June 29, 2011

(ሰበር ዜና) - የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም መነኮሳት አስተዳዳሪውን አባረሩ


  • To Read in PDF, Click HERE.
  • ፓትርያርኩ በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ልመና አስተዳዳሪውን በኀይል ለማስገባት ደብዳቤ መጻፋቸው ተሰምቷል፤
  • በአሁኑ ሰዓት የገዳሙ የውስጥ ጥበቃ በመጠናከሩ “ይመጣል” ከተባለው የፖሊስ ኀይል ፍጥጫ እንዳይፈጠር ተሰግቷል፤
  • ለገዳሙ ገቢ ለማስገኘት የተሠራው አዲሱ ሁለገብ ሕንጻ ከተቀመጠለት ዲዛይን ውጭ እና ከተገመተው ዋጋ በላይ ያወጣ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 29/2011)፦ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበረ መነኮሳት “የገዳሙን ት/ቤት እና ሁለገብ የአገልግሎት ሕንጻ ከገዳሙ አስተዳደር በመለየት ከወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ጋራ በዝብዘዋል” ሏቸውን አስተዳዳሪውን መልአከ ሰላም ተክለ ማርያም ዘውዴን አባረሩ።


ከትናንት በስቲያ የማኅበረ መነኮሳቱን ተወካዮች ያነጋገሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ “አስተዳዳሪው ቢያንስ ለሦስት ቀናት በገዳሙ ቅጽር በሚገኘው ቤታቸው አድረው ከዚያ በኋላ በሌላ አስተዳዳሪ እንደሚተኩ” ያቀረቡላቸውን “መፍትሔ መሰል ማዘናጊያ” ሳይቀበሉ ቀርተዋል፡፡ እንዲያውም ማኅበረ መነኮሳቱ የገዳሙን የፊት ለፊት በር ብቻ ለእግረኛ ክፍት አድርገው ሌሎች ደጃፎቻቸውን በመዝጋት የውስጥ ጥበቃቸውን አጠናክረዋል፡፡ “ገዳሙ የተከበረ ነው፤ ማኅበሩ በሴትዮዋ የእጅ አዙር አገዛዝ ውስጥ አይወድቅም፤ አስተዳዳሪው የሚመለሱ ከሆነ ደም ይፋሰሳል” ብለዋቸዋል - ለአቡነ ጳውሎስ፡፡ የገዳሙ አስተዳዳሪ በቅርቡ ለኤጲስ ቆጶስነት ሹመት ከታጩት ቆሞሳት አንዱና “እጅጋየሁ እያለችልኝ ምን አሆናለሁ” በሚል አዘውትረው በሚናገሩት ማስፈራሪያ የሚታወቁ ናቸው፡፡

ይህ ዜና በሚጠናከርበት ሰዓት አቡነ ጳውሎስ ለፖሊስ የጻፉትን ደብዳቤ መነሻ በማድረግ አስተዳዳሪው በፖሊስ ታጅበው እንደሚመጡ እየተጠበቀ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ የገዳሙን በሮች ለእግረኛ ተሳላሚ ምእመናን ብቻ ክፍት በማድረግ የገዳሙ ጥበቃ መጠናከሩ ተስተውሏል፡፡


የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት ቀደምት አብያተ ክርስቲያናት መካከል የሚቆጠር ሲሆን በአአገልግሎት ጥንካሬው፣ በልማት ሥራው እና በጥንቁቅ አሠራሩ ሲመሰገን የቆየ ነው። ገዳሙ የራሱ ት/ቤት በመመሥረት ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናት አርአያ የሆነ መሆኑም ይታወቃል።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)