July 31, 2011

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በፖሮቴስታንታዊ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ዙሪያ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ላቀ ምልልስ

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በፖሮቴስታንታዊ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ዙሪያ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ላቀ ምልልስ::

ቃለ ምልልሱን በደንብ ለማንበብ  ይህንን ይጫኑ
“አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የዘገበውን ዜና ቀጥሎ ያንብቡ

የእርስ በርስ ቀውስ - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
 • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር ከፓትርያሪኩ ጋራ ሳይወያዩ ቀሩ፤ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ደርሷል
(አዲስ አድማስ፣ ሐምሌ 24 ቀን 2003 ዓ.ም፤ ጁን 30/2011፤ ቅጽ 10 ቁጥር 602/ READ IN PDF)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የ131 አድባራት እና ገዳማት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር ከፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ጋራ በትላንትናው ዕለት እንደሚያካሂዱ የተጠበቀው ውይይት ሳያሳካ ቀርቷል፡፡

July 29, 2011

የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴን አስመልክቶ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራር ጋር ውይይት አደረጉ

(EOTCMK):- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ከማኅበረ ቅድሳን ሥራ አመራርና አስፈጻሚ ጉባኤያት ተወካዮች ጋር ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ስለ ማኅበሩ አገልግሎትና በተለይም የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን የማኅበሩ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

July 28, 2011

የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች ታሪካዊ መግለጫ አወጡ፤ ተሐድሶን ተቃወሙ


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2011/ READ IN PDF):-  የሰ/አሜሪካ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ፕሮቴስታንታዊ የተሐድሶ ኑፋቄ በመቃወም ታሪካዊ መግለጫ አወጡ በአዲስ አበባ የሚገኙ ወንድሞቻቸው እህቶቻቸው የሰንበት ት/ቤቶች አባላት ያሳለፉትን ውሳኔ ደገፉ። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ሰፍሯል።

“ማኅበረ ቅዱሳን የውይይት እና የምክክር ባሕሉን ይቀጥል” (ደጀ ሰላም)


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2011/ READ IN PDF):-  የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን ጽሑፍ ካስነበበንበት ወቅት ጀምሮ ብዙ ደጀ ሰላማውያን እጅግ በጣም ገንቢ ሐሳቦችን፣ ምክሮችን እና ቁም ነገሮችን ለግሳችሁናል። ብዙዎቻችሁ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት “የዓይናችን ማረፊያ” ያላችሁትን የማኅበረ ቅዱሳንን “ገመና” እና መለያየቱን በአደባባይ ማቅረባችን ትልቅ ሐዘን እንደፈጠረባችሁ ገልጻችሁልናል። አንዳንዶቻችሁም በሥራችን መከፋታችሁንከፍተኛ ቁጭት እና ሐዘን እንደፈጠረባችሁ ደጀ ሰላም ተረድታለች

July 27, 2011

ፍ/ቤቱ አባ ሰረቀ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ወሰነ


 • ሦስተኛው የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጫና እየተደረገባቸው ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 27/2011, READ IN PDF):- በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በማኅበረ ቅዱሳን የቀረበባቸውን የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወሰነ፤ ተከሳሹ የመምሪያው ዋና ሓላፊም አሉኝ ያሏቸውን 12 የመከላከያ ምስክሮች ለሐምሌ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ላይ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

July 22, 2011

"ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን" (By Mesfin Negash)(አቦይ) ስብሐት ነጋ
"በምርጫ 97 ማግስት ድንጋጤ ያርበተበው ፓርቲ/መንግሥት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሰርና በመፍታት ስራውን አላጠናቀቀም ነበር። ይህን ተከትሎ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ “ለምን ተሸነፍን? የጦስ ዶሮዎቹን አድኑ” የሚል አውጫጪኝ ተካሂዶ ነበር። ይህ በየክልኩ የደኅንነት አካሎችና በፓርቲው መዋቅር (አንድም ሁለትም ናቸው) የተካሄደው “ጥናት” አስደናቂ ውጤቶችን አስገኝቷል። ከእነዚህ ውጤቶች አንዱ “በአማራ እና በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢሕአዴግ ለደረሰበት ሽንፈት፣ ተቃዋሚዎች ላገኙት ድጋፍ ሚና ከነበራቸው አካሎች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው” የሚል ነበር።" (ከጽሑፉ የተወሰደ)
 (To Read in PDF, Click HERE)
“ዝነኛው” አቦይ ስብሐት የዛሬ ሦስት ሳምንት ገደማ በ“ፍትሕ” ጋዜጣ ለወጣባቸው ትችት የሰጡት መልስ አስተያየት የሚጋብዝ ነው።  የ“ፍትሑ”  አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም አቦይ ስብሐት ሕዝብ በተሰበሰበበት የተናገሩትን ለንባብ ማቅረቡ የሚጠቅም ነው፤ “ሰውየው መዘባረቅ ልማዳቸው ነው” ብሎ አለመተዉን ለማድነቅ ነው። (ተጨማሪ ምልልሶችን በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል።)

July 21, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን በለንደን ታላቅ ዐውደ ርእይ አዘጋጀ

(ጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ፤ በተለይ ለደጀ ሰላም፤ ጁላይ 21/2011)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቀደም ሲል ለአገሪቱ ያደረገቻቸው  ታሪካዊ አስተዋጽዎችን፣ በአሁኑም ወቅት እያደረገች  ያለውን ልማታዊ እና ሃይማኖታዊ  እንቅስቃሴዎችን  እንዲሁም ወደፊት ምን ለማድረግ እንደታቀደ  የሚያመላክት ታላቅ ዐውደ ርእይ  በለንደን   ከተማ ውስጥ  ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ታሪካዊ መግለጫ አወጡ፤ ተሐድሶን እና አባ ሰረቀን ተቃወሙ


 • ከአዲስ አበባ ውጪ በየአህጉረ ስብከቱ ያሉትም ይደግፏቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፤
 • በሰሜን አሜሪካ ያለው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አጋርነቱን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 20/2011/ READ IN PDF):-  በፕሮቴስታንታዊ - ተሐድሶ - ኑፋቄ ላይ ውስጥ ውስጡን እየተቀጣጠለ የሚገኘው የምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ቁጣ ፈንድቶ አስከፊ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አስፈላጊው የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ጠየቁ። ፌዴራል ፖሊስ በሰንበት ት/ቤቶቹ የቀረበው አቤቱታ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠው የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊን አሳስቧል ተብሏል:: “ለሰንበት ት/ቤቶች የሚጠቅም አንዳችም ተጠቃሽ ሥራ አላበረከቱም” የተባሉት ዋና ሓላፊው አባ ሰረቀ ስለ ተሐድሶ መናፍቃን የሰጡት መግለጫ ሰንበት ት/ቤቶችን አይወክልም፤ መግለጫው በመምሪያ ሓላፊነታቸው እንዳይታመኑ የሚያደርግና በብዙኀን መገናኛ ተገቢው ማስተካከያ ሊሰጥበት የሚገባ እንደሆነ ተመልክቷል።

July 19, 2011

አቡነ ፋኑኤል በአትላንታ ክህነት ሰጡ፤ የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አላስፈቀዱም


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 19/2011/ TO READ IN PDF):-  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ፋኑኤል አትላንታ ጆርጂያ በሚገኘውና ራሱን ገለልተኛ ብሎ በሚጠራው በአትላንታ መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ወኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ተገው ክህነት መስጠታቸውን የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ቀሲስ ኤፍሬም ከበደ ጁላይ 10 ቀን 2011 በአትላንታ አካባቢ በሚተላለፈው AM 1100 የሬድዮ ጣቢያቸው በሰጡት የደስታ መግለጫ አስታውቀዋል።

July 17, 2011

እነበጋሻው “የምእመናንን ተቃውሞ የሚያበርድ” ያሉትን አዲስ ቪሲዲ እያዘጋጁ ነው


 • የቅጥር ማመልከቻቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሠራተኞች አስቆጥቷል
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2011/ TO READ IN PDF)፦ በጋሻው ደሳለኝን እና አጋሮቹ ራሳቸውን “ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ” መሆናቸውን ለማሳየት ያዘጋጁት ነው የተባለ  ቪሲዲ በቅርቡ ለመልቀቅ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ቪሲዲው እነበጋሻው እንባቸውን እንደ ማየ ክረምቱ ሲያንዠቀዥቁ የሚያሳዩበት እንደሆነም ተነግሮለታል። በካሜራ ፊት በደቦ የተደረገ የልቅሶ ትዕይንት የሆነው የዚህ ቪሲዲ ተዋንያን በጋሻው ደሳለኝ፣ ትዝታው ሳሙኤል፣ ያሬድ አደመ፣ ዕዝራ ኀይለ ሚካኤልና ምርትነሽ ጥላሁን ሲሆኑ ልቅሶውን በመሪ ተዋናይነት በመምራት የሚያላቅሳቸው /አስለቃሹ/ ደግሞ በሪሁን ወንደወሰን ነው ተብሏል፡፡

July 14, 2011

እነሆ 19 ዓመት ሆነ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 12/2011/ READ IN PDF)፦ አምስተኛው ፓትርያርክ በመንበረ ፕትርክና ከተቀመጡ እነሆ ዛሬ 19 ዓመት ሆናቸው። እርሳቸው ወደዚህ ሥልጣን ሲመጡ ቤተ ክህነቱ የተለያዩ ችግሮች ነበሩበት። ከ19 ዓመታት በኋላ ስንመለከተው እነዚህ ችግሮች አድገውና ሰፍተው፣ ዓይነታቸውም ተበራክቶ፣ ይልቁንም ይህንን ችግር ይቀርፋሉ የተባሉ ርዕሰ ቤተ ክርስቲያን የችግሩ ፊት-አውራሪ ሆነዋል። 19 ዓመት የአንድ ወጣት ዕድሜ ነው። ለተሳሳተ ሰውም ለመመለስ 19 ዓመት ረዥም ጊዜ ነበር። ከጥፋት ከመመለስ ይልቅ በበደል ላይ በደል መጨመርን ተካኑበት እንጂ። ከዚህ በታች ያለውና (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2009) ያወጣችው ጽሑፍ ምን ማለታችን እንደሆነ የበለጠ ይገልጸው ይሆናል።

July 13, 2011

አባ ሰረቀ ፍ/ቤት ቀረቡ


 • ፍ/ቤቱ አባ ሰረቀ የብር 4000 ዋስትና አስይዘው ሰኞ ሐምሌ 11 ቀን እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል::
 • ኢ.ቢኤስ ቴሌቪዥን የአዲስ አበባ ቢሮ እነበጋሻው ደሳለኝ ለስድስት ተከታታይ ሳምንታት ባስተላለፉት ፕሮግራማቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በስም ጠርተው የተናገሩት ውንጀላ እንዳይደገም ማሳሰቢያ ሰጠ፤ ትዝታው ሳሙኤል “የተሐድሶ ምንጩና መፍለቂያው ማኅበረ ቅዱሳን ነው” ሲል የተናገረው ስላቅ ከሕግ ዐይን አኳያ እየተጤነ ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 12/2011; TO READ IN PDF)፦ በቅርቡ የሀገር ውስጥና የውጭ ብዙኀን መገናኛዎችን በጽ/ቤታቸው ጠርተው ባዘጋጁት ጋዜጣዊ ጉባኤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ በሰጡት መግለጫ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ሐምሌ 4 ቀን 2003 ዓ.ም ረፋድ ላይ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ፡፡

July 11, 2011

(ታሪክ በዚህ ሳምንት) - “መስለህ አስተምር በሚለው የመናፍቃን የማስተማር ዘይቤ” የሃይማኖት ሕጸጽ ባሰራጩ ሰባክያን ላይ ቅ/ሲኖዶስ የወሰደው ርምጃ ሲታወስ


 • “ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ የሚታየውን ችግር የማስወገድ አቅሙን እያጎለበተ በመምጣቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመናፍቃን ወራሪ ነጻ በማውጣት የሚካሄደው የሥራ እንቅስቃሴ በአጀንዳ ከቀረቡለት የወቅቱ ጥያቄ አንዱና ዋነኛው ሆኖ ተመዝግቧል(የቅዱስ ሲኖዶስ የ1990 ዓ.ም ውሳኔ መግቢያ)
 • ሕገ ወጥ ሰባክያኑ (አሰግድ ሣህሉ፣ በጋሻው ደሳለኝ) በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች ውስጥ ለመቀጠር ማመልከታቸው እየተነገረ ነው፤
 (ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 11/2011/ TO READ IN PDF CLICK HERE)፦ 13 ዓመት ወደ ኋላ፤ ወርኀ ግንቦት 1990 ዓ.ም - በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ የከተተው የአዲስ አበባ ከተማ ምእመን ዐይኖች በአዳራሹ ውስጥና ዙሪያ በተደረደሩ ከ20 ያላነሱ ቴሌቪዥኖች ተከብቧል፡፡ ምእመናኑ የጽርሐ ጽዮን አንድነት ማኅበር ቤተሰብ በሆነው እንደ መ/ር ታዬ አብርሃም ባሉ ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን አስተባባሪነት ቀደም ሲል በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ሰባክያነ ወንጌል በወሰኑት መሠረት በተመሳሳይ ቀንና በአንድ ላይ በዐውደ ምሕረትና በተለያዩ መንገዶች ባደረጉት ቅስቀሳ ጥሪ የተላለፈላቸው ነበሩ፡፡

July 6, 2011

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ሕገ ወጥ ሰባክያንን አገደ

 •  የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአጥቢያውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በተመለከተ ‹‹በበላይነት መምራትና ማስተዳደር አልቻለም›› ባለው የደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስጠንቅቆ ነበር
 • ሰንበት ት/ቤቱ በሕገ ወጥ ሰባክያኑና የእነርሱ ተባባሪ በሆኑት የአጥቢያው ስ/ወንጌል ሓላፊዎች የሚመራው የስብከተ ወንጌል አካሄድ ‹‹ወዳልተፈለገ ግጭት›› እንደሚያደርስ በመጥቀስ ለሀ/ስብከቱ አቤቱታ አቅርቦ ነበር
 • በሙሰኛነቱና ባለበት የሥነ ምግባር ችግር ተቃውሞ የተነሣበት ናሁ ሠናይ ነጋ የተባለው የአጥቢያው ስብከተወንጌል ሓላፊ የእገዳውን ምክንያትና ፋይዳ ለማስተባበል እየተፍጨረጨረ ነው
 • ሥላሴ አትበሉ ብያለሁ፤ ሥላሴን አትመኑ ግን አላልሁም” (በጋሻው ደሳለኝ- በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን)
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 6/2011, Read in PDF.)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጽ/ቤት በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና በሀገረ ስብከት ያልተፈቀደላቸው ሰባክያን ከሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በአጥቢያው እንዳይሰብኩ መታገዳቸውን አስታወቀ፤ ጽ/ቤቱ ይህን ያስታወቀው የእገዳውን ውሳኔ ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደርጉ የደብሩ ስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች ለሆኑት መ/ር ናሁ ሠናይ ነጋ እና መ/ር ታሪኩ አበራ በቁጥር 6020/03 በቀን 28/10/03 በጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡

July 5, 2011

የማ/ቅዱሳን ዋና ፀሐፊ መምህር ሙሉጌታ ኃ/ማርያም፤ ከ“ዕንቁ” መጽሔት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

 Dear all,
Most of our readers have complained that the interview was not readable. Here (click) we tried to get a better copy, with better clarity. We thank you for your comments and suggestions.
DS Team
 
የማ/ቅዱሳን ዋና ፀሐፊ መምህር ሙሉጌታ ኃ/ማርያም፤  ከ“ዕንቁ” መጽሔት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ: (PDF)::

July 3, 2011

“ጳጳሶቹ አይረቡም … (ቤተ ክህነቱ) ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው” (አቦይ ስብሐት ነጋ)


(ደጀ ሰላም፤ ላይ 1/2011, To Read in PDF, click HERE)፦ የሕወሐት/ኢሕአዴግ የፖለቲካ መሐንዲስ መሆናቸው የሚነገርላቸው አረጋዊው አቶ ስብሐት ነጋ ስለ ቤተ ክህነት በሰጡት ግልጽ አስተያየት ላይ “ጳጳሶቹ አይረቡም”፣ ቤተ ክህነቱም “ወደሞት አፋፍ እየሄደ ነው” ሲሉ ተናገሩ። ዛሬ አርብ ሰኔ 24/2003 ዓ.ም በወጣው “ፍትሕ” ጋዜጣ ላይ ረዥም ጽሑፍ ያስነበቡት አቶ ስብሐት ነጋ (በተለምዶ አቦይ ስብሐት ይባላሉ) ስለ ቤተ ክህነቱ በከፋ አስተዳደራዊ ብልሽት ውስጥ መውደቅ ምክንያቱ “ራሱ ቤተ ክህነቱ” እንጂ መንግሥት አለመሆኑን አብራርተዋል። 

July 2, 2011

ሁለት ሊነበቡ የሚገባቸው ቃለ ምልልሶች

Dear all, We know the scanned pages are blurred, but that is all we have. We apologize for the inconvenience. በአዲስ አበባ ከሚታተሙት መጽሔቶች መካከል ሁለቱ ማለትም "ዕንቁ" እና "አርሒቡ" ደጋግመን ስንዘግባቸው በቆየናቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የማ/ቅዱሳን ዋና ፀሐፊ የሆኑትን መምህር ሙሉጌታ ኃ/ማርያምን እና ዘማሪ እስጢፋኖስን ቃለ መጠይቅ አድርገውላቸዋል።
 • መምህር ሙሉጌታ ከዕንቁ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ለማንበብ (PDF) ይህንን  ይጫኑ፤
 • ዘማሪ እስጢፋኖስ ከአርሒቡ ጋር ያደረገውን ለማንበብ (PDF) ይህንን ይጫኑ፤

በ“ሰባት ወይራ ሆቴል” አስተዳደር ጉዳይ የቅዱስ ላሊበላ ደብር እና ጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተወዛገቡ ነው


 • አስተዳዳሪውን ያባረሩት የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበር በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሽምግልና አስተዳዳሪው “ለተወሰነ ጊዜ ወደ ገዳሙ ማረፊያቸው ገብተው በክብር እንዲወጡ” በሚል ተስማምተዋል፤ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ በበኩላቸው “ሳልበታትነው” በሚል በገዳሙ ማኅበር አንድነት ላይ መዛታቸው ተሰምቷል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 2/2011, TO READ THE NEWS IN PDF, CLICK HERE)፦ የቅዱስ ላሊበላ ደብር እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የቤቶችና ሕንጻዎች አስመላሽ ኮሚቴ  በ“ሰባት ወይራ” ሆቴል አስተዳደር ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)