June 10, 2011

የማ/ቅዱሳንን ሕትመቶች የሚገመግሙ ሊቃውንት ተመደቡ

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 9/2011)፦ በማ/ቅዱሳን እና ከበላዩ ባለው በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ መካከል ለዓመታት ለዘለቀው አለመግባባት በመምሪያው በኩል በምክንያትነት የሚቀርበውን “ማህበሩ ሕትመቶቹን ለመምሪያው አያሳይም” የሚለውን ሰበብ ለመዝጋት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ባደረገው እንቅስቃሴ ከሊቃውንት ጉባኤ ሦስት ሊቃውንትን መመደቡን በድጋሚ አስታወቀ።


በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ተፈርሞ ዛሬ በወጣው ደብዳቤ ማ/ቅዱሳን “የሚያሰራጫቸው የሕትመት ውጤቶችና የሚዲያ ስርጭቶች ሁሉ በሊቃውንት እየታዩና እየታረሙ እንዲታተሙና እንዲሰራጩ በተወሰነውና በታዘዘው መሠረት ከሊቃውንት ጉባኤ … ከተመደቡት በመ/ታቦር ተሾመ ዘሪሁን፣ በመ/ብሉይ እዝራ ለገሠ እና በመ/ር አእመረ አሸብር እየታዩና እየታረሙ ከሥራ ላይ እንዲውሉ  … የማህበረ ቅዱሳን ጽ/ቤትም ከላይ እንደተገለጸው ከሰኔ 1 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ሳያስመረምር ሕትመትና ስርጭት ላይ እንዲያውል በድጋሜ በዚህ ደብዳቤ ግልባጭ” ታዟል።

ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሁለት በኩል ተወጥሮ ባለበት ሁኔታ ችግሩን በመጠኑ ለማቃለል ይህንን ደብዳቤ ይጻፍ እንጂ በሦስት ሰዎች በወር ሁለት ጊዜ የሚወጣ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ እና በየወሩ የሚወጣ ሐመር መጽሔት እንዲሁም ሌሎች የሕትመት ውጤቶችን ለማረም  እነዚህ ሦስት ሊቃውንት ምን ያህል ጊዜ ሊያገኙ እንደሚችሉ ከአሁኑ የሚያሰጋ ነው። ነገሩ በተፈለገው መልኩ የማይሄድ ከሆነ እና ሕትመቶቹ ከሚታተሙበት ጊዜ እንዲዘገዩ የሚያስገድድ ነገር ቢፈጠር አሁን የተዳፈነው ችግር ድጋሚ መፈንዳቱ እንደማይቀር መገመት ይቻላል።

ማ/ቅዱሳን መጽሔት እና ጋዜጣ ማሳተም ከጀመረበት ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ባሳተማቸው የሕትመት ውጤቶች አንድም ጊዜ በነገረ ሃይማኖት ጥፋት ተገኝቶበት እንደማያውቅ አምና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት “ማ/ቅዱሳንን የመክሰስ” ሸንጎ ላይ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ በነአባ ሰረቀ እንደ ጥፋት የተቆጠረበት አንድ ጉዳይ ሕትመቶቹ ፖለቲካንም በስውር ይጠቅሳሉ የሚለው ክስ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። እነ አባ ሰረቀ በዚያ ክሳቸው የመንግሥት ባለሥልጣኑ አቶ ተፈራ ዋልዋ “ቤተ ክርስቲያን የነፍጠኞች ዋሻ ናት” ማለታቸውን ለመጠየቅ የተደረገላቸውን አንድ ቃለ ምልልስ በአስረጂነት አቅርበዋል። በእምነት በኩል ግን ሕትመቶቹ ጥፋት አጥፍተዋል የሚባል አንድም ነጥብ ሳይገኝባቸው ቀርቷል።


ጠቅላይ ቤተ ክህነት አሁን በጀመረው መልኩ በመቀጠል በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት የሚታተሙ መጽሔቶች እና ጋዜጦች ተመሳሳይ የሊቃውንት እርምትና ክትትል እንዲደረግባቸው በማድረግ መዝለቅ ቢችል ለወደፊቱ ሊበጅ የሚችል ተግባር ሊሆን ይችላል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)