August 30, 2011

“የሚሌኒየሙ አዳራሽ ጉባኤ ገንዘብ ደብዛው ጠፍቷል” (ነጋድራስ ጋዜጣ)

(ነጋድራስ፣ ቅጽ 08 ቁጥር 293፤ ዐርብ፣ ነሐሴ 20 ቀን 2003 ዓ.ም/ READ IN PDF)፡- “ገቢው ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናትና ጠዋሪ ቀባሪ ለሌላቸው አረጋውያን መርጃ” በሚል ታኅሣሥ 25 ቀን 2002 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደገባ አለመታወቁን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወቃል፡፡ የ(ነጋድራስ)ጋዜጣው ዘጋቢ በጉዳዩ ላይ ያሰባሰባቸውን መረጃ ይዞ ይመለከታቸዋል የተባሉ ወገኖችን ለማነጋገር ባደረገው ጥረት፣ በወቅቱ “ቅድስት ማርያም የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ” በመባል ይታወቅ የነበረው ማኅበር ተነሣሽነቱን መውሰዱን አረጋግጧል፡፡

የአሮጊቷ ሣራ» ወለደች ዐዋጅ ተሐድሶ ዘመቻ የጥፋት ፈትል እንደማጠንጠኛ

(ሐመር 19ኛ ዓመት ቁጥር 2):- በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በብሉያትና በሐዲሳቱም የምትነሣው ሣራ አበ ብዙኃን ሥርወ ሃይማኖት የምንለው የአብርሃም ሚስት ነች፡፡ እግዚአብሔር ለአብርሃም የብዙዎች አባት እንዲሆን ቃል ኪዳን ሳይገባለት በፊት፣ በመካንነት ታዝን፣ ተስፋም አጥታ ትተክዝ በነበረችበት ጊዜ ሦራ ትባል ነበር፡፡

August 27, 2011

ፓትርያርኩ ዱባይ ናቸው

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 27/2011, READ IN PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከሐሙስ ጀምሮ ዱባይ ገብተዋል፤ በዱባይ ከኤምሬትባለሥልጣናት ጋራ ይወያያሉምእመኑንም አግኝተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሊባኖስ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ ፈቃድ ሳይገኝና በሊቀ ጳጳሱ ሳይባረክ በባር ዱባይ በቅዱስ ሚካኤል ስም ‹‹ቤተ ክርስቲያን አቋቁሜያለሁ›› ያለው ሕገ ወጥ ቡድን አገልጋይ የሆነ ቀሲስ ተስፉ እንዳለ የተባለ ካህን በዱባይ-ሻርጃ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ምእመናን በደረሰበት ተቃውሞ ከቤተ መቅደ መከልከሉ እና ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያንም እንዲወጣ መደረጉ ተገለጸ፡፡

August 20, 2011

የዜና ቤተ ክርስቲያን ልዩ ዕትም ርእሰ አንቀጽ ሲኖዶስ አይወግንም

(ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ 56 ዓመት ቁጥር 121፤ ነሐሴ 2003 ዓ.ም/ PDF)በአሁኑ ጊዜ የጠቅላላው ኅብረተሰብ የየዕለቱ የመነጋገሪያ አጀንዳና ጊዜ ማሳለፊያ ከሆኑት ነገሮች ዋና ዋናዎቹ ሦስት ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ሦስት ነገሮች የእግር ኳስ ጨዋታ፣ ገመና ድራማ እና በቤተ ክርስቲያናችን ስም ተጠቃሚዎች የሆኑት ማኅበራትና ፍንዳታ ሰባክያን በሃይማኖት ሽፋን በነጻ ፕሬሶች የሚያደርጉት የጥቅም ሽኩቻና ውዝግብ ነው፡፡

August 16, 2011

ስለ ተሐድሶ እና ተያያዥ ጉዳዮች የዘሪሁን ሙላቱ ቃለ ምልልስ


“የሃይማኖታችን ጉዳይ የፓትርያርኩ ብቻ አይደለም” የሚለው ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ከቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ  የመጀመሪያ ዲግሪውን በሥነ መለኮት፣ ሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር በፊሎሎጂ ትምህርት ተመርቋል። በአሁኑ ወቅትም ደግሞ የዶክትሬት (ፒ.ኤች.ዲ) ጥናቱን በማገባደድ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ወቅታዊ ሁኔታ እና ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከተለው አስተምህሮ ዙሪያ ከዕንቁ መጽሔት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።  TO READ IN PDF, CLICK HERE.

ስለ "ብፁዕ አቡነ ሚካኤል" የማ/ቅዱሳን ዘገባ

(Mahibere Kidusan):- የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ነሐሴ 8 ቀን 2003 ዓ.ም አርፈዋል። በአንብሮተ ዕድ ከተሾሙበት ከነሐሴ 22 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ በአሁኑ ሀገረ ስብከታቸው የተሾሙ ሲሆን በመካከል ለተወሰኑ ወራት የወላይታ፣ ዳውሮና ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል።

የሐሞት ጠጠር ሕመም የነበረባቸው ብፁዕነታቸው የቀዶ ጥገና ሕክምናቸውን በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በመከታተል ላይ የነበሩ ሲሆን በመካከል ከሰመመናቸው መንቃት ሳይችሉ እንደቀሩ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ቀጣይ የአስከሬን ምርመራ ከተደረገ በኋላ ምክንያቱ ሊገለጽ እንደሚችልም ይገመታል።

August 15, 2011

የማ/ቅዱሳን መልእክት ምን ያስተምረናል?


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 15/2011/ READ IN PDF)፦ ከዚህ በታች የተቀመጠውና ማ/ቅዱሳን በወርሃዊ ልሳኑ በሐመር መጽሔት ላይ ባወጣው መልእክቱ ማህበሩ አጠንክሮ ለያዘው “ፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ” እንቅፋት በሆኑ ነገሮች ላይ በድጋሚ ማብራሪያ እና አቋሙን አሳይቶበታል። በተለይም “ተሐድሶ” የለም ለሚሉ አካላት መኖሩን ለማሳየት ሞክሯል በዚህ ጽሑፍ። ጽሑፉ “ተስፋ እየቆረጠ ያለው ተሐድሶመሠሪ ኃይል ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ተላላኪዎቹ በኩል ሊነዛ የፈለገው ተራ ማታለያተሐድሶ የለምተሐድሶየሚል ነገርን የፈጠረው ማኅበረ ቅዱሳን ነውየሚለውን አባባል” በጽኑ ይኮንናል። እነዚህ “ተላላኪዎች” ያላቸውን አካላት ማንነትን ግን እንድንገምት ለአንባብያን ትቶልናል።

(ሰበር ዜና)፦ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አረፉ


ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 14/2011)፦ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በአብርሃም እቅፍ ያሳርፍልን። ለወዳጅ ዘመድ በሙሉ መጽናናትን ያድልልን።
(ዝርዝሩን ወደፊት እናቀርባለን።)

August 12, 2011

የጠ/ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክት፤ እንወያይበት


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 12/2011/ READ IN PDF)፦ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በቅርብ ወራት ከሾማቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት  አቶ ልዑልሰገድ ግርማ (ሥልጣነ ክህነት ካላቸው አቶ በማለታችን ይቅርታ፣ ስላላወቅን ነው) ሰሞኑን በድረ ገጽ ባወጡት በሚከተለው ጽሑፋቸው ብዙ የመወያያ ነጥቦችን አንስተዋል። በተለይም በቤተ ክህነቱ ውስጥ ስለተንሰራፋው ብልሹነት

August 11, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁለት መግለጫዎች ሰጠ


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 10/2011)፦ ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ እና አንገብጋቢ ጉዳዮችን በተመለከተ ሁለት መግለጫዎች ሰጠ። ቀደም ሲል በዕቅድ ከተያዘለት ጊዜ (ነሐሴ 23 - 24 ቀን 2003 ዓ.ም) ቀደም ብሎ ሐምሌ 30 እና ነሐሴ1/2003 ዓ.ም በተጠራ ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አስቸኳይ ጉባኤ ውጤት እና......

August 9, 2011

የሚዲያዎች ትኩረት ማ/ቅዱሳንን ይጎዳዋል ወይስ ይጠቅመዋል?

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 9/2011/ TO READ IN PDF, CLICK HERE)፦ ማ/ቅዱሳን ላለፉት 19 ዓመታት ድምፁን አጥፍቶ እና አንገቱን ሰበር አድርጎ አገልግሎቱ ላይ ብቻ በማተኮር የዘለቀ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘሩ ትችቶች እና ስም ማጥፋቶች በጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ መጻሕፍት እና ድረ ገጾች በማስተናገድ ላይ ያለ ማኅበር ነው። የሚዲያ ሽፋኑ በፊትም የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው መልክ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ ግን አያውቅም ነበር። አገር ውስጥ በሚታተሙ ጋዜጦች እና መጽሔቶች እንዲሁም ድረ ገጾች በሰፊው ስማቸው ከሚነሣው መካከል፣ ምናልባት ከመንግሥት ቀጥሎ፣ ማ/ቅዱሳን የመሪነቱን ቦታ ይዟል።

Priest fills Church’s void after test of faith

(By Chris Hong, August 8, 2011):- Despite its odd location in a small commercial center next to a bar on Ninth Street, the St. Nicholas of Myra Orthodox Church isn’t out of the ordinary. On Sundays, 35 to 50 people cram into the makeshift church to worship. Afterward, the congregation shares a meal. They value community outreach, preparing food once a month for the LINK community kitchen.

የአቦይ ስብሐት “አስተያየት” እና አንድምታው

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2011/ TO READ IN PDF, CLICK HERE)፦ የኢሕአዴግ ፖለቲካ መሐንዲስ የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ ባለፈው ባስነነቡን ጽሑፋቸው ስለ ቤተ ክርስቲያን (እርሳቸው ቤተ ክህነት እያሉ አጠቃለውታል) ብዙ ቁምነገሮች አንሥተዋል። ደጀ ሰላም ለረዥም ጊዜ ስትዘግብበት፣ ርእሰ አንቀጾችን እና ሐተታዎችን ስታቀርባበቸው በነበሩ እና አሁንም በቀጠለችባቸው ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ብያኔዎችን በመስጠት ውይይቱን አንድ ርምጃ አራምደውታል። አቶ ስብሐት በዚህ በዓይነቱ ልዩ በሆነው ጽሑፋቸው የሚከተሉትን ነጥቦች አንሥተዋል። እነዚህም ነጥቦች፦

August 7, 2011

(ሰበር ዜና) ማ/ቅዱሳን በይቅርታ እና በዕንባ ችግሩን ፈቷል፤

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 7/2011)፦ ቀደም ሲል በዕቅድ ከተያዘለት ጊዜ (ነሐሴ 23 - 24 ቀን 2003 ዓ.ም) ቀደም ብሎ በአስቸኳይ እንደተጠራ በተገለጠው የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አስቸኳይ ጉባኤ የቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003 ዓ.ም ስብሰባ ማበሩ በገጠሙት ውስጣዊ ችግሮች ላይ በጥልቅ ከተወያየ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

August 6, 2011

የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬና ነገ ያካሂዳል

  • “ጽሑፉ ዲያቆን ዳንኤልን በሕግ የሚያስጠይቁ እና ከአባልነት እንዲወገድ የሚያደርጉ ጉዳዮች የተነሡበት ቢሆንም ወንድማችን ነው፤ አሳልፈን አንሰጠውም” (/ን ሙሉጌታ ኀይለ ማርያም)
  • በማኅበሩ የአዲስ አበባ ማእከል ከሐምሌ 29 - ነሐሴ አንድ ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የሦስት ቀን ጸሎተ ምሕላ ታውጇል፤
  • ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሰሜን አሜሪካ ቆይታውን አቋርጦ ተመልሷል፤
 (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 6/2011/ READ IN PDF)፦ ቀደም ሲል በዕቅድ ከተያዘለት ጊዜ (ነሐሴ 23 - 24 ቀን 2003 ዓ.ም) ቀደም ብሎ በአስቸኳይ እንደተጠራ የተገለጠው የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ ጠቅላላ ስብሰባ ዛሬ ሐምሌ 30 እና ነገ እሑድ ነሐሴ አንድ ቀን 2003 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ “የንኡሳን ማእከላት ተወካዮችን የሚያጠቃልል የሥራ አመራር ጉባኤ ጠቅላላ ስብሰባ በየስድስት ወሩ አንድ ጊዜ በዋናው ማእከል ጽ/ቤት ይደረጋል” በሚለው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሰበሰብ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 15/ዠ ያዛል።  

August 5, 2011

አሰግድ ሣህሉ “ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ” አለ


  • በስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት አባ ሰረቀ ከሀገር ሊወጡ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2011; READ IN PDF)፦ ወደ ቤተ ክርስቲያን የውስጥ መዋቅር በመግባት የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን ዓላማ ለማሳካት ከሚፍጨረጨሩትና ከእነርሱም መካከል እንደ ዋነኛ ከሚታዩት የወቅቱ የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ቅጥረኞች አንዱ ሆነው አሰግድ ሣህሉ “ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ” ሲል በገዛ አንደበቱ መናገሩ ተሰማ፡፡ አሰግድ ይህን ምስክርነት ስለ ራሱ የሰጠው ከነገ በስቲያ ቅዳሜ ለንባብ እንደሚበቃ በተጠቆመ አንድ መጽሔት ሰሞኑን በሰጠው ቃለ ምልልስ ነው፤ ንግግሩንም በአንድ ወቅት በ‹ተሐድሶ› ጉዳይ ላይ ለጠየቀችው አንዲት ሴት የመለሰው መሆኑ ተገልጧል፡፡

August 3, 2011

አቡነ ጳውሎስ "ተሐድሶ" ላይ የሚካሄደው እንቅስቃሴ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲደረግበት መመሪያ ሰጡ

  • ዛሬ በመንበረ ፓትርያኩ አዳራሽ የተሰበሰቡ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የስብከተ ወንጌል ተጠሪዎች በሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ንባብ መመሪያውን እንዲሰሙት ተደርጓል፤ ጥያቄ ለማቅረብና አስተያየት ለመስጠት ተከልክሏል፤ መመሪያው በተመለከተ የሚዘግብ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ልዩ እትም ከዋና አዘጋጁ ዕውቅና ውጭ እየተሰናዳ መሆኑም ተሰምቷል፡፡
  • “ቤተ ክህነቱ እንደቀድሞው ዘመን ለችግሩ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ የችግሩ አካል ወደሆነበት ጊዜ መድረሳችን ፈተናውን አክብዶታል፡፡ ሲኖዶሱ የተሐድሶ ችግር ስለ መኖሩ በመረጃ ከተረዳ በማስተካከል፣ በማውገዝና በመለየት መፍትሔ ማበጀት ይገባዋል፡፡. . .ችግሩ በማእከላዊ አካሄድ የማይፈታ ከሆነ ምእመኑ በተናጠል ወደ መፍትሔ ፍለጋ ያመራል፡፡ ይህ ደግሞ በጣም መጥፎና አደገኛ አካሄድ ይሆናል፡፡” (ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለ‹ዕንቊ› መጽሔት)
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 3/2011/ READ IN PDF)፦ ከወርኀ ጥቅምት 2003 ዓ.ም አንሥቶ በስፋት ተጀምሮ ጥልቀት እያገኘ በቀጠለውና ምእመኑ ከዳር እስከ ዳር በሃይማኖታዊ ቀናዒነት የተደራጀበት የፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ እንቅስቃሴ፣ “የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን ሰላም ለማወክ የሚካሄድ” እንደሆነና ይህም “በስም አጥፊነት በሕግ ከማስጠየቅ ያለፈ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም” ሲሉ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አስጠነቀቁ፡፡

August 2, 2011

(ሰበር ዜና) ማኅበረ ቅዱሳን በአባ ሰረቀ ላይ የመሠረተው ክስ ለጊዜው እንዲቋረጥ ታዘዘ

  • ትእዛዙ ፓትርያርኩ ለፍትሕ ሚኒስቴር የጻፉትን ደብዳቤ መነሻ ያደረገ ነው::
  • የማኅበሩ የሕግ አገልግሎት የፍርዱ ሂደት የሕግ የበላይነትን በሚያስከብር አኳኋን የሚቋጭበትን መንገድ እያጤነ ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 2/2011/ READ IN PDF):- በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በፈጸሙት የስም ማጥፋት ድርጊት የመሠረተባቸው ክስ እንዲቋረጥ የፍትሕ ሚኒስቴር አዘዘ፡፡ ትናንት ለዐቃቤ ሕግ በተጻፈውና በሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ፣ “አባ ሰረቀ ብርሃን በተከሰሱበት የስም ማጥፋት ወንጀል ማጣራት የምንፈልገው ስላለ ክሱ ለጊዜው ተቋርጦ መዝገቡ እንዲላክልንሲል ትእዛዝ መሰጠቱን ያስረዳል፡፡

August 1, 2011

የዜና ቤተ ክርስቲያን፤ ርእሰ አንቀጽ


የነጻነት በዓለ ሢመት (ርእሰ አንቀጽ)
/ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ 56 ዓመት ቁጥር 121፤ ሰኔና ሐምሌ 2003 ዓ.ም, READ IN PDF/፦ የአምስተኛው ፓትርያሪክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 19 ዓመት የፓትርያሪክነት በዓለ ሢመት የአንድ ግለሰብ የሥራ ፍሬ የሚገለጥበት፣ ክብርና ዝናው የሚንጸባረቅበት ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችን ለ1600 ዘመናት ያህል በግብጻውያን የአገዛዝ ቀንበር ሥር ስትማቅቅ ኑራ ነጻ የወጣችበት ዘመን የሚታሰብበት በዓለ ሢመት ነው፡፡ ስለዚህ ብሔራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ እመርታን ያስገኘችበት በዓለ ሢመት በመሆኑ መንፈሳዊ ነጻነትን ሙሉ በሙሉ የተጎናጸፍንበትን ይህን የነጻነት በዓለ ሢመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ብቻ ሳንሆን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት የሆን በሙሉ በታላቅ መንፈሳዊ ሐሤትና በታሪካዊ ትዝታ ልናከብረው ይገባናል፡፡

የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የመቃብር ቦታ ተገኘ


(ሪፖርተር ጋዜጣ፤ ሐምሌ 24/2003 ዓ.ም፤ ጁላይ 31/2011):- በፋሺስት ኢጣሊያ ከ75 ዓመት በፊት ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ የተቀበሩበት ቦታ በአዲስ አበባ በስተደቡብ በለቡ አካባቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስታወቀች፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፉሪ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ሳሙኤል ተክለ ማርያም ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት ከሆኑ በኋላ የተቀበሩት ፋሺስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረው “ሙኒሳ ጉብታ” ላይ ነው፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)