July 19, 2011

አቡነ ፋኑኤል በአትላንታ ክህነት ሰጡ፤ የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አላስፈቀዱም


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 19/2011/ TO READ IN PDF):-  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ፋኑኤል አትላንታ ጆርጂያ በሚገኘውና ራሱን ገለልተኛ ብሎ በሚጠራው በአትላንታ መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ወኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ተገው ክህነት መስጠታቸውን የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ቀሲስ ኤፍሬም ከበደ ጁላይ 10 ቀን 2011 በአትላንታ አካባቢ በሚተላለፈው AM 1100 የሬድዮ ጣቢያቸው በሰጡት የደስታ መግለጫ አስታውቀዋል።


አስተዳዳሪው ይህ ቀን (ጁላይ 10 ቀን 2011) ለቤተ ክርስቲያ ታላቅ የደስታ ቀን እንደሆነና ታላቅ የምራች መሆኑን ገለፀው አቡነ ፋኑኤል ለአንድ ዲያቆን የቅስና ማዕረግና ለሁለት መዘምራን የድቁና ማዕረግ መስጠታቸውን ገልፀዋል። አቡነ ፋኑኤል ያለ ሀ/ስብከታቸው ገብተው ክህነት በሚሰጡበት ወቅት ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር እንዲያውቁ አልተነገራቸውና ፈቃድም ያልተጠየቁት የዲሲና የአካባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሐምሌ 5 ቀን 2003 ዓ ም ተከብሮ የዋለውንና ቅዱስ  ጳውሎስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ታላቅ በዓል ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ለማክበር በአትላንታ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ነበር። ይህ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰው ድርጊት የተፈጸመው የክህነት አሰጣጥ ጉዳይ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እውቅና ውጭ መሆኑ ጉዳዩን በእጅጉ አሳሳቢና አጠያያቂ እንደሚያደርገው ብዙዎች ይስማማሉ።

አቡነ ፋኑኤል አሜሪካ መግባታቸው እንኳን በደንብ ባልታወቀበት ሁኔታ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እውቅናና ቃድ ው ወደ አትላንታ ሹልክ ብለው መጥተው ራሱን ገለልተኛ ነኝ ብሎ በሰየመ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው እንዲህ ይነት ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ውጭ የሆነ ድርጊት መፈጸማቸው ምን ያህል ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የማይገዙ መሆናቸውን ከማሳየቱም በላይ በአዋሳ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸሙትን የግፍ ተግባር በቀጣይነትም በሚመጻደቁባትና የዜግነት መብት ባገኙባት በሀገረ አሜሪካ የመቀጠል ድብቅ ዓላማ እንዳላቸው የሚያመላክት ነው ተብሏል

ወደቦታው የጠሯቸው እና ሥልጣነ ክህነቱ እንዲሰጥ ያደረጉት የአትላንታ መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ወኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቀሲስ ኤፍሬም ከዚህ በፊት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይከበርቤተ ክርስቲያኒቷ ገንዘብ በአግባቡ ይያዝ ብለው ጽኑ አቋም ይዘው የነበሩ ምዕመናንን በፖሊስ ኃይል ከቅዳሴ በፊት ተገደው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲውጡ እንዳስደረጉም ታውቋል


ይኸው ሕገ ወጥ የክህነት አሰጣጥ በተከናወነበት ወቅት ቤተ ክርስቲያኑ  ተሃድሶ የሚባል ነገር እንደሌለና እንዳንድ ማኀበራትና የተወሰኑ ግለሰቦች የሚያናፍሱት አሉባልታ እንደሆነ በመናገራቸው የሚታወቁት መምህር ተስፋዬ መቆያ  በቦታው ተገኝተው ማስተማራቸው ታውቋል።

ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልጠበቀው የክህነት አሰጣጥ እና ተያያዥ ጉዳዮቹ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያ መከበርና አንድነት የሚቆረቆሩትን ሁሉ በእጅጉ የሚያሳስብ ከመሆኑም በላይ ወደፊት ተስፋ የምናደርገውን የቤተ ክርስቲያ አንድነት የከፋ አደጋ ውስጥ የሚከት ስለሆነ ይመለከተናል የምንል ሁላችን ነገሩን ልናጤነውና በጸሎት ወደ ፈጣሪ ልናሳስብ ይገባል።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)