August 2, 2011

(ሰበር ዜና) ማኅበረ ቅዱሳን በአባ ሰረቀ ላይ የመሠረተው ክስ ለጊዜው እንዲቋረጥ ታዘዘ

  • ትእዛዙ ፓትርያርኩ ለፍትሕ ሚኒስቴር የጻፉትን ደብዳቤ መነሻ ያደረገ ነው::
  • የማኅበሩ የሕግ አገልግሎት የፍርዱ ሂደት የሕግ የበላይነትን በሚያስከብር አኳኋን የሚቋጭበትን መንገድ እያጤነ ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 2/2011/ READ IN PDF):- በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በፈጸሙት የስም ማጥፋት ድርጊት የመሠረተባቸው ክስ እንዲቋረጥ የፍትሕ ሚኒስቴር አዘዘ፡፡ ትናንት ለዐቃቤ ሕግ በተጻፈውና በሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ፣ “አባ ሰረቀ ብርሃን በተከሰሱበት የስም ማጥፋት ወንጀል ማጣራት የምንፈልገው ስላለ ክሱ ለጊዜው ተቋርጦ መዝገቡ እንዲላክልንሲል ትእዛዝ መሰጠቱን ያስረዳል፡፡


ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ለፍትሕ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ፡- አባ ሰረቀ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣ ግንቦት 20 ቀን 2003 ዓ.ም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ስለ ማኅበሩ የሰጡት መግለጫ ባለባቸው የሥራ ሓላፊነት አግባብ የተነገረ እንጂ የስም ማጥፋት ድርጊት አለመሆኑን፣ የክሱ ፍሬ ነገር ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት እየተመለከተ ባለበት ሁኔታ በተፈጠረ ግጭት ላይ የተመሠረተና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን፣ እንዲህ ዐይነት የውስጥ ጉዳዮች ወደ ክስ ማምራታቸው ለሌሎቹ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካላት መጥፎ አርኣያ ሊሆን እንደሚችል በማስረዳት ክሱ እንዲቋረጥ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

ሚኒስቴሩ በፓትርያርክ ደረጃ የቀረበውን አቤቱታ መሰል ጥያቄ መታየት እንዳለበት በማመን የክሱ ሂደት እንዲቋረጥ ቢያዝም፣ አቤቱታው በክሱ ከተመለከተውና አባ ሰረቀ በሰው ምስክር፣ በሰነድ እና በምስል ወድምፅ ከቀረበባቸው ማስረጃ ጋራ ያለውን አግባብነት ከትክክለኛ የፍትሕ አሰጣጥ አኳያ እንደሚመረምረው ተስፋ ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የማኅበሩ የሕግ አገልግሎት በበኩሉ ክሱ ለጊዜውም ቢሆን እንዲቋረጥ የተደረገበትን መነሻ በመፈተሽ የፍርዱ ሂደት የሕግ የበላይነትን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲቋጭ ብርቱ ጥረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም አባ ሰረቀ በዐቃቤ ሕግ የቀረቡባቸውን የሰው ምስክር፣ የሰነድና የምስል ወድምፅ ማስረጃዎች እንዲከላከሉ በታዘዙት መሠረት ያስረዱልኛል ያሏቸውን 12 ምስክሮች አቅርበው እንዲያሰሙ የታዘዙበት ቀጠሮ ነበር፡፡ ዐቃቤ ሕጓ ክሱ ለጊዜው እንዲቋረጥ ከሚኒስትሩ የተሰጣቸውን ደብዳቤ በማስረዳት ወደፊት መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብታቸው እንዲከበርላቸው ይጠይቃሉ ተብሏል፡፡

ጉዳዩን የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ የአባ ሰረቀ ተጠሪነት ለመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እንደመሆኑ በፓትርያርኩ የቀረቡት አቤቱታዎች በእርሳቸው ዕውቅና እና የሓላፊነት ደረጃ መቅረብ ይገባው እንደ ነበር በመጥቀስ የጥያቄውን አቀራረብ ይተቻሉ፡፡ በዛሬው ጊዜ-ቀጠሮ አባ ሰረቀ ምስክሮቼ ባሏቸው ክሱን እንዲከላከሉ ተደርጎ ሂደቱ ወደ ብይን መቀጠል ይገባው እንደነበር የሚናገሩ ተቺዎች በበኩላቸው፣ የመጨረሻ ውሳኔ እስካልተሰጠ ድረስ ሂደቱ በተገለጸው መልኩ ሊቋረጥ የሚችልበት ሁኔታ ቢኖርም ማኅበረ ቅዱሳን ጠበቃ በማቆም እንዲቀጥል ለማድረግ የሚችልበት አግባብ እንዳለ አስረድተዋል፡፡

አባ ሰረቀ ማኅበረ ቅዱሳን በመምሪያ ከቀረበለት ጥያቄ ለመሸሽ ታላላቅ አባቶችን በፍርድ ቤት መክሰሱን፣ ይህም የጥቂት አመራሮች ፍላጎት መሆኑን በመግለጽ የማኅበሩ ብዙኀን አባላት ለማነሣሣት እየሞከሩ ነው፡፡ ሰሞኑን ወደ አደባባይ የወጣውን በማኅበሩ ውስጥ የተከሠተ አለመግባባት የተመሠረተባቸውን ክስ ለማድበስበስ ሊጠቀሙበት እየጣሩ ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡ ከዚህ አኳያ አባ ሰረቀ የውስጠ-ማኅበር አለመግባባቱን ከዐውድ ውጭ እየወሰዱ በመበዝበዝ የማኅበሩን አባላት ልብ ለመብላት የሚሞክሩበት ከፋፋይና የአዛኝ ቅቤ አንጓች ፕሮፓጋንዳ እንደማይሠራላቸው የማያሻማ መልእክት ሊተላለፍላቸው እንደሚገባ ደጀ ሰላም ታምናለች፡፡

31 comments:

Anonymous said...

አባ ሰረቀ የመከላከያ አቅጣጫ እንደማያዋጣው ስለገባው ሌላ መፈትሄ ያገኘ ቢመስለውም እውነት እውነትነቱን አይለቅም፡፡

Anonymous said...

woye anchi Bete kirestian, sintun chaleshew

Anonymous said...

Ewunet yetefabete zemene new yederesenew.Egiziabehere becherenetu betechrstianene yitebikelene, egnanem yitebeken, le abatochem lebona yistachew.

Anonymous said...

Yes indeed እውነትም አዛኝ ቅቤ አንጓች !

Anonymous said...

ልጆችን የሚጠብቅ እረኛ አሰዳጃቸው ሲሆን ያሳዝናል :: አስታርቆ ክሱን ቢያስነሱ እንደአባትነታቸው መልካም በሆነ ነበር
እሳቸውም/አባሰረቀ/በሰው አይመኩም ነበር በእግዚአብሄር እንዲመኩ ቢመክሯቸውም ጥሩ ነበር አሁን የያዙት አካሄድ እኮ ...አይመልሰኝ አይነት ይመስላል ለማንኛውም ለሁላችንም ልቦና ይስጠን አፅራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን አሜን

Anonymous said...

Matt,
it seemes a good idea but there is hidden secret beyond aba sereke. 'terter kegenfo weste aytefamena senter' dengel mariam mestirun tefetaw.

Anonymous said...

Truth is pushed & challanged 2 z maximum before it Shines like Sun!
And here also z issue is letting some people 2 reviele their true anti-stand more clearly,like Aba Paulos
So MK should b happy with ups & downs,coz
'Linega sil Yichelimal'
(AGE)

Dawit said...

የአባሰረቀ ልጆቻቸው ስላሴ አትበሉ ብለው ሲያበቁ አሁን ደግሞ ስላሴን አትመኑ አላልንም ብለው እርፍ አሉት፡፡ ይህ የተቀበዘበዘና ማረፊያ ያጣው ልባቸው በገሃድ በመታዎቁ አይናችሁ ላፈር ተብለው ግብራቸው ጥሏቸዋል፡፡
አባ ሰረቀም ማን እደሆኑ እሳቸው ስለነገሩን እናቃቸዋለን፡፡ ክርስቲያኑን የማይወክሉ ነገር ግን በጥቂት መሰል አባቶቻቸው የተነሱበትን አላማ ለማሳካት ቦታውን እንዲይዙ ተደርጎ ሰይጣናዊ ስራ ለመስራት ደፋ ቀና እያሉ የሚገኙ ናቸው፡፡
በዚህ ግብራቸው የማህበሩን አባላት በግዜው የተፈጠረውን ችግር ተጠቅሞ አገኛቸዋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፡፡ ዳቢሎስ የሰውን ልጅ ከጣለበት መንገድ ይልቅ የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆች የድህነት መንገድ እጅግ ድንቅ ነበር፡፡ አባ ሰረቀ እኛ ይህንን ከጌታችን ተምረናል፡፡ እርሶ የሚጠበቅቦትና የሚያዋጣዎት የንስሃ መንገድ መከተል ነው፡፡ ምክንያቱም ስራዎ እጅግ ክፍ ነውና፡፡
እውነተኛ ፍርድ ከእግዚአብሔር ነውና እሱን እንጠብቃለን፡፡ ይሁን እንጂ የተጀመረውንም ክስ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እስከፍጻሜው ማድረስ ግድ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የማህበሩም አባላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችም አቋማቸው አንድ ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችንን ከመናፍቃን መጠበቅ፡፡
እግዚአብሔር መናፍቃንን ከቤታችንን ያርቅልን፡፡

Anonymous said...

Eunet hule tigefalech.Gin Ewunetegna Dagnaallena tashenifalech. Esti Egziabiher LebeteKirstiyan Endihum Le MK Yemibejewun Endiyaderig Enileminewu.
Weladite Amilak Bemilijawa Atileyen!

Anonymous said...

It is time for those who/double face/brought the problem to MK are you happy now??? If it helps what you said show us that members of hmmmm .......proceed this legal case to the finally point unless please back MK to the orginal. Tired of double agenda

danf said...

balafaw yasatawut astayayat ba ethiopia wust ya hig yabalayinat manor alamanor yamiragagatibat naw biye nabar indalkutim honowal yahig yabalayinat ba ethiopia wust indalela aragagitanal. iwnatagnawun fird elshaday kahonaw kA ISRAEL AMLAK INTABIKALAN KAMDRAWI FIRD BIYAMALTUM KASAMAYAWI FIRD GIN MANIM AYADNACHAWUM

Anonymous said...

Ayiiiii dn Daniel!!! Amlak yikir yibelih, libonawun yisith. What you messed up helped Aba Serke indirectly. Now, they found a reason to challenge MK becasue of your wrong deeds.

Please, dn Daniel come back to your heart as you are currently on the wrong side of history of challenging Tehadiso.
You have to work with MK and Sunday schools in stead of running alone for the sec of becoming a famous person.

You have never written any thing in your blog about Tehadiso and the Awasa case but you blame others.

May God help our church and the MK association.

Tazabi

Anonymous said...

"አባ ሰረቀ የውስጠ-ማኅበር አለመግባባቱን ከዐውድ ውጭ እየወሰዱ በመበዝበዝ የማኅበሩን አባላት ልብ ለመብላት የሚሞክሩበት ከፋፋይና የአዛኝ ቅቤ አንጓች ፕሮፓጋንዳ እንደማይሠራላቸው የማያሻማ መልእክት ሊተላለፍላቸው እንደሚገባ ደጀ ሰላም ታምናለች፡፡"

ደጀ ሰላሞች ይህ የኔም የጸና አቋም ነው። ነገር ግን አሁን ያሉት የማኅበሩ አመራር በግትርነታቸው ከቀጠሉ አሳዛኝና አሳፋሪ ክስተት መፈጠሩ አይቀርም። በአዲስ አድማስ ላይ የወጣው እገዳ እውነት ከሆነ የማናውቀው ሴራ አለ ማለት ነው። ለማኅበሩም በማሰብ አይመስልም። ማንም የማኅበሩ እውነተኛ አገልጋይ ውድቀቱን አይመኝም። እንኳን አገልጋዩ ከማኅበሩ በሆነ መንገድ ስለ ቤተክርስቲያኑ የተሰበከ እውነተኛ ክርስቲያን ሁልጊዜም እድገቱን የሚመኝለት ነው። በብዙሃኑ የቤተክርስቲያን አለኝታነቱን ሲያስመሰክር ቆይቷል። ይህ ሊቀጥልም ይገባዋል። የተደበቀ የሚባል ነገር የለም። እውነትን የያዘ ሁሌም በሰዎች ፊት ብርሃኑ ሲበራ ይኖራል። ማኅበሩም ብርሃን ሲያበራ የሚያስችል አቅም አለው። ምን አልባት ይህን ለማጨለም ሆን ተብሎ ወይም ሳይታወቅ መነገድ የተጀመረ ይመስላል። በጊዜ መንቃት ጥሩ ነው። ማኅበሩ ብዙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፈታኝ ታሪኮች አስተምሮናል፤አስነብቦናል፤ተርኮልናል እንዲሁም ሰብኮናል። አሁን በተግባር ፈተናው ራሱ ላይ የመጣ ይመስላል። እውነትን ይዛ ቤተክርስቲያን ለዛሬ እንደ ደረሰች ሁሉ ማኅበሩም እውነትን እየመሰከረ መቀጠል ይኖርበታል። ያልተጻፈ ታሪክ፤የሌለ እውነት ለመፍጠር የተነሱበት ካሉ በጊዜ መንቃት አለበት። የመረጃ ዘመን መሆኑን ማኅበሩ በደምብ የሚያውቅ ይመስለኛል። ስለዚህ ውሸትን ይዘው አይናችሁን ጨፍኑ እናሞኛችሁ እንደሚሉት እንደ እነዚያ ራሱን ማውረድ ያለበት አይመስለኝም። ለእኔ ፈተናው በዝቶበት መጥፋት ካለበትም እውነትን ይዞ ቢጠፋ፤ እውነትን ይዞ ቢፈራርስ፤እውነትትን ይዞ ቢሰቃይ ከቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አንድ ጉልህ የሆነ ምዕራፍ ይዞ ተሻገረ ነው የምለው። ስለ እውነት ተቋሙን ቢያጠፉት በሰዎች ልብ የዘራውን የእውነተኛ ወንጌል ፍሬ ማንም ሊያወጣው አይችልም። እንዲያውም እየተጠቀሰ ይኖራል እንጂ። የባሰ ነገር ቢመጣ፤ ይህም ይቻላል ብለን ከተስማማን አሁን ያለውን ነገር መስመር ማስያዝ አስፈላጊ ነው። መስመር ሳያሲዙ በዙሪያው በተሰበሰቡና ውስጠ ወይራ ምክር በሚለግሱ ሰዎች እየተገፋፉ የማይሆን መንገድ መከተል አደጋ አለው። አደጋውም ማኅበሩን ሲያስወቅሰው አይኖርም። ነገር ግን ማኅበሩን እየመሩ ወደዚህ አቅጣጫ የከተቱት ወንድሞችና እህቶች ጥፋታቸው ለትውልድ ሲዘከር የሚኖር ይመስለኛል። እግዚአብሔር ከዚህ ይጠብቃቸው። ልቦና ሰጥቶ ማዕበሉን ጸጥ ሊያሰኝ የሚችል የማረጋጊያ ቃል ከእነዚህ አመራሮች እንዲወጣ አምላክ ይርዳን።
መከፋፈል ከሰይጣን እንጂ ከእግዚአብሄር አይደለም። ድርቅናም እንዲሁ። እኒህ ሰዎች ህሊና አላቸው ብዬ አስባለው። ፊት ለፊታቸው ወደ የት እየሄዱ እንደሆን ህሊናቸው ያውቀዋል። ከሃዲዱ እንዳያወጡን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ችግር ካለም ለአባላቱ ድምጻቸውን አሰምተው ይጩሁ። እንሰማቸዋለን። ድረሱልን ይበሉ። ካለበለዚህ ምንም ችግር የለም፤ የጠላት ወሬ ነው እያሉ ይዘውን መሰመጥ ከጀመሩ አደጋ አለው። አደጋውም ቀላል አይደለም። ችግር ሲመጣ በአለማዊው እንኳ ምሩን የተባሉት ሰዎች ችግሩን ጠቅሰው፤መክረው ዘክረው ለማስተካከል ይሞክራሉ። ካቅም በላይ ሲሆን፤ አቅም ያለውን ጠርተው ቦታውን ይለቃሉ። ማኅበሩ እጅግ ጥበበኛና አቅም ያላቸው አባላት በስሩ አሉት። እኒህ አመራሮች አእምሮአቸውን ሰብሰብ አድርገው ወደ ውስጥ በመመልከት እኒህን ሰዎች ያግኙአቸው። ይግሩን ማንም ከአባልነት ውጭ የሆነ መጥቶ ሊፈታለት አይችልም። ቢፈታም ለራሱ እንዲመቸው አድርጎ ነው። እናም እንዲሁ ስሙን ብቻ ለማኖር የምሯሯጥ እንዳይሆን አደራ።

ድንግል ሆይ አሳስቢ።

Anonymous said...

Let us be strong. Mahibere Kidusan should continue and look for all legal ways. God bless all of us.

Anonymous said...

MK ewunet le betekirisitiyan yekome kehone aba sereke berehaninin bicha sayihon ke kunichow yalutin lehulum neger minchi yehonutin abune pawulosin fird bet megeter neberebet, esachew esikalu dires negeru ayiteramina bitasebibet

Anonymous said...

ሰው አባሰረቀን ይከሳል እርሱ እኮ የደረቁ ግንድ አንድ ጭራሮ ነው።
ወይ አርፎ መቀመጥ ነው አለበለዚያ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን ከገባችበት ከባድ መከራ ሊታደግ የሚችለውን ፣ የብዙዎችን ሰማእትነት የሚጠይቀውን መራራ ግን መጨረሻው በእግዚአብሔር የሚጣፍጠውን እውነተኛ ትግል መጀመር ነው።
አይ አንች ኢትዮጽያ/ተዋሕዶ ምነው የጀግንነታችን ወኔ ጥሎን ጠፋ ወኔችን ሸሸን።ጀግኖችሽ ምንኛ መካኖች ሆነው ቀሩ።ምነው ሰው ጠፋብሽ?አይ ....ምነው ቴዎድሮስን በወለድሁት ምነው በላይን በወለድሁት ምነው ጼጥሮስን በወለድሁት አይኔ በእንባ እየታጠበ ማሕፀኔ ደረቀ ወይኔ ተዋሕዶ.......

Anonymous said...

The small thief get covered by the big thief.I hope they will fight when they share the profit.This is shame for aba paulos.This shows his leadership sides with thiefs and dogs.mk should be wise before going to court because the court,serke,and aba paulos are one and the same.we know the result before the procedure.who win today?theoretically

Temelkach said...

To my understanding the root of the problem of our church is Paulos. Sereke is just one of the million branches. No matter how hard we struggle we are not going to solve this problem as far af the root exists.

Let us try harder to work against the root please!! or else we will end up like nothing. Yes we are nothing with out Orthodox Tewahdo!!!!!!!!!TEKATELN IKO!!!!!!!

Anonymous said...

To my understanding the root of the problem is paulos not sereke.
sereke is one of the millions of branches to this man.
No matter how many branches we deal with and fight againts, we are not moving an inch from the problem. We will still be there talking and doing nothing!


Please let us deal with the root of the problem. I don't believe it is the wish of God for this man to be in this position. I simply don't because loving God has no intention at all for us to be in never ending problem.
paulos has to go!!!!!!!!!!!!!!

Man yazewal said...

ጠቅላይ ሚኒስቲራችን አቶ መለስ ዜናዊ በዚች አገር ማንም ሰው ከሕግ በላይ አይደለም ሁላችንም ከሕግ በታች ነን የሚሉትን አነጋጋር የፍትህ ሚኒስቲሩ በቤት ክርስቲያን ስም ከላይ እስከ ታች የሚሰራውን ወንጀልና ስም ማጥፋት ለመከላከል ጥረት የሚያደርጉትን በሕግ ሊያሳፍራቸው ይገባል፤

Anonymous said...

+++ don't post this one b/c I don't want brothers and foes alike to make this a center of discussion again.

Here we go. this was what I was concerned about. you should never have posted that messy document. we are here now paying the price for a silly mistake. I don't know what you can do to undo the tragedy.

Lib yisten

Kesis Wendemseshaa said...

የዚህ ደብዳቤ ግልባጩ ሲነበብ የሁለቱ ጉዳይ በመጣራት ላይ እያለ አባ ሰረቀም መግለጫ መስጠቱ ተገቢ አልነበረም እንደሚል ገብቶኛል። ስለዚህ ግልባጩ ለሚዲያዎችም ተነቦ መግለጫው ወቅቱን ባለመጠበቁ ስሕተት ነበረበትና ይታረም ብለው ይዘግቡት። ይህንን ሎጂክ ፓትርያርኩና መንግሥት መዘንጋታቸው ግን.... በተለይም ኢቲቪና ቪኦኤ

Anonymous said...

ደጀሰላሞች, ሰሞኑን እጅግ እጅግ እጅግ እጅግ ትልቅ ጥፋት አጥፍታችኋል፤ ችኩሎች ሆናችኋል። የዳንኤል ክብረትን የማንአለብኝነት ጽሑፍ ለጥቂት ሰዓታትም ቢሆን ማውጣታችሁ እጅግ ከባድ ጥፋት ነው። ይሄን ሁሉ የፈጠረው የእናንተ መቸኮልና የዳንኤል ጽሑፍ ነው። በማደራጃ መምሪያው ስር ነን እያልን የማደራጃ መምሪያውን ሐላፊ መክሰስ ምን ማለት ነው? ለሚሰማውስ ትንሽ አይሰቀጥጥም? የሚያዋጣ ጦርነትስ ነው? ሌላ ዘዴ ጥፍቶ ነው? አሁንስ እናንተ ማህበረ ቅዱሳንን በዘዴ ለማፍረስ የተላካችሁ እየመሰለኝ ነው።

Anonymous said...

ከአባ ሰረቀ በስተጀርባ ምን ማን እንዳለ የሚያረጋግጥ ውሰኔ ነው፡፡
የምድሩን ፍርድ በዚህ መልክ ሸወዳችሁት እንበል
እናንተ የምታስተምሩን እውነተኛውን የሰማይ ፍርድስ እንዴት ትሸውዱት ይሆን ?

lizib Tekelemariam (D.n) said...

እዉነት አትመነምን
ይደር ይዋል እንጂ እዉነት አትመነምንም።ለእዉነት ናፋቂዎች ያለች ተስፋ ነች። ነገር ግን ስትጠወልግ ስትለመልም የፈጀችበትን ጊዜ ላስተዋለዉ ሰላምና እረፍት የሚነሱ ብዙ ጉዳዮች ይነሳሉ። ወንበዴዎች አድርባዮች ባለችዉ አነስተኛ የጊዜ ክፍልፋይ ዉስጥ ሕይወትን የመሰለ ታላቅ ነገር፣ተቋምን የመሰለ ታላቅ ድርጅት ሀገርን የመሰለ ታላቅ ክብር መናዳቸዉ አይቀርም።ይህ ሁሉ ግን በራስ ወዳዶችና ቀሳጢዎች የሚመጣ ፈተና ነዉና የታሪክና የትዉልድ ነቀርሳ ጥሎ ያልፋል።በተለይ በኣሁኑ ጊዜ በእናት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተጋረጠዉ ፈተና እዉነቱን ከሚያቀጭጩ መናፍቃን፣ለሆዳቸዉ ካደሩ ዘራፊዎች መሆኑ ግልጽ ቢሆንም እዉነት እስክትወጣ በምእመኑ መካከል የሚያሳድረዉ ተጽዕኖ ቀላል ግምት የሚሰጠዉ አይሆንም። እንደሌሎቹ፤ ኃይል እንደሚቀናቸዉ የሃይማኖት ተቋማት ለረከሰና ለከፋ ጥፋት ክርስቲያኑን ህዝብ እየመሩተ እንደሆነ ጣልቃ የሚገቡ የህግም ሆነ የመንግሥት ኃላፊዎች ደጋግመዉ ሊያስቡበት ይገባል። ለአንድ ግለሰብ ይልቁንም በኑፋቄና በክህደት ቤተ ክርስቲያንን ለሚያምስ ሰዉ ተብሎ የብዙዎችን አንገት የሚያስደፋ ሥራ መሥራት ድፍረት ከድፍረትም አልፎ ወንጀል ነዉ። በዚህ ሳምንት በዲ/ን ዳንኤል ክብረት የተሰነዘረዉ አስተያየት በማህበረ ቅዱሳን አባላትና በማህበሩ ላይ ተጽእኖ አለዉ ብሎ የሚገምት ካለ ስህተት ነዉ። እንደ አስተያት ዲ/ን ዳንኤል የፈለገዉን የመሰንዘር፣ የመናገርና የመጻፍ መብት እንዳለዉ ማንም ሰዉ ሊያዉቀዉ ይገባል ። እንደ ማህበር ግን የዲ/ን ዳንኤል ክብረት አስተያየቶች እዉነትንና የማህበሩን ቀና አገልግሎት ሊያዛቡ አይችሉም።ይህ የሚያሳየዉ ማህበረ ቅዱሳን በግልጽ በአደባባይ ሲሳሳት በሌላ ሳይሆን በራሱ አባላት ሊተች እንደሚችል ነዉ። ዛሬ በይፋ አዉድ ይዉጣ እንጂ በሁለት አሥርት አመታት ተሞክሮዉ በዉስጡ አለመግባባቶች ሲከሰቱ በሰከነ ዉይይትና ተግባቦት የሚፈታ እንደሆነ ከማህበሩ አባላት ዉጭ የሆኑ የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ተጋባዥ እንግዶች ሳይቀሩ የሚያዉቁት ነዉ። የዛሬዉን ለየት የሚያደርገዉ ግን ለብዙዎች ተነባቢ በሆነ መንገድ መለቀቁ ነዉ። ይህ የአንድ የዲ/ን ዳንኤል ክብረት አስተያያት ከሁለት መቶ ሺ ያላነሰ አባላት ለያዘ ማህበር ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ይገባል። እንደ እኔና መሰሎቼ ግን ምንም ነዉ። አባላቱ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያኑ ብሎም ለሀገሩ ካለዉ ፍቅር አንጻር ሲመዘን እንደ ፈተና እንደማይቆጥረዉ እርግጠኛ ነኝ። ገና ብዙ ለመጓዝ የሚጥር ትዉልድ በአጭር የሚፈታ ወኔ የለዉም። ተስፋዉን የሚያቀጭጭ ዓላማዉን ሊንድ የሚችል አይኖርም። እዉነትና ታሪክ ግን ሁሌም ይኖራሉ። ይህ ዓለምና ትዉልዱ እስኪያልፍ። ምናልባት የዲ/ን ዳንኤል ክብረት በማህበሩ ዉስጥ ከነበረዉ ሰፊ አገልግሎትና ቆይታ አንጻር ዜናዉ አስደንጋጭ ቢመስልም ከቤት ዉስጥ የሚነሳ እሳት እንዳለ ለተረዳ ማጥፊያዉን ለማቅረብ ጊዜ አይወስድበትም። የዚህ እሳት አደጋ መከላከያዉም ጾምና ጸሎት ነዉ። እንበርታ።

ማህበሩን ለሚጠሉና የቤተ ክርስቲያንን የወደፊት አገልግሎት ለማጨለም ለሚጥሩ አነስተኛ ሻማ በርቶላቸዋል። ይሁን እንጂ እዉነት እዉነት ናት፡፡ ዛሬም ነገም ወደፊትም። ያሰባሰበን የማህበረ ቅዱሳን ዓላማ ለእናት ቤተ ክርስቲያናችን መበጀቱ እንጂ ሌላ አለመሆኑን ስለ ምናዉቅ በዚህ ጠላት ይፈር።

Anonymous said...

አይ ደጀ ሰላም -- ስማችሁ ደጀ ሰላም ተባለ እንጂ ብጥብጥ ሳትወዱ አትቀሩም

Anonymous said...

tegremalachehu dn daneil kiberten endeamelak setamelku ahunn degimo ende derg aweredachehut ayee ethiopiyanoch gudd eko new yesletan kimeyaaa daniel eko ewenetun new yaseredan ebakachehu edemena tenaa yesetew

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ ስንት ዘመን እንደቀረዎት የትኛው መልአክ ይንገርዎት ? መቶ ሃያ አመት አለን ያሉት የኖህ ዘመን ሰዎችን ታሪክ አስተምረውን ነበረ፡፡ ዛሬ እርስዎም ከነርሱ የባሱ የለየልዎት ሆኑ፡፡ ዛሬ የዘሩትን ነገ እንደሚያጭዱ ከዘነጉት ቆይተዋል፡፡ ይህችን ቤ/ክ የሚያስዳድራት እኮ እግዚአብሔር ነው!! መቼም ቢሆን እርሱ አይተዋትም ነገር ግን በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ይከብሩባታል ወይንም ይኮነኑባታል፡፡ በቤ/ክ ታሪክ እንደተማርነው ቤ/ክ ከፈተና የተለየችበት ጊዜ አልነበረም ወደፊትም አይኖርም ነገር ግን እሰከ መጨረሻው ትኖራለች፣ ታሪክም ይለወጣል ነገ ደግሞ የቤ/ክ ወርቃማው ዘመን ይመለሳል!!! የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን!!!

Anonymous said...

dejeselamoch ebakachihu hulachinm yebetekirstiyan lijoch ande honen tehadson yemiyaramdutn yemnleyibet menged fiteruln. patriarku bebete krstiyan lay eyayele yemetawn yetehadso werera meketa eyehonu new. kezi belay masreja ket yimta?
mk ebakachu beand lib honachu lebetecrsiyan siru adera!

Anonymous said...

Who ever wrote this,"ሰው አባሰረቀን ይከሳል እርሱ እኮ የደረቁ ግንድ አንድ ጭራሮ ነው።
ወይ አርፎ መቀመጥ ነው አለበለዚያ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን ከገባችበት ከባድ መከራ ሊታደግ የሚችለውን ፣ የብዙዎችን ሰማእትነት የሚጠይቀውን መራራ ግን መጨረሻው በእግዚአብሔር የሚጣፍጠውን እውነተኛ ትግል መጀመር ነው።
አይ አንች ኢትዮጽያ/ተዋሕዶ ምነው የጀግንነታችን ወኔ ጥሎን ጠፋ ወኔችን ሸሸን።ጀግኖችሽ ምንኛ መካኖች ሆነው ቀሩ።ምነው ሰው ጠፋብሽ?አይ ....ምነው ቴዎድሮስን በወለድሁት ምነው በላይን በወለድሁት ምነው ጼጥሮስን በወለድሁት አይኔ በእንባ እየታጠበ ማሕፀኔ ደረቀ ወይኔ ተዋሕዶ..." PLEASE LEAVE TEWAHDO ALONE.
I am diappointed reading your comment. You are confused that you couldn't differentiate b/n heavenly institiution "the church" and "a government". Either you are emotional or do know what write,or may be you are not christian at all. Insulting a COMOS, a priest is not a character of good christian. I do not believe you are a member of MK.
Tewahdo belongs to our lord Jesus Christ. He died for her,he bought her by his blood, he paid the full price to own her. So she belongs to him. We believe that he is in charge and sees every details of what is going on. But you want to have "ቴዎድሮስን" and "በላይን", for what. If you refer back to the teaching of Tewahdo, those "courageous Ethiopians" died or killed in a battle defending our motherland, and as far as I know they are not "Tewahdo's SEMAITAT". I know you are trying to play politics hiding in the church, Please for the sake of her savior leave TEWAHDO ALONE. If you have a hidden agenda go somewhere else. No matter how hard it looks/is, TEWAHDO IS in safe and good hands, her GROOM as the word of God teaches us,
"Nothing in all creation is hidden from God’s sight. Everything is uncovered and laid bare before the eyes of him to whom we must give account", HEBREW 4:12.

Anonymous said...

በእውነት በእኛ ዘመን ደስ አያሰኙም የተባሉት ወራት/ዓመታት/ ከእያንዳንዳችን ሕይወት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያንና በሀገር ላይ እየኾነ የምንሰማው አሳዛኝ ነገር ሁሉ መፈጸሙን ስንመለከት ከመቸውም ይልቅ ቆም ብለን ልናስብና ልናስተውል የሚገባን ጊዜ እንደኾነ ይሰማኛል፡፡ አዎን የቤተ ክርስቲያን ፈተና ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ በየዘመናቱ መልኩና ቅርጹ ቢለያይ እንጂ ፈተናው የተቋረጠበት ጊዜ የለም፡፡ ወደፊትም ይኖራል፡፡ የሚያስቱትንም ኾነ የሚሳሳቱትን እግዚአብሔር ልቡናቸውን ይመልስልን፡፡ ነገር ግን በመጣው የፈተና ማዕበል ተጠርጎ ላለመወሰድ እያንዳንዳችን በጠንካራ ዐለት ላይ የተመሠረተና የማይናወጽ የክርስትና ሕይወት ሊኖረን ይገባል፡፡ ይህ ከኾነ በስንጥቅ ዐለት ውስጥ ያለችን ትል የማይዘነጋ አምላክ እኛንም ኾነ ቤተ ክርስቲያናችንና ሀገራችንን ከፈተናው ማዕበል ይታደገናል፡፡ ስለዚኽ ማንም ያሻውን ሊያደረግ ቢሞክር ከእግዚአብሔር ፍርድ አያመልጥም፡፡
ይልቁንም በሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የተመሰለ ክርስያናዊ ሰውነታችንን ጠብቀን በጸሎትና በእንባ ብንለምን ለሰብኣ ነነዌ የተለመነ አምላክ ለእኛም የመሐሪነቱን ጠል ለእኛም አይነሳንም፡፡
ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በአንድም በሌላም መልክ ተሰግስገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ደመወዝ እየበሉ ነገር ግን ለሌላ ዐላማ የተሰለፉትን ልና ያሰበውን ኩላሊት ያመላለሰውን የሚያውቅ አምላክ ለንሥሓ ዕድሜ ሰጥቶ ከስሕተት ወደ እውነት እንዲመልስልን እኛም ከሐሳውያን መምህራንና ቀሳጥያን እንድንጠበቅ እናንተስ ወንድሞቻችን ራሳችሁን በተቀደሰች ሃይማኖት አንጻችሁ ኑሩ ተብሎ በቅዱስ መጽሓፍ እንደተነገረን ራሳችንን በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ታንጸን ልንዘጋጅ ይገባናል፡፡ ይኽን ማድረግ ከቻልን ደግሞ የቤተ ክርስቲናችን ያልኾኑትን ለይተን ስለምናውቅ ከአባቶቻችን የተማርነው ይኽን አይደለም ብለን አስረግጠን በመናገር የምናሳፍርበት የዕውቀት ጋሻ ሊኖረን ይገባል፡፡ ለዚኽም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት አይለየን፡፡
አሜን!
በእውነት በእኛ ዘመን ደስ አያሰኙም የተባሉት ወራት/ዓመታት/ ከእያንዳንዳችን ሕይወት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያንና በሀገር ላይ እየኾነ የምንሰማው አሳዛኝ ነገር ሁሉ መፈጸሙን ስንመለከት ከመቸውም ይልቅ ቆም ብለን ልናስብና ልናስተውል የሚገባን ጊዜ እንደኾነ ይሰማኛል፡፡ አዎን የቤተ ክርስቲያን ፈተና ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ በየዘመናቱ መልኩና ቅርጹ ቢለያይ እንጂ ፈተናው የተቋረጠበት ጊዜ የለም፡፡ ወደፊትም ይኖራል፡፡ የሚያስቱትንም ኾነ የሚሳሳቱትን እግዚአብሔር ልቡናቸውን ይመልስልን፡፡ ነገር ግን በመጣው የፈተና ማዕበል ተጠርጎ ላለመወሰድ እያንዳንዳችን በጠንካራ ዐለት ላይ የተመሠረተና የማይናወጽ የክርስትና ሕይወት ሊኖረን ይገባል፡፡ ይህ ከኾነ በስንጥቅ ዐለት ውስጥ ያለችን ትል የማይዘነጋ አምላክ እኛንም ኾነ ቤተ ክርስቲያናችንና ሀገራችንን ከፈተናው ማዕበል ይታደገናል፡፡ ስለዚኽ ማንም ያሻውን ሊያደረግ ቢሞክር ከእግዚአብሔር ፍርድ አያመልጥም፡፡
ይልቁንም በሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የተመሰለ ክርስያናዊ ሰውነታችንን ጠብቀን በጸሎትና በእንባ ብንለምን ለሰብኣ ነነዌ የተለመነ አምላክ ለእኛም የመሐሪነቱን ጠል ለእኛም አይነሳንም፡፡
ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በአንድም በሌላም መልክ ተሰግስገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ደመወዝ እየበሉ ነገር ግን ለሌላ ዐላማ የተሰለፉትን ልና ያሰበውን ኩላሊት ያመላለሰውን የሚያውቅ አምላክ ለንሥሓ ዕድሜ ሰጥቶ ከስሕተት ወደ እውነት እንዲመልስልን እኛም ከሐሳውያን መምህራንና ቀሳጥያን እንድንጠበቅ እናንተስ ወንድሞቻችን ራሳችሁን በተቀደሰች ሃይማኖት አንጻችሁ ኑሩ ተብሎ በቅዱስ መጽሓፍ እንደተነገረን ራሳችንን በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ታንጸን ልንዘጋጅ ይገባናል፡፡ ይኽን ማድረግ ከቻልን ደግሞ የቤተ ክርስቲናችን ያልኾኑትን ለይተን ስለምናውቅ ከአባቶቻችን የተማርነው ይኽን አይደለም ብለን አስረግጠን በመናገር የምናሳፍርበት የዕውቀት ጋሻ ሊኖረን ይገባል፡፡ ለዚኽም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት አይለየን፡፡
አሜን!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)