June 9, 2011

ተስፋ ኪ/ምሕረት የተባለው ማኅበር ተፈረደበት፤

To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF). ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ።
  • የወሰደውን ገንዘብ እንዲከፍል ተወሰነበት፤
 (ደጀ ሰላም፤ ጁን 9/2011)፦ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት የፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና ልማት ማኅበር የሚባለውና በቅርቡ በሐዋሳው የአብያተ ክርስቲያናት ብጥብጥ ስሙ ጎልቶ የሚጠራው ማኅበር ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችን እረዳለሁ በሚል  ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የወሰደውንና በምንጥቅም ላይ እንዳዋለው ማስረጃ ያላቀረበበትን 73 ሺህ ብር እንዲከፍል፣ እንዲሁም ንብረቱ እንዲታገድ ሲል የሐዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።


ፍርድ ቤቱ ትናንት ከሰዓት በስቲያ ባሳለፈው በዚሁ ውሳኔው መሠረት አብያተ ክርስቲያናትን በመበጥበጥ፣ የምዕመናንን አፍንጫ በመስበር በሌሎች ወንጀሎች የተፈረደበት የቀድሞ የማኅበሩ ሊቀመንበር በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ሌሎች ሁለት የማኅበሩ አመራር አባላት ደግሞ እየተፈለጉ ነው ተብሏል።

በሐዋሳ ያለውን ችግር ለአንዴም ለመጨረሻውም ለመፍታት በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ ይህንን ማኅበር ልክ እንደ ቤተ ክርስቲያን አካል በመውሰድ ሪፖርት ከማድረጉም በላይ ከማ/ቅዱሳን ጋር በማስተካከል “ሁለቱም እንዲታገዱ” የመፍትሔ ሐሳብ እንዳቀረበ ይታወሳል። ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፣ በጋሻው ደሳለኝን እና ያሬድ አደመን በመደገፍ የከተማውን አንዳንድ ወጣቶች ለብጥብጥ በመቀስቀስ የድብደባ ወንጀል የፈፀመው ይህ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ማኅበር በሕግ በመጠየቁ በሐዋሳ ያለውን የምዕመናን ልብ ያሳርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)