August 9, 2011

የአቦይ ስብሐት “አስተያየት” እና አንድምታው

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2011/ TO READ IN PDF, CLICK HERE)፦ የኢሕአዴግ ፖለቲካ መሐንዲስ የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ ባለፈው ባስነነቡን ጽሑፋቸው ስለ ቤተ ክርስቲያን (እርሳቸው ቤተ ክህነት እያሉ አጠቃለውታል) ብዙ ቁምነገሮች አንሥተዋል። ደጀ ሰላም ለረዥም ጊዜ ስትዘግብበት፣ ርእሰ አንቀጾችን እና ሐተታዎችን ስታቀርባበቸው በነበሩ እና አሁንም በቀጠለችባቸው ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ብያኔዎችን በመስጠት ውይይቱን አንድ ርምጃ አራምደውታል። አቶ ስብሐት በዚህ በዓይነቱ ልዩ በሆነው ጽሑፋቸው የሚከተሉትን ነጥቦች አንሥተዋል። እነዚህም ነጥቦች፦

 1.   ለቤተ ክህነቱ አስተዳደራው ብልሹነት ተጠያቂው ቤተ ክህነት እንጂ መንግሥት አይደለም፤
 2.  ጳጳሳቱ “ለሃይማኖታቸው አይረቡም”፤
 3.  ቤተ ክህነት ከመንግሥት ሥር ወጥቶ አያውቅም፤ ምሳሌ፦ አጼ ኃ/ሥላሴ “ቅዱስ ተብለው ጽላት ተቀርጾላቸዋል”፤
 4. ለቤተ ክህነት በመንግሥት ሥር መውደቅ ተጠያቂዋ ራሷ ቤተ ክህነት ናት፤
 5. ቤተ ክህነቱ “ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው”፤
 6. ስለ ቤተ ክህነት እንደዚህ መሆን “አማኙ ሐቁን የመስማት መብት” አለው፤
 7. ሌሎች ሃይማኖቶች እንደ ቤተ ክህነት ለምን እንደዚህ አልሆኑም?
 8. ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ፦ የቤተ ክህነት ዕዳ ነው፤ የቤተ ክህነት አስተዳደራዊ ብልሽት ያውቃል ነገር ግን ዝም ይላል፣ ብልሽቱ እንዲስተካከል አይሠራም፣ የሚሠሩትን ያደናቅፋል፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክ ነው፤ …  የሚሉት ናቸው።

እነዚህን ነጥቦች በይዘት ደረጃ ለመመደብ ብንሞክር፦
 1. ቤተ ክህነት አስተዳደራዊ ብልሽት አለበት። ይህም አስተዳደራዊ ብልሽት ወደ ሞት አፋፍ አድርሶታል።
 2. የቤተ ክህነቱ ብልሹነት ይስተካከል ዘንድ ትልቁን ሚና መጫወት የነበረባቸው ጳጳሳት ምንም ርምጃ እየወሰዱ አይደለም፤ ጭራሹኑ ይፈራሉ። ፓትርያርኩ ደግሞ የአስተዳደራዊው ብልሹነት ዋነኛ አቀንቃኝ ናቸው።
 3. ቤተ ክህነቱ ለገባበት ቀውስ ተጠያቂ ናቸው ተብለው የሚጠቀሱ የተለያዩ አካላት ቢኖሩም (ለምሳሌ መንግሥታት) በዋነኝነት ግን ሓላፊነቱን መውሰድ ያለበት ራሱ ቤተ ክህነቱ ነው። በተለይ ደግሞ ኢህአዴግ መንግሥት ተጠያቂ ሊሆን አይችልም። እንዲያውም ምሉዕ ነጻነት ሰጥቶ “ሃይማኖት እና መንግሥት” እንዲለያዩ ያደረገው ኢሕአዴግ ነው። … የሚሉ ናቸው።

የአቶ ስብሐት ጽሑፍ ትልቁ ቁምነገሩ ቤተ ክህነቱ በከፍተኛ ዝቅጠት ውስጥ እንደሚገኝ ከአንድ ትልቅ የመንግሥት ባለሥልጣን (ወይም የቅርብ ጊዜ ባለሥልጣን) የተገኘ መሆኑ ነው። አስተዳደራዊ ብልሽቱ ስር የሰደደ መሆኑን ለረዥም ጊዜ የምናውቀው ቢሆንም መፍትሔ ለመስጠት ከብልሹው አስተዳደር ጎን ቆሟል ተብሎ ይፈራ የነበረው የኢሕአዴግ መንግሥት “ብልሽቱን ማወቁ” መፍትሔ ለሚፈልጉ አካላት ትልቅ እፎይታ ነው።

አቶ ስብሀት እንዳሉት “ቤተ ክህነቱ በሞት አፋፍ ላይ” ብቻ ሳይሆን በመሞትም ላይ ነው። ቤተ ክህነቱ በራሱ የሞተ ሳይሆን “ተገድሎ” ነው። ገዳዮቹ ደግሞ የመንግሥትን አለኝታነት እንደመከታ የሚጠቀሙ ከፓትርያርኩ እና ከቤተሰቦቻቸው እስከ ዓላማቸው አስፈጻሚዎቻቸው ያሉ ጥቅመኞች ናቸው። እነዚህ ጥቅመኞች ዓላማቸውን ለማስፈጸም የመንግሥትን ክንድ ይጠቀማሉ። የሚቃወማቸውን “በተቃዋሚ የፖለቲካ አራማጅነት” በመክሰስ እና ያስመታሉ። ለዚህም ምሳሌዎችን ለማንሳት እንወዳለን።

ባለፈው ዓመት በተደረጉ የተለያዩ የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔዎች ብፁዓን አበው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተንቀሳቅሰው ነበር። ነገር ግን እንቅስቃሴው ከግብ ሳይደርስ አፋኝ ማፊያዎች የቤተ ክህነቱን በር ጥሰው በመግባት ቤተ ክርስቲያን በማታውቀው ድፍረት ብፁዓን አባቶች ላይ እንግልት እና ማስፈራሪያ ደርሷል። አቶ ስብሐት “አይረቡም” ያሏቸው አባቶች ለእምነታቸው ለመናገር ባደረጉት ጥረት ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። ይህንን ወንጀል ሊያጣራ የሚገባው መንግሥትም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ማለትን መርጧል። አብዛኞቹ አባቶችም ይህንን የመንግሥት ዝምታ “እርሱም አለበት” ከሚል ተርጉመውታል።

የቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ ብልሹነት ፊት-አውራሪዎች ከመንግሥት ጋር ንክኪነት ያላቸው ሰዎች እንጂ ተራ ሰዎች አይደሉም። ከፓትርያርኩ ጀምሮ፣ ቤተሰባቸውን ይዞ እስከ ደብር ፀሐፊዎች ድረስ በአምቻ ጋብቻ፣ በአገር ልጅነት እንዲሁም በደፈናው በትግራይ ልጅነት እና በትግራዋይነት የሚያስፈራሩ ዘራፊዎች ቤተ ክህነቱን እና መዋቅሩ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ደሙን እየመጠጡት ነው። ፖሊስ የማይፈሩ፣ ፍርድ ቤት “ሃይ” የማይላቸው የሚመስሉ፣ መንግሥት ጓደኛቸው የሆነ የሚያስመስሉት እነዚህ ዘራፊዎች በእርግጥም ቤተ ክህነቱን “ወደ ሞት አፋፍ” አድርሰውታል።

መንግሥት የሙስናን ነገር በተመለከተ፣ በተለይም ስለ ቤተ ክህነት የሚገደው ከሆነ፣ በአገሪቱ ከሚፈጸሙ እና ከፍተኛ የሕዝብ ንብረት ከሚመዘበርባቸው ተቋማት መካከል ቅድሚያነቱን ሊይዝ ይገባ የነበረውን የቤተ ክህነትን ሙስና እንደ ቀላል ማየቱ  በአባ ጳውሎስ ላይ ብቻ ሳይሆን በራሱ በመንግሥትም ላይ ብዙዎች ፊታቸውን እንዲያዞሩ እና ውሎ አድሮ ደግሞ ጥርሳቸውን እንዲነክሱ የሚያደርግ ነው። ምንም እንኳን አቶ ስብሐት እንዳሉት ለብልሽቱ በዋነኝነት መጠየቅ ያለበት ቤተ ክህነት ቢሆንም መንግሥት እኔ የለኹበትም ብሎ እጁን ሊታጠብ የሚችልበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም። የአንድ መንግሥት ተግባር ሕዝቡን እና ንብረቱን መጠበቅ እንደመሆኑ ሕዝቡ በቀማኞች በጠራራ ፀሐይ እየተመዘበረ በሕዝብ ታክስ የሚተዳደረው ፖሊስ እና መንግሥት ምንም የማያደርግ ከሆነ ዞሮ ዞሮ ከተጠያቂነት የሚድን አይሆንም።

ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች ለመጥቀስ እንደተሞከረው “ሃይማኖት እና መንግሥት” የተለያዩ ናቸው ቢባልም ቤተ ክርስቲያናችን አሁንም በምሉዕነት ነጻነቷን አግኝታለች ብለን ለመናገር አንደፍርም። በአገር ውስጥ “ተራራውን ባንቀጠቀጠው ትውልድ” ከአገር ውጪ ደግሞ በ“ያ-ትውልድ” እና በመሰሎቹ ተጠፍንጋ ተይዛለች። በአንድ ወቅት መጣጥፋችን እንደጠየቅነው በተለያዩ የፖለቲካ ካምፖች የተደራጃችሁ ኢትዮጵያውያን “ልጆቿ፤ እባካችሁ ለእናታችሁ ለቤተ ክርስቲያን ነጻነቷን ስጧት” ብለን እስከመጠየቅ ደርሰናል።

ኢሕአዴግ በእርግጥም ለቤተ ክርስቲያን ነጻነቷን መልሶላት ከሆነ በኢሕአዴግ ፓርቲ አባልነታቸው እና በካድሬነታቸው እየተመኩ ንብረቷን የሚዘርፉትን “ሃይ” ሊልላት ይገባል። ምእመናንንም አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ፖሊስ እና ፍርድ ቤት መልስ ሊሰጡ ይገባል። ለምሳሌ ያህል በቅርቡ አቤቱታቸውን ለማሰማት ወደ አዲስ አበባ ይመጡ የነበሩ የሐዋሳ ምእመናን ቃሊቲ ላይ በፖሊስ ታግተው እንግልት ደርሶባቸዋል። ወደ ቅ/ሲኖዶስ እንዳይደርሱም ተደርጓል። ይህንን ያስደረጉት ደግሞ የኦህዴድ/ ኢሕአዴግ አባል የሆኑት ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ መሆናቸውን ማወቃችን አቶ ስብሐት “መንግሥት ተጠያቂ አይደለም” የሚሉትን ድጋሚ እንዲመለከቱት እንድናስታውሳቸው ያደርገናል።

በመስከረም 2002 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተጠራ እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተገኙበት ስብሰባ እንዲካሄድ ያደረጉት እና አሁንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ከፍተኛ የሃይማኖት ሙስና (ኑፋቄ) በማስፋፋት ላይ የሚገኙት አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል “የኢሕአዴግ አባል” መሆናቸውን በይፋ በመናገር እና በማስፋራራት ለመጠቀማቸውስ ምን ትርጉም ሊሰጠው ይሆን? 

ሌላው ቀርቶ ለኦርቶደክሳውያን የመወያያ እና ሐሳብ መለዋወጫ መድረክ የሆነችውን ይህቺን የጡመራ መድረክ ለአንባብያን እንዳትደርስ ያደረገው ማን ነው ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። በመንግሥት ቴክኖሎጂ ሐሳባችን እንዳይሰማ ሊያፍነን የሚሞክረው አካል ይህንን ወንጀል ሲፈጽም በእርግጥ መንግሥት አያውቅም ለማለት ይቻላል? ታዲያ የቤተ ክህነቱ ብልሹነት መፍትሔ እንዳያገኝ እየተዋጋን ያለው ማን ነው ማለት ነው?

አቶ ስብሐት ነጋ በጽሑፋቸው ያለምንም ርኅራኄ የሰላ ትችታቸውን ያወረዱባቸው ጳጳሳቱን ነው። በዚህ የሰላ ትችት ብዙ ሰዎች ላይስማሙ ይችላሉ። ይህንንም ከአንባብያን ያገኘናቸው መልሶች ምስክሮች ናቸው። ነገር ግን ተቃዋሚዎቹ የአቶ ስብሐትን ሐሳብ ያልደገፉት በመሠረታዊ ሐሳቡ የአቶ ስብሐትን አስተያየት “ሐሰት ነው” ወይም “አይ፤ ጳጳሳቱ እርሶ እንደገለጿቸው አይደሉም” ከሚል አመክንዮ ሳይሆን “አቶ ስብሐት ምን አገባቸው?” በሚል ነው።

በእኛ አስተያየት አቶ ስብሐት (“ፖለቲከኛም ቢሆኑ”) ቢያንስ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በመሆናቸው ስለ ሃይማኖታቸው ያገባቸዋል ብለን እናምናለን። ነገር ግን እንደማንኛችንም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች አንድ ድምጽና ሐሳብ ቢኖራቸው ችግር የለበትም። እርሳቸውም እንዳሉት ደግሞ ስለ ቤተ ክህነት እንደዚህ መሆን “አማኙ ሐቁን የመስማት መብት” አለው። እርሳቸውንም ጨምሮ።

በተለያዩ ጊዜያት እንደገለጽነው፣ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ችግር በተመለከተ ምእመናን የማወቅ መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ስላለባቸው እነዚህን ዜናዎች፣ ሐተታዎች እና ርዕሰ አንቀጾች ማቅረባችንን ቀጥለናል። ይሁን እንጂ አሁን በዓይናችን ፊት እየተደረገ ያለው ነገር ብዙ ሰዎችን በቀቢጸ ተስፋ ከእምነት ሊያናውጽ የሚችል ነገር ሊሆን እንደሚችልም ግልጽ ነው። ይሁን እንጂ “ደካሞችን” በቃለ እግዚአብሔር እያጽናኑ የመጣብንን ችግር ግን በእውነት እና በመንፈሳዊ ወኔ ፊት ለፊት ልንገጥመው ይገባናል። ከዚህ ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ የለንም።

አቶ ስብሐት ያነሡት ሌላውና ትልቅ ቁምነገር ማኅበረ ቅዱሳን  ነው። ስለዚህ ማኅበር ማንሣታቸው መልካም ሆኖ ሳለ ከጽሑፋቸው ጋር ምንም ባልተገጣጠመ መልኩ ዱብ ያደረጉበት መንገድ ይገርማል። እርሳቸው መልስ የሰጡትም የፍትሕ ጋዜጣ ፀሐፊ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን  አላነሣም። ታዲያ እርሳቸው ለምን ለማንሣት ወደዱ ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው። የተናገሩት ሲጠቃለል ማኅበሩየቤተ ክህነት ዕዳ ነው፤ የቤተ ክህነት አስተዳደራዊ ብልሽት ያውቃል ነገር ግን ዝም ይላል፣ ብልሽቱ እንዲስተካከል አይሠራም፣ የሚሠሩትን ያደናቅፋል፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክ ነው”  የሚሉት ሐሳቦች ዋነኞቹ ናቸው።

በመጀመሪያ ደረጃ ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላላው ከተመለከትነው ለቤተ ክርስቲያኒቱ፣ በአስተዳደር ደረጃ ጠበብ አድርገን ካየነው ደግሞ ለቤተ ክህነቱ “ትልቅ ሀብት” (asset) እንጂ “ዕዳ” (liability) ሊሆን አይችልም።  በጭራሽ። ይህንን ደግሞ ከፓትርያርኩ ጀምሮ ብዙዎቹ የቤተ ክህነቱ ሰዎች አልተረዱትም፣ አቦይ ስብሐትም አልተረዱትም። እንዳለመታደል ሆኖ በታዳጊ አገር እና ባልሰለጠነ አእምሮ መካከል መገኘታችን ካልሆነ በስተቀር ለ19 ዓመታት መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎትን በቅንነት የሰጠ ተቋም “ዕዳ” ሊሆን ነው ሊባል አይገባውም ነበር። በሁሉም መስክ ብናነጻጽረው፣ በአገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጪ ካሉ ኢትዮጵያዊ-መንግሥታዊ-ያልሆኑ ተቋማት እንደ ማኅበረ ቅዱሳን  ዓላማውን ዝንፍ ሳያደርግ እና የተከታዮቹን እምነት ሳያጎድል የዘለቀ የለም ማለት ይቻላል። ስንቱ ተደራጀ፣ ስንቱ ፈረሰ? ስንቱ ገንዘብ ሰበሰበ፣ ስንቱ ዘረፈ? ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ በኩል ንጽሕናውን እንደጠበቀ የዘለቀ ከመሆኑ አንጻር በቤተ ክህነቱ ብቻ ሳይሆን በቤተ መንግሥቱም ሊመሰገን ይገባው ነበር።

በእርግጥ “ዕዳ” ነው ከተባለ ዕዳነቱ በቤተ ክህነቱ ሙስና ለተጨማለቁ ሰዎች ነው። ይህ ደግሞ የዚህ ብልሹነት ፊት-አውራሪ ከሆኑት ፓትርያርክ ይጀምራል። የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕንጻዎች እንደ ግል ንብረታቸው የሚጫወቱበትን እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነን እና ተከታዮቻቸውን፣ በዚህ ውዥንብር መካከል በተሳሳተ ትምህርት የአማኙን ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን ነፍሱንም ሊዘርፉት የተዘጋጁትን እነ አባ ሰረቀን፣ እነ በጋሻውን እና ጓደኞቻቸውን ያጠቃልላል።  

ማኅበረ ቅዱሳን  የቤተ ክህነቱን ብልሹነት ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ጽሑፎቹ፣ ተግባሮቹ እና አገልግሎቶቹ ይመሰክራሉ። ነገር ግን ችግር አፈታት ላይ ከብዙዎቹ የተለየ አካሔድ እንደነበረው የ19 ዓመት አገልግሎቱ ምስክር ነው። የቤተ ክህነቱ ችግር የሚፈታው “በአብዮት ሳይሆን በአዝጋሚ ለውጥ” (By Evolution, not by Revolution) የሚል ይመስላል። ይህም ቢሆን ግን “ፀረ ለውጥ፣ ፀረ መሻሻል” ሊያስብለው አይገባም ባይ ነን። ጭራሹኑ “መሻሻል የማይፈልግ” ተደርጎ የቀረበው ሐሳብ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን (ማኅበረ ቅዱሳን ን እንደዚህ ማለቱ) በእውነቱ “It is not fair”!!!!

“የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክ” የሚለውንም ለመቀበል ያስቸግራል። በዚህ የሚጠረጠር ብቻ ሳይሆን በእርግጥም ማስረጃ የሚገኝበት ቢሆን ኖሮ እስካሁን የቀን ፀሐይ ለማየት ይበቃ ነበር ብሎ ለመገመት አይቻልም። በዚህ በኩል ኢሕአዴግ የማያወላዳ መሆኑን እናውቃለን። ኢሕአዴግ፣ እንኳን በተቃዋሚ ዋሻነት እና መድረክነት የሚያገለግልን፣ ይሆናል ተብሎ ፍንጭ የተገኘበትን ከዋለበት የማያሳድር፣ ካደረበት የማያውል መሆኑን እናውቃለን።

መስፍን ነጋሽ የተባሉ ፀሐፊ እንዳሉት (Claim እንዳደረጉት) በ1997 ዓ.ም (2005) ምርጫ ማግስት የነበረው ግምገማ ማኅበረ ቅዱሳን ን በጠላትነት ያስፈረጀው ከነበረም ማስረጃዎቹ እስካሁን ሊሰወሩ አይችሉም ነበር። እውነቱ ግን ማኅበረ ቅዱሳን  የፖለቲካ ያለው ፍላጎት የሞተ መሆኑ ነው። ለዚህም ማስረጃው አንድ ግልጽ አመክንዮ እና ሎጂክ ነው።

የማኅበረ ቅዱሳን  አባላት ተረ ጀሌዎች (footsoldiers) ሳይሆኑ ማገናዘብ የሚችሉ ናቸው። አመራሩ የሚጭንባቸውን ብቻ በቀላሉ ተቀብለው የሚሔዱም አይደለም። በተለይም ከሃይማኖት ውጪ ባሉ ጉዳዮች ላይ የራሳቸው አመለካከት እና አስተሳሰብ ይኖራቸዋል። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ እንደየማንነታቸው የተለያየ ነው። ስለዚህ ማኅበሩን እና አባላቱን አንድ ያደረጋቸው የሃይማኖታቸው ጉዳይ እንጂ በዘር እና በቋንቋ፣ በፖለቲካ አስተሳሰብ እና አስተያየት ፍፁም የተለያዩ መሆናቸውን ለመገመት ምሁር መሆን አይጠይቅም። በፖለቲካ ጉዳይ አሐዳዊ አስተያየት እና አስተሳሰብ መጠበቅ ከባድ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን  የቃዋሚዎች መድረክ ለመሆን አደረጃጀቱ አይፈቅድለትም የምንለውን ያህል የኢሕአዴግም መድረክ ለመሆን አይመችም ማለታችን ነው።

በእርግጥ የማኅበረ ቅዱሳን  ዋና ፀሐፊ በቅርቡ ለ“ዕንቁ” መጽሔት በሰጠው እና እኛም በስፋት ባስነበብነውቃለ ምልልስ አባላቱ “በአብዛኛው የኢሕአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው” ያለበት “Claim” እጅ እግር የሌለው ግምት የሚሆነውም በዚህ መነሻ ስንመለከተው ነው። ነገር ግን የኢሕአዴግ አባላት የሆኑ ሰዎች የማኅበረ ቅዱሳን  አባላት ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ መሆኑ እርግጥ ነው። የፓርቲው አባላት ቢሆኑም የፓርቲያቸውን አጀንዳ እና ዕቅድ ወደ ማኅበሩ ይዘው ይመጣሉ ማለት አይደለም። ቢያመጡም የሚቀበላቸው አይኖርም። አባላቱ ጀሌዎች (foot-soldiers) አይደሉም ያልነውም ለዚህ ነው። አቶ ስብሐት ይህ አልጠፋቸውም።

ነገር ግን ማኅበሩ “በሕገ መንግሥት ጥሰት” የመከሰስ ትልቅ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል “ጠቆም” በማድረግ አባላቱ “ሰጥ ለጥ ብለው” እንዲኖሩ፣ አመራሩም “ነጻ መሆናችንን ኑና ማረጋገጫ ስጡን” እንዲል በር ለመክፈት የተደረገ በር ማንኳኳት ይመስላል። እንዳሉትም ተሳክቶላቸው ከሆነ አመራሩ አቦይ ስብሐትን ለማነጋገር ሄዷል ተብሏል። መሔዱ ብቻ ግን “ተንበርካኪ” አሰኝቶ ሊያስወግዘው የሚገባ አይመስለንም። ችግሩ “የተቃዋሚዎች መድረክ አለመሆኑን ለማሳየት የኢሕአዴግ መድረክ ለመሆን ከፈቀደ” ነው። በርግጥም አቦይ ስብሐት ማኅበረ ቅዱሳን ወደዚህ ዓይነቱ የተንበርካኪነት ደረጃ እንዲወርድ የሚያስገድዱት ከሆነ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል እየፈጸሙ ነው ለማለት እንደፍራለን። ለቤተ ክርስቲያኒቱም፣ ለአገሪቱም ሲሉ ያንን ከማድረግ ይቆጠባሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

30 comments:

Anonymous said...

ይቺ ጽሑፍ የማሕበሩ ወይስ የደጀ ሰላም?

Anonymous said...

anibib keziya merimir keziya yemitekim kemeseleh tetekemibet kalihone degimo arifeh tekemet, kin libona yinurih, bego begow yitayih

Anonymous said...

But me when i observe z current situation & all z country has passed through, z only hope 4 z future 4 Ethiopia, perhapse Africa too, lies on Mahibere Kidusan who is dedicated 4 Truth & lives guarded by God, z Owner of Power!
I begged God let me live 2 c this Miracle!
(AGE)

Anonymous said...

ውድ ደጀሰላማዉያን
እጅግ ግሩም የሆነ ሀተታ ነዉ!!
በጠዋቱ ተነስቸ አንብቤ ስጨርስ ቁርስም አላስፈለገኝ::
እግዚአብሄር ስራችሁን ይባርክ!
በመካከሉ ስለ ድረ-ገፃችሁ የጠቀሳችሁት ግን አልገባኝም ደጀሰላም ኢትዮጵያ ዉስጥ አሁን ታፍናለች እንዴ?

mesfing said...

deje selamoch melkam new hulu neger seweyew ende and yebetechristian abal asteyayet mestet yechelalu bebete chrisian yewest gudaye gebtew gen mefetfet aychelum

Fitsum said...

Koy gin mindenew yeminetibekew neger? Eske mecha derese new yesim Orthodox Tewahido lijoc nen yeminilew? Ende kirch siga sikerametuat mayet new yenafeken wes teamir enetebek. Esu eigna sinsera esum yagezinal Ye India orthodox be tehadso yeteberezechew Egziabhare teltoachew new? Weyes teamiru lenesu ayseram? Ebakachiu wede meftihaw enhide yalenin mestnaigna Mahibere Kidusanin behegemengist kihidet lemeferege endemisu begilst tenagrewal tadia mendenew yemifeligew? Seimatinet libetekirstian kiber enji berk aydelem. Eske mecha derese new yesim Orthodox Tewahido lijoc nen yeminilew? Ende kirch siga sikerametuat mayet new yenafeken wes teamir enetebek. Esu eigna sinsera esum yagezinal Ye India orthodox be tehadso yeteberezechew Egziabhare teltoachew new? Weyes teamiru lenesu ayseram? Ebakachiu wede meftihaw enhide yalenin mestnaigna Mahibere Kidusanin behegemengist kihidet lemeferege endemisu begilst tenagrewal tadia mendenew yemifeligew? Seimatinet libetekirstian kiber enji berk aydelem.

Anonymous said...

ይቺ ጽሑፍ የማሕበሩ ወይስ የደጀ ሰላም? ብለው ለጠየቁት ግለሰብ

ደጀ ሰላም ራሷ ያዘጋጀቻቸውን ጽሑፎች “ደጀ-ሰላም” ብላ ትጠቅሳለች።

የማንስ ቢሆን ጉዳይህ ከማንነት ጋር ወይንስ ከሀሳቡ?

Anonymous said...

Dear readers,
Betechristian yemecheresha tesfachin nech. Esua sititefa zim bilen keminay, egna binalf yishalal. Whatelse can we hope for then? Aba Pawulos ecko tenegna nachew lemalet yikebidal. Is he really christian? Ersun bicha amlak yimermirew. I saw his reaction when we went to claim from Awassa about the problem a year ago. That was the day when I lost hope about the Patriarch. Along with much prayer, we have to fight struggling with those evil people around the church until they free our church. We should act in all ways we can. May the mercy of God be with us

Aragaw said...

Ere Mekatel New Gobez.

Anonymous said...

ኢህአዴግ ግን መጥፊያዉን እሳት እያዳፈነ መሆኑን አያዉቅም እንዴት? ቆይ ግን መካሪ አጣ እንዴ? ለምን ግን ቤተክርስቲያንን ለቀቅ አያደርጋትም? ግን ኢህአዴግ ሐይማኖት የለበሰ ተቃዉሞን እንደ ምርጫ 97ቱ ጊዜ በጉልበት የሚያፍን ይመስለዋል፣ ምናለበት ድህነታችንን ብናዳምጥበት!!! ቤተክርስቲያን የመጨረሻዋ መጽናኛችን ነችና ከርሷ ጋር መቀጠል ወይም መጥፋት . . . እመብርሃንን!!!!!!!!

Anonymous said...

I really felt sad now a days when I am reading those news because most of the people in "Betekihenet" are devil and they stand along with those TEHADESO and other people who want to destroy our church. Please every body should pray to GOD and let us all start to find solution to our church like "GIEORGIS HABIB" in Egypt. Please gobeze zim malet ketarik tewokashint aydinenem. Seatu Ahun new, enenesa.

ተስፋ said...

ደጀሰላሞች

እግዚአብሔር ይባርካችሁ ድንቅ ሥራ ነው ከዚህ በበለጠ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ላልሆነው ሕዝበ ክርስቲያን መልዕክታችሁን የምታዳርሱበትን መንገድ እስኪ አስቡበት

የኢንተርኔት እድሉ ያለን ደግሞ ላልሰማው ኅብረተሰብ የማሰማት ኃላፊነት አለብን ለዚህ ደግሞ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉት የሰንበት ትምህርት ቤቶችና ማኅበረ ቅዱሳን ናችሁና ከእናንተ ብዙ እንጠብቃለን

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን

Anonymous said...

የእንግሊዞች የጥንት ሴራ

የነጮችን የበላይነት ለማረጋገጥ - ኦርቶዶክስ የተባለ ሃይማኖትና ኢትዮጵያ የምትባልን አገር ማጥፋት

የወያኔ/ህወሓት ሴራ

የትግራይ ጎጠኞችን የበላይነት ለማረጋገጥ አማራ የተባለውን ብሔር እና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ማጥፋት - ለዚያ ነው የወያኔዎቹ ባለስልጣኖች ባደባባይ ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ምሽግ ነች ብለው የተናገሩት


ይህንንም ለ 20 ዓመታት ያለመታከት ቤተክርስቲያናችንን ሲያፈራርሱ ኖረው የእነሱ ጉዳይ ፈፃሚዎችን ከሰገሰጉ በኋላ ጳጳሶቹ አይረቡም ይሉናል - ከደሙ ንጹህ ነን ለማለት

ታዲያ ምን እንጠብቃለን - እናት አገር ወይም ሞት የሚለው መፈክር በራስ ወዳድነታችንና በተጨማለቀ አመራር መሳለቂያ ሆኗል ሃይማኖት ወይም ሞት ግን የሚያስከፍለው መስዋዕትነት ቀላል አይሆንም ለኢህአደግም ጭምር

ስለዚህ ወያኔ ሆይ እጃችሁን ከቤተክርስቲያናችን ላይ ብታነሱ ይሻላል

Anonymous said...

Wondimoch ena ehitoch, egna beye kiflehageru yemininor yebetechristian lijoch, begziabher redatinet yeakimachinin eyetagelin new. Wongel endisfafa, betechristianoch endayizegu yilikunim adadisoch endikefetu asiratachinin egnam lelochinim endikefilu eyadergin new. Neger gin ketikit ametat jemiro ketekilay betekinet yeminisemaw neger hulu ende christian yemiasazin new. Beteley patriarchu letehadisowoch yemisetut shifan. Ahunima hulum miemenan eyawokut silepatriarchu sinesa bemiret menager jemirewal. Beteley betechristian wust yalew musina enditefa mesewatinet kefilen matsidat alebin. Beye atibiawu yalu wotatoch mesiwatinet mekifel jemirewal. Hulum beyalebet metagel alebet. Sile mahiber (Mahibere kidusan) woyim silegileseb mawurat tewuna, betechristianin kemusina ena ketehadiso lematsidat mesiwatinetim bihon kefilen ketarik tewokashinet medan alebin. mengist kefelegem yirdan. yaleza gin mengistin sanitebik beyalenibet atibia enitagel. Mawok yalebin kemengist balesiltanat andandoch lebetechristian yemitagelu alu. Leloch demo endititefam yemifeligu alu. betechristianin magelgel gin yegna halafinet new. betselot eyeberetan tenkiren enitagel. Tsidik yalemesiwatinet ayigegnim ecko wogenoch. Egziabher amlakachin yirdan!

Anonymous said...

Gif ena Tigab kequatu Molto Mefises Jemirual "Teb Yalesh Bedabo" yimesilal Yaboy Sibihat Asteyayet Melikam Bemimesil Yegnan Bisot Bemanisat Mefitihe Layametulet Endagerachin Asilekash kusilachinin eyenekaku asilekesewu chirashunu likebirun yemekabir bota yifeligulinal woyim eyefelgu newu woyi gizie? Engidih Amlake Egiziyabehere Yemiyametawu neger ale enji mechem wodewu ayidelem yigermal " Eda " alu ahooooooooooooooo? Ante Amilak Gifu Bekachihu Atilenim Eskemeche?

Anonymous said...

aboy sibhat hoy mechem kehlinb dagninet yemiamelt yelemna bezih besterjinawe wekt lewnet bikomu melkam neber. Mechem beljnewot kebetekrstian fidel saykotru endalkeru egemtalehunaa bezih besterjinawe wekt lewnet bikomu melkam neber. Mechem beljnewot kebetekrstian fidel saykotru endalkeru egemtalehuna

Anonymous said...

Dear Blogger, In Ethiopia there is a satellite TV called EBS whose owner I donot know yet. They have got a religous program every sunday morning. They sold satellite time to different types of religion. The surprising thing is that the Orthodox church is being represented by an illegal group like Dn. Begashaw and Yared ademe. I am sure they donot have official letter of licence from the chrch. Why Dejeselam is not covering about that? Ene yared ena Dn. Begashaw gin ayigermum? Hizbu mejemeria nisiha gibu, temaru silachew enesu gin begid kalsebekin bilew betechristian medirek siatu demo be EBS yadenagiralu. Ewunetegna christianoch bihonu noro elih sayihon yikirta neber yemiaskedimut. Bitibit ena huket mefiter min yadergilachewal? Lemanignawum bezih zuria sefa yale zegeba bitakerbu tiru new. EBS degmo alamaw, lebego kehone biasibubet tiru new. Egziabher lenersum libona yistilin ena wode betachew yimelisachew.

Anonymous said...

Yes, It is not fair!!!!

tibebe said...

there is a saying in tigray:derg gedlo yfokral;woyane gedlo lekso ydersal.after killing derg announces while woyane express condolences !

that is exactly what is happening with aboy sbhat comment....

123... said...

ከላይ የ ፃፉት ፀሐፊ አባባል ሃሳቤን ሁሉ ትገልፃለች አንዲህ ትላለች ''ደርግ ገድሎ ይፎክራል ወያኔ ገድሎ ለቅሶ ይደርሳል'' ቤተክርስትያንን ከገደሉ በሁአላ መንግስት ከ ደሙ ንፁህ ነው አያሉ የ አዞ አንባ ማንባት ማንን ይጠቅም ይሆን???????

Anonymous said...

sharing is happiness

http://debelo.org/

http://www.zeorthodox.org/

http://www.melakuezezew.info/

http://www.kesisyaredgebremedhin.com/

http://www.adebabay.com/

http://www.betedejene.org/

http://www.aleqayalewtamiru.org/

http://www.mahletzesolomon.com/

http://degusamrawi.blogspot.com


http://www.tewahedomedia.org

http://www.eotc-mkidusan.org/site/

http://suscopts.org/

http://www.dejeselam.org/

http://mosc.in/

Anonymous said...

I read a very,very important comment about a satelite tv broadcast by Begashaw and Yared. This is a huge issue.Do they have approbation from and legally allowed by EOTC to preach in its name on that TV station? If not,it is so dangerous that the approach is going to pave the way for heretics to transmitting heresy in the name of the church.

Anonymous said...

ወገኖች እስካሁን ድረስ አንድ ያልተረዳነው ነገር ያለ ይመስለኛል
እነዚህ ሰዎች (ወያኔዎች)እኮ እሰካሁን እየሰሩ ያሉትና ወደፊትም ለመሥራት ያቀዱት ሁሉ ጫካ ውስጥ ሳሉ ባረቀቁት ፖሊሲ ነው ፡ የጨመሩት ነገር ቢኖር የወቅቱን የዓለም አሰላለፍ ተከትሎ ፐሮገራማቸውን ማደስ (upgrade ማድረግ)ብቻ ነው ።

ለነሱ ሃይማኖት ማለት ሰውን ማደንዘዣ ነው ፡ እርግጥ ነው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከአማራው ገዢ መደብ ጋር ደርቦ ማየታቸው የታወቀ ጉዳይ ነው ።

ቤተ ክህነቱ የራሱን ሃይማኖታዊ ተግባር ወደ ሗላ ብሎ የነሱን ፖለቲካ ብቻ ተከትሎ እንዲሄድ ነው የሚፈልጉት ፡ ከዚህ ውጭ የሚያስብ ግለሰብም ይሁን ቡድን በኢተዮጵያ ውስጥ ሊኖር ከቶውንም አይችልም ።

አሁን ማድረግ ያለብን ፡ ወይ ራስን ለሠማዕትነት አዘጋጅቶ እስከ መጨረሻው ዓላማን ጠብቆ መቀጠል ፡ ካልሆነልን ደግሞ ወያኔዋ በምትሰጠን መስመር ብቻ መጓዝ ነው ።

ከላይ እንዳልሁት ፡ ቤተ ክህነቱን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል ። እስኪ ወደ ውስጥ ገባ ብላችሁ ተመልከቱ ፡ የየትኛው መምሪያ ሃላፊ ነው የኢሕአዲግ አባል ያልሆነው ? እንኳን ተራው ሰው አዳዲሶቹ ጳጳሳትም እየታሙ ነው ።
አሁን የቀረው ማህበረ ቅዱሳን ሲሆን ፣ እሱም , ወይ የራሳቸው ፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን ማድረግ, ካልሆነ አፍርሶ በሌላ አዲስ ማህበር መተካት ነው ። በዚህ ሂደት ውስጥ ደ ግሞ ብዙ ንጹሃን አባላቱ ዋጋ መክፈል አለባቸው ፡ ከየሥራ መስካቸው ይባረራሉ ፤ ይታሰራሉ ፤ ይሰደዳሉ ግፋ ካለም ይገደላሉ ። ይህ ነው ሰማዕትነት ማለት ፡ እስከ አሁን ያለው ሠማዕትነት ያለ ደም ነበር ከአሁን በሗላ ግን መስዋዕተንትን የሚጠይቅ አገልግሎት ነው እየመጣ ያለው ።

ከዚህ በሓላ ስልታዊ ስትራቴጂኪ ምናምን የሚባለው ሁሉ ጊዜ ያለፈበት ነው ። ወይ አባልና የጥፋት ተባባሪ ትሆናለህ ፡ ካልሆነ ትወገዳለህ ።

አባይ ፀሀዬ ያለውን ረሳችሁት እንዴ ? “”ማህበረ ቅዱሳን በፖለቲካ ውስጥ (ተቃዋሚ) መግባቱን ደርሰንበታል ፡ እናንተ አባቶች ትምክሩታላችሁ ብለን ነው እስካሁን የታገስነው….”” እኮ ነው ያለው ። የዚህ አንድምታው ምን ይመስላችሗል?

አባ ሠረቀ ይህን እንደፈለጉ ተዝናንተው የሚናገሩት ዝም ብለው ይመሰላችሗለ? አባ ሠረቀን በተሐድሶነት ከመጠርጠር ይልቅ ማህበረ ቅዱሳንን ሊቃወም የሚችልን አካል ሁሉ ድጋፍ በመስጠት የህጋዊነቱን መንገድ ለማመቻቸት ይንቀሳቀሳሉ የሚለው ሃሳብ ይቀርባቸዋል ።

Anonymous said...

ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ፡፡
ደጀሰላም የሚቀርበው መጣጥፍ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የሴጣኑንም የመንፈስ ቅዱሱንም መመርመር ይገባናል፡፡
አቦይ ስብሀት ስለቤተ ክርስቲያን ሊናገር መነሳቱ አስደናቂ አይደለም፡፡ ለምን ቢሉ አባቶች ስለቤተ ክርስቲያን አንድ ሆነው በተነሱበት የቅርብ ግዜ ትውስታችን ቤታቸው በዱርዬ ሲደበደብ የቤተ መንግስቱ አባዎራዎች አስታራቂ ሆነው ነበር የገቡት፡፡
ይህ የሚነግረን እኮ የማይረቡት እነርሱና እነርሱን ተገን አድርገው በቤተ ክርስቲያናችን የተሰገሰጉ ወንበዴዎች ናቸው ቁንጮውን ጨምሮ፡፡ እነርሱ ህግ አልባ ሆነው ቤተ ክርስቲያንንም ሕግ አልባ ለማድረግ የሚሯሯጡ የቀን ጅቦች ናቸው፡፡ እነርሱ ያልገቡበትና የማያምሱት ቦታ የት ይሆን ያለው በዚህ አለም፡፡
አነዚህን ሰዎች እና ስራቸውን ያየ ሰው የአለም ፍጻሜ መቅረቡን አስረጂም አይፈልግም፡፡

Anonymous said...

Below are MK (mahibere kidusan)blogs and web to share with my fellow friends:-Enjoy it !

http://debelo.org/

http://www.zeorthodox.org/

http://www.melakuezezew.info/

http://www.kesisyaredgebremedhin.com/

http://www.adebabay.com/

http://www.betedejene.org/

http://www.mahletzesolomon.com/

http://degusamrawi.blogspot.com

http://www.tewahedomedia.org

http://www.eotc-mkidusan.org/site/

http://www.dejeselam.org/

EHETE MICHEAL said...

ይህንን ሳነብ የሰውየው ነገር ለካ ብዙ አላማ አለው እንድል አደርጎናል፤ሁሉንም ነገር ግልፅ ነው ወያኔ እየሰራ ያለው ነገር ግልፅ ነው፤ቤተ ክርስቲያናችንን በጣም እየጎዳችሁት ነው ያ ማለት ደግሞ የራሳችሁን መጨረሻ እያቀረባችሁት ነው በዚህ መከራ በበዛበት ዘመን ሰው አምላኩን እያመለከ እንዳይፅናና መንገዱን ሁሉ በስጋም በነፍስም ለማጨለም እየሞከራችሁ ነው የምትዋጉት ሰውን ብቻ ሳይሆን የሰማይ አምላክንም ነው እጃችሁን ከቤተክርስቲያን እንድታነሱ አሁንም በጥሞና ትለመናላችሁ እንቢ ካላችሁም ዋጋችሁን የሰማይ የምድሩ አምላክ በቅርብ ይከፍላችዋል የሙሴንና የፈርኦንን ታሪክ ደጋግማችሁ አንብቡት ። ዳዊት በትንሿ ጠጠር ጎልያድን እንደጣለ አትርሱ ዛሬም ያ እግዚአብሔር ከኛ ጋር መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ልብ ይስጣችሁ።

Anonymous said...

hayemanotachenen manekate kamane gara eyatalo mahonone yawekaloo ato......

Anonymous said...

'በሰው የሚታመን፤ ስጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከ እግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ይሁን' ኤር. 17፤ 5
አቦይ ስብሃት ፍረሃተ-እግዚአብሔርን የማያውቁ፤ በመንገዳገድ ላይ ባለው ደም-መጣጭ ረጋ-ሰራሽ ድርጅታቸው የሚተማመኑ፤ ሞት ሞት የሚያሸት አፍንጫ ያላቸው የዘመዩ የዲያብሎስ ከንድ ናቸው
አቦይ ስብሃት ሁሉንም ለማድረግ እና ለእሳቸውና ለወያነ የማይስማማ ነገር እንቅልፍ ትተው ይሮጣሉ።
ምንም ይበሉ ምንም...የቤተክርስቲያን ጸሎት አቦይ ስብሃትን እና መሰል ዲያብሎስን ጋላቢ አቅመ-ቢስ ሸክላ ፍቱራንን ለዘላለም ከነዘራቸው ያፈርሳል እንጂ ቤተ-ክርስቲያን አትፈርስም፡።

W/GIORGIS Z ATLANTA said...

WEDE ANBABIAN EBACACHHU WEDE EGZIABHER ENALKS. MAHEBERE KIDUSANIN MANENET EGZABHER ENA BEGEDAM ENDEHUM BEGETERITU BETECRISTIAN YEWEDKU MENANIAN ENA MENECOSAT YAWKALU GEN YEH SERA BEMDERE LAY SHUMET LYASETACHEWS WAYNEM LYASMESEGNACHEW SELALHONE KEMENGESTM HONE KE ABUNU MESGANA MAGGNET AYTEBEKM, MELKAM YEMISERA HULU YEMITAWEKW BEMIDERSBET ENGLIT ENA MEKERA NEW. GETACHIN SELESME YETETELACHHU TEHONALACHU ALE ENGEE YETEWEDEDACHHU ALALEM ENA. EGZABHER ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHDO BETECRISTIAN YETEBEK YEMENSASUBATNEM FETNO YASGEZALAT BEWSTWA HONEW YEMIGEZEGZUATNEM LEB YESTACHEW. AMEN

Anonymous said...

ኢህአዴግ ግን መጥፊያዉን እሳት እያዳፈነ መሆኑን አያዉቅም እንዴት? ቆይ ግን መካሪ አጣ እንዴ? ለምን ግን ቤተክርስቲያንን ለቀቅ አያደርጋትም? ግን ኢህአዴግ ሐይማኖት የለበሰ ተቃዉሞን እንደ ምርጫ 97ቱ ጊዜ በጉልበት የሚያፍን ይመስለዋል፣ ምናለበት ድህነታችንን ብናዳምጥበት!!! ቤተክርስቲያን የመጨረሻዋ መጽናኛችን ነችና ከርሷ ጋር መቀጠል ወይም መጥፋት . . . እመብርሃንን!!!!!!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)