July 2, 2011

በ“ሰባት ወይራ ሆቴል” አስተዳደር ጉዳይ የቅዱስ ላሊበላ ደብር እና ጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተወዛገቡ ነው


  • አስተዳዳሪውን ያባረሩት የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበር በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሽምግልና አስተዳዳሪው “ለተወሰነ ጊዜ ወደ ገዳሙ ማረፊያቸው ገብተው በክብር እንዲወጡ” በሚል ተስማምተዋል፤ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ በበኩላቸው “ሳልበታትነው” በሚል በገዳሙ ማኅበር አንድነት ላይ መዛታቸው ተሰምቷል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 2/2011, TO READ THE NEWS IN PDF, CLICK HERE)፦ የቅዱስ ላሊበላ ደብር እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የቤቶችና ሕንጻዎች አስመላሽ ኮሚቴ  በ“ሰባት ወይራ” ሆቴል አስተዳደር ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው፡፡
የደብሩ አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኮንን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ፊርማ ተጠርተው ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ትናንት ሰኔ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ወደ ኮሚቴው ቀርበው “በሰባት ወይራ ሆቴል ጉዳይ ሕዝቡን እያነሣሱ ነው” በሚል “ተግሣጽና ምክር” ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡
“ተግሣጽና ምክር” ተደርጎበታል በተባለውና የደብሩ አስተዳዳሪ ከአራት ተወካዮች ጋራ በተገኙበት ስብሰባ በጉዳዩ ላይ “ብቻዬን አልወስንም” ያሉት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ፣ “የሆቴሉ ባለቤትነትና አስተዳደር ጉዳይ በቋሚ ሲኖዶስ ተጠንቶ  መፍትሔ ይሰጥበታል” በማለት ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እንደመሩት ተዘግቧል፡፡

የደብሩ አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኮንን በስብሰባው ላይ፣ “የባለቤትነት ጥያቄ የጠየቀው ሕዝቡ ነው፤ እኔ አይደለሁም፤ ደብዳቤ ጻፉና (ኮሚቴውን) ካስፈለገ በሕዝብ ፊት ይነበብ፤ ሕዝቡ ይጠየቅ” በማለት አቋማቸውን አጠንክረው እንዲገልጹ አደራ ካሏቸው ምእመናን ተቃራኒ አካሄድ መከተላቸው ተገልጧል። ከፓትርያርኩ ጋርም ሳይገናኙ እንዳልቀረ እየተነገረ ይገኛል፡፡ አስተዳዳሪው ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለኤጲስ ቆጶስነት ከታጩት 30 ያህል ቆሞሳት አንዱ የነበሩና ለወደፊቱም ተስፈኛ በመሆናቸው የምእመኑን ጥያቄ “ጉዳዩ የእኔ አይደለም” በሚል መንፈስ እንዳቀረቡት ተደርጎ ተወስዶላቸዋል - አንድም ኤጲስ ቆጶስነቱ ታስቦ እንዳይቀር፣ ዳግመኛም ከእልቅናቸው እንዳይነሡ፡፡

የደብሩ አስተዳደርና የከተማው ምእመናን ሆቴሉ እንዲመለስላቸው ለረጅም ጊዜ አበክረው ሲጠይቁ የቆዩ ቢሆንም ሆቴሉ የሚገኝበት ሥፍራ የዓለም ቅርስ የሆነው ሕንጻ ላሊበላ በሚገኝበት አቅራቢያ በመሆኑ በቅርቡ ይፈርሳል ተብሏል፡፡

የግርማዊ ቀዳማዊ ዐጼ ኀይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ የሆኑት የልዕልት ኂሩት ደስታ ንብረት የነበረውና ልዕልቲቱ በ1963 ዓ.ም “ለቅዱስ ላሊበላ ደብር መርጃ ይሁን” በሚል የሰጡት የሰባት ወይራ ሆቴል ባለቤትነት የቅዱስ ላሊበላን ደብር አስተዳደርን ከመንበረ ፓትርያርኩ የቤቶችና ሕንጻዎች አስመላሽ ኮሚቴ ጋራ እያወዛገበ ያለው ሆቴሉ ልዕልቲቱ ደብሩ ሆቴሉን በባለቤትነት ይዞ እያስተዳደረ ገቢውን ለማስቀደሻ እና ለጧፍ እንዲጠቀምበት የጻፉትን ደብዳቤና በሕይወት የሚገኙ የዐይን እማኞችን ምስክርነት፣ የመንግሥት ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በ1991 ዓ.ም የሆቴሉ ንብረትነት የደብሩ መሆኑን ያረጋገጠበትን ሰነድ እንዲሁም ደብሩ ለፍ/ቤት ባቀረበው የይገባኛል ጥያቄ መሠረት የባለቤትነት መብቱን ያረጋገጠበትን ውሳኔ በማስረጃነት ይጠቅሳሉ - ለደብሩ የሚሟገቱ ምንጮች፡፡

በደርግ/ኢሕዴሪ መንግሥት ተወርሶ ከለውጡ በኋላ ከ1991 - 1997 ዓ.ም በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ሥር የቆየው ሆቴሉ በ1997 ዓ.ም ነበር ከደብሩ ጋራ ርክክብ ለማድረግ የወሰነው፡፡ በዚህ ወቅት “በደርግ መንግሥት ተወርሰው የነበሩትን ቤቶችና ሕንጻዎች የማስመለሰው እኔ ነኝ፤ የሰባት ወይራም ጉዳይ ማለቅ ያለበት በእኔ ሥር ነው” ያለው በጠቅላይ ቤተ ክህነት የቤቶችና ሕንጻዎች አስመላሽ ኮሚቴ ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ተረክቦ ለሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት፣ ሀገረ ስብከቱም ለደብሩ ሊሰጥ ስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡ ይሁንና በዚሁ በ1997 ዓ.ም አስመላሽ ኮሚቴው ሆቴሉን ለማከራየት ጨረታ ያወጣበታል፤ ለደብሩም “የባለቤትነት” በሚል ብር 2500 ለመስጠት ይወስናል፡፡

በጨረታው መሠረት ቸሩ አበበ የተባሉ ምእመን በየወሩ ብር 32,000 በማቅረብ ከፍተኛውን የኪራይ ዋጋ ቢያቀርቡም ብር 25,000 ኪራይ ላቀረቡትና የአቡነ ጳውሎስ ዘመድ ናቸው ለተባሉት ለአቶ አምኃ ኀይለ ሥላሴ ይፈቀዳል፡፡ ይህ የኪራይ ዋጋ እንደተባለው በየወሩ ለቤተ ክህነቱ መከፈሉን እንደሚጠራጠሩ የሚገልጹት ምንጮቹ፣ ለደብሩ ባለቤትነት ተብሎ የሚከፈለው ብር 2 ሺህ 500 በታኅሣሥ 2003 ዓ.ም ወደ ብር 5000 ከፍ ቢልም በየጊዜው ሲስተጓጎል መቆየቱን ያስረዳሉ፡፡

በየዓመቱ በቅዱስ ላሊበላ ደብር በድምቀት በሚከበረው የልደት በዓል ወቅት ብቻ ከብር አንድ ሚልዮን በላይ ገቢ እንደሚያስገኝ በተመለከተው የሰባት ወይራ ሆቴል ሥራ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ዳጎስ ያለ ገቢ ሲያካብቱ የቆዩት ግለሰቡ ለመንግሥት የሚከፍሉት ግብር አልነበራቸውም፤ “የቦታ ግብርና የአከራይ ተከራይ ተጠይቀውም አያውቁም፡፡” ጉዳዩን ያጠና የሚመስለው የገቢዎች ጽ/ቤትም ባለቤትነት የሚለው አካል ብር 216,000 ውዝፍ ግብር እንዲከፈል ያዝዛል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓለም የቅርስ ይዞታዎች መስፈርት መሠረት “ኮር ዞን” ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ግንባታ እንዲፈርስ/እንዲጸዳ የሚያዝዝ በመሆኑ በ”ኮር ዞን” ውስጥ ያረፈው ሰባት ወይራ ሆቴልም ተነሥቶ ምትክ ቦታ እንዲሰጠው ይወሰናል፡፡ የአቶ አምኃ ኀይለ ሥላሴ ተወካይ ሆነው ሆቴሉን የሚያስተዳድሩት ግለሰብም ሆቴሉ ፈራሽ መሆኑን በመረዳት የሆቴሉን ጥንታዊ ዕቃዎች በአሸተን ማርያም አቅራቢያ ወዳሠሩት ሎጅ ማጋዝ ይጀምራሉ፤ እጅ ከፍንጅ ተይዘውም በደብሩ ጽ/ቤት ክስ ይመሠረትባቸዋል፡፡

በዚህ ወቅት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቤቶችና ሕንጻዎች አስመላሽ ኮሚቴ ሊቀ መንበር መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም በተልእኮ ገሥግሰው ሄደው፣ “መክሰስ ያዋጣል ወይ? ብንስማማ አይሻልም ወይ? ሆቴሉ ይመለስልን ካላችሁም 100,000 እንስጣችሁ …” በማለት ለማግባባት ይሞክራሉ፡፡ የደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤትም የቅዱስ ላሊበላ ከተማን ምእመን ድምፅ/አደራ በመያዝ የመጋቤ ካህናቱን ማባበያ ይቃወማሉ፤ ስለተቃውሟቸው ከመጋቤ ካህናቱ የተሰጣቸው ማስፈራሪያም “አንለቃችሁም፤ ክስ የትም አያደርሳችሁም፤ ምድር ትገባላችሁ!!” የሚል እንደነበር ምንጮቹ አጋልጠዋል፡፡

የቤቶችና ሕንጻዎች አስመላሽ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ከ1987 ዓ.ም አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በቀድሞው መንግሥት ተወርሰው ከነበሩት ቤቶችና ሕንጻዎች 700 ያህሉን በማስመለሱ የተመሰገነ የሥራ አፈጻጸም ያላቸው መጋቤ ካህናቱ እንዲህ ያለ ዛቻ በመናገራቸው የደብሩን አስተዳደርና ምእመኑን ክፉኛ አሳዝነዋል ተብሏል፡፡ ከእርሳቸው በባሰ አኳኋን ለሕግ የበላይነት እንዲቆሙ የሚጠበቅባቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ነገረ ፈጅ “ስለ ተሰረቀው ንብረት ምን አገባችሁ!” በማለት ለመገሠጽ መሞከራቸው ግርምትን ፈጥሯል፡፡

በሌላ በኩል እሑድ፣ ሰኔ 19 ቀን 2003 ዓ.ም የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ተክለ ማርያም ዘውዴ ከወጡበት ተመልሰው እንዳይገቡ በማገድ ርምጃ የወሰዱት የገዳሙ ማኅበር አባላት፣ አስተዳዳሪው ወደ ገዳሙ ተመልሰው የተወሰነ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ጉዳዩን ከሸመገሉት አባቶች ጋራ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጧል፡፡ “የገዳሙን ት/ቤት፣ ክሊኒክና ኬክ ቤት እንዲሁም ለሙዓለ ሕፃናትና ሁለገብ አገልግሎት የተሠራውን ሕንፃ አስተዳደር ከገዳሙ በመለየት ለብዝበዛ አጋልጠዋል፤” በሚል ባለፈው ሳምንት እሑድ ከቅዳሴ በኋላ አስተዳዳሪውን በወጡበት ያስቀሩት 67 የገዳሙ ማኅበር አባላት የአስተዳዳሪውን መኖሪያ ቤት አሽገውና ስልካቸውን ቆርጠው የውስጥ ዙሪያ ጥበቃቸውን በማጠናከር የሚመጣውን ተጽዕኖ ለመቀበል ተዘጋጅተው ነበር፡፡

ይሁንና ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጠዋት የገዳሙ የበላይ ጠባቂ በሆኑት ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ ገብረ አማኑኤልና ቀሲስ በላይ መኮንን አማካይነት በተደረገው ውይይት አስተዳዳሪው ወደ ገዳሙ ተመልሰውና ከማንኛውም ሓላፊነት ተገልለው በማረፊያቸው ጥቂት ቆይታ ካደረጉ በኋላ በሌላ እንዲተኩ ስምምነት መደረሱ ተዘግቧል - “የመፍትሔው አካሄድ አለቃው በወጡበት ከቀሩ ሌላ የሚቀበለን ደብር አይኖርም የሚል ይመስላል፤” ብለዋል የጉዳዩ ታዛቢዎች፡፡

በዚህም መሠረት ወደ ገዳሙ ማረፊያቸው ሲመለሱ ከ67 ማኅበር መካከል በሁለት ወዳጆቻቸው ብቻ አቀባበል የተደረገላቸው አስተዳዳሪው ከፍተኛ መረበሽ ይታይባቸው እንደነበር ተመልክቷል - “አስታርቁኝ እንጂ” ሲሉ ሽማግሌዎቹን ቢማፀኑም “የለም፣ እኛ አድርሱ ነው የተባልነው፤ የቀረውን እርስዎ ይጨርሱ” በሚል ተመልሶላቸዋል፡፡ አስተዳዳሪው ለምን ያህል ጊዜ በገዳሙ እንደሚቀመጡ የተወሰነ ቀነ ገደብ የለም፡፡ መልአከ ሰላም አባ ተክለ ማርያም በግንቦቱ ርክበ ካህናት ለኤጲስ ቆጶስነት ከታጩት ቆሞሳት መካከል አንዱ እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡

ቀደም ሲል በአሜሪካ የ12 ዓመት ቆይታ እንዳላቸው የሚነገርላቸውና በዚያ በተደረገላቸው የወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ መስተንግዶ ውለታ እንዳለባቸው፣ አሁንም ከዚያ ተጠርተው እንዲሾሙ ሚና በተጫወቱት ወይዘሮዋ አስተዋፅኦ ውለታው ጭራሽ የከበደባቸው መልአከ ሰላም አባ ተክለ ማርያም፣ የገዳሙን የልማት ተቋማት አስተዳደር በእጅ አዙር በወይዘሮዋ ተጽዕኖ/ቁጥጥር ሥር እንዲወድቅ በማድረጋቸው ይወቀሳሉ፡፡ በእርሳቸው አስተዳደር የገዳሙ ት/ቤት አክሳሪ መሆኑን የሚናገሩት የገዳሙ አለቃ አሁን ከተሠራው አዲሱ ሁለገብ ሕንጻ የሚገኘው ገቢ ት/ቤቱን ለመደጎም እንጂ ለገዳሙ የሚያደርገው ፈሰስ እንደማይኖር በመግለጽ አስተዳደሩን ከገዳሙ ለይተዋል፤ በዚህም የሕንፃውና የት/ቤቱ ሠራተኞች ከገዳሙ ማኅበር ጋራ የጥቅም ግጭት ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ በመካከላቸው ቅራኔ ፈጥረዋል፡፡

አሁን የገዳሙ ማኅበር አባላት ቀዳሚ ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ኦዲት ሳይደረግ ለሙስና ተጋልጦ የቆየው የት/ቤቱ፣ የክሊኒኩ፣ የኬክ ቤቱ ሒሳብ እና የንስሓ ልጆቻቸውን እያስተባበሩ ያሠሩት የአዲሱ ሁለገብ ሕንፃ ሥራ ዲዛይንና ግንባታ ወጭ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር፣ ለልማት ተቋማቱ የተመራጭነት እሴት የሚሰጠው የገዳሙ መንፈሳዊ አገልግሎት ከተቋማቱ አሠራር ጋራ በአንፃራዊ አሠራር ተደጋግፎ የሚተዳደርበት ዘይቤ እንዲመቻች ነው፡፡

ይኸው የገዳሙ ማኅበር ጥያቄ ያስቆጣቸው ወ/ሮ እጅጋየሁ ተቃውሞ ከተጠናከረበት ቀን አንሥቶ በማግባባት ስም በሚልኳቸው የተለያዩ ግለሰቦች አማካይነት “ማኅበሩን እንደሚበታትኑት” መዛታቸው ተሰምቷል፡፡ ሆኖም ማክሰኞ ሰኔ 21 ቀን 2003 ዓ.ም ሁለት ጊዜ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ የተወያዩት የማኅበሩ ተወካዮች ቀድሞም ጉዳዩ እልባት እንዲበጅለት ሲያቀርቡ የቆዩትን ጥያቄ ግልጽ በማድረግ እንዲህ ነበር ያሏቸው - “ገዳሙ ተከብሮ የቆየ ነው፤ ማኅበሩ በሴትዮዋ ጣልቃ ገብነት/በእጅ አዙር አይተዳደርም፤ የነበሩት አለቃ የሚመለሱ ከሆነ እስከ ደም መፋሰስ እንደርሳለን፤ የሚመጣውም አለቃ ቢሆን አቋሙን ግልጽ እንዲያደርግና ቃል እንዲገባ የምናደርገው ጥያቄ ይኖረናል፡፡”

9 comments:

Anonymous said...

ebakachihu begnbotu sinodos lishomu yeneberutn sim zirzir giletsulntsuln

Anonymous said...

ebkachu bate krstyanen leahzabe mesakay atadrgwat mestrwan adebabay eyawtachu weyet yemteta ena atent yemget alena sele egzabhare blachue .

Anonymous said...

yimaharene weyisahalene!!!!!!

Anonymous said...

ወይ መድሀኒያለም!!! ሴትዮዋ ምን ነክቷቸው ነው???ቆይ የበላይ ሆነው የተሾሙት መቼ ነው???እረ ኤልዛቤል እባክዎ ንግዱን ከውጭ አርጉት ምን መአት መቶብዎ ነው እንዲህ ቤቱን የሚያምሱት???እኔስ ፈራሁልዎ

Anonymous said...

Are we going to gather together and rise up to make a difference or just sit down and see whats being done to our beloved country and Church by an Eritrian woman named ejegayehu. She has a mission to destroy the country so let's do something about it.Only talking is not going do any good.

Anonymous said...

batame yasazenale kaethiopia wochea yalanawe endate ewenataga abatochen maredate enedamenchele takomone ebakachohe

Anonymous said...

batame yasazenale kaethiopia wochea yalanawe endate ewenataga abatochen maredate enedamenchele takomone ebakachohe

Anonymous said...

To whom it may concern

I do not understand what is going on?
Who is this lady after all , please idle lady can not lead Church ,even she can not lead herself.I think it is time to say no for everyone who is acting on the drama rather than worshiping God.

Who gave them power? no one.They just using the opening. Like it is done about other we need to follow up on this kind of rude.We need to tell their story to all people.

It is time to raise different issues and discuss in here and decide something all over the world.

Let us do one thing in a day after discussing and putting pressure on them ,we have talked for many years.

For example.Let us give whatever evidence we have and discuss

fikerteselasie said...

ende ende beande set endehe entamese ende endet teye melate ehete atache. egiziaber amelake astewaye lebona yesteshi lela menie yebalae!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)