! The coming days are going to be blessed. This is so much like christian.

ATHNATIUS (CA) said...

Very good. However, don't forget the people. We need answers to the questions he raised. They need to be corrected ASAP for it is very crucial. There is a saying "Alebabsew biyarsu barem yimelesu." We are waiting for the answers and the corrections. God bless.

Anonymous said...

Thanks God, Telat teshenef. Hulem Fiker yashenefal. Melkam arayanet new. Keahun behuala tsome, tselot, sigedet. Melkam subae, tsome felseta lehulachenem yehun. Dingel mariam betekirstianachenen tetebeke, tibarken!!

ርብቃ ከጀርመን said...

እግየአብሄርይመስገን በጥዋቱ ደስየሚል ዜና ነው ያሰማችሁን እንዲህ ነው ክርስትና ተፋጭቶ ተናጭቶ ለመልካምነገር አንድመሆን! የመጣውን የፈተና ማእበል እንኩዋን ተወጣችሁት ዳኒ ይቅርታ መጠየቅ የትልቅሰውነት ምልክትነው እግዚአብሄር ይባርክህ እናንተም የማህበሩ የስራ አመራሮች ከተሰጣችሁ አስተያየት በመነሳት ጥፋታችሁን ለማስተካከል ተዘጋጁ የተዋህዶ አምላክ እግዚአብሄር ይመስገን ይልቅኑም የፍቅር እናት ወላዲተ አምላክ ከናንተጋር ትሁን!

Anonymous said...

God is always with them to those who are working for the church from heart!!! No words to express my feelings. Thanks to God!!

Anonymous said...

ተመስገን አምላኬ ላንተ ምን ይሳንሃል እመቤታችን ምስጋና ይድረስሽ

የእኛም እምባ ይጨመርበት

Anonymous said...

Kiber Mesegana Lemedhanialem!

Anonymous said...

belete senbet endih yale zena endasemachihun cher yasemachihu

Anonymous said...

egzioo yemeyasbel new mejemereyam bihon lefugera endetechekachekachehu minem teyake ayasfelegewem dejeselam yemahebre kidusan nat endatebal zede keyesachehu neber doron seyataleluat bemechagna talewat alu ato mels zenawii enkuanem tarekachehu gin lemein kebtekehenetem keleloch wendemoch kene tezetawem gar atetarekum hulum and ye ethio ortodox lijoch ayedelu???

S.G said...

የራሔልን እንባ ያበሰ አምላከ እስራኤል ሃገረ ኢትዬጵያን እና ቤ/ክርስቲያንን እንዲሁም ማህበረ ቅዱሳንን እንባቸውን ያብስልን::
የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት የእግዚአብሔር ቸርነት ሃገረ ኢትዬጵያንና ቤ/ክርስቲያንን ይጠብቅልን!!

Anonymous said...

የራሔልን እንባ ያበሰ አምላከ እስራኤል ሃገረ ኢትዬጵያን እና ቤ/ክርስቲያንን እንዲሁም ማህበረ ቅዱሳንን እንባቸውን ያብስልን::
የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት የእግዚአብሔር ቸርነት ሃገረ ኢትዬጵያንና ቤ/ክርስቲያንን ይጠብቅልን!!

Anonymous said...

የራሔልን እንባ ያበሰ አምላከ እስራኤል ሃገረ ኢትዬጵያን እና ቤ/ክርስቲያንን እንዲሁም ማህበረ ቅዱሳንን እንባቸውን ያብስልን::
የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት የእግዚአብሔር ቸርነት ሃገረ ኢትዬጵያንና ቤ/ክርስቲያንን ይጠብቅልን!!

Desalew said...

oh amlakae!!!!.elelelelel!!. endet des yilal!!!!!.

የብስራት እይታ Bisrat Gebre's View said...

ተወያይቶ ችግሮችን መፍታት ለሁሉም ነገር መሠረት ከመሆኑም በላይ እንደ ማህበር ከዚህም የከበዱ ችግሮች ቢመጡ በዚህ መልክ ሊፈቱ እንደሚችሉ ማሳያ ይሆናል:: በማህበሩም ላይ ጥያቄ ላላቸው 'በተወሠነ' መልኩ ነገሮችን ያቀላል:: ለዳንኤልም ያለኝን አክብሮት በዚው አጋጣሚ መግለፅ እፈልጋለሁ ለብዙዎችም አርዓያ የሚሆን ነው::

Anonymous said...

መልካም ነገር ነው::

Anonymous said...

melkam hasab

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ፣ አሜን

እፎይ... ተመስገን! ለእግዚአብሔር ምን ይሳነዋል!


የቅዱሳን አምላክ ተዋሕዶ እምነታችንንና ማኅበራችንን ይጠብቅልን፣ አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን።

አሜን

Anonymous said...

Seyten Yifer, Egzibher Yikber

We need to pray very hard in Felsat for our church.

Anonymous said...

Mentenu aaseyeke bente kulu zegebrke lene wegenoche besebsebaw yetegnachihu Egziabher abzeto yibarkachihu wagawen belj lejochachihu tagegnutalachihu maheberu yemiamrebet yihe yefker enba new

Anonymous said...

በመጀመርይ መስጋና ዪገባዉ ቸሩ መድሃኒትአለም ሁሉን የሚመለከት ሁሉን የሚያስተካከል የጠላትን እራስ የሚቀጠቅጥ

በዚህ አገለገሎት ደከመኝ ሰለችኝ ሳትሉ ብፀሎት የ ተጋቸሁ ወንደሞች እና እህቶች አሁንም የ አባቶቻችን ፀሎት ከናንት ጋር ነው የ አንዲት ቅደስት ቤተከርስቲያን አምላክ ክቅደሞ አብዘቶ እየጎበኝን ነዉ ።

Kalkiyas said...

Irr bel telat

Anonymous said...

ተመስገን ጌታዬ!!!!!! አመብርሃን መተሳስብን መተራረምን መከባበርን አድይን!! አሜን!! የቀሲስ ሙሉጌታም አንዲሁ ቢጨርሱት መልካም ነው::

yared said...

እፎይ የተደሰተው ጠላት በሶስት ቀን ምህላ እንኳን አፈረ ፡፡ ምን አለ እርስ በርስ በሚዲያ መነካከሱ እና መቆሳሰሉ ቀርቶ ለቤተክርስቲያን ሰላም እና ለበጎቻችን ደህንነት ሲባል ልክ በዚሁ መልኩ በጾም፣ በጸሎት እና በምህላ በተዋህዶ እናታችን እና በህዝባችን ላይ ልቡናዉን እና ዙፋኑን ያደላደለዉን ጠላት በአጭር ጊዜ ድል ብናደርግ ::

የተዋህዶ አዕማድ የሆናችሁ የቅዱሳን አንድነት ልጆች ማሕበረ ቅዱሳን ከ45 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ እና በጾም በጸሎት ዘወትር የሚራዱዋችሁ የብዙ አባቶችም ተስፋ እናንተ ናችሁና አንድነታችሁን አጽኑ ::

yared said...

እፎይ የተደሰተው ጠላት በሶስት ቀን ምህላ እንኳን አፈረ ፡፡ ምን አለ እርስ በርስ በሚዲያ መነካከሱ እና መቆሳሰሉ ቀርቶ ለቤተክርስቲያን ሰላም እና ለበጎቻችን ደህንነት ሲባል ልክ በዚሁ መልኩ በጾም፣ በጸሎት እና በምህላ በተዋህዶ እናታችን እና በህዝባችን ላይ ልቡናዉን እና ዙፋኑን ያደላደለዉን ጠላት በአጭር ጊዜ ድል ብናደርግ ::

የተዋህዶ አዕማድ የሆናችሁ የቅዱሳን አንድነት ልጆች ማሕበረ ቅዱሳን ከ45 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ እና በጾም በጸሎት ዘወትር የሚራዱዋችሁ የብዙ አባቶችም ተስፋ እናንተ ናችሁና አንድነታችሁን አጽኑ ::

yared said...

እፎይ የተደሰተው ጠላት በሶስት ቀን ምህላ እንኳን አፈረ ፡፡ ምን አለ እርስ በርስ በሚዲያ መነካከሱ እና መቆሳሰሉ ቀርቶ ለቤተክርስቲያን ሰላም እና ለበጎቻችን ደህንነት ሲባል ልክ በዚሁ መልኩ በጾም፣ በጸሎት እና በምህላ በተዋህዶ እናታችን እና በህዝባችን ላይ ልቡናዉን እና ዙፋኑን ያደላደለዉን ጠላት በአጭር ጊዜ ድል ብናደርግ ::

የተዋህዶ አዕማድ የሆናችሁ የቅዱሳን አንድነት ልጆች ማሕበረ ቅዱሳን ከ45 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ እና በጾም በጸሎት ዘወትር የሚራዱዋችሁ የብዙ አባቶችም ተስፋ እናንተ ናችሁና አንድነታችሁን አጽኑ ::

Anonymous said...

I just knew that Daniel is the true christian and the discussion was really like our forefathers.

We all humans have up and downs.

Anonymous said...

ምን ተብሎ እንደሚመሰገን ባይታወቅም ብቻ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው!!! ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ!!! ድንግል ወላደተ-አምላክ ያቺ ብዙ ጊዜ በመድረክ የሰበክክላት/ያስተምርክላት እናት አሁንም ፍቅሯን ጨምራ ታሳድርብህ!! ‹‹ሰው ኦክስጂን ሳያገኝ እንደማይኖር ሁሉ እንዲሁ ያለእመቤታችን መኖር አይታሰብም›› ለቤተክርስቲያንም በዚህ የፈተና ዘመን ማ/ቅ እንደ 02 ያስፈልጋታል!!! የውስጡን ችግር እንደተለመደው መፍታትና ዲያቢሎስን ማሳፈር ያስፈልጋል፡፡ እባካችሁ ከአሁን በኃላ እንዲህ ያለ ስህተት ባይደገም፡፡ በበለጠ ለዚህች ቤ/ክ በፍቅር ና በትህትና እንድናገለግል አንድነታችንን የሚንድ ምንም ንፋስ (ዲያቢሎስ) እንዳይገባ፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል!!
ብሥራተ ገብርኤል
ከሀላባ

Anonymous said...

የራሔልን እንባ ያበሰ አምላከ እስራኤል ሃገረ ኢትዬጵያን እና ቤ/ክርስቲያንን እንዲሁም ማህበረ ቅዱሳንን እንባቸውን ያብስልን::
የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት የእግዚአብሔር ቸርነት ሃገረ ኢትዬጵያንና ቤ/ክርስቲያንን ይጠብቅልን!!

Anonymous said...

dese yemile zana! amlake yerdane!

Anonymous said...

malqes siyansachu new yiliqunis bezi tsom bedenb alqisu. Egziabher kehulachin gar yihun

Anonymous said...

በዚህ ሒደት 3 ነገሮች ተከስተዋል
1ኛ. ማኅበረ ቅዱሳን ሁለት ዓይነት አባላት አሉት። የመጀመሪያዎቹ በብዙ ሺህ የሞቆጠሩ የተመዘገቡ አባላቱ ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ያልተመዘገቡ አባላቱ ወይም ደጋፊኦቹ ናቸው። በዚህ ፈተና ወቅት ከያሉበት ሆነው የደረጉት ግፊት ማንም ሊቋቋመው የማይችል እና ውጤታማ መሆኑን
2ኛ የማኅበረቅዱሳንን ችግሮችን የመፍታት ልዩ ስጦታውን እና ለሌሎች መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ጭምር አርአያ ሊሆን የሚችል መሆኑን
3ኛ. ዳንኤል ህዝበ ክርስቲያኑ ከእሱ ምን እንደሚጠብቅ የተራዳበት እና አሁን ደግሞ እውነትም ትልቅ ሰው መሆኑን ያየንበት ነው።
ይበል ይበል ያሰኛል። በሉ አሁን ወደዋነኛው ሥራችን በፍጥነት።

Anonymous said...

'DANIEL Endegena Abziten Liniwodih New Malet New!?!'

If u did it really, u 'll become 2 b printed in depth in our heart!

And if i were in Addis, i w/d hv carried u on my shoulder & run 2 z church 2 praise my God!

Mk hv already 'swallowed saliva'; we hv seen it, strong in love!
(AGE)

Anonymous said...

Egziabeher yemesegen. Mechereshawen yasamerelen.

Orthodoxawi said...

Egziabher Yimesgen!

Dejeselam:- Cher Silasemachihun enamesegnalen.

This is a real proof showing how much the Holy Spirit was(is) leading our brothers and sisters.

Those of you who have been using this internal difference for your cheap purpose....pls wake up, stop and think. You are preaching hatred and evil. Come back to our mother church (Tewahedo). Come and renew yourself. You can't "Renew" our Holly Church! Nu ena rasachihun Adsu!!!

Dear MK members, pls resolve all internal issues within yourselves. Keep on your good job! God be with you!!!

Anonymous said...

Waw!!! Melkam Zena Newu!

Yimesgen Amlakachin!!!

Dn. Daniel kelbu yikrta siteyiq lemayet guaguchalehu!

Keziya behuala siyastemregn esemawalehu.

Cher werie yaseman!

T... said...

ይህን መልካም ዜና ያሰማን እግዚአብሔር አምላክ ይክበር ይመስገን:: ወንድማችን ዳንኤልን እንወደዋለን እናከብረዋለን ያለፈውን ትተን ቀጣዮን የሂወት ዘመናችን ከማህበራችን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን ንጽህት የምትሆን ቤተርስትያናችንን እናገለግላለን:: ይህን በልካም ዜና እንዳሰማን በቀጣይም የቅድስት ቤተ ክርስትያናችንን አንድነት የ አባቶቻችን አንድነት እግዚአብሔር ያሳየን:: አሜን::

ካሌብ ብርሃኑ ዘ ብሔረ ኢትዮጵያ said...

ተመስገን በማኅበራችን ኮራሁ ደጀ ሰላም እድሜ ይስጥሽተመስገን በማኅበራችን ኮራሁ ደጀ ሰላም እድሜ ይስጥሽ

Anonymous said...

Ahun kirisitinan be nuro asayun malet new, yih new ke sew yemitebekew, dirom endih mechachal binor metesaseb binor mechi yihen yahil yizelik neber gudayu, ahunim cher yaseman, gudayu zelaki endihon ewunetun afiretirito mewoyayet yasifeligal, bertu, tinatun yisitachuh

Anonymous said...

«ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በማስተዋልም ይጸናል» ምሳሌ 24፣3

መልካም ዜና ነው
ሠናይ

Gebre Z Cape said...

This is how Christians are. Civilisation is to believe in discussion and to reach at some level of understandation. We love you all MK senior and current member. I can see that we fight, argue for the better future of MK. GOD bless you, keep the good job.

samueldag said...

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
9፥15 ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።

gonderew said...

ebakachu yetwahido ligoch yikiretan endezih adirigachihu astemirun astemiruachew sayitanim yifer "wenid elilili ayileme yalew manew elililililili biyalehu kedesita eniba gara EGIZIABIHAR YIMESGEN.
Lenanite lemastemar ayidelem gini EGIZIABIHAR bebezabet bota hulu sayitan silemikena lalemesenakel tegiten mesteley yinoribinal.Wegenoche EGIZIABIHARIN engi lesew ena lesigachin anichenek. mahiberachen mehabere kidusan ketilo orthodox tewihido hayimanotachen bemecheresha wid ethiopia hagerachen enidibezulin bestelot,besigidet ena belekiso eniberita.
eniwaded anileyay ewinet enihun EGIZIABIHAR ENA ENATU DINGIL MARIAM kegna gara nachew
AMILAKE ESRAEAL AYILEYEN
AMEN

Dawit said...

‹እንግዲህ እግዚአብሔር እንደመረጣቸው ቅዱሳንና ወዳጆች ምሕረትንና እርኅራኄን ቸርነትንና ትህትናን የውሀትንና ትዕግስትን ልበሱት፡፡ ባልንጀሮቻችሁን ታገሱአቸው እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ፡፡ ባልንጀሮቻችሁን የነቀፋችሁበትን ስራ ተው ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እንዲሁ አድርጉ፡፡ ከዚህም ሁሉ ጋር ዘወትር ተፋቀሩ፡፡ የመጨረሻው ማሰሪያ እርሱ ነውና፡፡ ›
ቆላስይስ 3 = 12-14
የፍቅር እንባችንን የመለሰ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ለዘላለሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡
ማህበራችን ማሕበረ ቅዱሳንን እግዚአብሔር ይጠብቅ፡፡

Anonymous said...

ማንም በህይወቱ ፍጹም የለም:: አንዴ ይወድቃል ሌላ ጊዜ ይነሳል:: ይህ በእውነት ታላቅነት ነው:: መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ያስተማረንም ይቅር መባባልን ነው
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና። ማቴ 5:7
በእውነት አንዳንዶች ሰባኪ ወንጌል ነን ባዮች ይቅርታ እንዳትጠይቅ ሁሌ ተሸማቀህ ትኖራለህ ብለው በሚናገሩበት ወቅት የእግዚአብሄር ልጆች ይህንን በማድረጋችሁ
እኛን አረጋጋችሁ, ኮራንባችሁ ጠላት ግን አንገቱን ደፍ:: ልዩነቶች በርግጥ ሊኖሩ ይችላሉ:: እባካችሁ! ይህችን ጊዜ ኬግዚአብሄር ጋር እንለፋት...

Anonymous said...

Egziabher Amlak Yetemesegene yihun! D/n Daniel Enkuwanm Tsafk. Yikr mebabaln ena Chigrn Be wiyiyt Meftatn kenante enmaralen. Amlak Eske mechereshaw yatsnachu! Agelglotachunm Yibark!

123... said...

ትልቅ ነገር ነው። ለወደፊቱ ትምህርት ይወሰድበታል። አንባ የማያትበው ምን አለ። የ አምላክ ልብ አንኩዓን የሚከፈተው በ አንባ ነው። ኮራንባችሁ!! በርቱ።
አመብርሃን በ አማላጅነቷ አትለየን።

atlanta said...

Temesgen getaye menenlalen.

Anonymous said...

Just back from church & saw the news no words. I was not sure what the result would be but God was with them as always.i read all 70 comments every one's comment is priasing God. that is what God want from us. May God give you more wisdom to all who was involved in the soln.

hiwot said...

"Atalito Yemeyasitarik fiker yestachihu" alu And Abat Simeriku.Next time be wise every one's eye is on u.

Anonymous said...

Geta hoy enwedhalen...mahiberachinin tebikilin

Anonymous said...

menager Akatecgna Aleksu...

T/selase ከስዊድን said...

መዝሙረኛውም አለ ''አቤቱ አመሰግንሀለው፣ ታምራትን ሁሉ እነግራለሁ፣ በአንተ ደስ ይለኛል ሀሴትም አደርጋለሁ፡፡''

T/selase ከስዊድን said...

መዝሙረኛውም አለ ''አቤቱ አመሰግንሀለው፣ ታምራትን ሁሉ እነግራለሁ፣ በአንተ ደስ ይለኛል ሀሴትም አደርጋለሁ፡፡''

Anonymous said...

amlak ymesgen

Anonymous said...

Fetari yetemesgene yehun ! Fetari Mahebere Kidusanen yebarkelen. Wondemochachen sele feker ena tehtena setelu yeker mebabalachehu tafach yefeker enbachehun mafesesachehu le hulachenem telek temehert new. Betam des yelal. Abzeto yebarkachehu !

Dn. kumlachew

Anonymous said...

ደጀ ሰላማውያን እንደምን ሰነበታችሁ? የምታስነብቡን ዜናወቻችሁ አብዛኛውን ጊዜ ተወዳጆችች ናቸው። የዛሬው ደግሞ ከንጊዜውም በላይ አስደቶኛል።የማህበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉብኤ ለረጅም ጊዜ ቤተ ክርሥቲያንን እናአ ማህበሩን በማገልገል የሚታወቀውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ማግለሉ አግባብ አልነበረም። አሁን ግን ችግሩ በውይይት መፈታቱ እጅግ በጣም አስደስቶናል።ማህበሩ ወደፊትም የውስጥ ችግሩን በውይይት የመፍታት ልምድ ሊኖረው ያስፈልጋል።

Tsige said...

``Le Getaye Le Egziabiher
Siladeregelign min ekefilewalehu
Misgana newu enji(2x)
Lela min elalehu

Le Embete Le Dingil Mariam silamaldechign min ekeflatalehu
Lamesginat enji Lela min elalehu ``

Amilake Kidusan mechereshawun Yasamirilin!!!Atsrare Betekirstiyanin Yasitagisilin!

Anonymous said...

Erku balkefa nebere. However, do you think simple erke would solve the horrendous problems the mahebere is facing? I think it also needs fundamental rethinking of the mahebere's direction, tactic and strategy.

Anonymous said...

Egziabher yimesigen!!!! Lebeletew neger yatigan........

Anonymous said...

ደግ ዜና ነውና ደስ ቢያሰኝም እናንተ ግን ወገንተኝነት አይታይባችሁ!!! TEBAREKU!!!

Anonymous said...

Good News.

Peace up on You

yemelaku bariya said...

ፈተናውን ያመጣው ለከባዱ ፈተና ሊፈትነን ቢሆንስ ብየ አሰብኩ:: አሁንም ለወንድሞቻችን እንጠንቀቅ:: ሙሉጌታ ፣ ዳንኤል ማለቱን ትተን እነሱ ዛሬ ያገኙትን ማስተዋል የሰጣቸውን ምስጋና ከንቱ የማይሆንበትን እግዚአብሔርን እናመስግን:: ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ሁሉም በቤተ ክርስቲያናችን የመጣው ፈተና መፍትሄ በመፈለግ ላይ ከፍተኛ ኃላፊነት ስላለባቸው ማወደሱን ትተን ማስተዋሉን ከነጥበቡ እንድሰጣቸውና የተሻለ ነገር እንድሰሩ በጸሎታችን እናስባቸው:: ለኛም ለወደፊቱም ለኛ ብዙ የተማርነው ብዙ ነገር አለ:: ለማንኛውም ማኅበራችን የውስጥ ድክመቱን መገምገም የዘወትር ስራው መሆን አለበት:: ለኛ የሚያሰጋን የራሳችን ድክመት እንጅ የጠላቶቻችን ብርታት አይደለም:: እነሱ ለጥፋት የተጉትን ያክል ምንም አያመጡም መፍራት ማድረግ ያለብንን ሳናደርግ ቀርተን እንዳይሆን መጠንቀቅ ብቻ ነው:: ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን ማስተዋሉን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን::

Tesfu said...

የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው!!!

tesfu said...

የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው!!!

Anonymous said...

እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ዜና ነው እግዚአብሔር አምላክ አሁንም ማህበራችንን ከጠላት ፈተና ይጠብቅልን ለእያንዳንዳችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯን በረከቷን በሁላችን ላይ ታሳድርብን አሜን!

Anonymous said...

GOD give these kind of love for MK. Please keep every time thanks to GOD and pray for all things to GOD.

Anonymous said...

I have no words to express my feeling except tear thank you God.

Anonymous said...

ነገር ሁሉ ለበጎ ነው! ስለሆነልንም ስለሆነብንም ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ከውሳኔዎቹ የማኀበረ ቅዱሳንን ጥንካሬ አይቻለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር በዚህ ዘመን ይሔ ስሕተታችን ነው ይታረም ፤ ይሔ ደግሞ ማስተካከያ ይሰጠው ፤ ይሔ ደግሞ ያላግባብ የተደረገብን ነው ብሎ የሚቀበል አካል ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ደጀ ሰላም ትንሽ ሚዛኑን ያልጠበቀ ዜና በማቅረብሽ የተሰማኝን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡ ማኀበሩ ያወጣውን ግልጽ መግለጫ በጊዜው አለመዘገብ በተለይ ደግሞ የዲ/ን ዳንኤልን ጽሑፍ እንደማስተናገዳችሁ አግባብ አይደላም፡፡ ይስተካከል፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ከላይ አንድ ምህመን እንደገለጹት እዚህ ይገኛል፡፡

Anonymous said...

ነገር ሁሉ ለበጎ ነው! ስለሆነልንም ስለሆነብንም ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ከውሳኔዎቹ የማኀበረ ቅዱሳንን ጥንካሬ አይቻለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር በዚህ ዘመን ይሔ ስሕተታችን ነው ይታረም ፤ ይሔ ደግሞ ማስተካከያ ይሰጠው ፤ ይሔ ደግሞ ያላግባብ የተደረገብን ነው ብሎ የሚቀበል አካል ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ደጀ ሰላም ትንሽ ሚዛኑን ያልጠበቀ ዜና በማቅረብሽ የተሰማኝን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡ ማኀበሩ ያወጣውን ግልጽ መግለጫ በጊዜው አለመዘገብ በተለይ ደግሞ የዲ/ን ዳንኤልን ጽሑፍ እንደማስተናገዳችሁ አግባብ አይደላም፡፡ ይስተካከል፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ከላይ አንድ ምህመን እንደገለጹት እዚህ ይገኛል፡፡

Anonymous said...

የውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
በኮንፈረንስ ስልክ
“ እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው::” ሉቃ 1፡48-49
ለተወደዳችሁ አባቶች፡ እናቶች ወንድሞችና እህቶች፡ በሙሉ :
የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን!

የማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማዕከል የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ ነሐሴ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ጾም በሊቃውንተ ቤ/ክን አባቶች አማካኝነት የእመቤታችንን ውዳሴና ቅዳሴ ትርጓሜ ሲያቀርብ ቆይቷል። ዘንድሮም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከዋዜማው ቅዳሜ ሐምሌ 30 2003 ዓም አንስቶ ይጀምራል።ስለዚህ እርስዎም በሰዓቱ በስልክ ጉባኤው ላይ በመሳተፍ ነፍስዎን ቃለ እግዚአብሔር ይመግቡዋት፡ ከወላዲተ አምላክ ውዳሴና ቅዳሴ ይሳተፉ፡ ስለሀገር፡ ወገንና ስለቅድስት ቤ/ክንዎ በጋራ ይጸልዩ። ሌሎች ወንድሞችና እህቶችም እንዲገኙ ይጋብዙ።ቀናት፡ ከቅዳሜ ሐምሌ 30 - እሑድ ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም/ August 6-21, 2011
ሰዓት፡ ከምሽቱ 9:00PM-10:00PM PST(ሲያትል ሰዓት)
12፡00AM - 1:00AM EST (ዲሲ ሰዓት)
የኮንፈረንስ ቁጥር፡ (712) 432-1001
Access Codes 428585128#

Anonymous said...

Temesgen amlake Kidus Amanuel mesebasebachun(MK) yebark. From Canada

Anonymous said...

እግዚአብሔር ታላቅ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳች እንደዲለው ኑ እንዋቀስ የሚለውን በማየታችን ለእመቤቴ ክብር ምስጋና ይግባትና ለልጆሽ ልቦና ስጭልን ብዬ ለምኛት ነበርና ፀሎቴን ሰማችኝ፡፡ አሁን ደግሞ ተባብረን እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት በሱሳኤ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐይማኖታችንንና ቤተክርስቲያናችንን እንድትጠብቅልን፣ እኛንም በእምነታችን እንድታፀናን፣ ከጠላት ፈተናና መከራ እንድትታደገን፣ አገራችንን ኢትዮጽያን የክርስቲያኖች ደሴት አድርጋ እንድትባርክልን እንማፀናት፡፡

Anonymous said...

የተመኘንውን ያልነሳን አምላክ ክብሩ ይስፋ!

ባለፈው ይህን ብየ ነበር……በርግጠኝነት ዳኒና ሙሌም ያው በተለመደው በMK ልማድ መሰረት ፊት ለፊት በወንድሞቻቸው መካከል ተወያይተው በክርስቲያናዊው ይቅርታ መሰረት ለነበረው አለመግባባት ይቅር ተባብለው ሲላቀሱና ሲያላቅሱን እንደምናይ እምነቴ ነው፡፡ በስራ አመራሩም ላይ የተነሱት ቅሬታዎችና አስተያየቶች ጭምር በጥልቀት ታይተው አገልግሎታችንን አጠናክረን መቀጠል ይገባል፡፡ ግልፅ ዉይይት ባህላችን መሆን አለበት፤ እንዲሆንም መጣር ያስፈልጋል፡፡ ልማደ MK ም እንዳየነውና እንደሰማነው ይሄው ነውና ለእኔ ይበልጥ ደስ የሚለኝ ባህሉም MK በሌሎች ከመገምገሙና ከመታየቱ በፊት በራሱ አይን ራሱን ማየት የሚችል መሆኑ ነው፡፡

ቀድሞ ከአባቶቻችን ጋር የነበርክ አምላክ አሁንም ከልጆችህ ጋር እንዳለህና እንደምትኖር አሳይተኸናልና ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን!

የማይወግኑንን ልቦና ሰጥቶ እንዲማሩ ያድርግልን ፤ወንድሞቻችንንና ማኅበራችንን ይጠብቅልን፡፡
ዲ/ን ኃይለጊርጊስ

ኢትዮጵያ said...

ተመስገን።

Anonymous said...

Please PGF I cam not read my phone dejeselam tebaberune

Anonymous said...

THANKS TO THE ALMIGHTY GOD! NOW IT IS TIME FOR A HOLY FASTING TO PRAY FOR THE MERCY OF GOD THROUGH THE INTERCESSION OF St. MARY. FASTING WILL HAVE A REAL REWARD ONLY AFTER LOVE AND FORGIVENESS.

Anonymous said...

Temesgen!

Anonymous said...

selamayenagare setotawe Egizabehare yemasegane

Anonymous said...

Dejeselamaweyan Cher were yasemachihu.

asbet dngl said...

እውነትም ጊታ ከኛ ጋር አለ::
በቅድሜያ እንደኔው ስትጨነቁ ለሰነበታችሁ የተዋህዶ ልጆች እንኳን ደስ አለን ማለት እፈለጋለሁ። በተጨማሪም የምእመኑን ስነ ልቦናዊ ሀሳብ በመረዳት እና
በተለይ በዚች ፈታኝ ወቅት የበተክርስትያናችን ችግር ቅድሜያ በመስጠታችሁ
ዳኒ ከድሮም አክብሪ እወድህ አለሁ የአሁኑ ግን መሰል ጔደኟችህን ያካተተ ነው።
የድንግል ቸርነቱዋ አይለያችሁ።ግዚውም የጾም ወቅት ስለሆነ እንጸልይ።

እናታችሁ፣ ዓጽባእተ ድንግል

Sara Adera said...

Sara Adera
እንኳንስ ትልቅ ቁም ነገር ይዘው ቀርቶ ወንድማማቾች በማይረባ ነገርም ይጋጫሉ:: በእንባ ይቅርታ ሲጠያየቁ በጣም የሚያስደስት እና እናት በልጆቿ የምትኮራበት እንኳንም የእኔ ሆናችሁ የምትልበት ትልቁ ጊዜ ነው:: ... ጊዜያዊ ያለመግባባታቸው በሰላም እንደሚስተካከል መግባባት በመካከላቸው እንደሚሰፍን ሁላችንም የምናውቀው ነው::
ትንሽ ያናደደኝ የአራጋቢዎች መካከል ገብተው ነገሩ እንዲባባስ የበኩላቸውን ሰይጣናዊ አስተዋዕፆ መፈጸማቸው ነበር:: ይሁንና ሰይጣን ይፈር ክርስቲያኖች ማለት እንደዚህ ነው:: ፆም ፀሎት ሱባኤ በእርቀ ሰላም ተጀመረ
እንግዴ ሰላም ሆነ ፈጣሪ አምላክ ቸሩ መድኃኒዓለም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም አሁንም ሰላም እና ጤናን ለሁላችን ያድሉን አሜን!!!

Anonymous said...

+++
+++

እፎይ ተመስገን
ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለአምላክ ለመድኃኒታችን እልል እንበል።
በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል መዝሙረ ዳዊት 95:1-2
ወንድሞች እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ ጠላታችን አፈረ::

Anonymous said...

Abet Yegziabehere Cherent! Endet megletse yichalal! Enatalem daseschachehu! tekorarfachehu yemetamesegenuate misgana yemtezemirute mezmure lemekebel kir selemilat! Awoye yanten sira endet menger Yichalal! Yewushotu fetena albekachehu belo benanetem wost gebeto lebetenachuh neber leka! Abetu wodefitem temesasay cherenetehen atenfegen!
Egziabhere Ethiopian Yibark, Tewahidon Yitebik Mah Kud Yatsena Tatega!
Melkamu Amare (Kalehubet)

Yodit said...

efoooooyyyyyy tadilen you see God is with us all the time. It seems my mind start working.

Sam ze Edmonton said...

It is a must to happen. The basic difference is to be honest and ask apology to each other in Christianity. Hope it will make all of you our brothers more together and be one. Thanks to God the Almighty. Amen

Anonymous said...

እልልልልልልልልል!!!
በእውነት!!! ሰበር ዜና ነው
በአባታዊ ፍቅሩ የሚጎበኘን ለጠላት መሳቂያነት የማይተወን እንደዚህ ክርስትናን በምግባር የሚያስተምሩ ወንድሞችና እህቶች የሰጠን እግዚአብሔር አምላካችን ይመስገን! ፍጻሜውንም ያሳምርልን
በሀዘን የሰነበታችሁ ሁላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እኔም በጣም በጣም በጣም ደስ ብሎኛል ደስታዬን ለመግለጽ የሚበቃ ቃላት የለኝም ሰሞኑን ስናለቅስ የሳቀ ጠላት ዛሬ በተራው ያልቅስ

Sertsedingle said...

ምንተኑ አአስዮ ለእግዚአብሄር በእንተ ኩሉ ዘገብረ ሊተ

Melkamuamare said...

Benanete Mihalema Telat sisletine zim belo ayayim! Yazegajachehu echo esu new1 endeiaw endititenkiru mekerun liasayachehu new enji! Wodimoche gena min aytachehu edeme yistachehu bicha lezich hager benanete gena bizu yemiseraw alew! Atirsu yemeseretuachehu echo Abune Gorgorios nachew eneh yezederowochu meselwachehu new Yeneian eje echo medhanialem semotal! selezih ejachewn chenew yadokonuachew enia yemejemeriawochu enesu yesrute sera aywodikim! Amlakachehu Amlake yihen yemesele fetena endimeta awoko new enian yetekedesu abat mikeniate adergo ke-eyerusalem amitito enaneten yasebasbew! Ayzuachehu hulachenem yetewahido ligoch kegonachehu nen
Egziabehere Yezichin ager wudeket Ayasdayegne! Ayasayen! Amen
Melkamu A.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)