July 11, 2011

(ታሪክ በዚህ ሳምንት) - “መስለህ አስተምር በሚለው የመናፍቃን የማስተማር ዘይቤ” የሃይማኖት ሕጸጽ ባሰራጩ ሰባክያን ላይ ቅ/ሲኖዶስ የወሰደው ርምጃ ሲታወስ


  • “ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ የሚታየውን ችግር የማስወገድ አቅሙን እያጎለበተ በመምጣቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመናፍቃን ወራሪ ነጻ በማውጣት የሚካሄደው የሥራ እንቅስቃሴ በአጀንዳ ከቀረቡለት የወቅቱ ጥያቄ አንዱና ዋነኛው ሆኖ ተመዝግቧል(የቅዱስ ሲኖዶስ የ1990 ዓ.ም ውሳኔ መግቢያ)
  • ሕገ ወጥ ሰባክያኑ (አሰግድ ሣህሉ፣ በጋሻው ደሳለኝ) በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች ውስጥ ለመቀጠር ማመልከታቸው እየተነገረ ነው፤
 (ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 11/2011/ TO READ IN PDF CLICK HERE)፦ 13 ዓመት ወደ ኋላ፤ ወርኀ ግንቦት 1990 ዓ.ም - በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ የከተተው የአዲስ አበባ ከተማ ምእመን ዐይኖች በአዳራሹ ውስጥና ዙሪያ በተደረደሩ ከ20 ያላነሱ ቴሌቪዥኖች ተከብቧል፡፡ ምእመናኑ የጽርሐ ጽዮን አንድነት ማኅበር ቤተሰብ በሆነው እንደ መ/ር ታዬ አብርሃም ባሉ ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን አስተባባሪነት ቀደም ሲል በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ሰባክያነ ወንጌል በወሰኑት መሠረት በተመሳሳይ ቀንና በአንድ ላይ በዐውደ ምሕረትና በተለያዩ መንገዶች ባደረጉት ቅስቀሳ ጥሪ የተላለፈላቸው ነበሩ፡፡


(ጽጌ ስጦታው)
የቴሌቪዥኖቹ መሳክው /መስኮቶች/ ሚያዝያ 28 ቀን 1990 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ቆባቸውን እንደ ባርኔጣ እያወለቁና እያጠለቁ፣ ምንኩስናንና ኦርቶዶክሳዊነትን እያንኳሰሱ፣ ቤተ ክርስቲያንን በ”አሮጊቷ ሣራ…” ዲስኩራቸው እያሳነሱ እብደታቸውን በአደባባይ የገለጡትን የእነ ‹አባ› ብእሴ ሰላምንና ‹አባ› ዮናስን ጩኸትና ግርግር ለምእመናኑ ዐይኖች አሳይቷል፡፡ በዚያው ጉባኤ ወቅት ራሱን “የኦርቶዶክስ ተሐድሶ መነኮሳት ኅብረት” እያለ የሚጠራውና ከቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት በወጡና በእነርሱ አስኮብላይነት ከልዩ ልዩ ቦታዎች ፆር ጸንቶባቸው ከገዳማት ወጥተው በተሰበሰቡ የስም መነኮሳት ላይ ቋሚ ሲኖዶስ ያስተላለፈው የውግዘት ርምጃ በብፁዕ አቡነ ገሪማ በንባብ ተሰምቷል፡፡

“የተሐድሶ መነኮሳት ኅብረቱ” አባላት የቤተ ክርስቲያናችንን የማዕርገ ምንኩስና ክብር መግለጫና መለያ የሆነውን ቀሚስና ፈረጅያ ለብሰው፣ ቆብ ደፍተው፣ የቤተ ክርስቲያናችንን ቋንቋ ተጠቅመው በፕሮቴስታንቶች የገንዘብ ድጋፍ ምእመናንን ግራ ለማጋባትና ለማስኮብለል የተላኩ ነበሩ፡፡ እነዚህ ሐራጥቃዎች በውግዘት ከቤተ ክርስቲያን ከተለዩ በኋላ የተበታተነ ሲሆን ዛሬ እኩሎቹ ከሀገር ውጭ በአሜሪካ በተለያዩ ስቴቶች ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል እኩይ ሥራ ሲጠመዱ በሀገር ውስጥም ሕዝቡ ምንኩስናን እንዲጸየፍ፣ ኦርቶዶክሳዊ እምነት እንዲጠላና እንዲዋረድ ለማድረግ የእነርሱ የግብር ወንድሞች ብዙ አሳፋሪ ድርጊቶችን በስውርና በአደባባይ ሳይቀር በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡

የዛሬ 13 ዓመት ግንቦት ወር በእኒህ የስም መነኮሳት ላይ አስቸኳይ ውሳኔ የሰጠው ቅዱስ ሲኖዶስ በዚሁ ዓመት ሐምሌ 2 ቀን 1990 ዓ.ም ደግሞ በእነ ግርማ በቀለና ጽጌ ስጦታው መዝገብ ክስ በቀረበባቸው አምስት ግለሰቦች ላይ ታሪካዊ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ “በቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ዘርፍ ተመድበው እየሠሩ የወር ደመወዝ እየተከፈላቸው ሳለ የባዕድ እምነት ተከታዮችና አስፋፊዎች ሆነው ተገኝተዋል፤ የመናፍቅነት ጠባይ አሳይተዋል፤ በዚህም የክርስቶስን ተማላጅነትና የቅዱሳንን አማላጅነት የደመሰሰ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም ክብር የቀነሰ፣ በአጠቃላይም ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ያፋለሰ የሃይማኖት ሕጸጽ ትምህርት አሰራጭተዋል፤ ይህም በጥቆማ ተደርሶባቸው፣ ሊቃውንት ጉባኤ በ51 ገጽ አቀናብሮ ባቀረበው የሰውና የጽሑፍ ማስረጃ ተረጋግጦባቸዋል፤” ይላል የውሳኔው መግለጫ፡፡

በአምስቱ ሰባክያን ላይ ከቀረበውና በማስረጃ ከተረጋገጠው 34 የክስ ጭብጥ መካከል፡- “ክርስትናን በኢትዮጵያ ዙሪያ አትመልከቱ፤ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ተወት አድርጋችሁ ሌሎችን ተከተሉ፤ ተኣምረ ማርያም ጠቅሳችሁ አስተምሩ ብትባሉ ባታምኑበትም ማስተማር አለባችሁ፤ ክርስቶስ ሰው የሆነው ለአማላጅነት ነው፤ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እግራቸው የተቆረጠው ከይኩኖ አምላክ ጋራ ሲዋጉ በጦርነት ላይ ነው ይባላል፤  ኦርቶዶክስ በመሆን ማንም ገነት አይገባም፣ ካቶሊክ በመሆን ማንም ሲኦል አይወርድም፤ የእነ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ ስብከት ለአሁኑ ትውልድ ተራ ነው፤ ዛሬ ቢኖሩ ትምህርት ቤት መግባት ይኖርባቸው ነበር፤ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ አልመጣችም፣ ዛሬም በአክሱም የለችም፤ ክርስቲያን የሆንክ ወገን ሁሉ የእምነት ቅጽሮቿ ወደፈረሰባት ቤተ ክርስቲያንህ ተመለስ” የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

በተለያዩ ስውር የስብሰባ መድረኮች የመናፍቃኑን ትምህርት ሲያሰራጩ በካሴት ተቀርፆ የተገኘው የሰባክያኑ ድምፅ፣ ከሊቃውንት ጉባኤ በቃል ለቀረበላቸው የእምነት ክሕደት ጥያቄ በሰጡት መልስ፣ በጽሑፍ ለቀረበላቸው ጥያቄ መዝግበውና ፈርመው ባቀረቡት የመልስ ሰነድ፣ በተለያዩ ጊዜያት በጻፏቸው መጽሔቶች፣ ቴአትሮችና ልዩ ልዩ ፓምፍሌቶችና በድምሩ ሃያ ዘጠኝ ሰዎች በሰጡት የምስክርነት ቃል የሰባክያኑ የክስ ጭብጥና የተሳሳተ አባባላቸው ተጣርቶ ሊታወቅ እንደቻለ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ላይ የተጠቀሰውና በ51 ገጾች የተመዘገበው የሊቃውንት ጉባኤ አስተያየትና የውሳኔ ሐሳብ አረጋግጧል፡፡

በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ በበቂ ማስረጃ ተጣርቶ በቀረበለት የውሳኔ ሓሳብ መሠረት ቀኖናዊና አስተዳደራዊ ርምጃ መውሰድ የሚቻል መሆኑን በውሳኔው ያመለከተው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰባክያኑ ምናልባት በፈጸሙት ኢ-ቀኖናዊ ድርጊትና የተሳሳተ አባባል ተጸጽተው የሚመለሱ ቢሆን ያልተረዱትንና የረቀቃቸውን ምሥጢር አብራርቶ ለማስረዳት፣ ለማስተማር፣ ለመምከርና ለማስተካከል እንዲቻል በቅድሚያ ከያሉበት ቦታ ተፈልገው ለጥያቄ እንዲቀርቡና በሕጉ መሠረት የተከሳሾችን የመፋረጃ ሐሳብ ተቀብሎ መወሰን ማስፈለጉን ያስረዳል፡፡ በዚህም መሠረት እያንዳንዱ ተከሳሽ የቀረበበት የክስ ጭብጥና የሰጠው የመቃወሚያ መልስ የተመዘገበበት ማስረጃ ቀደም ሲል የሊቃውንት ጉባኤ ካሳለፈው የውሳኔ ሐሳብ ላይ እየተነበበ የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር ተከፍቶለት በሐዲስ ኪዳን፣ በብሉይ ኪዳንና በአጠቃላይም ቤተ ክርስቲያናችን በምትቀበላቸው ቅዱሳት መጻሕፍት የሰፈረው አከራካሪ ነጥብ ሁሉ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አስረጅነት እየተተረጎመና እየተብራራ የጠመመውን በማቃናት የተዛባውንም በማስተካከል ለማስረዳት ጥረት መደረጉን ይገልጣል፡፡

ለዘለቄታውም የተወሰኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተመድበውላቸው በመማር ማስተማሩ መርሐ ግብር የበለጠ በመረዳት ከስሕተት ታርመው እንዲመለሱ እንደሚደረጉ ለተከሳሾቹ በተገለጸው መሠረት፣ እያንዳንዱ ተከሳሽ ስሕተቱን አምኖ የቀኖና ቅጣት መፈጸም ይቻል ዘንድ በመጀመሪያ መንፈሳዊ ሕይወቱንና የቤተ ክርስቲያን ልጅነቱን በሚገልጽ ማመልከቻ ይቅርታ እንዲጠይቅ መመሪያ መሰጠቱን የውሳኔው መግለጫ ዘግቧል፡፡


ይሁንና ለሲኖዶሱ ከቀረበው የተከሳሾቹ ማመልከቻ መካከል ዲያቆን ግርማ በቀለ ባቀረበው ማመልከቻ፣ “ከመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ከሌሎች የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት በመጥቀስ ትክክለኛ ትርጉማቸውንም ባለመረዳት ስለተናገርኩት መልስ ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ያደርግልኝ ዘንድ በታላቅ ትሕትና እጠይቃለሁ፤” ሲል ዲያቆን ጽጌ ስጦታውም “ያስተማርኩት፣ የተናገርኩትና የጻፍኩት ሁሉ ስሕተት መሆኑን ስለ አመንኩ ይህን ሁሉ ስሕተቴን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቶልኝ ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ትምህርቱን እንድማር ይፈቅድልኝ ዘንድ በታላቅ ትሕትና አመለክታለሁ፤” በማለት ጠይቀው ነበር፡፡ በዚህም ወደፊት ግለሰቦቹ ከሚሰጣቸው ትእዛዝና መመሪያ ውጭ እንደማይሠሩና እንደማያስተምሩ፣ በየደረጃውም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማእከላዊ አስተዳደር በተዋረድ የሚተላለፈውን ሁሉ ተግባራዊ እንደሚያደርጉና የተመደቡበትን የቤተ ክርስቲያን ሥራ በመንፈሳዊ ስሜት እንደሚሠሩ ገልጸው ባለፉት ወራት ለፈጸሙት ኢ-ቀኖናዊ ድርጊት ሁሉ ምልአተ ጉባኤ ይቅርታ ያደርግላቸው ዘንድ በአጽንዖት መማፀናቸው በቃለ ጉባኤው ላይ ተገልጧል፡፡

በዚሁ መሠረት እነ ግርማ በቀለ አምስት ሠራተኞች በፈጸሙት የኑፋቄ ትምህርት ተጸጽተው መመለሳቸውን በቃልም ሆነ በጽሑፍ ካረጋገጡ በኋላ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በሚያዝዘው ድንጋጌ መሠረት ንስሐ ገብተው የረቀቃቸውን ትምህርተ ሃይማኖት እየተከታተሉ እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ ማድረግ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሚጠበቅ ድርሻ በመሆኑ በአምስቱ ሰባክያን ላይ ውሳኔ መስጠቱን የሲኖዶሱ ውሳኔ ያብራራል፡፡ በውሳኔው በአንደኛ ተራ ቁጥር በተለመከቱት ዲያቆን ግርማ በቀለና ዲያቆን ጽጌ ስጦታው ላይ በተላለፈው ውሳኔ የሚከተለው ሰፍሯል፤

“እስከ ሐምሌ 27 ቀን 1990 ዓ.ም ድረስ በታሪክና ሥነ ጽሑፍ ማደራጃ መምሪያ/በሊቃውንት ጉባኤ/ እየተማሩ እንዲቆዩ፤ ይሁንና ግለሰቦቹ ለጥያቄ በቀረቡ ጊዜ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መምህራን እንደሚመደቡላቸው በተገባላቸው ቃል መሠረት፤
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በሊቃውንት ጉባኤ ቢሮ እየተገኙ ከአባላቱ ጋራ በማስተማሩ ሥራ እንዲረዱ፤
ሀ/ ከሐምሌ 28 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ ለአዳሪ ተማሪዎች የተፈቀደውን የድርጎ ሒሳብ በየወሩ እያገኙ በደብረ ሊባኖስ ገዳም በመጻሕፍተ ሐዲሳት ቤት ገብተው የተከሰሱበትን ትምህርተ ሃይማኖት እንዲከታተሉ ሆኖ ከዚህም ጋራ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዐትና ገዳማዊ ሕይወት እያጠኑ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 1990 ዓ.ም ድረስ የረቀቃቸውን ምሥጢር እያደላደሉ እንዲቆዩ፤

ለ/ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጽ/ቤትም የእነ ግርማ በቀለን የትምህርት ይዘት እየተከታተለና እየተቆጣጠረ የተወሰነው የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ በተከሳሾቹ መንፈሳዊ ሕይወት ስላለው ሁኔታ ሪፖርት እንዲያቀርብ፤

ሐ/ የሥራ ምደባው ግን ከግለሰቦቹ የቀኖና ቅጣት ፍጻሜ በኋላ በሚቀርበው ሪፖርት አፈጻጸማቸው ተመርምሮ እንዲወሰን የሚል ይገኝበታል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ባለበት ዓላማ ከላይ በተገለጸው መልኩ ያሳለፈውን ውሳኔ አፈጻጸም ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት መርቶት ነበር፡፡ በ13 ዓመታት ሂደት የታየው እውነታ ግን ግርማ በቀለ ከ17ቱ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ማኅበራት አንዱ የሆነው “የእውነት ቃል አገልግሎት” ድርጅት መሥራች መሆኑ ነው፡፡ ድርጅቱ የቴዎሎጂ ምሩቃንና ተማሪዎች ላይ አተኩሮ ወስዶ እያሠለጠነ መልሶ በማስገባት በተናጠልም በቡድንም የኑፋቄ ትምህርቶችን በየአቅጣጫው ያሰራጫል፤ ተልእኮውም ዐውደ ምሕረቱን መቆጣጠር ነው፡፡“የርቀት ትምህርቶችን በማስተማር፣ በራሪ ጽሑፎችን በማሰራጨትና ቤተ ክርስቲያናችንን የሚነቅፉ መጻሕፍት በማሳተምና በማሰራጨት በርብርብ እየሠራ ይገኛል፤ በአዲስ አበባና በሰሜን ኢትዮጵያ ከተሞች ላይ ቢሮ ከፍቶ እየሠራ ይገኛል፤”/የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ፤ ገጽ 81/፡፡ ጽጌ ስጦታውም ከ17ቱ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራት አንዱ የሆነውን “የጽዋ ኮኔክሽን ቸርች” በማቋቋም የጽዋ ማኅበራትን ለመበከል በመሥራት ላይ ይገኛል፤ “አሁንም ኦርቶዶክስ ነኝ” እያለም መርከብ በተሰኘ የግል ጋዜጣው ኑፋቄውን ሲያስፋፋና የግለሰቦችን ስም ሲያጠፋ በሕግ ተጠያቂ ሆኖ ዘብጥያ ወርዶም ነበር፡፡

ከ13 ዓመት በፊት የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነበትን ሓላፊነት የመወጣት ችሎታ የነበረው ቅዱስ ሲኖዶስ ችግር ያለባቸው የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ መልእክተኞች ቢያንስ ጥፋታቸው ታውቆ ተወግዘው እንዲለዩ፣ ገሚሶቹም ስሕተታቸውን አምነው በትምህርት የሚታረሙበትን ታላቅ ተግባር ፈጽሟል፡፡ ዛሬ ግን ለተመሳሳይ ድርጊቶች ምን ዐይነት ምላሽ እየሰጠ እንዳለ ማሰቡ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

ሰሞኑን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካባቢ እንደተሰማው “ክርስቶስ ዛሬ በአብ ቀኝ ቆሞ ይማልዳል” በማለት የሚታወቀው አሰግድ ሣህሉ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፣ “ሥላሴ አትበሉ ተባለ እንጂ በሥላሴ አትመኑ አልተባለም፤ ጠበል፣ መስቀል አያድኑም” ብሎ በአንደበቱ የነገረን በጋሻው ደሳለኝ በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በተዘዋዋሪ ሰባኪነት ለመቀጠር በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አማካይነት ለመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ጥያቄ የማቅረባቸው ዜና ተጠናክሮ እየተሰማ ነው፡፡ ከእነርሱም ጋራ በሪሁን ወንድወሰን፣ ትዝታው ሳሙኤል፣ ያሬድ አደመ ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡ ጥያቄያቸው ከፓትርያርኩ ቢሮ ለዋና ሥራ አስኪያጁ ቢሮ መመራቱም ተነግሯል፡፡ የመቀጠር ሙከራው በውጭና በዐውደ ምሕረት ያልተሳካላቸውን የጥፋት እንቅስቃሴ ሕጋዊ ለማድረግ ከማለም የተነሣ እንደሆነም ተገምቷል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ በእኒህ ሕገ ወጥና የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ ምንደኞች በሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚታየው ሕዝባዊ ቁጣ እያየለ መሆኑን ከዲላና እና ከአዲስ አበባ ከደረሱን ዘገባዎች ተረድተናል፡፡ በዲላ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን “በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የምንሰጠው ገለጻ አለን፤ ጠላቶቻችንን ልናሳያቸው ነው፤ ውጊያው ሊጀመር ነው፤” እያሉ ብጥብጥ ሊያስነሡ የሞከሩት በጋሻው ደሳለኝ፣ ትዝታው ሳሙኤልና ተረፈ አበራ ከሌሎች 13 ግለሰቦች ጋራ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርጓል፤ ያሬድ አደመ በግርግር ተሰውሯል ተብሏል፡፡ ኀሙስ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ 22 ካልዲስ ካፌ አካባቢ በጋሻው ደሳለኝን በድንገት የከበቡት ወጣቶች “የንፍሮ ቀቃይ ልጅ! ከወንጌሉ ይልቅ በዕድር ደንብ ነው ያለነው” ሲል በተናገረው ድፍረት ተጠይቋል፤ በስሕተቱ የሚቀርብበትን ተቃውሞ “ረብሻ፣ ጫጫታ፣ ዝላይ” በማለት የሚገልጸው በጋሻው ግን በድፍረት ስለተናገረው ቃል ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ስሕተቱን ማብራራት በመምረጡ በወጣቶቹ ሊደርስበት ከነበረው ጥቃት በገላጋዮች ብርታት እንደተረፈ ተዘግቧል፡፡

ሐምሌ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 19 ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ያከብራሉ፡፡ ሙስናና ኑፋቄ ተሳስረውና ተመጋግበው በጎለበቱበት የአምስተኛው ፓትርያርክ የሁለት ዐሥርት ዓመት ዐምባገነናዊ አስተዳደር ቤተ ክርስቲያናችን በቅርብ ታሪኳ ባላየችው መጠን የቤተ ክህነቱን መዋቅር አልፈስፍሶታል፡፡ በዚህም በመጠቀም እኒህ አጉራ ዘለልና የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ መልእክተኞች ሠልጥነው ቆይተዋል፡፡ ይሁንና ለሃይማኖታቸው ቀናዒ በሆኑ አገልጋዮችና ምእመናን መነሣሣትና መቀናጀት ኀይላቸው እየተዳከመ ቢሆንም ቀደም ሲል በተገለጸው መልኩ በአንዳንድ ስፍራዎች እየተሹለከለኩ በሚፈጽሙት ምእመኑን የሚያስቆጣ ተግባር ሁኔታው ወዳልተፈለገ ውጤት ከማምራቱ በፊት ሊታሰብበት ይገባል፤ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የውስጥ መዋቅር ለመግባት አቅርበውታል የተባለው ጥያቄ ተፈጻሚ ከሆነም የሚከተለውን ጥፋት ማንም ሊገምተው እንደማይችል በተለይም ለፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

13 comments:

Anonymous said...

With God everything is possible. Dejeselam, God bless your service.We are geting very important information about our church from you. Now, we all are responsible. We need to address the problem from the source not the symptom. We shouldn't think that Begasha is the only problem. He is now lost and he will not recover again. Because, our people has tolerance limit and he abuse the people over that limit. Morover,he has not confessed his mistake. He still want confuse the people and even he undermind the thoughtfulness of the people.The people knows what they are doing.Let us think to the cause of the problem. I personaly participated the conference organized by Mahibere Kidusan. Just go and see it on Hamle 10, 2003 E.C at Kokeb Adarash.

yemelaku bariya said...

አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እየሆነ ነው ነገራችን:: አሁን እኮ የቤተ ክርስቲያናችን ዋናው አመራር እኮ የተሃድሶው አራማጅ አይደሉም ለማለት የሚያስችል ትንሽ እንኳ ምክንያት የለም:: ስለዚህ የመናፍቃኑ፣ የሙሰኞቹ፣የደናቁርቱና የሙዳየ ምጽዋት ገልባጮቹ ከለላና መከታ የሆኑት አባ ጳውሎስ ከስልጣናቸው ሊወርዱ እና ሊወገዙ የሚገባቸው ሲሆን:: ዘርፈው ላዘረፉት ንብረትና ገንዘብ በሕግ መጠየቅ አለባቸው::
Paulos and his crew has to go!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

Ye Ethiopia hizibe hoye le Egiziabehere tseleyu ebakachihun. Egiziabehere hoye betchrstianachinene tebikilene, le sewochim lebona sitachew. Ebakachihun hulachinem be nitsuh lebona entseley.

Temelkach said...

The solution is one and only one. Paulos has to go!! Not only leave us alone but also pay for all the damages he caused on our church, our digniy, our belief............
I mean for whatever crime he commit. He is more than criminal. We lost not only lives but also our church's dignity!!

Let the people force him out and take very serious action on him!!

What are we afraid of? I know what people think (meles??).I clearly understan meles is with this criminal. But what we have is far far more powerful than what paulos has behind him. God is with us and for sure we are the winners!!

Oh God! please save your people and TEWAHDO!!

gonderew said...

I DON'T GET WHAT ETHIOPIANS THINK,WE READ IN DIFFERENT ETHIOPIAN ORTODOX TEWAHIDO CHURCH AND ETHIOPIAN HISTORY BOOKS KIDUSANS,SEMATANS,HAWARIATS AND CHRISTIANS FIGHT AND DIED FOR THIER RELIGION .EVEN NOW IN EGYPT CHISTIANS FIGHT AND DIED.WHEN WE COME TO ETHIOPIAN ORTODOX CHURCH OUR FATHERS AND MOTHERS ALSO FIGHT AND DIED FOR THIER RELIGION /e.g during emperor sisinios the father of atse fasil more than 25.000 people died,and the king loss his power./ BUT THIS GENERATION INCLUDING ME, ARE VERY SELFISH.WE DON'T WENT TO FIGHT AND DIED INSTEAD WE COVER OUR SELFISHNESS AND SCARE BY SAYING GOD WILL GIVE US SOLUTION OR PRAY TO GOD.I KNOW GOD CAN DO. BUT ARE WE READY TO PRAY? ARE WE READY TO KNOW AND READ WHAT GOD SHOWS AND TELL US? EXCEPT SOME,THE ANSWER WILL BE NO.EVEN SOMETIMES ABOUT ABA G/MEDIHIN;GOD MAY ALLOW HIM TO DO ALL THIS THING IF NOT, GOD CAN REMOVE THIS GUY.A LOT OF PEOPLE SAYS.
NO!BY THIS KIND OF WAYS,TRUST ME WE WILL NOT GET ANY SOLUTION IN STEAD WE LOSS OUR CHURCH TURN BY TURN.
AS I SAW RESENT CASES IN CHURCH e.g CASE OF GETACHEW DONI AFTER HE REMOVE FROM HIS POSITION IN AWASSA,THE HEAD OF THE CHURCH APPOINT HIM IN THE OFFICE /WHEN I SAID THE HEAD OF THE CHURCH IT IS NOT MEAN SINODOS RATHER ABA G/MEDIHIN/.FROM THIS WHAT YOU UNDERSTAND BEGASHAW AND HIS GROUP ALSO THEY HAVE BIG CHANCE TO GET THE POSITION WHAT THEY WANT. BELIVE ME.
"getawan yetemamenech beg latun wichi tasadiralech" ABA G/MEDIHIN IS THE ONLY PROBLEM FOR OUR CHURCH.DON'T GO ANY WHERE TO FIND THE PROBLEM. PLEASE CHRISTIAN OPEN YOUR EYES OR DON'T SCARE TO FIGHT THE CHALLANGE OF THE CHURCH.IF WE REMOVE THIS PERSON FROM OUR CHURCH, OTHER GROUP WHO DISTURB OUR CHURCH WILL NOT GET CAVE TO HIDE.THAT IS THE MAIN SOLUTION.
I WILL TELL YOU ONE THING DON'T FORGET ETHIOPIA IS THE COUNTRY OF GOD NO ONE CANN'T TOUCH.
GOD BLESS GREAT ETHIOPIA
AMEN

Anonymous said...

Paulos and his crew has to go!!!!!!!!!!!!!

danf said...

kamachewum gize balay ya Igziabher tsega yibzalachu. yamitisatun maraja hulu kabaki balay naw bihonim gin lamalaw ethiopia madras yamichil radio wayim biyans gazeta kaljamarachu bastakar ahunim ka 80% balaay yalawun hizb madras atchilum, ina ibakachu biyans gazetoch yanantan maraja yizagbu zand fikad situwachaw. salama Igziabher kananta gar yihun.

Anonymous said...

Pauli has to go,
Pauli has to go,
pauli has to go.

let us stand together
let us free up our chuch
let us stand now

Anonymous said...

"Yenifro Kekay Lijoch"

Anonymous said...

dejeselamn yamenekattatale bageleme behone ega hagare wosette lahaymanotachen eyatagalo yaloten memane basalote enereda.pray pray pray

Anonymous said...

dejeselamn yamenekattatale bageleme behone ega hagare wosette lahaymanotachen eyatagalo yaloten memane basalote enereda.pray pray pray

Anonymous said...

watatocheo bareto yaabaten lebe wada lejoche

የብስራት እይታ Bisrat Gebre's View said...

እግዚአብሔር ይመስገን ::
ሁሉም የሚገባውን ያገኛል; ምዕመኑም በወሳኝ ሠዓት መንቃቱ 'መናፍቃን' ያለሙት ላይሆን ከጫፍ ደርሷል::
ብቻ አሁንም ጥንቃቄ ያስፈልጋል !
የድንግል ማርያም ጥበቃ አይለየን::
አሜን::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)