July 3, 2011

“ጳጳሶቹ አይረቡም … (ቤተ ክህነቱ) ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው” (አቦይ ስብሐት ነጋ)


(ደጀ ሰላም፤ ላይ 1/2011, To Read in PDF, click HERE)፦ የሕወሐት/ኢሕአዴግ የፖለቲካ መሐንዲስ መሆናቸው የሚነገርላቸው አረጋዊው አቶ ስብሐት ነጋ ስለ ቤተ ክህነት በሰጡት ግልጽ አስተያየት ላይ “ጳጳሶቹ አይረቡም”፣ ቤተ ክህነቱም “ወደሞት አፋፍ እየሄደ ነው” ሲሉ ተናገሩ። ዛሬ አርብ ሰኔ 24/2003 ዓ.ም በወጣው “ፍትሕ” ጋዜጣ ላይ ረዥም ጽሑፍ ያስነበቡት አቶ ስብሐት ነጋ (በተለምዶ አቦይ ስብሐት ይባላሉ) ስለ ቤተ ክህነቱ በከፋ አስተዳደራዊ ብልሽት ውስጥ መውደቅ ምክንያቱ “ራሱ ቤተ ክህነቱ” እንጂ መንግሥት አለመሆኑን አብራርተዋል። 


ባለፈው ሳምንት አርብ ሰኔ 17/2003 ዓ.ም ወጥቶ በነበረው የፍትሕ ጋዜጣ ላይ አቶ ተመስገን ደሳለኝ የተባሉ ግለሰብ ለሰጡት አስተያየት መልስ በሆነው በዚህ የአቶ ስብሐት ማብራሪያ ቤተ ክህነት ከጥንት ዘመን ጀምሮ ከመንግሥት ጋር ተጣብቃ እንደኖረች፣ አጼ ኃ/ሥላሴ “ቅዱስ ተብለው ታቦት ተቀርጾላቸው እንደነበር”፣ ለዚህ ደግሞ በዋነኛነት ተጠያቂው ቤተ ክህነቱ ራሱ መሆኑን ዘርዝረዋል። “ኦርቶዶክስ ከመንግሥት ሳይለያይ ለመቆየቱ ዋናው ተጠያቂዎች የቤተ ክህነት ኃላፊዎች የነበሩ ሰዎች ናቸው። መንግሥታቱ በሁለተኛ ደረጃ ይጠየቃሉ። ‘ፕሮፌሰሮቹ (እነ ፕሮፌሰር መስፍንን ለማለት ይመስላል) እና ሌሎች አማኞች ያን ጊዜ ባለመናገራቸውና ባለመጻፋቸው በምን ደረጃ ይጠየቃሉ?’ የሚል ጥያቄም ሊነሣ ይገባዋል” ሲሉ ጽፈዋል።

“ዋናው ነገር ቤተ ክህነት ከመንግሥት ተጣብቆ በመቆየቱ፣ የሃይማኖት ተቋምነቱ እየወደቀ መጥቷል። አሁንስ ሃይማኖትና ፖለቲካ በሕገ መንግሥቱ ደረጃ በጽኑ እምነት ከተለየበት ወዲህ (ቤተክህነቱ) ከደረሰበት ድቀት እያንሰራራ ነው ወይስ በነበረበት ጉዳት ደረጃ ነው ያለው? የአሁኑ ፓትርያርክ ሥራ ከጀመሩ ጀምሮ ስለ ቤተ ክህነቱ የሚወራው እጅግ በጣም ዘግናኝና አሳፋሪ የአስተዳደር ጉድለት ተነሥተን ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው የሚያሰኝ ነው” ብለዋል።

በመቀጠልም “የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ብልሽት የሚባሉ ዘርፈ ብዙ ናቸው። አማኝ ሐቁን የመስማት መብት ያለው ይመስለኛል። ሌሎች ሃይማኖቶች እንደ ቤተ ክህነት ለምን ክፉ ወሬ አይወራባቸውም። በራሱ ውስጣዊ ድክመት እየተጎዳ የመታ ቢሆንም ኦርቶዶክስቤተ ክርስቲያን በታሪኩ የሀገር ፀጋ ሆኖ ነበር የቆየው፤ ፀጋነቱ በዚህ ደረጃ መውደቅ የለበትም ነው የምለው በዚህ አጋጣሚ” ሲሉ አበክረው አሳስበዋል።

ብዙ ጊዜ እንደሚነገረው “የቤተ ክህነቱ አሳዛኝ ቦታ መውደቅ ተጠያቂው መቶ በመቶ ራሱ (ቤተክህነቱ)ነው። ሕገ መንግሥት ከፖለቲካ ነጻ አድርጎት እያለ ለምን?” ሲሉ ይጠይቁና “ባይኖርስ (ከፖለቲካ ነጻ ባይሆንስ?) ለእምነታቸው ለምን አይሠሩም? ጳጳሳቱ አይረቡም ያልኩበት ምንክንያት ከዚህ አጠቃላይ መርሕ ብቻ ተነሥቼ አይደለም። አብዛኞቹ ከድሮ ጀምረው በአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር እንደሚያለቅሱ አውቃቸዋለሁኝ። ነገር ግን ትርጉም ያለው ሥራ አልሠሩም። ለዚህ ነው አይረቡም ያልኩበት ምክንያት። አሁንም ልጨምርበትና ለእምነታቸው አልረቡም።” ብለዋል።

ስለ ማ/ቅዱሳንም እግረ መንገዳቸውን ያነሡት አቶ ስብሐት “እኔ እንደሚመስለኝ፣ ባለኝ ቀጥተኛ ትዝብትም፣ ማህበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት እዳ ነው። ቀጥተኛ ትዝብቴ፣ የቤተ ክህነትን አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ (ገንቢ ሚና) ከመጫወት አፍራሽነት ይበዘበታል። አልፎ አልፎም ብልሽት እያዩ ዝምታ ይበዛል። የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክነትም እንዳለበት ይወራል። ይህ ትክክል ከሆነ እጅግ በጣም የሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የሃገር ስርዓት ማለት ህገ መንግስት የመጣስ ክህደት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ቤተ ክህነት የራሱን ድክመት እንዳያይ ማድረግ … ቤተ ክህነቱንም በጣም ይጎዳል። …  ቤተ ክህነትን ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነው የመዳከምህ ምክንያት አንበለው። ድክመቱ የራሱ የውስጡ ሁለገብ አስተዳደራዊ ብልሽት ነው። ተደጋግሞ አቤቱታ ቀርቦለት ያላጣራው ከሆነ  አሁንም ብልሽቱ የራሱ ነው።” ሲሉ አብክረው ገልጸዋል።



35 comments:

chuni said...

ወይ ጉድ...... የባሰ አታምጣ!!!!!!

Anonymous said...

ken telone enji benate Afe yemisedebu Abatoche aledelem yaferanew gin be Hulet Bilawa yeminore sew bezana kefuna degun meleyet Akaten .... Esti ..man Yawekal Mewedekiaychu ...betekenet Yehonal Aboye Sebehate

Anonymous said...

የምትችሉ ከሆነ ሙሉ ቃለ ምልልሱን ብታስነብቡን::

Ben said...

ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ ..ደቂቅ እስጢፋኖ.. መጽሓፋቸውን አሁን ለምን ጻፉት የሚል የኔም የሌሎችም ጥያቄ ነው፡፡ የአፄ ዘርኣ ያዕቆብ ጭካኔና የፖለቲካና ሃይማኖት መደባለቅን በመቃወም ነው ወይስ የነገደ ጐበዜ የፖለቲካ ስትራቴጂ በሌላ መልክ? የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ይህን ጥያቄ ለጊዜው እንተወው፡፡
ቤተክህነት በመንግስት ስር ወድቆ መቆየቱን አሁን ነው የነቁት? በዘመናችን በዘመናቸው አፄ ኃ/ስላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሆነው ሲቀጥሉ ፕሮፌሰሮቹ የት ነበሩ? አፄ ኃ/ስላሴ ቅዱስ ተብለው ታቦት ተቀርፆላቸው እንደነበረም ካህናቶች ይገለፃሉ፡፡
በዚህ ሂደት ዋናው ተጠያቂ ቤተክህነት ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ሃይማኖትና መንግስትን /ፖለቲካ/ ከፋፍሎ ያላስቀመጠ ቢሆንም፤ ቤተክህነቱ ለዚህ ጉዳይ ታጥቆ ለእምነቱ መታገልና እስከ መጨረሻው መዋደቅ ነበረበት፡፡ ከነጭራሹ ተመችቶአቸው ቤተክህነት ሲጨማለቅ ነበር እያወደሱ ለሰው እየሰገዱ የነበሩት፡፡ ለሁሉም ነገር ወሳኙ ውስጣዊ ሁኔታ ስለሆነ ኦርቶዶክስ ከመንግስት ሳይለያይ መቆየቱ ዋናው ተጠያቂዎች የቤተክህነት ሀላፊዎች የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ መንግስታቱ በሁለተኛ ደረጃ ይጠየቃሉ፡፡ ፕሮፌሰሮቹ እና ሌሎች አማኞች ያን ጊዜ ባለመናገራቸውና ባለመፃፋቸው በምን ደረጃ ይጠየቃሉ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይገባዋል፡፡
ዋናው ነገር ቤተክህነት ከመንግስት ተጣብቆ በመቆየቱ፤ የሃይማኖት ተቋምነቱ እየወደቀ መጥቷል፡፡ አሁንስ ሃይማኖትና ፖለቲካ በህገ መንግስት ደረጃ በፅኑ እምነት ከተለየበት ወዲህ ከደረሰበት ድቀት እያንሰራራ ነው ወይስ በነበረበት የጉዳት ደረጃ ነው ያለው? የአሁኑ ፓትርያርክ ስራ ከጀመሩ ጀምሮ ስለ ቤተክህነቱ የሚወራው እጅግ በጣም ዘግናኝና አሳፋሪ የአስተዳደር ጉድለት ተነስተን ስናየው ግን በነበረበት የመዳከም ደረጃ ሳይሆን ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው የሚያሰኝ ነው፡፡
የሚወራው ወሬና ቀረቡ የተባሉ አቤቱታዎች በጊዜው ግልፅና አሳማኝ በሆነ ደረጃ ለአማኙ ካልተገለፀ ህዝቡ እንደ እውነት ቢወስዳቸው ተገቢ ነው፡፡ የሚወሩት ሁሉ በግልፅ እስካልተጣሩ እኔም እንደ እውነት ነው የምወስዳቸው፡፡ ሌላ የወሬው ተለዋጭ መገኘት አለበት፡፡ የቤተክህነቱ አስተዳደር ብልሽት የሚባሉ ዘርፈ ብዙ ናቸው፡፡ አማኝ ሃቁን የመስማት መብት ያለው ይመስለኛል፡፡ ሌሎች ሃይማኖቶች ለምን እንደ ቤተክህነት ክፉ ወሬ አይወራባቸውም፡፡ በራሱ ውስጣዊ ድክመት እየተጐዳ የመጣ ቢሆንም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታሪኩ የሀገር ፀጋ ሆኖ ነበር የቆየው፣ ፀጋነቱ በዚህ ደረጃ መውደቅ የለበትም ነው የምለው በዚህ አጋጣሚ፡፡
አቶ ተመስገን የሚሰጡኝ መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ የቤተክህነቱ አሳዛኝ ቦታ መውደቅ ተጠያቂው መቶ በመቶ ራሱ ነው፡፡ ህገ መንግስት ከፖለቲካ ነፃ አድርጐት እያለ ለምን? ባይኖርስ ለእምነታቸው ለምን አይሰሩም፡፡ ጳጳሳቱ አይረቡም ያልኩበት ምክንያት ከዚህ አጠቃላይ መርህ ብቻ ተነስቼ አይደለም፡፡ አብዛኞቹ ከድሮ ጀምረው በአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር እንደሚያለቅሱ አውቃቸዋለሁኝ፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያለው ስራ አልሰሩም፡፡ ለዚህ ነው አይረቡም ያልኩበት ምክንያት፡፡ አሁንም ልጨምርበትና ለእምነታቸው አልረቡም፡፡
አቡነ መርቆርዮስን የሚመለከት ያቀረቡብኝ ቅሬታ አለ፡፡ ማብራርያ ጠይቄ አለሁኝና ይመለስልኝ፡፡ ነገር ግን አቡነ መርቆርዮስ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ..ወከባ.. ደርሶብኛል ብለው አሜሪካ ይግቡ? ለአንድ ጳጳስ ከዚህ የበለጠ ውርደት ምን አለ፡፡ ለምን ለእምነታቸው አይሰየፉም? ፓትርያርክነታቸውን ለመጠበቅ መፅናት ነበረባቸው፡፡ እስከ መጨረሻ ተፋልመው ካቃታቸው ገዳም ይገባሉ፡፡ ከአፄ ኃ/ስላሴ መኮብለል የአቡነ መርቆርዮስ ይብሳል፡፡
እኔ እንደሚመስለኝ ባለኝ ቀጥተኛ ትዝብትም ማህበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ ነው፡፡ ቀጥተኛ ትዝብቴ፣ የቤተክህነትን አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ ከመጫወት አፍራሽነት ይበዛበታል፡፡ አልፎ አልፎም ብልሽት እያዩ ዝምታ ይበዛል፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክነትም እንዳለበት ይወራል፡፡ ይህ ትክክል ከሆነ እጅግ በጣም የሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የሃገር ስርዓት ማለት ህገ መንግስት የመጣስ ክህደት ነው፡፡
ፕሮፌሰር መስፍንና አቶ ተመስገን ቤተክህነትን የሚጐዳ አመለካከትና አካሄድ ነው ያላችሁ፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው የማንኛውም ህብረተሰባዊ ጉዳይ ወሳኙ ውስጣዊ ሁኔታ ነው፡፡ የውጭ ሁኔታ ለወስጣዊ ሁኔታ፣ በበጐም ይሁን በመጥፎ ያለው ሚና ወሳኝ አይደለም፡፡
አሁን በኢትዮጵያ ከቤተክህነት ውጭ ያለው ሁኔታ በጐ ነው፡፡ በፅኑ እምነት የተመሰረተ የሃይማኖት ነፃነት የደነገገ ህገ መንግስት አለ፡፡ በዚህ ሁኔታ በማንኛውም ሃይማኖት፣ በቤተክህነትም የሚያጋጥም የራሱ የሃይማኖት ተቋሙ ነው፡፡
ቤተክህነት የራሱን ድክመት እንዳያይ ማድረግ፤ እንኳን ከተማረ ካልተማረም አይጠበቅም፡፡ ቤተክህነቱንም በጣም ይጐዳል፡፡ ድሮ አፄ ኃ/ስላሴ የኢትዮጵያ ህዝብ ከፋኝ ተራብኩ ካለ የውጭ ጠላት እጅ አለበት ነበር የሚሉት፡፡ ለፖለቲካ አላማቸው ይጠቀሙበት ነበር ማለት ነው፡፡ ለጊዜው ጠቀማቸው እንጂ በዘላቂነት አልጠቀማቸውም፡፡ አሁንም ቤተክህነትን ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነው የመዳከምህ ምክንያት አንበለው፡፡ ድክመቱ የራሱ የውስጡ ሁለገብ አስተዳደራዊ ብልሽት ነው፡፡ ተደጋግሞ አቤቱታ ቀርቦለት ያላጣራው ከሆነ አሁንም ብልሽቱ የራሱ ነው፡፡ ብልሽቱ የራሱ እያለ ለፖለቲካ አላማችሁ ሌላን ለማጥላላት አትጠቀሙበት፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን ለፖለቲካና ለሌላ አላማ መጠቀም በሃይማኖቱ ብቻ ሳይሆን በሀገርም ትልቅ በደል መፈፀም ነው፡፡
ፍትህ

አቦይ አሁን በቅርብ እንክዋን የነበራቸው ሚና ምን ነበር?
Ben

Anonymous said...

tadiya lemen mengeste ejun(hand) ayanesame papasu(abyna Pawelose)yememekute bensu ayedel enda? manes shomachew?

Zeraf said...

Even if I don't like weyane, what Aboy Sebehat says is fair enough. We know some have bribed their way to the bishop position. In the old days, our fathers were running away from that responsibility considering themselves as unworthy. These days, I hear some merkato chulules (the smarts from merkato) have been ordained as papas. Yes, papasochu ayerebum. to be fair, there may be very few who are worthy.

Our church needs significant clean up. Hoepfully, God will do it as He cannot abandon His own body in such a mess. We love our church and we love the true obedient and worthy fathers. Aba Paulos, respectfully, is the head of the mess makers.

The De.... said...

This site is mixing up things.As if weyane did not put Aba Paulos as head of the church to protect the benefits of the 'government' Abay Tsehaye says bla...bla...bla....,eh? You should have posted a commentary exposing the truth that all this mess is because of weyane,not papasat! As if they did not have hand in the church's affairs,Abboy Tsehaye,says.....amezing! When the fight between MK and Aba Paulos took heat two years ago,was not that Abay Tsehaye who took the seat of the Holy Synod and threatend MK? Dejeselam,you should have written extensively about the decisions the papasat passed and the illegal actions of Aba Paulos not to obey the synod's decisions instead of featuring this baseless,trash accusations.

YeAwarew said...

Thanks DS, Keep it coming

I think "Tegadalay" Aboy Sibhat might be right on some issues. But he remains a politician who goes around picking up any opposition and throwing them in jail, etc, etc,....
He remains a politician and that is it... I don't think he cares one bit if EOTC goes up in flames.

And , I wonder if someone wrote an article criticizing him and his office or the gov't today, would that person be left alone (alive)? .....

God bless, peace!
YeAwarew

Anonymous said...

bemeseretu yemengest eje baynorebetema ato aboy eweneten yeminagerute papast baltedebedebom,debdabewochum lefitehe bekerebu neber.musenan etagelalehu yemelenim mengist yehe hulu zerefa bebetkiristian sikahede zim balale neber.

Anonymous said...

እኝህ ሰውዬ ትክክል ብለዋል። አንድም ጳጳስ ለሃይማኖቱ ጠበቃና አርበኛ ጴጥሮሳዊ መንፈስ ያለው የለም። ሁሉም የሚያፈገፍግ፤ የሚሸሽና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ እንዲጠብቀው የሚሻ ነው። አባ ጳውሎስን ለመንቀፍ ካልሆነ በስተቀር አንዱም በመልካም ምስክርነት የተመረጠ ፤በቅድስና፤በጥሩ አስተዳደር፤ ገንዘብን በመናቅ፤በልማት ውጤታማ በመሆን፤ አልፎ ተርፎም ከይሉኝታና ከፍርሃት ተላቆ ለኦርቶዶክሳዊት እምነት እስከመጨረሻው ለመታገልና ለመሞት ቃል የገባ ጳጳስ የለም። ለራሳቸው መብትና ጥቅም ከመታገል፤ ቤተክርስቲያን እየወደቀች ለደመወዝ ጭማሪያቸው ከመሰብሰብ፤ ሐቀኛ መስሎ ለመታየት ከመሞከር ባሻገር ለቤተክርስቲያን ትንሣዔ ለመታሰር፤ ለመገረፍ እስከሞትም ቢሆን ችግሯን ለመቀበል የተዘጋጀ አንድም ጳጳስ የለም። ጉባዔያቸው ሁሉ ውጤታማ የማይሆነው የአባ ጳውሎስን የተግማማ አሰራር በመቀየር ቤተክርስቲያንን ለመታደግ ሳይሆን የሚሰነዘርባቸውን አምባ ገነንነት በማስቆም፤ በተባበረ ድምጽ የየራሳቸውን መብትና ጥቅም በያሉበት ተከላክለው ሳያስነኩ ለመቀጠል በመሆኑ የእግዚአብሔር እጅ የለበትና ውጤታማ ሆነው አያውቁም።በእውነት አንድም የአቡነ ጴጥሮስን መንፈስ የታጠቀ ጳጳስ የለም። የጴጥሮስ ሞት እኮ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን በሮማ ካቶሊክ እጅ ከመውደቅ ታድጓታል። አቦይ ስብሐት ጳጳሶቹ አይረቡም ያሉት ትክክል ነው።

Anonymous said...

Meelikam adirigen binisedeb Waga alen. Besinifinachin, behatiyatachin, betifatachin, balemetazezachin siletesedebin waga yelenim. Zare lay abatoch mesedebachihu, menekefachihu kejegininet bihon melikam. Alem endih nat. Zim bilen binalifew yisedibunal. Tadiya manin enageligil? Abatochin biniketel nuro Be Stega LAy TSega yibezalin Neber. Hulum wedeke.

Tesadabiwim, kedimo betekiiristian lay ejachewin kemekeset yalarefu sewoch and nachew. Ende Mengist Mesideb sayihon, michu akababin mefiter neber.
Igziabheer Yirdaan Esti
Sew Teffaa Ekko

with prayer said...

አቦይ ስብሐት ያሉት የፖለቲካ እርሾ ቢኖረውም የማይፋቅ ሐቅ አለበት።እውነትም ጳጳሳቱ አይረቡም፤ ለግል ጥቅም መሯሯጥ፣በቅዱስ ሲኖዶስ የሚደረገው ስብሰባ እገሌ እንዲህ አለ እያሉ ወሬ ማቀበል፣በአቡነ ጳውሎስ ብቻ መማረር፣ ቢያንስ ለሀገረ ስብከታቸው ዓላማ መቆም-ማልማት ሲኖርባቸው በልጆች ስራ መዋል፣ ነገሮችን ከማርገብ ማርገብገብ ሆኖአል ስራቸው።
ብጹዓን ጳጳሳት ሆይ! አሁንም ጊዜው ያመጣብን ስድብ ሌላ ጊዜ እስከሚሽረው እንተኛ የምትሉ ከሆናችሁ በታሪክ ተጠያቂዎች ብቻ ሳትሆኑ “ማህበረ ቅዱሳን የ ቤተ ክህነት ዕዳ” እንዳሉት ሰውየው እናንተም የሰማይና የምድር ዕዳ መሆናችሁ ልብ በሉ።
ለቤተ ክርስቲያን ልማት ሲባል ከዕንቅልፋችሁ እግዚአብሔር ያንቃችሁ!

Anonymous said...

With all do respect to Aboy Sebehat it is just like saying that no body to blame for the farmers to be poor but themselves. What if the EPRDF would had left the farmers alone,without any mechanism to stand on there foot, they would have been in the mercy of "no mercies". Maybe unintentionally, that is exactly what the EPRDF left the church to "no mercies" without facilitating any mechanism to protect herself and the nation as she has done for centuries. At the end of the day, this mess is not only destroy the church but also the Government and the country. Therefore the sooner the government get to the bottom of it the better.

Anonymous said...

አይ... እራሳቸዉ የረቡ ከሆነ ግድየለም ይበቃናል!!

Anonymous said...

"ለጎረቤቶቻችን ስድብ፥ በዙሪያችንም ላሉ መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን። በአሕዛብ ዘንድ ምሳሌ፥ በሕዝብም ዘንድ የራስ መንቀሳቀሻ አደረግኸን።" መዝሙረ ዳዊት 44:13-14
በአባቶቻችን ዘመን ማንም ተነስቶ የፈለገውን አባቶቻችን ላይ አይናገርም ነበር:: አቤቱ አምላካችን ሆይ የተበላሸውን አስተዳደር እና የኛን መንፈሳዊ ህይወት አስተካክል የአባቶቻችንን ዘመን መልስልን ሁላችንንም ለሃይማኖታችን የቆምን አድርገን::

Anonymous said...

"ለጎረቤቶቻችን ስድብ፥ በዙሪያችንም ላሉ መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን። በአሕዛብ ዘንድ ምሳሌ፥ በሕዝብም ዘንድ የራስ መንቀሳቀሻ አደረግኸን።" መዝሙረ ዳዊት 44:13-14
በአባቶቻችን ዘመን ማንም ተነስቶ የፈለገውን አባቶቻችን ላይ አይናገርም ነበር:: አቤቱ አምላካችን ሆይ የተበላሸውን አስተዳደር እና የኛን መንፈሳዊ ህይወት አስተካክል የአባቶቻችንን ዘመን መልስልን ሁላችንንም ለሃይማኖታችን የቆምን አድርገን::

Anonymous said...

This message is for Ben
When you comment, please don't copy and paste what's already been read. It really irritates me when people do that because we already read what you are posting that's why we are on the commenting board.

Zeraf said...

The De....

Yes, you are right weyane is the root cause of all evils in the country. However, did the papasat tell Abay Tsehaye that the church and the state are separate and that he cannot tell them what to do and waht not to do. Why did they allow Abay Tsehaye to lecture to them? Can the papas make political decisions for the country given the weyne constitution?

Also, did MK resist the intervention of the weyane guy? Without putting up resistence, you cannot fix the blame on weyane, which we know is evil all the time. If there was resistence, then the maximum will be some will be killed and some will be arrested. This would have been martyrdom. Why would the papasoch fear weyane if they were spiritual? John the Baptist rebuked the ruler of his time and got martyred. The coptic bishops always resist government intervention in their affairs? Why are the ethio bishops different? The answer is the majority of the bishops are yemayerebu nachew!!!

The first step is to remove the weyane pope and revoke the ordination of some of the bishops who may be found to be clearly unworthy. The second step is to change the patriarch election procedure. I suggest that the electorate should elect three capapble candidates from among many and allow the Holy Spirit to select whomever He cooses to lead the church like how the Apostles selected the replacement for Jude. After selecting the three candidates, the church should declare 7 days of fasting and prayer that every faithful should do asking God to give them the right father to lead the church. Finally, a child not older than 10 years should draw a lot in the name of the Holy Trinity. Whoever is picked has been anointed by the Holy Spirit.

Then , the new adminstration should listen to all grievances, admin issues, and doctrinal conflicts and resolve them for good. If we allow the Holy Spirit to choose the right person for the church, we can have peace and a strong chruch. Weyane should not be allowed to meddle in the affairs of the church, except executing its standard government functions.

Anonymous said...

ለአቶ ስብሐት መልስ ከአባቶች እንጠብቃለን። በአደባባይ እንዲህ አንድ ግለሰብ አይረቡም ብሎ ሲሰድባቸው እነ አቡነ ጳውሎስ ስማችን በከንቱ ጠፋ ብለው መልስ ካልሰጡ እውነትም አይረቡም ማለት ነው።
የአቶ ስብሐት አስቂኝ ነገር ግን የኦርቶዶክስ ምዕመናን ኢህአዴግአዊ አመለካከት እንዲኖረን ያስተላለፉልን መልዕክት ነው። በመሰረቱ እምነትና ፓለቲካ የተለያዩ ናቸው። ሐይማኖቷ ምዕመናኑ ምን አይነት የፖለቲካ አመለካከት መያዝ እንዳለባቸው አታስገድድም! የእያንዳንዱ ምዕመን መብት ስለሆነ። አባል፤ደጋፊ፤ተቃዋሚ እንደፍላጎቱ መሆን ይችላል። ነጻነቱም እዚህ ላይ ነው። አንድ ጥያቄ ልጠይቀዎ ‘የኢህዴግ አባላት የሚፈልጉትን እምነት መከተል መብታቸው አይደለም ወይ?‘ የድርጅቱ አባላት የተለያዬ እምነት ያላቸው እንዳንዶች ደግሞ ጭራሽ የማያምኑም ናቸው። ድርጅቱ ይህን መብት እስከጠበቀላቸው ድረስ ኦርቶዶክስ ሐይማኖትም ይህን የመጠበቅ መብት አላት። እናንተ ግን ይህን መብቷን በመጋፋት ነው ካናቷ ላይ የእናንተን አመለካከት ተቀባይ ሰው ያስቀመጣችሁብን። ለዚህ ስራችሁ የማይሳነው አማላክ ጊዜውን ጠብቆ የስራችሁን ዋጋ እንደሚሰጣች እርግጠኛ ነኝ። ለማንኛውም ‘‘ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት በሐላፊነት እኛ ያስቀመጥናቸው ጳጳሳት አይረቡም‘‘ ቢሉን ንሮ ምንኛ ባማረ። ነገር ግን ስራችሁን ሰርታችሁ አሁን ደግሞ ‘‘የአዛኝ ቅቤ አንጓች----‘‘ እንዲሉ ለምዕመኑ አሳቢ ለቤተክርስቲያኗ ደግሞ ተዎርቋሪ መስለው ይህን ተራ ወሬ ይዘው ብቅ አሉ። ይህ ማንን ይጠቅም ይሆን? ውጤቱን አብረን የምናዬው ነው። ለማንኛውም ልቦና ይስጣችሁ።

gondarew said...

EVEN IF INSULTING IS FORBIDON, I WILL ACCEPT THE COMMENTS,BECAUSE WE ARE THE WITNESS IN OUR RELIGION WHAT IS GOING ON.I BEG ALL OUR MEMBERS OF CHURCH TO STAND WITH THE SIDE OF GOD AND FIGHT FOR.DON'T FORGET THE POWER OF GOD.PLEASE READ MATTHEW CHAPTER 6 NUMBER 24 WE CANN'T DO THAT.THE MEMBER OF ETHIOPIAN ORTODOX CHURCH MUST READ AND KNOW WHAT IS THE LAW AND DOCTRIN OF THE CHURCH SAY,AND USE YOUR OWN BRAIN DON'T FOLLOW BY SOMEBODY WHAT EVER HE IS BECAUSE READ MATTHEW CHAPTER 7 NUMBER 15-23.INGENERAL ETHIOPIAN IN SIDE AND OUT SIDE PLEASE PLEASE PLEASE PROTECT OUR CHURCH FOR THE SECK OF OURS,DON'T THINK WE ARE DOING THIS FOR GOD.

Ben said...

@This message is for Ben
are you sure you read the whole thing?
I don't know for you but or me there is a difference in format as well as content. For instance,
አቡነ መርቆርዮስን የሚመለከት ያቀረቡብኝ ቅሬታ አለ፡፡ ማብራርያ ጠይቄ አለሁኝና ይመለስልኝ፡፡ ነገር ግን አቡነ መርቆርዮስ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ..ወከባ.. ደርሶብኛል ብለው አሜሪካ ይግቡ? ለአንድ ጳጳስ ከዚህ የበለጠ ውርደት ምን አለ፡፡ ለምን ለእምነታቸው አይሰየፉም? ፓትርያርክነታቸውን ለመጠበቅ መፅናት ነበረባቸው፡፡ እስከ መጨረሻ ተፋልመው ካቃታቸው ገዳም ይገባሉ፡፡ ከአፄ ኃ/ስላሴ መኮብለል የአቡነ መርቆርዮስ ይብሳል፡፡
did you read it before? If you did I'd say sorry , if not I'd fell sorry for you.
Ben

Anonymous said...

(ከፖለቲካ ነጻ ባይሆንስ?) ለእምነታቸው ለምን አይሠሩም? ጳጳሳቱ አይረቡም ያልኩበት ምንክንያት ከዚህ አጠቃላይ መርሕ ብቻ ተነሥቼ አይደለም። አብዛኞቹ ከድሮ ጀምረው በአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር እንደሚያለቅሱ አውቃቸዋለሁኝ። ነገር ግን ትርጉም ያለው ሥራ አልሠሩም። ለዚህ ነው አይረቡም ያልኩበት ምክንያት። አሁንም ልጨምርበትና ለእምነታቸው አልረቡም።” 100000000% agreed in his view.
Even if i don't agree in his political thinking but i agree in everything he said in criticism of our church. Some of you say how dare he say like that? you have to see him beyond his politics. And his view of mk is some of true and some of wrong,
1- Mk knows most of the wrong things that the church fathers do but act like they didn't see,he is very right.
2- when it comes about politics he is very wrong.he is just scared of Mk,the opposition accuse MK as the government,the government accuse as opposition
3- MK did a lot for the church not little

ten said...

ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ስሟን ጅግራ ናት ይሏታል አሉ። ይህ ሰው ለቤተክርስትያን ተቆርቁሮ አይመስለኝም። ከቅንነት ከሆነ አስተያየቱ መልካም ነገሮች አሉት። ነገር ግን ከጳጳሱ ጋር ተባብሮ አይረቡም በሚል ሰበብ ቀናኢና ትክክለኛ ጳጳሳትን በመግፋቱ ረገድ ጣልቃ እንዳይገባ እሰጋለሁ።

Anonymous said...

Before blaming any one, first the government has to do its part. At least, the church fathers (the Synod) they started their best to clean up the mess by making a difficult decisions. Now it is time for the government to do a difficult decisions as well, based on nothing but the truth.

gash975 said...

abune paulos bete kerestianachinen bemarkes lefetsemut defret hulu ketetegna teteyakiew ye aboy sebehat woyane new.
manew lezih shumet yabekachew? manew yezer medlo astedader yastemarachew? papasatun woyane betachew deres hedo aldebedebem woy? yebete kehenet sebseban beglts yemeraws abay tsehaye alnberem? lelam lelam gef be abotoch ena bete kehnet lay sifetsem fit awrari yeneberut aboy sebahat zare denget tegelbetew papasochu ayrebum yelunal.
yeh asteyayet yegeleseb endayemeslen nege bezu papasatena amagnoch metaserachew aykerem bezia lay bete kehenet yetekawamiwoch medebekia hunalech eyaluen new.
ebakachehu yemnet botachenen enkua tewelen hulun neger yepoleticegna ena ye aderbay terekem ataderguben !

T/selase ከስዊድን said...

አዬ አቦይ ስብሐት

እንዴት ነው ነገሩ፣ ተረሳ እንዴ ጳጳሳቱን (እነ አቡነ መልከጼዴቅን) ማዋከቡና የማ/ቅዱሳን አመራሮችን አስራለሁ ብሎ ማስፈራራት ምን ሊባል ነው፡፡

Anonymous said...

እንደነዚህ ካሉ ሰዎች (ዛሬም ሆነ ነገ) ከዚህ በላይ ቃል/ አስተያየት ባንጥብቅ! ‘እንዲህ _ _አድርጉ/ ይሁን/ እናድርግ/ እንስራ...’ የሚል ቃል-ማ ለባለ ጉዳዮቹ! ለእኛ !!

ጆሮ ያለው ይስማ! ፈረስ ያደረሳል እንጂ ......፤

አረጋዊው አቶ ስብሐት ነጋ ስለ ቤተ ክህነት ብሎም ስለ ቤ/ክናችን የሰጡት ቀና አስተያየት በጥቅሉ ይበል የሚያሰኝ ነው።

ኤልያስ/ ዳላስ-ቴክሳስ

Anonymous said...

response for Ben my brother you do know about why patriarch mirkorios went to America.

123... said...

መንግስት በ ቤተክህነት ውስጥ ጣልቃ አልገባም? አባይ ፀሐዬ መስከረም አስራ ሁለት 2002 ዓም ቤተክህነት ገብተው ማኅበረ ቅዱሳንን ከ ጧቱ ሁለት ሰዓት አስከ ምሽቱ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ ጠረቤዛ አየደበደቡ የዛቱት ምን ሊባል ነው? አቦይ አድሜ ሲገፋ ትንሽ አየዘነጉ ይሆናል አንጂ ያንቀን አባይ ፀአዬ ሻይ ሊጠጡ አደለም የመጡት። ሰውን ባናፍር አግዝያብሔርን አንፍራ።

Anonymous said...

አቦይ ስብሐት ነጋ, ጳጳሳቱን አይረቡም ለማለት ድፍረት የሰጦት ለመሆኑ ማነው? ጳጳሳቱም ሆኑ ህዝበ ክርስቲያኑ ለቤተክርስቲያን ውድቀት ምክንያት ሊሆኑ አይገባም:: ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሁገሪቱ ወደኋላ መሄድ ዋናው ምክንያት መንግስት ብቻ ነው:: መንግስት ከአባ ጳውሎስ ጀርባ ቢቀመጥም ብጹዓን አበው ግን ለቤተክርስቲያን የሚበጃትን ከመወሰን ወደኋላ ያሉበት ጊዜ የለም:: ጳጳሳቱ የሚወስኑትን ውሳኔ ግን መንግስት ለአባ ጳውሎስ ከለላ በመስጠት እንዳይፈጸሙ ያረጋል:: ጳጳሳቱ እንግዲህ ለሃገርና ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ውሳኔ ከመወሰንና 'እቀብ ህዝባ ወሰራዊታ ለሃገሪትነ ኢትዮጵያ...የኢትዮጵያን ህዝብና ሰራዊት/ወታደር ጠብቅ' ብለው ወደ ፈጣሪ ከመለመን ባለፈ ጠመንጃ ይዘው ከመንግስት ጋ አይዋጉም::
አቦይ ስብሐት ነጋ, ንግግርዎ ባብዛኛው እውነት መሆኑን አልክድም ነገር ግን ይህ ንግግርዎ በእውነት ለቤተክርስቲያን ከማሰብ የመነጨ ከሆነ እስኪ ብጹዓን አበው በቅዱስ ሲኖዶስ የወሰኗቸውንና ወደፊትም የሚወስኗቸውን በማስፈጸም መንግስት ይተባበራቸው:: ቢያንስ ለአባ ጳውሎስ ወንጀልን ሲፈጽሙ መንግስት ከጎናቸው አይቁም:: አንድ ምሳሌ ልንገሮት ጳጳሳቱ ከቤተ ክርስቲያን ስርዓት ውጭ የተሰራውን ያባ ጳውሎስን ሐውልት እንዲፈርስ ወስነዋል: ነገር ግን እስካሁን አልፈረሰም:: እስኪ እውነት እንነጋገር አሁን ያን ሃውልት ከጓደኞቼ ጋር ሄደን ብናፈርስ መንግስት የእድሜ ልክ እስራት አይፈርድብንም? አረ እንዲያውም እዛው ካልገደሉንም ጥሩ ነው:: ሴትዮዋ (ወ/ሮ እጅጋየሁ) ወደ ቤተ ክህነት ግቢ እንዳትገባና ቤተ ክህነቱን እንዳታውክ አበው ወስነዋል ግን እንዲያውም የበለጠ ተመቻችቶላታል:: አባ ጳውሎስ የመንግስትን ወታደር ከጠቅላይ ሚንስትራችን እኩል የማዘዝ ስልጣን ስላላቸው ማንም አይደፍራቸውም:: እረ ሌሎች ብዙ መጥቅስ ይቻላል::ሁሉም ያልፋል: ብለን ዝም አልን እንጂ አቦይ ምን አለበት ምንም እንደማናውቅ ባያረጉን:: የቤተክህነትንም ጉዳይ ሆነ ያገራችንን ጉዳይ ምናልባትም ከርሶ በተሻል እናውቃለን ብለን እናስባለን::

ስለዚህ የኔ ምክር ለርስዎ ሊሆን የሚችለው አባቶቻችን ስራቸውን በትክክል እየሰሩ ነው:: ለቤተክርስቲያን የሚበጃትን ሁሉ ባግባቡ እየወሰኑ ነው:: ለሃገራችንም ለህዝቡም የሚገባውን ጸሎት ከማድረግ የተቆጠቡበት ወቅት የለም:: ይልቅስ ስራቸውን ባግባቡ የማይሰሩትን እንውቀስ:: መንግስት ስራውን ባግባቡ እየሰራ አይደለም:: ሐገሪቱ ላይ ማንኛውም ነገር በስርዓት እንዲጓዝ የማድረግ ግዴታ አለበት:: ስርዓት ማስጠበቅ ማለት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ማለት አይደለም:: መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ሲባል በነሱ ጉዳይ ላይ አይወስንም ነው እንጂ ሰው በሃይማኖት ምክንያት ቢደባደብ ዝም ማለት አለበት አይደለም: በሃይማኖት ተከልሎ ወንጀል ሲፈጽም ዝም ብሎ ይመለከታል አይደለም:: ማንኛምውም ወንጀል (irrespective of religion, age, sex, race....) ሃገሪቱ ላይ ሲፈጸም መንግስት ይመለከተዋል:: ስርዓት የማስፈጸም ሃላፊነትም አለበት:: ሌላው ደግሞ መንግስት ላባ ጳውሎስ እንደ ማንኛውም ሰው ወንጀል እንዳይፈጸምባቸው ከለላ ሊሰጣቸው ይገባል እንጂ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ወንጀል ሲፈጽሙ ለወንጀላቸው ከለላ መስጠት የለበትም:: መንግስት በዚያ ካልተባበረ ግድ የለም አባቶቻችን ለቤተክርስቲያንና ለሃገር የሚበጀውን ይወስኑ እኛ ህዝበ ክርስቲያኑ እንፈጽማለን እናስፈጽማለን:: የርስዎ መንግስት በወንጀል ካባ ጳውሎስ ጋር መተባበሩን እንዲያቆም ይምከሩልን:: ኤርስዎ ይህን ካረጉልን መንግስትም በወንጀል የማይተባበር መሆኑን በማስ ሚዲያ ይንገረን አሁኑኑ ሄደን ያባቶችን ውሳኔ እናስፈጽማለን:: እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሀገሪቱም ሆነ ቤትክርስቲያን ወደ ውድቀት ሳይሆን ወደ ልማት መንገድ ይጓዛሉ::

Mekonen

Ben said...

@response for Ben my brother you do know about why patriarch mirkorios went to America.

July 04, 2011

this is what Sebhat Nega said about his/his party involvment during that period not mine. You could accept or reject his ideas. However, it has its own truth though.
Ben

Anonymous said...

Oh! aboy Sibhat, selam newot?

I really appreciative your idea that create a fertile ground for you mission. I think everything is changed, everyone knows what and how politics of EPRDF going on?

Let me the truth, every one knows abba Patriotic is a representative of EPRDF. What ever logic and talk you can bring, we don not believe that EPRDF is not with the Patriotic. You are insisting the Bishops to remove the head. They know what the government did, and will do.

I really appreciate your stand for your mission. You See the Bishops do not have any trust on the government so that they are smarter than you, they are contemplating and waiting the right the time. This is wisdom.

Again let me the truth. If they try to remove the Head, you will demolish the church, like you manipulate the Islamic Council. Then you know how to set up the church administration in the next seasons.

Anonymous said...

አቦይ ምን ነካዎት? ፓርቲዎን ወክለዉ የሐይማኖታችንን አባቶች ለምን ይሰድቡብናል? ለነገሩ ኢሕአዴግ እኮ የአርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን መነቅነቅ የጀመረዉ ከ1983 ጀምሮ ነዉ!! በአርባ ጉጉ የታረዱት ክርስቲያኖች፣ በታምራት ላይኔ እወጃ፤ በ1997 ዓ/ም አቶ ተፈራ ዋልዋ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን "የነፍጠኞች ዋሻ" ብለዉ በጅምላ የሐይማኖታችንን ልዕልና ማንኮታኮታቸዉ፣ አሁን ደግሞ እርስዎ አባቶቻችንን በጅምላ ይሰድቡብናል? ለመሆኑ ግን ለ30 ዓመታት ሲገድልና ሲያስገድል የኖረ ሰዉ ስለሐይማኖት ለዚያዉም ስለክርስትናና ስለሞራላዊ እሴቶች እንዴት ሊተነትን ይችላል? የፖለቲካዊ ስሌትና የሐይማኖታዊ ሚዛን እንደ ነጭና ጥቁር የተቃረኑ ርዕዮተ አለሞች መሆናቸዉ ጠፍቶብዎት ይሆን? አንዱ ለሌላዉ ከንቱነት ነዉና!! ግን እርስዎ አሁን በሽምግልናዎም እስካሁን የሰሩት ስራ ከንቱ መሆኑን መመዘን አቃተዎ!! ለዚያዉም የቤተ ክርስቲንን አካሄድ በፓለቲካዊ ቀንበር ተጭናችሁ፣ ምዕመኖቿን በማሳቀቅ እንዳታድግ ራሷን እንዳትችል ስትከላከሉ 20 አመት ሙሉ ቀፍድዳችሁ እየተጫወታችሁብን፣ ግፈኞች!!! አምላክ ልቡናችሁን ይመልሰዉ!!!

Anonymous said...

ye orthodox fathers yemewaredut brasachaw kelet new . abouye sebeht said good idea about them. They are not real church fathers , most of them are racist, jealous, lack of purity, lack of confidence, in general to be honest 90% of them are not religious fathers they built villahouse, deposit alot of money, corrupted.
so abouye said that we hide and hold in secret.
abouye even if you are politician ,you touch the truth God bless you abouye

Hassen W. Tewodros said...
This comment has been removed by the author.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)