July 22, 2011

"ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን" (By Mesfin Negash)(አቦይ) ስብሐት ነጋ
"በምርጫ 97 ማግስት ድንጋጤ ያርበተበው ፓርቲ/መንግሥት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሰርና በመፍታት ስራውን አላጠናቀቀም ነበር። ይህን ተከትሎ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ “ለምን ተሸነፍን? የጦስ ዶሮዎቹን አድኑ” የሚል አውጫጪኝ ተካሂዶ ነበር። ይህ በየክልኩ የደኅንነት አካሎችና በፓርቲው መዋቅር (አንድም ሁለትም ናቸው) የተካሄደው “ጥናት” አስደናቂ ውጤቶችን አስገኝቷል። ከእነዚህ ውጤቶች አንዱ “በአማራ እና በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢሕአዴግ ለደረሰበት ሽንፈት፣ ተቃዋሚዎች ላገኙት ድጋፍ ሚና ከነበራቸው አካሎች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው” የሚል ነበር።" (ከጽሑፉ የተወሰደ)
 (To Read in PDF, Click HERE)
“ዝነኛው” አቦይ ስብሐት የዛሬ ሦስት ሳምንት ገደማ በ“ፍትሕ” ጋዜጣ ለወጣባቸው ትችት የሰጡት መልስ አስተያየት የሚጋብዝ ነው።  የ“ፍትሑ”  አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም አቦይ ስብሐት ሕዝብ በተሰበሰበበት የተናገሩትን ለንባብ ማቅረቡ የሚጠቅም ነው፤ “ሰውየው መዘባረቅ ልማዳቸው ነው” ብሎ አለመተዉን ለማድነቅ ነው። (ተጨማሪ ምልልሶችን በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል።)


ስብሐት በይፋዊው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከፓራላማ አባልነት የዘለለ ቦታ ይዘው ባይታዩም በተግባራዊው ዓለም ግን ከአገሪቱ ስውር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችአንዱ ናቸው። እናም ተለቅ ያለ ቢዝነስ ለመጀመርም ሆነ በፖለቲካው ባህር ላይ በመጋኛ ሳይመቱያለስጋት ለመራመድ የአቦይ ስብሐትንና የእመት ምክርና ቡራኬ የሚጠይቁ ብዙ ሰዎች እንደነበሩም እንዳሉም የታወቀ ነው። አሁን ደርሶ የሩቅ ተመልካች ነንሊሉን ሞከሩ እንጂ በቤተክህነቱም ጉዳይ ምእመናን ደጅ የሚጠኑላቸው፣ ሰይጣናችሁን አስታግሱልን፣ ምን ብናደርገው ይሻላል?” እየተባሉ መፍትሔ የሚጠየቁ አዋቂዎችናቸው።

አቦይ ስብሐት ከብዙዎቹ የህወሓት ሹማምነት በተለየና በግሌ በማደንቀው ሁኔታ ከሕዝብ ጋራ የመገናኘት እድል አላቸው። የሕይወት ዘይቤያቸውም ለዚህ የተመቸ ነው፤ ወይም ደግሞ ይሁነኝ ብለው ይህን አኗኗር ተከትለዋል። እዚህ ዝርዝር ውስጥ ገብቶ በሚወራው ነገር ላይ አስተያየት መስጠት አልፈልግም፤ አያገባኝም፤ ለውይይታችንም ጠቃሚ አይደለም። ሰውየው በአጭሩ ቢያንስ የተወሰኑ ሰዎችን አመለካከት፣ ፍላጎትና ብሶት የደኅንነቱ ሜክአፕ ሳያሳምረው በቀጥታ የማግኘት እድል አላቸው። ከዚሁ የአኗኗር ዘይቤ የሚመነጭ በሚመስል ሁኔታም ሐሳባቸውን በየአጋጣሚውየመግለጽ ልምድ አካብተዋል።

ጋዜጠኛ ተመስገን እንዳስነበበን አቦይ ስብሐት ሁለት አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች አንስተዋል። እርሳቸውም ያላቸውን አቋም በድጋሚ በሰጡት መልስ አረጋገጥዋል። የአድዋ ጉዳይ እና የቤተ ክህነት ጥገኝነት። ወደ ዝርዝሩ ከመግባቴ ከመግባቴ በፊት ስብሐት በድፍረት የተናገሯቸውና እኔም የምስማማባቸው አጠቃላይ እውነታዎች እንዳሉ ላረጋግጥ። ለዚህም ስብሐትን ማመስገን ይገባኛል። ማንም ሊቃወማቸው የማይችላቸውን አጠቃላይ እውነታዎች አስከትለው የሚያቀርቡት ዝርዝር ግን ራሳቸውንና ድርጅታቸውን ከተጠያቂነት ለማዳንና ለማድበስበስ የቀረቡ ናቸው። (የተመስገንን ቀዳሚ ጽሑፍና የአቦይ ስብሐት ነጋን መልስ የፌስቡክ ወዳጄ ዘላለም እዚህ ለንባብ አቅርቦት አግኝቸዋለሁ።)

1. አድዋ
የአገራችን ታሪክ እንደማንኛውም አገር በሒደት በጥናትና በምርምር የሚጠሩ ብዙ ነገሮች እንዳሉት ብዙዎቻችንን እንስማማለን። ይህ አቦይ ስብሐት የተለየ ዋጋ የከፈሉለትና የሚከፍሉበት በኢትዮጵያ ላይ የወረደ ቁጣ ወይም የምኒልክ ሴራ አይደለም። እንኳን እንደኢትዮጵያ ረጅምና ብዙ ሕዝቦች የተሳተፉበት ታሪክ ቀርቶ የትናንትናዎቹ አዳዲስ አገሮችም ከታሪክ ትርጉምና አተራረክ ውዝግብ አልወጡም። ከዚህ ውጭ ያለው አንድም ፖለቲከኞች የሚጽፉት ታሪክ ነው፤ አለዚያም ሕዝባዊታሪክ ነው። ሁለቱም ያስፈልጋሉ፣ መኖራቸውም አይቀርም፤ የታሪክ ጥናትና ምርምርን ግን አይተኩም። ሦስቱም በተቻለ መጠን በየክልላቸው ቢታቀቡም መታደል ነው። ከዚህ አጠቃላይ መነሻ አንጻር የኢትዮጵያ ታሪክ በሰፊና ጥልቅ ምርምር እየጠራየሚሄድ ገጽታ እንዳለው አምናለሁ፤ ከስብሐትም ጋራ እስማማለሁ።

የአድዋው ጉዳይ አቦይ ስብሐትና ፓርቲያቸው በብሔር መነጽር ብቻ እንደገና ሊጽፉት የሚሞክሩት የኢትዮጵያ ታሪክ አንዱ ምእራፍ ነው። የነስብሐት ችግር ከዚህ በፊት የተጻፈው ሁሉ ስሕተት ነውየሚል መሆኑ እንጂ በተጻፈው ውስጥ ያለው እውነት በምርምር ይጣራ የሚል ጥያቄ ቢነሣ አግባብ ነው። አድዋን ልዩ የሚያደርገው ነገር ካለ እነስብሐት የአድዋ አካበቢ ተወላጆች ስለሆንን ታሪኩን የመጻፍ መብቱ የእኛ ብቻ ነውበሚል ስሁት እምነት የታጀበ መሆኑ ነው። እውቀት ከጠመንጃ አፈሙዝ ይመነጫል የሚለውን ብሒል ብቻ ያስታውሰናል።

ከጽሑፋቸው ለመረዳት እንደሚቻለው የአቦይ ስብሐት ችግር የታሪክን ፖለቲካ (Politics of History) ከታሪክ፣ ከታሪክ ጥናት እና አጻጻፍ ጋራ እያምታቱ መመልከታቸው ነው፤ ሆን ብለው አይመስለኝም። ስብሐት እንዲህ ይላሉ፤

ስለኢትዮጵያ ተጽፎ የሚገኘው ታሪክ በጣም የተዛባ ቅጥ ያጣ ሕዝብ ለሕዝብ የሚያጣላ ታሪክ ነው፡፡ ተጽፎ የምናገኘው የቤተ መንግሥት ታሪክ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ አይደለም፡፡ በአንድ ሕዝብ አንድ ቋንቋ አንድ ሃይማኖት ወዘተ አመለካከት የተጻፈ የሕዝቦች እኩልነትን መሠረት ያላደረገ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ችግር እየፈጠረ ያለ ነው ታሪካችን፡፡ስለዚህ ታሪካችንን በትክክል ማስቀመጥ የሃገራዊ ደኅንነትና ልማት አንዱ መሣሪያችን ነው፡፡

ሕዝብን የሚያጣላውታሪኩ ነው ወይስ ታሪኩ የተጻፈበት መንገድ? “ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለማረጋገጥየሚያስችለው የታሪክ አጠናን እና አጻጻፍ ምን አይነት ነው? ታሪካችንን በትክክል ማስቀመጥማለት ምን ማለት ነው? አንድ የታሪክ ጽሑፍ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን የሚያረጋግጥወይም ታሪካችንን በትክክል ያስቀመጠመሆኑን የሚወስነው ማነው? አንድ የታሪክ ተመራማሪ እና/ወይም ጸሐፊ ይህንን የአቦይን አስተሳሰብ እንዲከተል የሚያስገድደው ምን መነሻ አለ? አቦይ ስብሐት ትክክልየሚሉትን ታሪክ አንድ የታሪክ ተመራማሪ ወይም ተራ ዜጋ ባይቀበለው ምን ችግር አለው? “የቤተ መንግሥት ታሪክመጻፉ በራሱ ስሕተት ነው? የአቶ ስብሐት ኢቲቪ ከኢትዮጵያ ቀደምት ነገሥታት ጸሐፊዎች የባሰ አሳፋሪ የቤተ መንግሥት ታሪክጸሐፊ አይደለም እንዴ? ለመሆኑ የቤተ መንግሥትታሪክ ራሱ የሕዝብ ታሪክ አካል አይደለም ወይ? “ቤተ መንግሥቱአንድን የታሪክ ክስተት የተመለከተበት አንጻርና የመዘገበበት/የተረከበት መንገድስ ቢሆን የአገራችን ታሪክ አካል አይደለም ወይ፣ ለታሪክ ምርምርስ እጅግ አስፈላጊ ግብአት አይደለም ወይ? በየትኛው የፊውዳልማኅበረሰብ እነስብሐት የሚንቆጫቆጩበት የሕዝብ ታሪክተጽፎ ያውቃል? ታሪክን ለመጻፍ ከቤተ መንግሥቱ የተሻለ አቅምና እድል ያለው ተቋም ወይም ግለሰብ ባልነበረበት የቀድሞ ማኅበረሰብ የተለየ የታሪክ መዝገብ አለማግኘታችን ምን ያስገርማል፣ ምንስ ያናድዳል? “ሕዝቡአቅምና አጋጣሚ ቢፈቅድለት ኖሮ እኮ ታሪኩንጽፎ ያቆይልን ነበር። ለመሆኑ የሕዝብ ታሪክማለት ምን ማለት ነው? አሁን እነአቦይ የሚያጽፉት ታሪክ አዲስ የቤተ መንግሥትታሪክ አለመሆኑን ማን ይነግረናል?

ብዙ ጥልቅ ትንተና የሚሹ፣ አልፎም ወደ ታሪክ ፍልስፍና (philosophy of history) የሚጠቁሙ ጥያቄዎችን መደርደር ይቻላል። እነዚህን ጥያቄዎች በምሳሌነት የዘረዘርኩት እነአቦይ ስብሐት የሚያቀርቡት ጥያቄ በታሪክ ፖለቲካነቱእንጂ በደንበኛው የታሪክ ፍልስፍናና ጥናት መስክ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ለመጠቆም ያህል ብቻ ነው። ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለማረጋገጥብሎ ታሪክን የሚያጠና እና/ወይም የሚጽፍ ባለሞያ ስለመኖሩ ሰምቼ አላውቅም፤ አዳዲሶቹ የአገራችን የታሪክ ምሁራንእንደዚያ ያደርጉ ከሆነ በሒደት እናየዋለን። ያን ጊዜ የታሪክ ጥናት ዘርፍ ወደ ሽምግልናና ወደፖለቲካ ይሸጋገራል።

ለአገራችን የሚበጀው እነስብሐት እጃቸውን በተቻለ መጠን ከታሪክ ጥናትና አጥኚዎች ቢሰበስቡ፤ ብዙም የማያሻሙ ጠቃሚ የታሪካችንን ገጾች ለአገራዊ ማንነታችን ማጉያነት መጠቀም (“የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ነውኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ተገዝታለችእያሉ ከመዘላበድ መቆጠብን ጨምሮ)፤ የአካዳሚክ ነጻነትን አክብሮ በታሪካችን ላይ ግልጽ ምርምሮችና ውይይቶች እንዲካሄዱ መፍቀድ፣ ከዚህም አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ወደ ሕዝባዊ እውቀትነት መቀየር ናቸው። ቀሪው ጉንጭ አልፋ የታሪክ ፖለቲካክርክር ነው።

2. ከቤተ ክህነት እስከ ማኅበረ ቅዱሳን

. ቤተ ከህነቱ

አቦይ ስብሐት ከተናገሩት ሁሉ ብዙ የምስማማበት ነገር ያገኘሁት ስለ ቤተ ክህነቱና ስለጳጳሳቱ የገለጹት ነው። ለፍትሕጋዜጣ ከሰጡት መልስ ለማስታወስ ያህል፤
ለሁሉም ነገር ወሳኙ ውስጣዊ ሁኔታ ስለሆነ ኦርቶዶክስ ከመንግሥት ሳይለያይ ለመቆየቱ ዋናው ተጠያቂዎች የቤተክህነት ሐላፊዎች የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ መንግሥታቱ በሁለተኛ ደረጃ ይጠየቃሉ፡፡
ቤተክህነት ከመንግሥት ተጣብቆ በመቆየቱ የሃይማኖት ተቋምነቱ እየወደቀ መጥቷል፡፡ አሁንስ ሃይማኖትና ፖለቲካ በሕገ መንግሥት ደረጃ በጽኑ እምነት ከተለየበት ወዲህ ከደረሰበት ድቀት እያንሰራራ ነው ወይስ በነበረበት የጉዳት ደረጃ ነው ያለው? የአሁኑ ፓትርያርክ ሥራ ከጀመሩ ጀምሮ ስለ ቤተክህነቱ የሚወራው እጅግ በጣም ዘግናኝና አሳፋሪ የአስተዳደር ጉድለት ተነስተን ስናየው ግን በነበረበት የመዳከም ደረጃ ሳይሆን ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው የሚያሰኝ ነው፡፡
ጳጳሳቱ አይረቡም ያልኩበት ምክንያት ከዚህ አጠቃላይ መርህ ብቻ ተነስቼ አይደለም፡፡ አብዛኞቹ ከድሮ ጀምረው በአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር እንደሚያለቅሱ አውቃቸዋለሁኝ፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያለው ሥራ አልሠሩም፡፡ ለዚህ ነው አይረቡም ያልኩበት ምክንያት፡፡ አሁንም ልጨምርበትና ለእምነታቸው አልረቡም፡፡

ቋንቋውና አቀራረቡ ቢለያይም በእነዚህ የአቦይ ስብሐት አጠቃላይ ምልከታዎች ላይ አለመስማማት አልችልም። በዚህ የማይስማማ ካለ አንድም የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክና አሁን የደረሰችበትን አሳፋሪ ውስጣዊ ዝቅጠት የማያውቅ ነው፤ አንድም፣ እውነታውን ቢያውቅም በአደባባይ  የመነገሩን ሕመም መጋፈጥ የማይፈልግ ነው፤ አንድም፣ ፈጣሪ ተአምር እንዲሰራ በመመኘት በመጽናናቱን የመረጠ ነው፤ አለዚያም የምናወራው ስለተለያዩ ተቋማት ነው ማለት ነው። ይህ የመጨረሻው ሰው ከዚህ ቀጥሎ የተጻፈውን ማንበብ አያስፈልገውም።

የድቀቱ መታሰቢያ
አቦይ ስብሐት እንዳሉት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመንግሥት ጥገኝነት እንላቀቅ የሚሉቆራጥ ጳጳሳትን አላፈራችም፤ ጥቂቶች ቢኖሩም በብዙሃኑ ለእምነታቸው የማይረቡ” (ስለቋንቋው ከይቅርታ ጋራ) አበው ታፍነው ቀርተዋል። በውስጥም በውጭም ከሚያለቅሱት የሚበዙት የዚህ አበሳ ተካፋዮች ናቸው። በሃገረ ስብከቱ ሙስናን እስከመጨረሻ የተዋጋው ጳጳስ ማነው? ችግሩ ሲብስበት ስልጣኑን ትቶ ገዳም በመግባት በጸሎት ፈጣሪውን፣ በተቃውሞ ፓትርያርኩንና መንግሥትን ያስጨነቀው አባት ማነው? (መቼም ስለግብጹ አቡነ ሼኖዳ አልሰሙም አይባልም።) አቡነ መርቆሪዎስ በመንግሥት ተጽእኖና በገዛ ወንድሞቻቸው የሴራ ተባባሪነት ከሥልጣን ሲሻሩ የትኛው አባት እውነትን አደባባይ ቆሞ ተናገረ? የትኛው አባት ከመንበሩና ከክብሩ ይልቅ ለምእመኑ ሕይወት ቅድሚያ ሰጠ? ለመሆኑ አባ ጳውሎስን እንዲህ መረን የለቀቃቸው ማነው- ሲኖዶሱ አይደለም እንዴ? አባ ጳውሎስን ስለተቃወሙ ወንድሞቻቸው ሲደበደቡ፣ ሲታገቱ፣ እንደወንጀለኛ በለሊት ከቤታቸው ተወስደው ሲመረመሩ አሁንስ በዛያለው ቀናኢ አባት ማነው? በማግስቱ የጥፋቱን ፊት አውራሪ- አባ ጳውሎስን- ደጅ ለመጥናት ያልተሰበሰቡት ስንት ናቸው? ንጹሐን በአደባባይ ስለመሞታቸው አዝኖ ነፍስ ይማርለማለት በኀዘነተኞቹ ቤት የተገኙ ስንት ናቸው? ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱና ስለቤተክነቱ ጥፋት በአጥቢያው (በሃገረ ስብከቱ አላልኩም) ምህላ ያዘዘ አባት አለ? ዓለም ሞቱየተባሉ መነኮሳትና ጳጳሳት የዚህ ዓለም ኑሮ እንደሚያሳሳን ሁሉ ለስደት የሚሽቀዳደሙት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማን ትተው ነው? ምንስ ለማግኘት ነው? ከከሰረው ፖለቲካ ጋራ እየነፈሱ በብሔር ላይ የተመሠረተ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት የሚሽቀዳደሙት ያልሞቱጳጳሳት በምን ሞራል መንግሥትነ ይወቅሳሉ? የስነ ምግባሩ፣ የዘረኝነቱ፣ የሙስናውችግር እዚህ ዘርዝረን የምንጨርሰው አይደለም።  ስንቱን በመንግሥት ማሳበብ ይቻላል? ስንቱንስ ጥፋት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውእያሉ ራስን ማጽናናት ይቻላል? ከዚህስ በላይ ለእምነት አለመርባት ያለ አይመስለኝም።

አሁን ከአቦይ ጋራ እንለያይ። ስብሐት የመንግሥት ተጠያቂነት በሁለተኛ ደረጃ ነው ባሉት እስማማለሁ። ሃይማኖቱን፣ ቤቱን መጠበቅ መጀመሪያ የባለቤት ፋንታ ነው። ሌባ የሚጋበዘው በባለቤቱ አቅምና ቁርጠኝነት አንጻር ነው። ይህ ግን ሌባውን ከተጠያቂነት አያድነውም። ሌባው የአቶ አቦይ መንግሥት ነው። አባ ጳውሎስ እኮ ፊት ሳያዩ አይደለም ወደዚህ ደረጃ የደሱት። ልጆቻችን እስካሉ ምንም አንሆንምእያሉ ጳጳሳቱን የሚያስፈራሩት እኮ ፊት አይተው ነው። አቶ መለስን ጨምሮ አባ ጳውሎስን እንደ እዳ የሚመለከቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳሉ ይነገራል። ችግሩ ግን በዚሁ መንግሥት ውስጥ በጥቅም፣ በገንዘብና በደም የተገዙ ቀንደኛ ደጋፊዎችም አሉዋቸው። ለመሆኑ የጳጳሳቱ ድብደባና እገታ በፖሊስ ሳይጣራ የቀረው ለምንድን ነው? ይቺን የምታህል ቤተ ክርስቲያን አባቶች በአደባባይ መዋረድ መንግሥትን አይመለከተውም ነበር? ነገሩ ሌላ ነው፤ ጳውሎስ ከሙስና መሠረታቻው ሊፈናቀሉ የመሆኑ አደጋ ያሰጋቸው የመንግሥት አካላት አሉና በነፍስ ደረሱ።

የአቦይ ስብሐት መንግሥት አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያኑቱን እንደግል ንብረት ሲበውዙዋት፣ በብሔር ፖለቲካ ሲበጠብጡዋት ችግሩ ለሕዝብ ይተርፋልበሚል ቅንነትምክር ያልሰጠው ለምንድን ነው? በተቃራኒው በምርጫ 97 ማግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅሮች እስከ አጥቢያ ድረስ በፓርቲ አባላት ለሙላት የተከፈተው ዘመቻ የሕገ መንግሥቱን ቃል ኪዳን የሚያፈርስ አይደለምን? የአባ ጳውሎስ የሥልጣን ኢምፓየር ገና ሲነቃነቅ በነፍስ ደርሶ የታደገው በአቡነ አባይ” (ይቺ ስያሜ በቤተ ክህነቱ አዋቂዎች ለአቶ አባይ ፀሐዬ የተሰጠች ነች) የተመራው ቡድን የነፍስ አድን ጣልቃ ገብነት ስሙ ምን ይባላል? ደግነቱ አቦይ ስብሐት መንግሥት ተጠያቂ አይደለምአላሉም። ደረጃው አያጣላንም። መቋጫውም ቤተ ክርስቲያኒቱ ከገባችበት የውደቀትና የድቀት አዙሪት ለመውጣት የምትችለው መንግሥት የድርሻውን ከተወጣ ብቻ ነው። እስከዚያ ድረስ ግን በውድቀቷ ተባብሮ ከደሙ ንጹህ መሆን እንደማይቻል ግልጽ ነው።  ይህ የመንግሥት አፍራሽ ሚና በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጎልቶ ቢታይም ሌሎቹንም የሃይማኖት ተቋማት ለጥፋት እንደዳረገ አስታውሼ ወደ ቀጣዩ ጉዳይ ልለፍ።

. ማኅበረ ቅዱሳን

 አቦይ ስብሐት ስለ ቤተ ክህነቱና ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ሲዘረዝሩ በአጭሩ ጠቀስ ያደረጉት ሌላው ጉዳይ ስለማኅበረ ቅዱሳን ያላቸው ቀጥተኛ ትዝብትነው። ነገሩ እግረ መንገድየተነሣ ቢመስልም የአቶ አቦይ መንግሥት ሁለትና ከዚያ በላይ ሆናችሁ በተሰበሰባችሁበት ሁሉ እገኛለሁየሚል አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ቃል ኪዳን እንዳለው ለማሳየት ጥሩ ምሳሌ መሆኑን በቅርበት ስለማውቅ ላልፈው አልፈለኩም። አቶ ስብሐት እንዲህ ይላሉ በ ፍትሕጋዜጣ ላይ፤

እኔ እንደሚመስለኝ ባለኝ ቀጥተኛ ትዝብትም ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ ነው፡፡ ቀጥተኛ ትዝብቴ፣ የቤተክህነትን አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ ከመጫወት አፍራሽነት ይበዛበታል፡፡ አልፎ አልፎም ብልሽት እያዩ ዝምታ ይበዛል፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክነትም እንዳለበት ይወራል፡፡ ይህ ትክክል ከሆነ እጅግ በጣም የሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የሃገር ስርዓት ማለት ሕገ መንግሥት የመጣስ ክህደት ነው፡፡

ይህን የአቦይን አነጋገር የማኅበረ ቅዱሳን የወቅቱ ዋና ጸሐፊ ከሆነው ከመምህር ሙሉጌታ ኀ/ማርያም ሰሞነኛ ቃለምልልስ ጋራ ስታገናኙት ነገሩ የበለጠ ሳቢ (interesting) ይሆንባችኋል። ሙሉጌታ እንዲህ ይላል፤

“…እነአባ ሰረቀ ብርሃን [አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ መምሪያ ሐላፊ ናቸው] አገር ውስጥ በተቃዋሚነት ይከሱናል። ውጪ ስንሄድ ደግሞ የአቡነ ጳውሎስ ካድሬዎችተብለን የወቀሳ ናዳ ይወርድብናል። ማኅበረ ቅዱሳን የምንም ፖለቲካ አራማጅ አይደለም። እውነቱን ለመናገር አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸው። በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የምኅበረ ቅዱሳን ሥራ አስፈጻሚ መሆን አይችልም፤ አባል ሆኖ መቀጠል ግን ይችላል።…” (“ዕንቁመጽሔት የሰኔ 2003 እትም፤ ሙሉውን ቃለ መጠይቅ እዚህያገኛሉ።)

አቦይ ስብሐት እንደዋዛ” “ይነገራልበማለት የገለጹት ክስ በመነገርየሚቆም ሳይሆን መንግሥታቸው አቋም የያዘበት ጉዳይ ነው። ነገሩ በአጭሩ እንዲህ ነው። በምርጫ 97 ማግስት ድንጋጤ ያርበተበው ፓርቲ/መንግሥት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሰርና በመፍታት ስራውን አላጠናቀቀም ነበር። ይህን ተከትሎ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ “ለምን ተሸነፍን? የጦስ ዶሮዎቹን አድኑ” የሚል አውጫጪኝ ተካሂዶ ነበር። ይህ በየክልኩ የደኅንነት አካሎችና በፓርቲው መዋቅር (አንድም ሁለትም ናቸው) የተካሄደው “ጥናት” አስደናቂ ውጤቶችን አስገኝቷል። ከእነዚህ ውጤቶች አንዱ “በአማራ እና በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢሕአዴግ ለደረሰበት ሽንፈት፣ ተቃዋሚዎች ላገኙት ድጋፍ ሚና ከነበራቸው አካሎች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው” የሚል ነበር። ይህ ደግሞ  በሹክሹክታ የተነገረ፣ በለሆሳስ የተወሳ ጉዳይ አልነበረም። የየክልል አካላት ባዘጋጁት ሪፖርት ጥራዝ ተካቶ ለውይይት የቀረበ፣ የክትትል ትእዛዝም የተሰጠበት ነው። ይህ መረጃም ለማኅበሩ እንዲደርሰው ተደርጓል። ኮፒ ለማድረግ ባይፈቀድልኝም በወቅቱ ሪፖርቱን ከሁለቱም ወገን አግኝቼ በማኪያቶ አወራርጄዋለሁ።

ከዚያ በኋላ ማኅበሩ የደኅንነቱ አንድ ኢላማ ሆነ። አባ ጳውሎስና ጋሻ ጃግሬዎቻቸውም የበኩላቸውን ሐላፊነት ለመወጣት በቤተ ክህነቱ ስር ማንም የማያውቀው በወቅቱ የቤተ ክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ የሚመራ ኮሚቴአቋቁመው ሪፖርት አቀረቡ። ለማን አትሉም? ለመንግሥት የደኅነነት አካል። የሪፖርቱ ግኝት” “ማኅበረ ቅዱሳን ቅንጅት ነውየሚል ዝርዝሩ ሲታይ ከባልቴት ወሬ የማይሻል ዝንቅ ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ በአገራዊ እርቅ ያላት ሚና በሐመርመጽሔት መጻፉ የተቃዋሚ ደጋፊነት ማሳያ ሆኖ ዛሬ ድረስ የሚሰማው ወቀሳ ስሩ ከዚያ ይጀምራል። ለማንኛውም ማኅበሩ በማጉያ መነጽር ይመነጠር ገባ። በኋላም በሚያስተዛዝብ የታሪክ ግምገማ የቅንጅት ደጋፊዎችየተባሉ አንዳንድ አገልጋዮች በውሃ ቀጠነ ፊት ተነሡ፣ ከቦታቸው ተነሡ። ምጸቱንና ታሪካዊ ስላቁን ፍጽም ለማድረግም የማኅበሩን ዋና ጸሐፊ ለመሾም የብሔር ማንነት በውስጠ ታዋቂ ለመጀመሪያ ጊዜ መመዘኛእንዲሆን ተደረገ። ክፉ ቀንን ለማለፍየተደረገ ማጎንበስቢመስልም መርሕ አልባ ስሕተት ሆኖ ተመዘገበ። በተቃራኒው ደግሞ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ምን ያህን ያገጠጠ እንደሆነም ያሳያል።

የማኅበሩ አመራር በአንድ በኩል በአባ ጳውሎስ በሌላ በኩል በመንግሥት የመጣበትን ጫና ለማሳለፍ የመረጠው መንገድ ከሞላ ጎደል ትልቁን ሽፍታ ማስደሰትሆነ። እኔ እስከማውቀው ማኅበሩ በተቋም ደረጃ የትኛውንም ፓርቲ ወይም የፖለቲካ አቋም ደግፎ ወይም ተቃውሞ አያውቅም። ይብሱንም ብዙዎቹ አባላቱ ፖለቲካንእንደሐጢአት የመመልከት አዝማሚያ ይታይባቸው እንደነበረ በእርግጠኝነት አውቃለሁ። እንኳን ስለፖለቲካ ስለቤተ ክህነት ችግር ማውራት የማይፈልጉም ጥቂት አልነበሩም። ለማንኛውም ይህ እውነታ ማኅበሩን አልታደገውም።

ከዳር ቆሞ ነገሮችን በቅርበት ለሚመለከት ማኅበረ ቅዱሳን እና አባ ጳውሎስ (ከነሠራዊታቸው) መንግሥትን አለማስቀየም ብቻ ሳይሆን ማስደሰትም ጭምር የሕልውናቸው መሠረት ሊሆን እንደሚችል ማመናቸውን ይታዘባል። የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ሰሞኑን የገለጸው እውነትም በዚህ ማእቀፍ ውስጥ የሚታይ ነው። ዋና ጸሐፊው ማኅበረ ቅዱሳን የምንም ፖለቲካ አራማጅ አይደለም።ብሎ ማቆም ሲችል እውነቱን ለመናገር አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸው።ያለን ለምን ይሆን? ይህ ንግግር  እውነት እውነትነው? “እውነት ምንድን ነው?” አለ መጽሐፉ።

ጸሐፊው ይህን ያለን ከምን ተነሥቶ ይሆን? “አሁን ባለንበት አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ በየሥራ በስኩ በሚደርስበት ጫና የኢሕአዴግ አባል ያልሆነ ሰው ቁጥሩ ጥቂት ነው፤ ይህ ደግሞ በማኅበሩ አባለትም ዘንድ መንጸባረቁ አይቀርምሊለን ፈልጎ ይሆን? እንደዚያስ ቢሆን ተገዶ አባል የሆኑ ሰዎችን ወደው ያደረጉት አስመስሎ አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸውማለትን ምን አመጣው? “የኢሕአዴግ አባልና ደጋፊ የሆኑ በመካከላችን አሉበማለትና አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸውበማለት መካከል ያለው ርቀት ስንት ነው? እነአቦይን እንዲህ በአደባባይ ተናዞ ካላስደሰቱ እረፍት ማግኘት ስለማይቻል ይሆን? እርግጥ የአቦይ ስብሐት ወቀሳም እኮ ማኅበሩ በፖለቲካ ይገባልአይደለም፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መድረክነት ይታያልየሚል ነው። ችግሩ ተቃዋሚን መደገፉነው። የሕገ መንግሥት ክህደቱምእርሱ ነው፤ ተቃዋሚን መደገፍ።

አቡነ ጳውሎስ እና መንግሥት በተለያየ ምክንያት የሚጠረጥሩትና የሚፈሩት ማኅበር የድኀረ ምርጫ 97 አፈና አንድ ማሳያ ከመሆን አላመለጠም። ችግሩ ግን መንግሥትም ሆነ አባ ጳውሎስ ማኅበሩን የሚፈሩት በተሳሳተ ምክንያት መሆኑን ገና  አልተረዱትም። ምናልባትም ደግሞ ሁለቱም (መንግሥት እና አባ ጳውሎስ) ባላቸው ከፍተኛ የተጣራጣሪነትና የበቀለኝነት ልምድ ማኅበሩን ሳይጨርሱትእንደማይለቁት መስጋት ይቻላል። ማኅበሩ ካለው ኅብረተሰብን ለመለወጥ የሚያስችል እምቅ አቅም አንጻር የሁለቱም ፍርሃት ለመረዳት የሚከብድ አይደለም። የምስራቹማኅበሩ ይህን የማድረግ ተልእኮም፣ ራእይም፣ አመራርም ሆነ ብቃት የሌለው መሆኑ ነው። አቦይ ስብሐት ካሉትም በላይ የመፍትሔው አካል የመሆን ጉዞን ወደመጨረሱ በመቃረብ ላይ የሚገኝ፣ በእንግሊዝኛ የችግሩ አካል ለመሆን (ቤተ ክህነቱን ለመቀላቀል) በማዝገም ላይ ያለ ነው። የኦቦይ ስብሐትን ጽሑፍ ተከትሎ ከማኅበሩ አመራሮች ገሚሶቹ የአቦይን ቡራኬደጅ መጥናት መጀመራቸው የቤተ ክህነቱ ዘይቤ ግልባጭ ነው። እንደዚህም ቢሆን ግን ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለአገርም ጭምር ያበረከታቸውን አስተዋጽኦዎች አሳንሶ መመልከት ስሕተት ይሆናል። በቤተ ክህነቱ አያያዝ ቢሆን ያለፉት 20 ዓመታት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ቀብር በይፋ በተፈጸመ ነበር ማለት አስተዋጽኦውን ማጋነን አይመስለኝም።

አቦይ ስብሐት በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጡት የመንግሥት መልከ ብዙ ጣልቃ ገብነት በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በሌሎች ማኅበራዊ ተቋማት ውስጥ በማስከተል ላይ ያለው ቀውስ ሰፊ ዘገባ የሚወጣው ነው፤ በአጭር ጊዜ የሚፈታም አይደለም። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በፖለቲካና በሃይማኖት ጉዳዮች ጥናት ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች አካባቢውን እንዳይዘነጉት እንጂ በሒደት ብዙ እንደሚያስነብቡን ተስፋ አደርጋለሁ።

90 በመቶ የማያንሱት የማኅበሩ አባሎች ይህን ሁሉ የአስተዳደር ውጣ ውረድና ፖለቲካ አያውቁም፣ አይረዱም። ቢያውቁም በአይናፋርነትማለፍን ይመርጣሉ። በየዋህነት የሚያገለግሉት ፈጣሪ ቅንነታቸውንና እንባቸውን እንደማይዘነጋው ተስፋዬ ነው።

(ማስታወሻ፤ በቤተ ክህነቱ እና በማኅበረ ቅዱሳን ጉዳዮች ላይ በሰነዘርኩት ሐሳብ ቅር የሚሰኝ ቢኖር ብዙ አልገረመም። አንዳንዱ የቋንቋ አገላለጼ ጠንከር ያለ ቢመስልም ከችግሩ የሚያንስ እንጂ የሚበልጥ አይደለም። ከዚያም በላይ ጽሑፉ ባነሳቸው ሐሳቦች ላይ ማተኮሩ የበለጠ ይጠቅማል እላለሁ።)

ምንጭ፦
http://addisnegeronline.com/2011/07/%E1%88%B5%E1%89%A5%E1%88%90%E1%89%B5-%E1%8D%A3-%E1%8A%A8%E1%8C%B3%E1%8B%8D%E1%88%8E%E1%88%B5-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%8A%A8-%E1%88%9B%E1%8A%85%E1%89%A0%E1%88%A8-%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B3%E1%8A%95/

12 comments:

Anonymous said...

Dejeselam, ciao!!! I fear you will be blocked from Ethiopia forever. Zare degmo minun "Copy Paste" adirgesh asinebebishin? Minewa mimi, libam hugni enji-kifu qen eko new?

Anonymous said...

Denke gemgema new. Kemereh wech meserat gezeawi tekem beyasgegnme sebebu bezu newena tenkek...

Ben said...

wow Mesfin Just Wow! you nailed it about MK.I had this feeling for long time now esp after Sereqe hold his office. Now it make sense to me.
Thanks
Ben

MelkamKene said...

Dear Writer thank u all r true. God bless u!

Anonymous said...

Dear Mesfin,

We really missed you here in Ethiopia. We were enjoying your matured political and socio-cultural analyses. You are always unbaised and reasonable. I liked the way you criticised all EPRDF, Aba Pawulos and even Mahibere Kidusan. Hope when God wills, you will be back home to write freely and contribute better. As a University lecturer in Ethiopia, I believe that your articles could build many youth. I saw many College students were reading the ex-Addis neger regularly. It is a pity that it could not continue. I am still optimist that everything will be improved and the centuries-long problems of the country will be resolved. Hence, the nations and nationalities will have a prosperous country.

God bless Ethiopia

Anonymous said...

Wawe. I like such kind of article. It has life in it, i.e. Truth. I hope, I will read it again and again and distribute to many persons around.

Let God be with the writer.

Dawit said...

እኔ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ነኝ። እጅግ ዘረኛ የሆነው የኢህአዴግ አስተዳደር ሰለባም ነኝ። እስርና ስቃይን ሽሽት ከምወዳት ሀገሬ በስደት እኖራለሁ። ዛሬ አብዛኞቹ የማኅበሩ አባላት የዚህ ድርጅት ካድሬዎች መሆናቸውን ያነበብኩ ቀን የተሰማኝ ሀዘን ከባድ ነው። የቄሳርን ለቄሳር ከመስጠት ይልቅ ከነ አባ ሠረቀ ጋር በቄሳር ወዳጅነት እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ ፉክክር ውስጥ መገባቱ በእጅጉ አሳዝኖኛል።

Anonymous said...

mesfin tebarek diniq new betam des yilal ewintim new

Anonymous said...

lemehonu enanete mahebre kidusan keman beletachehu new yalegna agelegay yelem eyalachehu anden patereyarik metsedebut balege yasadegew derom min yerebal medere wetader

first time said...

“ሁለትና ከዚያ በላይ ሆናችሁ በተሰበሰባችሁበት ሁሉ እገኛለሁ” የሚል አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ቃል ኪዳን ...

kkkkkkkkk Sorry, but I had to lauch for minutes on this one, even though the topic is no-laughing-issue.

Anonymous said...

ayi MK? Abalatun yemayawuq mahiber weyins Mahiberachewun yemayawuqu abalat? The interview given by Dn. Mulugeta is disgusting. I'm also devastated like Dawit.

Anonymous said...

dn mulugeta yetenagerew minu new sihtetu. Mk ende mahber politika wust endemaygeba aboym asamirew yawkalu, bayhonma

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)