July 21, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን በለንደን ታላቅ ዐውደ ርእይ አዘጋጀ

(ጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ፤ በተለይ ለደጀ ሰላም፤ ጁላይ 21/2011)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቀደም ሲል ለአገሪቱ ያደረገቻቸው  ታሪካዊ አስተዋጽዎችን፣ በአሁኑም ወቅት እያደረገች  ያለውን ልማታዊ እና ሃይማኖታዊ  እንቅስቃሴዎችን  እንዲሁም ወደፊት ምን ለማድረግ እንደታቀደ  የሚያመላክት ታላቅ ዐውደ ርእይ  በለንደን   ከተማ ውስጥ  ተካሄደ፡፡

 ይህ በኢ//ተቤተ ክርስቲያን በሰንበት  /ቤቶች  ማደራጃ  መምሪያ  ማኅበረ ቅዱሳን አማካኝነት   ከሐምሌ  1 - 3 ቀን 2003 ዓ∙ም  (ጁላይ  8-10/ 2011)  የተካሄደው  "ቤተ ክርስቲያን  ትናንት፣ ዛሬ እና  ነገ " በሚል ርእስ  ዙሪያ   ቤተ ክርስቲያኒቱ  ባለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት የታሪክ እና ሃይማኖታዊ ጉዞዋ ስላካበተቻቸው እና ስለአበረከተቻቸው ድንቅ የስነ ጥበባት፣ታሪክ፣ ትውፊት ልዩ ሀብት እና ሌሎችም  ያካተተው  በዓይነቱ  ልዩ የተባለለት ዐውደ ርእይ ቤተ ክርስቲያኒቱ  በብሔራዊ እና ለም አቀፋዊ  ደረጃ ያበረከተቻቸውን በርካታ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ትሩፋቶችን  ለጎብኝዎች በከፊል ለማሳየት የተሞከረበት መድረክ ነበር ፡፡

 ////ቤተ ክርስቲያን  በአገር አስተዳደሪነት እና በህግ ቀረጻዎች፣የአገር ሉአላዊነትን በመጠበቅ፣ ኢትዮጵያዊያን  ወራሪውን የጣሊያን  ጦርን  በአድዋ ጦርነት ላይ ድል ሲያደርጉ  ቤተክርስቲያን  ታቦት ይዛ   አብራ በመዝመት፣ ህዝቡ አገሩን፣ ሃይማኖቱን እና ባህሉን እንዲጠብቅ  በማደርግ፣  የኢትዮጵያዊያን  ሉአላዊነት መግለጫ የሆነው የባለ አረንጓዴ፣ቢጫ እና ቀይ ቀለሙ ሰንደቅ አላማ  እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ከገባለት የቀስተ ደመና  ቀለማት ጋር በማመሳከር  የአገሪቱ  ስንደቅ  አላማ  እንዲሆን  ከማበረከቷ በተጨማሪ ይህንኑ ቀለም በአሁኑ ሰአት 33 በላይ የአፍሪካ አገሮች በተለያየ ቅርጽ ተጠቅመው ዛሬ ድረስ ብሔራዊ ሰንደቅ አላማቸው አንዲሆን አርእያ  ሆናለች።

ከዚሁ ከአድዋ ድል ጋር በተያያዘ  ቁጥራችው 70 በላይ የሚገመቱ የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ህዝቦች  የኢትዮጵያን ገናናነት እና የቤተ ክርስቲያኒቱን በጸረ ቀኝ  አግዛዝ ዘመቻው ላይ ያደረገችውን ጉልህ ከግንዛቤ ውስጥ  በመክተት እምነታቸውን የኢ// ቤተ ክርስቲያን እምነት ያደረጉበት አጋጣሚ እንደ ነበር፤ በኋላ ግን በተከታታይ የወንጌል ሰብከት አማካኝነት ትክክለኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች እንዲሆኑ ንደተደረገ ተገልጿል፡፡

 በሰባተኛው /ዘመን  በመካከለኛው ምስራቅ በሙስሊም ወንድሞች  እና እህቶች ላይ ይካሄድ የነበረውን ጭፍጨፋ በመሸሽ  ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ወገኖች በዘመኑ የኢትዮጵያ ንጉሥ በነበሩት ንጉሥ አርማህ አማካኝነት እንክብካቤ አንደተደረገላቸው  በማውሳት  ቤተ ከርስቲያኒቱ በወቅቱ ለበርካታ ወገኖች መጠለያ በመሆን ሰብአዊ፣ አገራዊ እና ሐይማኖታዊ ላፊነቷን መወጣቷን የሚያሳዩ ማስረጃዎች በምስል እና በቻርት ተደግፈው  ለጎብኝዎች ቀርበዋል፡፡

 ዐውደ  ርእዩን  በማዘጋጀት  ከተባበሩት  እና በእንግሊዝ ሀገር የማኅበረ ቅዱሳን አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ዲያቆን  ሜሌዮን አጀብ ለዚህ ፀሐፊ በሰጡት አሰተያየት የኢ///ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሏትን ሃይማኖታዊ ቅርሶች እና አገልግሎት ከመጽፍ ቅዱስ ጋር ስላላቸው ግንኙነት፣ ምሳሌነት እና ትርጉም  ለምእመናኑ ሆነ ለሌሎች ወገኖች ለማሳወቅ የተደረገው ዐውደ ርእይን ለማዘጋጀት ከአንድ አመት በላይ የፈጀ ግጅት መደርጉን ጠቅሰው  ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ያበረከተቻቸውን  መልካም ተግባራትን በጥቂት ሰአት ውስጥ ጎብኝቶ መጨረስ ባይቻልም በስደት ለሚኖረው ትውልደ ኢትዮጵያ ለአገራቸው እና ሰለ ምነታቸው  መጠነኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው  የታቀደ ዝግጅት መሆኑን ጠቁመው ወደፊትም ቢሆን ተመሳሳይ የመማሪያ መድረኮች  በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ ለዐውደ ርእዩ መሳካት በመዲናይቱ የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ የባህላዊ የምግብ ቤቶች እና የንግድ ተቋሟት  ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸውን አክለው ገልጽዋል፡፡

 /  በላቸው  ጨክ (ከዚህ  ቀደም  ለታዳጊ  ህጻናት ከአማርኛ  ወደ እንግሊዘኛ፣  ጀርመንኛ እና ፈረንሳይኛ  ቋንቋዎች የተተረጎመ የመማሪያ ሲዲ  ያዘጋጁ  እና ከዐውደ ርእዩ አዘጋጆቹ መካከል አንዱበሰጡት አስተያየት  በዐውደ ርእዩ ላይ  ከቀረቡት ማስረጃዎች መካከል  የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ የቅዱሳት መካናት፣ ስነጥበብ ክፍል ወዘተ ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል የታመቀ  ሃብት እንዳላት እና እነዚህ የአገር ሃብቶች በተገቢው  መልክ ተጠብቀው  ለተተኪው ትውልድ ማስረከብ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት  እንደሆነ ጠቅሰው በቅርቡ በተደረገ አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ወደ ኢትዮጵያ  ከሚመጡ የውጪ አገር ጎብኝዎች 85% የሚገመቱት የኢ///ቤተ ክርስቲያን ያሏትን ሃብት ለመጎብኝት አንደሆነ አና የተቀሩት 15% ያህሉ ወንዙን፣ አራዊቱን፣ አእዋፉን፣ ተራራውን ለመጎብኝት የሚመጡ መሆናቸውን በማውሳት "የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሃብት ሲባል የአንድ ተቋም ሃብት ሳይሆን የአገር ቅርስ መሆኑን ዝቡ መገንዘብ አለበት" ብለዋል፡፡ በማያያዝም ወደፊት ማኅበረ ቅዱሳን በሚያዘጋጃቸው ተመሳሳይ ዐውደ ርእዮች ላይ ህበረተሰቡ   በመገኘት ስለአገሩ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ሃብቶች ማንነት  እና እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ቢረዱ መልካም ነው በማለት አሰተያየት ሰጥተዋል፡፡ ተዘዋውሮ ለመጎብኘት ከሁለት ሰዓታት በላይ በሚፈጀው በዚህ  ዐውደ ርእይ  ላይ ከተገኙት በርካታ የውጪ አገር ዜጎች መካከል አንዱ የሆኑት ሚስተር ሉዊስ ፓርከር የተባሉ እንግሊዛዊ አንዱ ነበሩ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ  የባህላዊውን  የእስክስታ ውዝዋዜን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ ለማቅረብ ወደ አዲስ አበባ  የተጓዘውን  ጓደኛቸው ግብዣን ተቀብለው በቅርቡ ለጥቂት  ቀናት በኢትዮጵያ ውስጥ ቆያታ ያደረጉት ሚሰተር ሉዊስ በቆይታቸው ወቅት የላሊበላ እና የአክሱም ድንቅ አብያተ ክርስቲያናትን  እንዲሁም የጎንደር የፋሲል  ቤተመንግስትን ለመጎብኝት እድል እንደገጠማቸው ገልጽው "በኢትዮጵያ ባህል፣ ታሪክ እና መልክአ ምድር  በጣም ተደንቄያለሁ፡፡ እዚህ ዛሬ የምመለከተው  ቅርሶች እና ትምህርታዊ ገለጻዎች  ከዚህ  ቀደም ሰለ ኢትዮጵያ  የነበረኝን  ቁንጽል  እውቅት  እጅጉን አሻሽሎልኛል" ብለዋል፡፡ አስተያየታቸውን ሲያራዝሙም  አርሳቸው  በሚኖሩበት የምእራቡ ዓለም  ሰለ ኢትዮጵያ ያለው አመለካከት አና የዜና ሽፋን ጥሩ እንዳልሆነ መታዘባቸውን ጠቁመው አገርን እና በውስጧ ያሉትን ቅርሶች  በማስተዋወቅ ደረጃ  ቻይናውያን  ከኢትዮጵያውያን  የተሻለ ልምድ እንዳላቸው  መገነዘባቸውን ተናግረዋል፡:
በኢትዮጵያ የደርግ መንግስት ለመውደቅ ሲቃረብ በጊዜው በነበሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መልካም ቃድ የተቋቋመው  ማኅበረ ቅዱሳን በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ እና በተለያዩ አለማት ውስጥ በአስር ሺዎች  የሚቆጠሩ አባላት ያፈራ ሲሆን፣ በአገሪቱ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 100ሺዎች የሚገመቱ  ተማሪዎች የስብከት ወንጌል ትምህርት እንደተሰጣቸው  እና  በአሁኑም ወቅት   ተመሳሳይ ቁጥር ላላቸው ወጣት ተማሪዎች  ሰበከተ ወንጌል አየተሰጣቸው መሆኑን  በዐውደ ርእዩ  ላይ ተገለጿል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ከገጠር ቀበሌዎች አንስቶ እስከ ትላልቅ   ከተሞች ድረስ  የተዘረጋ የልማት እና  የሰብከተ  ወንጌል   አንቅስቃሴ እያደርገ  የሚገኘው  ማኅበረ ቅዱሳን ከአባላቱ እና በጎ ፍቃደኛ ወገኖች በሚገኝ የገንዘብ  መዋጮ  አማካኝነት  በተለያዩ ገዳማት  እና አብያተክርስቲያናት የሚገኙ የአብነት አስተማሪዎችን፣ ተማሪዎችን፣ አረጋዊያን እና ወላጅ አልባ ህጻናትን በመርዳት እና በማቋቋም የብዙ ወገኖችን ህይወት በመቀየር ላይ መሆኑ  ተገልጿል፡፡  ወደፊትም  ቢሆን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም ቤተክርስቲያኒቱ  ያሏትን ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ሃብቶችን  ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ጥረት የማድረግ እንቅስቃሴ መኖሩ ተመልክቷል፡፡
በአገር ውስጥም በማኅበሩ አባላት ጥናት እና ቀረጻ ተደርጎባቸው  ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለው መልኩ የተጀመሩ በርካታ የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኙ  ከአዘጋጆቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዐውደ ርእዩ  ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ ምእመናን  እንዲሁም በለንደን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ዛት ያላቸው  ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  እና የውጭ አገር ተወላጆች ተገኝተዋል፡፡


Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)