August 1, 2011

የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የመቃብር ቦታ ተገኘ


(ሪፖርተር ጋዜጣ፤ ሐምሌ 24/2003 ዓ.ም፤ ጁላይ 31/2011):- በፋሺስት ኢጣሊያ ከ75 ዓመት በፊት ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ የተቀበሩበት ቦታ በአዲስ አበባ በስተደቡብ በለቡ አካባቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስታወቀች፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፉሪ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ተክለ ማርያም ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት ከሆኑ በኋላ የተቀበሩት ፋሺስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረው “ሙኒሳ ጉብታ” ላይ ነው፡፡


የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. ሰማዕቱን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ፣ ቀብራቸው በምስጢር መፈጸሙ መዛግብት እንደሚያስረዱ ያስታወሰችው ቤተ ክርስቲያኗ፣ የእኚህን ታላቅ አባት ቀብር በምስጢር የተፈጸመበት ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ምሁራን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የታሪክ ሰነዶችን ሲመረምሩ ቢቆዩም፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ “ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በምስጢር ቀበሯቸው” ከሚል ጠቅላላ ፍንጭ ያለፈ ምንም ዓይነት የተረጋገጠ ማስረጃ ሳይገኝ ቆይቶ ነበር ብላለች፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ከአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ “ለቡ” ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሰፈሩ ምዕመናን በአካባቢው ተወልደው ካደጉ አረጋውያን ጋር ባደረጉት ማኅበራዊ ግንኙነት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፋሽስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረው “ሙኒሳ ጉብታ” ላይ መቀበራቸውን ከወላጆቻቸው ሲሰሙ እንዳደጉ በእርግጠኝነት አስረድተዋቸዋል፡፡

የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን ባነሣ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከጦር ሥፍራ ለመለየት ስላልሆነላቸው፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው የመርዝ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሔደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሰላሌ አርበኞች በመስበክም ይታወቃሉ፡፡

አርበኞች አዲስ አበባን በሁለት አቅጣጫዎች ከሰሜናዊ ምዕራብ (ባሕር) እና በደቡባዊ ምሥራቅ (ሊባ) አቅጣጫ ለመቆጣጠር ውጊያ በከፈቱበት ጊዜ የተማረኩት አቡነ ጴጥሮስ፣ ለፋሺስት እንዲገዙ፣ የኢጣሊያ መንግሥት ገዢነትንም አምነው አሜን ብለው እንዲቀበሉ ግፊት ቢያደርጉባቸውም፤ እምቢኝ ለአገሬና ለሃይማኖቴ ብለው ለሰማዕትነት ያበቃቸውን የሞት ጽዋ መቀበላቸው በታሪክ ተመዝግቧል፡፡

ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የራሷን ሶች በ1921 ዓ.ም. በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ጊዜ ስታስ (ስትሾም) አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡

በተያያዘ ዜናም አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበትን 75ኛ ዓመት ለማሰብም ቅዳሜ ሐምሌ 23 ቀን 2003 ዓ.ም. ከ8 ሰዓት ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዐውደ ጥናት መካሔዱንና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁራን በሰማዕቱ ስ ዙርያ አራት ጥናቶችን ያቀረቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በ1875 ዓ.ም. የተወለዱት አቡነ ጴጥሮስ፣ “ስ ዘምሥራቀ ኢትዮጵያ” ተብለው፣ “ራሱ በሽሎ መለስ፣ እግሩ አቦክ ፈረንሳዊ ወሰን ድረስ (ጅቡቲ)” 21 አካባቢዎችን ያስተዳድሩ ነበር፡፡

በሔኖክ ያሬድ
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)