June 24, 2011

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ) ምእመኑን ይቅርታ እየጠየቀ ነው


  • Read this News in PDF.
  • “እኛ የአባቶችን አገልግሎት ለማስረሳት ሠራን፤ የእነርሱም ኀዘን እኛን ጣለን፡፡›› (እስጢፋኖስ ሣህሌ)
  • በተለያዩ አህጉረ ስብከት ሕገ ወጥ ሰባክያንንና እና ዘማርያንን የመከላከሉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፤
  • በጋሻው ደሳለኝ “በቪሲዲ የተሰራጨብኝ ማስረጃ በአኒሜሽን የተቀናበረ ነው!!›› አለ
  • በቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ዋዜማ በሜጋ - ሞያሌ መንገድ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ምርትነሽ ጥላሁን እና አሰግድ ሣህሉ በሕክምና ላይ ናቸው
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 24/2011)፦ በደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም የአካላዊ ቅጣት ርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል አንዱ የነበረው ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (በቅጽል ስሙ ቄሴ) የሕገ ወጥ ‹ሰባክያን› እና ‹ዘማርያን› አካል እና አባል በመሆን ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች የተጸጸተ መሆኑን በመግለጽ ካህናት እና ምእመናን ይቅርታ እንዲያደርጉለት እየጠየቀ ነው፡፡ “እኔ ከእነርሱ የተለየሁት ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ነው፤በዘማሪ ፈቃዱ አማረ የጋብቻ ሥነ ሥርዐት ዕለት ወጣቶቹ የወሰዱት ርምጃ ስለ ቅንዐተ ቤተ ክርስቲያን የፈጸሙት እንጂ በግል ጥላቻ ወይም በስሜታዊነት ተነሣስተው አለመሆኑን አምኜበታለሁ” ያለው ዘማሪ እስጢፋኖስ ከሕገ ወጥ ቡድኑ ጋራ ለረጅም ጊዜ አብሮ ስለቆየበት ሁኔታ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “ከዛሬ  ነገ የተሻለ ነገር አያለሁ በሚል ተስፋ በማድረግ ነበር” ብሏል፡፡

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሕገ ወጥ ‹ሰባክያኑ› እና ‹ዘማርያኑ› ዐውደ ምሕረቱን የሣቅ ቀን/መድረክ ሲያስመስሉ፣ ካህናቱን እና መሪጌቶቹን በስድብ ሲያሸማቅቁ፣ ራስን ባለመግዛት የተለያዩ አስነዋሪ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ በግልጽ ይቃወማቸው እንደ ነበር ለማስረዳት በመሞከር ላይ ይገኛል፡፡ ከሁሉም ነገር በላይ ለሰዓታቱ፣ ለማሕሌቱ እና ለቅዳሴው እንዳይተጋ “ባዶ ቤተ ክርስቲያን ሄደህ ምን ታደርጋለህ?›› እያሉ ያደረሱበት ጫና፣ ይሄዱባቸው በነበሩ አጥቢያዎች በአብዛኞቹ ካህናቱ እና መዘምራኑ የእነርሱን ሽሙጥና ዘለፋ በመሸሽ በመንደር ርቀው ይቆዩ የነበሩበት ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳዝነው ተናግሯል - ዘማሪ እስጢፋኖስ፡፡ መሠረተ እምነትን በማፋለስ፣ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በሚፈጽሙት ድርጊት መቼም ተባብሯቸው እንደማያውቅ ያስረዳው ዘማሪው፣ “በየዋህነት፣ በትምህርት ማነስ ምክንያት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አብሬያቸው በመቆየቴ በፈጸምሁት ስሕተት ቤተ ክርስቲያኔን አሳዝኛለሁ፤ በውስጣቸው ብቆይም በአቋም መለየቴን ገልጬ ማሳየት ነበረብኝ” ብሏል፡፡

“ተሐድሶ የለም›› እያሉ በዐውደ ምሕረት ለማስተባበል የሚሞክሩትን የሕገ ቡድኑን አባላት የተቃወመው ዘማሪ እስጢፋኖስ፣ “የእነርሱ ዋነኛ ዓላማ የአባቶችን አገልግሎት ማስረሳት ነው፤ እኛ የአባቶችን አገልግሎት ለማስረሳት ሠራን፤ የእነርሱም ኀዘን እኛን ጣለን” በማለት የተሰማውን ቁጭት ገልጧል፡፡ የይቅርታ ጥያቄውን ለብዙኀን መገናኛዎች በሚሰጣቸው ቃለ ምልልሶችና በተለያዩ አጋጣሚዎች እያቀረበ የሚገኘው ዘማሪ እስጢፋኖስ ከጥቃቱ ወዲህ በተለይም አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ መሆኑን በመግለጽ ወደ አገልግሎቱ ተመልሶ ለበደሉ መካስ እንደሚሻ ተናግሯል፡፡

በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል እና በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ሰበካዎች ባሉ ካህናት እና ምእመናን ዘንድ የሚታወቀው ዘማሪ እስጢፋኖስ ሦስት ካሴቶች ለብቻው፣ አምስት ደግሞ በጋራ የሠራቸው የ”መዝሙራት›› ሥራዎች አሉት፡፡ “ቄሴ” የሚለውን ቅጽል ስም ያገኘው በልጅነት ዕድሜው በአምሳለ ካህን ጠምጥሞ ጠበል በመርጨቱ፣ በክብረ በዓላት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እየዞረ በመዘመሩ መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ በማለዳው ባጣቸው ወላጆቹ ምትክ የሁለቱ አጥቢያ ምእመናን አባትም እናትም ሆነው ያሳደጉት ዘማሪ እስጢፋኖስ ወደ ገዳማት በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ በጨረታ በሚሰበሰቡ የርዳታ ማስተባበር ተግባራት የተመሰገነ ስጦታ እንዳለው ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡ “ለአገልግሎት መሰሰት አይታይበትም፤ ልግመኝነትን አያውቅም›› የሚሉት የቅርብ ወዳጆቹ በሐመረ ኖኅ ማኅበር በኩል ለቅዱስ ፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን/አዲስ አበባ/፣ በማኅበረ አቡነ አሮን መንክራዊ አማካይነት ለአቡነ አሮን ገዳም በተደረገው የርዳታ ማሰባሰብ ሥራ ያደረገውን ተሳትፎ ያስታውሳሉ፡፡

 
በተያያዘ ዜና የቅ/ሚካኤልን በዓል ለማክበር በሜጋ - ሞያሌ መንገድ ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት ምርትነሽ ጥላሁን እና አሰግድ ሣህሉ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው በኋላ አሁን በሕክምና ላይ መሆናቸው ሲታወቅ ወዲያው ወደ ያቤሎ ሆስፒታል ተወሰድው ርዳታ እንደተደረገላቸው ተገልጿል። ቀጥሎም በሐዋሳ ሆስፒታል የታከሙ ሲሆን ምርትነሽ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብርኤል ሆስፒታል ተጨማሪ ሕክምና እንደተሰጣት ምንጮቻችን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በጋሻው ደሳለኝ በበኩሉ በተለያዩ ሚዲያዎች እየወጡ ያሉ የስሕተት ትምርቶቹን እርሱ እንዳልተናገራቸው ይልቁንም እርሱ እንደተናገራቸው ተደርጎ “በአኒሜሽን” መቀናበራቸውን ለማስተባበል በመሞከር ላይ ነው።

ሁሉንም እግዚአብሔር ይማራቸው።

21 comments:

Anonymous said...

sanebew inba ayinen molaw wendime inkuan wedelibonah temelesik destaye wesen yelewim isti yehulunim lib degimo yimelisilin ina setanin inasafirew beidmena betsega yitebikih wendime

Anonymous said...

ayn lebonache EGEZEABEHER AMELAK meleslk wendeme

Anonymous said...

EGEZEABHER AMELAK Wedelebonach meleseh wendemachen ye BETKERSTN AMELAK

Anonymous said...

“እኛ የአባቶችን አገልግሎት ለማስረሳት ሠራን፤ የእነርሱም ኀዘን እኛን ጣለን፡፡›› (እስጢፋኖስ ሣህሌ)

Anonymous said...

Welcome to your mother!Pray to be blessed and serve God.

Anonymous said...

Egeziabher men yesanewal !! lelochunem libe yestachew

Anonymous said...

Diakon Estifanos silante yesemanilih zena melkam new, yederesebetin kitat "amen" bilo yemikebel sew degmo Egziabher limrew siwed lib yesetew sew newuna satiwul satadir leniseha abatih tenazezina kenonahin tekebel. Ende gil asteyayete gin wede medrek tolo batiweta emertalhu, mechem sew hulu ekul ayidelemina nidetu yalberedelet sew yibelt liyaderg silemichil kechalik ahun yeteleyehachew sewoch wedenakut se-atat ena mahilet be-ejigu tigana rasihin eyew , yetewesedebih tsegam kale yimelesilihal; Ye-Aba Giorgis Amilak zim ayilihimina befitsum libih belelit tiga. Tilehew yeneberewun simihin MEDHANEALEM wedebotaw yimelisilihal. Yekidus Dawit Amlak Yismah.

Moges said...

please try to handle being famous with humility and humbleness

Anonymous said...

konjo new. ke sew sihitet ke biret ziget ayitatawum. yikirta degimo ye christian tegbar new.

Anonymous said...

be adegawu yetegodutin EGZEABEHER yemarachew lehulum hegewetoch lebona yestachewu.

ብስራት ገብሬ ( Bisrat Gebre ) said...

Egizehabihair yewodedewin yaregale! Enatachin Dingle Mariam lehulachinim a'yene libonachinin tabiralin. Wondem ante bememelesih des lee'lihina tikikilegnaw bota endehonk lee'semak yegebal. Yetefaw begi wode betu simeles hulum des yilewal. Enkuan wode heezibeh kiristianun/deje selam tekelakelik. Amen!

Anonymous said...

"በተለያዩ አህጉረ ስብከት ሕገ ወጥ ሰባክያን ንና እና ዘማርያንን የመከላከሉ ጥረት ተጠ
ናክሮ ቀጥሏል፤"

ባለቤቱን፡ካልናቁ፣አጥሩን፡አይነቀንቁ፡እንድሚባ
ለው፡ነውና፡ቤተ፡ክርስቲያናችንን፡እንጠብቅ!የሉ
ተር፡ቅጥረኞች፡ከኛ፡ዘንድ፡ተመንጥረው፡መወገድ፡
አለባቸው!!!

ለምሳሌ፡ጌታቸው፡ዶኒ፡የመካነ፡ኢየሱስ፡ፕሮቴስስ
ታንት፡ድርጅት፡አባል፡ስለሆነ፣እርሱና፡እያወኩን፡
ያሉት፡ለጣዖቱ፡ሐውልቱን፡ያቆሙለት፡እንደነ፡በ
ጋሻው፡ያሉት፡በሙሉ፡ከተዋሕዶ፡ተረግመው፡ሊወ
ገዱ፡ይገባል።

ውስጣችን፡መሽጎ፡በተዋሕዶ፡ልጆች፡ላይ፡ማሳደደ
ን፡የቃጣው፡"አባ"ሰረቀም፡የጌታቸው፡ዶኒ፡ተብና
ባሪ፡እንደመሆኑ፡ሁሉ፡ከቤተ፡ክርስቲያናችን፡ተወ ግዞ፡ሊወገድ፡ይገባል።እንደርሱ፡ያሉትን፡ወረንጦ ዎች፡አቅፎ፡ለቤተክርስቲያንችንና፡ሕዝበ፡ክርስቲ ያን፡በጎ፡ይደረጋል፡ብሎ፡ማሰብ፡ከንቱ፡ዘበት፡መሆ ኑ፡መታወቅ፡አለበት።

እንደ፡ተክልዬ፡ልጆች፡በመላ፡ኢትዮጵያ፡በቅናት ና፡በቆራጥነት፡ጓዳችንን፡ለማጽዳት፡እንትጋ።ተሽ መድምደው፡ሊያሽመደምዱን፡የሚሻቸውን፡ደላሎ ች፡ወግዱ፡ብለን፡እናጋልጣቸው፤እናሳፍራቸው!

ዘማሪ፡እስጢፋኖስ፡ሣህሌም፡በተክልዬ፡ልጆች፡እር
ምጃ፡ዓይነ፡ልቡናው፡ተከፍቶለት፡ነው፡ይቅርታ፡ለ
መጠየቅ፡የበቃው።እንደርሱ፡ያሉትን፡ቅኖች፡ሲመ
ለሱ፡በፍቅር፡እንቀበላቸዋለን።እንኳን፡ተመለስክ፤
እንኳን፡ተመለሳችሁ፡እንላቸዋለን።

ተንግህዲህ፡በፍራቻ፡ከመጠቃት፣በንቃትና፡በቆራጥ ነት፡ቤተ፡ክርስቲያናችንን፡ለማጽዳት፡እንነሳ!

ዓመፀኞቹ፡ሉተራውያን፡መጡብን፡እንጂ፡ካሉበት፡ ሄደን፡ነገር፡አልፈለግናቸውም!!!

የአባታችን፡የሊቀ፡ሊቃውንት፡አለቃ፡አያሌውን፡
የተጋድሎ፡ቃል፡መርሃችን፡አድርገን፡እንነሳ!

የቅዱሳን፡ሰማዕታት፡አምላክ፡መድኃኔ፡ዓለም፡ክር
ስቶስ፡ከኛ፡ከተክለ፡ሃይማኖት፡ልጆች፡ጋር፡ነው!

የተክለ፡ሃይማኖት፡ልጅ፤
ሳሙኤል፡ዘአሰቦት

Anonymous said...

Yemigermew ye Begashaw (ye senga berew) shimteta new,le mertenesh "bizu gize tezelfo angetun yadenedene dinget yiseberal fewsem yelewem" Mesale 29:1 le Aseged "ke Betekeristian gar Yemitalu yidekalu " Mattew 21:8

Anonymous said...

Inkuan yeniseha zemenachihun arezemewu!! Mechem inde Feri'on indemathonu tesfa adergalehu.

Anonymous said...

aye dejeselamoch! ene Begashaw tilik sew hunew endezih zegeba siyasifelige? minew ethiopiawiyan hodam honin elalew andande! hodam! hager atiwedu! asimesayoch! abatochachihu lehager, lehaimanot, lekibirachew rasachewin asalifew setu! enante demo haimanotin letelat, hagerin lekififil, kibirin lewiridet! ere minew!

Bejegina bet anbesa megidel jegininet sihon...be leloch demo ayit meta bilo meterames, mesariya mefeleg! lemin ayituan lemegidel! ere tewu! ahun begashaw lenante anbesa huno new? simun endatiterubign kezare wediya!

Tewahedo said...

May God send His mercy upon you Mirtnesh. O'h God the true healer and saviour Send your power to the weak and sick people.

Setnet said...

amen yimaren!

Anonymous said...

Egziabeher lebona yistehena yalkewen lemetegber yabekah!!

Anonymous said...

ዘማሪ እስጢፋኖስ፣ እንኳን ደህና ተመለስክ፡፡
ምርትነሽና አሰግድ እግዚአብሔር ይማራችሁ እንደ ዘማሪ እስጢፋኖስም ይመልሳችሁ፡፡
በጋሻው፣ ስለማታውቀው አኒሜሽን ከመዘባረቅ መጀመሪያውኑ ልቡናህን አስተካክለህ አፍህን አርመህ መናገር ነበረብህ፡፡
ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ
እንደተባለው ሆኖብሃል፡፡

Anonymous said...

Yehatiyat hulu minch genzeb newuna genzebn kerasachin belay anwuded! Genzebn tilu maletie endalhone gin teredulign!
Be ewunet le ewunet enqom zend Qdist Dingil Mariam tirdan!
Amen

Anonymous said...

Kelebeh kehone enkwan temeleseh, mekniyatum ye'zeh zemen strategy k'Betekrestian alemewutat selhon bezuwoch sitawokebachew temelesen lilu yichilalu, .... lemanegnawum leben ye'mimermer Egziabher keleb Memeles Yadregleh. Y'Begashaw Animation teserabegn enkuwan ayawatahem 'Begashaw bedele ena min yitebese beleh'engna Debre altenagrehem I have the record ...min ale ande ken Ewunet betenagre.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)