August 5, 2011

አሰግድ ሣህሉ “ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ” አለ


  • በስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት አባ ሰረቀ ከሀገር ሊወጡ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2011; READ IN PDF)፦ ወደ ቤተ ክርስቲያን የውስጥ መዋቅር በመግባት የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን ዓላማ ለማሳካት ከሚፍጨረጨሩትና ከእነርሱም መካከል እንደ ዋነኛ ከሚታዩት የወቅቱ የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ቅጥረኞች አንዱ ሆነው አሰግድ ሣህሉ “ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ” ሲል በገዛ አንደበቱ መናገሩ ተሰማ፡፡ አሰግድ ይህን ምስክርነት ስለ ራሱ የሰጠው ከነገ በስቲያ ቅዳሜ ለንባብ እንደሚበቃ በተጠቆመ አንድ መጽሔት ሰሞኑን በሰጠው ቃለ ምልልስ ነው፤ ንግግሩንም በአንድ ወቅት በ‹ተሐድሶ› ጉዳይ ላይ ለጠየቀችው አንዲት ሴት የመለሰው መሆኑ ተገልጧል፡፡


ግለሰቡ ቃለ ምልልሱን ከሰጠና መጽሔቱ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ማተሚያ ቤት ከገባ በኋላ ይህ ቃሉ ከቃለ ምልልሱ እንዲወጣለት አልያም ቃለ ምልልሱ ጨርሶ እንዲቀር “ደኅንነቶች ናቸው” በሚላቸው ግለሰቦች ዋና አዘጋጁን ማስፈራራቱ ታውቋል፡፡ አሰግድ በተለያዩ አጋጣሚዎች “ደኅንነቶች ናቸው” በሚላቸው ግለሰቦች እያስፈራራ ሕገ ወጥ ፍላጎቱን እንደሚያስፈጽም ያስታወሱት የዜና ምንጮቹ ግለሰቡ ከዚህ መንገዱ እንዲታቀብ ሊገደድ እንደሚገባው ያሳስባሉ፡፡ 

አሰግድ ባለበት የሃይማኖት ችግርና ባቀረበው የተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከትምህርት ገበታ ቢያገደውም ታኅሣሥ 27 ቀን 2003 ዓ.ም በኮሌጁ ላይ በመሠረተው ክስ “የኮሌጁ ውሳኔ አግባብ አይደለም” በሚል ሐምሌ ሰባት ቀን 2003 ዓ.ም ትምህርቱን እየተከታተለ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱ ተዘግቧል፡፡ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ለክሱ በሰጠው ምላሽ፣ “ጉዳዩ የሃይማኖት ክርክርን የያዘ ስለሆነ ፍ/ቤቱ አከራክሮ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን የለውም” ሲል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል፡፡ የፍሬ ነገር ክርክሩንም በተመለከተ፣ “ከሳሽ ቤተ ክርስቲያን የማትቀበለውን ትምህርት የሚያራምዱ በመሆናቸው፣ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት በዚሁ ጉዳይ አቤቱታ ቀርቦባቸው ቤተ ክርስቲያንም ይህን ማረጋገጧ፣ ከሳሽ ያለሰበካቸው በማታለል የቀበና መድኃኔዓለም ሰበካ ጉባኤ አባል ነኝ በማለታቸው ያቀረቡት ማስረጃ በደብሩ አስተዳዳሪ የተሰረዘ በመሆኑ” የከሳሽ ክስ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር፡፡ ደጀ ሰላም የጡመራ መድረክ በጉዳዩ ላይ ተከታታይ ዘገባዎችን (http://www.dejeselam.org/2011/02/blog-post_10.html) ማቅረቧ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል በማኅበረ ቅዱሳን ላይ በየጊዜው በፈጸሙት የስም ማጥፋት ድርጊት ክስ ተመሥርቶባቸውና በማስረጃ ተመስክሮባቸው እንዲከላከሉ ትእዛዝ የተሰጣቸው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ በአቡነ ጳውሎስ ጥያቄ ፍትሕ ሚኒስቴር ክሱ ለጊዜው እንዲቋረጥ ካስደረጉ በኋላ ነገ ቅዳሜ ወደ አሜሪካ ዋሽንግተን - ዲሲ ለመብረር መዘጋጀታቸው ተጠቁሟል፡፡ በዋና ሓላፊው ጥብቅ ቁጥጥር ሥር በሚዘጋጀው የመምሪያው ድረ ገጽ ላይ “ክሱ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ በነጻ እንደተሰናበቱ” አስመስለው እንዲዘገብ ያደረጉት አባ ሰረቀ ከሕግ የበላይነት ለመሸሽ በጀመሩት መንገድ ከሀገር ለመውጣት መወሰናቸውን ነው ምንጮቹ የጠቆሙት፡፡ አባ ሰረቀ በድረ ገጹ ያወጡት የተሳሳተ ዘገባ እንዲታረም ክሱ ለጊዜው እንዲቋረጥ ባዘዘው በፍትሕ ሚኒስቴር ሰዎች ቢነገራቸውም “እምቢ፣ አይሆንም፣ አልሰርዘውም” አልኳቸው እያሉ በጀብድ መልክ ሲያወሩ መሰንብታቸው ተገልጧል፡፡ የ1200 ዜጎችን ከ56 ሚልዮን ብር በላይ አላግባብ ወስዷል የተባለው የአስካሉካን ትሬዲንጉ ግርማይ ከሕግ ተጠያቂነት መሸሽ እንደማይችል ታውቆ ሰሞኑን በኢንተርፖልና በመንግሥት ጥረት በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ሀገር ቤት ተመልሷል፡፡ የእኛው አባ ሰረቀስ? የፍትሕ ፈላጊ ኦርቶዶክሳውያን ጥያቄ ነው፡፡

16 comments:

Anonymous said...

However what r u waiting 4? Who is the concerned party? Pls do something. What about aba sereke, who take the responsible?

Rede mereat said...

Ewnet ena negat eyader yegeletal ena ...hulum yemegeletbet geze ale. Lehulum EGZEABHER yerdan!ehulum EGZEABHER yerdan!

Anonymous said...

O Great News DS!
Tnxs 2 God.
People Must hv been Strongly praying!
I hv started also, at least 2 share mine.
(AGE)

Anonymous said...

Min nekachihu Dejeselam? Aba Sereke eko Neqersa(Cancer) newu. Wede America mehedu yishalenal...eziya yalu yetewahedo lijoch lik yasgebulinal...aliyam ...Pastor Sereke hono yerasun "church" yikeftal.

Ende Abatu Ende Aba Paulos le nesha yetadele alhonem.

Aba Sereke:- ... degmo America min wenjel tisera yihon....yaltadelk...kifu, eshoh, gareta, neqersa.....Menafik!!!

Anonymous said...

hulum begizew erasachewen yemeyagaletubet gize ruk ayehonem. Becha egeziabher betekereseteyanen yitebekat.

Anonymous said...

abato amelaka griorges eredane

Anonymous said...

Ahunis sile enezih sewochi manibebim hone mesimat mereregn, yihen yahil medirek le enesu mesitetu berasu le enesu tilik neger new, beka kehadi nachew nachew, le 1 tera sew yawum le kehadi yihen yahil bota mesitet ayasifeligim, betekirisitiyan dirishi endayilu kemadireg wuchi.

Ymechal kehone yelik asitebabariwun enasiwogidew, wanaw esu new, lelaw teketayi woyim kirinichaf new

Anonymous said...

aba America semetu be America heg meteyek ayechalem kes mereto yesemen Americaw maekel ?

Anonymous said...

በጣም ያሳዝናል፡፡ እግዚአብሄር ይርዳን......።

Anonymous said...

What makes me so surprising is that not z escaping of aba serekebrhn rather the decision of ministry of justice & his holyness z patriarch. Our holy father please do not do like this every body must offer justice . Let our God Jesus z Lord keep our country.

T... said...

እኝህ ሰይጣን ሰው አሁን ሳይወዱ አንስተውታል:: ከ ማ/መ/ሰ/ት ቤት ድረ ገጽ ተነስቶአል::

Anonymous said...

ተዋሕዶን ወደመናፍቅነት በማርከስ በሚከተለዉ የስልጣን ሽሚያ ቱባ የስልጣን ወንበር ለመቀናጀት የሚደረግ "የተስፈኛ-ጅቦች" ማሽካካት ይመስላል።

Yemebetie Wodaj said...

My point is why does he need to tell us he is tehadisso?

Everyone in Tewahido already knows. We identified him not because he say so or someone say so but because of his devilish beheavior. Simply forget this guy!!!

Anonymous said...

Anonymous said.......emeberehane kene lejua beta kerstiyanene tetebekelen aba pauloseneme leneseha mote yabekatewe

Anonymous said...

yemaytamen new!!

Anonymous said...

kedama eruke aydalem enayawalen este!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)