July 27, 2011

ፍ/ቤቱ አባ ሰረቀ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ወሰነ


  • ሦስተኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጫና እየተደረገባቸው ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 27/2011, READ IN PDF):- በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በማኅበረ ቅዱሳን የቀረበባቸውን የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወሰነ፤ ተከሳሹ የመምሪያው ዋና ሓላፊም አሉኝ ያሏቸውን 12 የመከላከያ ምስክሮች ለሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ላይ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

አባ ሰረቀ ብርሃን
ችሎቱ በትንት ሐምሌ 19 ቀን 2003 ዓ.ም ውሎው በሰጠው በዚሁ ውሳኔው አባ ሰረቀ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ.ም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞችን በጠቅላይ ቤተ ክህነት መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም የሀገር ውስጥ የውጭ ጋዜጠኞችን በጽ/ቤታቸው በጠሯቸው ጋዜጣዊ ጉባኤዎች በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ተዋቅሮ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን የማኅበረ ቅዱሳንን ስም የሚያጠፋ መግለጫ መስጠታቸውን በዐቃቤ ሕግ የቀረቡለት የድምፅ እና ምስል፣ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩ አስረድቷል፡፡ ዐቃቤ ሕግ አባ ሰረቀ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እና በጽ/ቤታቸው የሰጧቸውን አላግባብ ስም የሚያጠፉ መግለጫዎች በምስል ወድምፅ እና ለእያንዳንዳቸው እንደ ቅደም ተከተላቸው ሁለት፣ ሁለት በአጠቃላይ አራት የሰው ምስክሮች እንዲሁም ማኅበሩ ባለፈው ዓመት ጳጉሜን ሒሳቡን በውጭ ኦዲተር ያስመረመረበትን የኦዲት ሪፖርት በሰነድ ማስረጃነት ማቅረቡ ዳኛው በንባብ ባሰሙት ውሳኔ ላይ ተሰምቷል፡፡

የተከሳሽ ጠበቃ ዋና ሓላፊው በሰጧቸው ሁለት መግለጫዎች ማኅበሩን እንደ ተቋም እንጂ ለይተው በመጥራት ያጠፉት የግለሰብ ስም እንደሌለ፣ ይህም ቢሆን በማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊነታቸው ከማኅበሩ ጋር ባላቸው የሥራ ግንኙነት የተነሣ የተናገሩት እንጂ ይሁነኝ ብለው ስም ለማጥፋት እንዳላደረጉት ቢናገሩም በሕግ ዕውቅና የተሰጠው ተቋም/ አካል ስሙ ከጠፋ መብቱን መጠየቅ እንደሚችል ዳኛው ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሽ የቀረቡባቸውን ማስረጃዎች እንዲከላከሉ ሲል ፍ/ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ለቀረቡብን ማስረጃዎች የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችን እናቀርባለን ያሉት የተከሳሽ ጠበቃም “የሰነድ ማስረጃ” ነው ያሉትን መከላከያ እዚያው ለዳኛው አቅርበዋል፡፡ እርሱም እንደ እርሳቸው አባባል ማኅበረ ቅዱሳን “ለከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ” የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ እንቅስቃሴን አስመልክቶ “የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ” በሚል ርእስ በቅርቡ ለንባብ ያበቃው መጽሐፍ እንደ ማስረጃ የቀረበበት ነው፡፡ ከዚህም ጋራ በሦስት ጭብጦች ላይ ተከፋፍለው ጉዳዬን ያስረዱልኛል ያሏቸውን በአጠቃላይ 12 ምስክሮች እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡ ተፈላጊው ጉዳዩን ጭብጡን በአግባቡ የሚያስረዱ ምስክሮችን ማቅረብ እንጂ የሰው ብዛት አለመሆኑን ያሳሰቡት ዳኛው ምስክሮቹ ሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ቀርበው እንዲሰሙ ትእዛዝ ከሰጡ በኋላ ችሎት መልስ ሆኗል፡፡

ሐምሌ 11 ቀን 2003 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤቱ ውሎ የዐቃቤ ሕግ ሦስተኛ ምስክር በመሆን አባ ሰረቀ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ.ም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞችን በመሰብሰብ፡-
         “ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ጠላት ነው፤ በጎ አድራጊ ድርጅቶችን ለቤተ ክርስቲያን ርዳታ እንዳያደርጉ ካህናት ወይም የቤተ ክርስቲያን ሓላፊዎች በትክክል ስለማያደርሱላችሁ እኛ እናደርሳለን እያለ ገንዘብ ይሰበስባል፤ ቤተ ክርስቲያንን የሁከትና የብጥብጥ መድረክ እያደረገ ይገኛል፤ ከፍተኛ መንፈሳዊ ተቋማት የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው ይላል፤ ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ ናት፣ ለሁለት ልትከፈል ነው በሚል ሽፋን ገንዘብ ይሰበስባል፤ በኅብረተሰቡ መካከል ከፍተኛ ውዥንብር እየፈጠረ ይገኛል፤ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትንና የፓትርያሪኩን ስም በማጥፋት በራሱ ሚድያ የሐሰትና የአሉባልታ ጽሑፎችን እያስተላለፈ ይገኛል፤ ማንኛውም የማኅበሩ አባል ለቤተ ክርስቲያን ዐሥራት አይከፍሉም፤ ለቤተ ክርስቲያን ገቢ ሊሆን የሚገባውን ገንዘብ ወደ ራሱ ካዝና ይሰበስባል”
በሚል የፈጸሙትን የስም ማጥፋት ድርጊት ለችሎቱ ያስረዱት ዲያቆን ደስታ ጌታሁን በዕለቱ በችሎቱ ተገኝተው በነበሩት በእነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነና አባ ሰረቀ አማካይነት ወደ አህጉረ ስብከት ከማዘዋወር ጀምሮ የተለያዩ ጫናዎች እንዲደረግባቸው ግፊት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡ ዲ/ን ደስታ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ጸሐፊ ሲሆ በቅርቡ “የሰባኪው ሕጸጽ” በሚል ርእስ በበጋሻው ደሳለኝ ጥቅመኛነት እና ሕገ ወጥነት ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ያሳተሙ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በተከሳሹ በአባ ሰረቀ ብርሃንና በማደራጃ መምሪያው ምክትል ሓላፊ በኩል ክሱ ከዋና ሓላፊው ተነሥቶ በመምሪያ ላይ እንዲሆንና ክርክሩ በመምሪያውና በማኅበሩ መካከል እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል፡፡ ሙከራውን ለፍትሕ ሚኒስቴር ደብዳቤ በመጻፍ እንዲያግዙ ለፓትርያርኩ የቀረበው ጥያቄም ተቀባይነት አለማግኘቱን ለመረዳት ተችሎአል፡፡

10 comments:

Anonymous said...

bemedrawium hone besemay ye serachewn fetari yekfelachew

Anonymous said...

የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ቤተ ክርስትያናችንን ይጠብቅልን እንጂ ከውስጥም ከውጭም ጦር እየተወረወባት ነው ቤተ ክርስትያናችንን !!!!!!
አሜን

Anonymous said...

ያ በድፍረት የተከፈተ አፍ … . . ከተጠያቂነት ያድናቸው ይሆን እናያለን እስኪ… ለሌላው ሰው መማርያ ይሁኑ . . . ምን ያመጣሉ ብለው ነበር የተናገሩት . . . የሚመጣባቸውን ነገር በሚቀጥለው ቀጠሮ ያዩታል…. አቦ እነሱ ነገረኛ ሆነው እኛንም ነገር አስተማሩን….ልቦና ይስጥልን ከማለት ውጪ ምን ይባላል
አንድ አድርገን ከአ.አ

Anonymous said...

bakachu yhin twutna wede tikusu y Daniel Kibret zena tamalsu!

kisu siyalqi witetun ensamaln

Anonymous said...

It is good that the judge decided he defend himself; an important step in the judiciary. But I am still afraid that that of Diredawa may be repeated. The mafia group lead by Wro Elsabeth is roaming around with a huge amount of money at hand.

Lets pray more than ever for our church.

danf said...

IWNAT INDAW BE ETHIOPIA WUST YEHIG YABALAYINAT INA TIKIKILAGNA FITH KALA,IWNATAGNAWUN FIRD INTABKALAN.NAGAR ABBA SERAKA YA ABBA PAULOS KAGN IJ BAMAHONACHAW FIRD BETU TAGABIWUN FIRD YISATAL YAMIL GIMTE BATAM ANSTAGNA NAW.BIHONIM INDI BILO MADAMDAM SILAMAYICHAL WUSANEWUN BAGUGUT INTEBKALAN

Anonymous said...

To all orthodox people

This is a big move , our church is a big organization and legal entity.

The church has responsibility, accountability and rights too.I wish all the rights of our church to be protected like this in every single aspect of our rules,regulations and everything.we all need to know our rights and be responsible for implementing the rules,regulations and guidelines and proper working procedure for every single matter performed in the church.

2.Even simple organizations registered as legal entity is responsible by law to whatever job done.

3.Our church need to be a model for implementing rules,not a place for generating problems,which was not the vision of the church. But some people consider the church as personal property and not property of God .
Please we need to discuss and reach
common agreement on this issues.

4.It is amazing and dangerous to play on Church, its people and all the properties that the church has, it is being aganist God who is the leader,those people need to get punishment in this world as well as in in "seol"

5.If anybody who has a problem to be a leader, get wealth and other uses from this world, he/she has to do it in his own/her own oganization.Nowadays some people are making the church a place to accomplish their non-spiritual goals when they are unaccepted by their friends and society, they got a free place to play on.

6. Let us see in this world starting from simple to complicated job, it needs to fulfill some requirement and needs some work skill, we need to have similar strong system in the church too. Every body has to know his gift from God and there needs some ethical and spiritual guidelines
and being blessed by Known blessed fathers to do even the simple things.


sharing

Anonymous said...

2 anonymous above
( sharing)
how c/d u dare 2 wish 'seol' as punishment!?
Do u want all 'bad' people go down 2 'seol'
Do u know ur destination?
What good r u doing 4 z Church?
Don't u think u took z chair of God!
Don't u afraid 2 judge like zat?
C ur self & check ßible.
Get confessed dear plse.
(AGE)

Anonymous said...

Photow yilewetilin. balefewim yihinin new yaderegachihut.

Anonymous said...

To Dejeselam Blogger
u had posted s/thing about dn daniel& MK, & u removed it. What is that & why u removed it? Why u wanted post zen 2 remove it?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)