June 16, 2011

ስለ ቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዘገባ

To Read in PDF, click HERE.
(ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ)፦ በመቐለ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ የሚሰጠው ትምህርት ‹‹የርዳታ ሰጭ ፈረንጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት›› እንጂ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሰጥ በሲኖዶሱ የተፈቀደው የትምህርት መርሐ ግብር ባለመሆኑ ጉዳዩን ቅድሚያ ሰጥተውና በሚገባ አጣርተው ለሐምሌው ጉባኤ ሪፖርት የሚያቀርቡ የምሁራን ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲመደቡ ከግንቦት 10 - 16 ቀን የተካሄደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መወሰኑን ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዘገበ፡፡


ጋዜጣው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ለኅትመት ባበቃው የግንቦት ወር፣ 56 ዓመት ቁጥር 1202003 .ም እትሙ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ስለ ጉባኤው ውሳኔዎች የሰጡትን ዝርዝር ውሳኔዎች መሠረት አድርጎ እንደዘገበው የትምህርት መርሐ ግብራቸው አፋጣኝ ጥናት ከሚያስፈልጋቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል የመቐለው ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ ‹‹ጊዜ የማይሰጠው›› ነው፡፡ ብፁዕነታቸው በጋዜጣው በተጠቀሰው ሰፊ መግለጫቸው፣ ‹‹የሌሎች ኮሌጆችና የአብነት ትምህርት ቤቶች ጉዳይም በሂደት ተጣርቶ እንዲቀርብ፣ ለዚህም በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርትም ሆነ በዘመናዊ ትምህርት የበሰለ ዕውቀት ያላቸው አባላትን ያካተተ አጥኚ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲቋቋም ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፤›› ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል ከመንበረ ፓትርያሪኩ ምንጮች ባገኘነውና የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን ሤራ በሚያጋልጠው ሰፊ ዘገባችን ሲም/Serving in Mission/ የተባለው አሜሪካዊ የፕሮቴስታንት እምነት ድርጅት ‹‹የተሐድሶን እንቅስቃሴ የትምህርት ጥረቶች ለማገዝና ለማጠናከር፣ ለመደገፍና ለማበረታታት›› አልሞ ከዚሁ ከመቐለ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ አስተዳደር ጋራ በመስማማት መምህራኑን ማሰማራቱን፣ ይህም ምእመናንንና ካህናትን በማስቆጣቱ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን መግለጻችን ይታወሳል፡፡ ጋዜጣው አጀንዳው በሲኖዶሱ ቀርቦ ይህን መሰሉ ውሳኔ እንዲተላለፍ የተደረገው የኮሌጁ ቦርድ አባላት በሆኑ ሊቃነ ጳጳሳት ጥረት መሆኑን ጨምሮ አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአክሱም ጽዮን ለሚሠራው የታሪካውያን ቅርሶች ማከማቻና መከባከቢያ ሙዚየም ሥራ ማስጀመሪያ ብር 15 ሚልዮን ለመስጠት መወሰኑን ይኸው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ የሙዚየሙ ሥራ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ጸሎተ ቡራኬ የተጀመረው ሚያዝያ 11 ቀን 2003 .ም መሆኑን ያስታወሰው ጋዜጣው፣ በወቅቱ ቅዱስነታቸው በሰጡት ቃለ ቡራኬ ሙዚየሙ ከሦስት ሺሕ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው ታሪካውያን ቅርሶች የሚቀመጡበትና ለጎብኚዎች ምቹ የሚደረጉበት በመሆኑ ለሙዝየሙ ሥራ የሚያስፈልገው ጠቅላላ ወጭ ከምእመናንና ጉዳዩ ከሚያሳስባቸው ለጋሽ ድርጅቶች እንደሚጠበቅ ማስገንዘባቸውን አመልክቷል፡፡ በሙዚየሙ ከወርቅ እና ብር የተሠሩ የጥንታውያን ነገሥታት ዘውዶች፣ የብርና ነሐስ፣ የወርቅ መስቀሎች፣ በወርቅ የተለበጡ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት፣ አልባሳትና የጥንታውያን ነገሥታት ኮርቻዎች የሚቀመጡበት እንደሆነ ተገልጧል፡፡ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በስተጀርባ ሰሜናዊ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚሠራው ይኸው ሙዚየም ባለሦስት ፎቅ ሲሆን 4975 ካሬ ሜትር ይዞታ እንዳለው ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል፡፡

በተያያዘ ዜና ከግንቦት 10 - 16 ቀን 2003 .ም የተካሄደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከጠቅላላ ገቢያቸው የ35 ከመቶ ፈሰስ በመላክ ለመንበረ ፓትርያሪኩ ፋይናንሳዊ አቅም መሠረት ለሆኑት አህጉረ ስብከት በሚያከፋፍለው ድጎማ ላይ ጭማሪ እንዲደረግ መወሰኑን በዚሁ የጋዜጣው እትም ላይ ተገልጧል፡፡ በዚሁ መሠረት ከግንቦት አንድ ቀን 2003 .ም ጀምሮ ለሁሉም አህጉረ ስብከት በወር ብር 235,000.00/ለእያንዳንዱ አህጉረ ስብከት በወር ብር 5000/ በአጠቃላይ በዓመት ብር 2,820,000.00(ሁለት ሙልዮን ስምንት መቶ ሃያ ሺሕ ብር) ክፍያ እንዲፈጸም ምልአተ ጉባኤው በሙሉ ድምፅ ወስኗል፤ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የተደረገውን የደመወዝ ጭማሪም ያጸደቀ መሆኑ ተመልክቷል፡፡


3 comments:

Sam said...

Letefetsaminet yeiyandandu iwnetegnoch yebete kirstian lijoch 'Abune zebesemayat' and 'yenedirsha minden new' yasfelgal. Inkfat kalemehon jemro. Long life to our true fathers.

Anonymous said...

Tiru New. I can see all z efforts of Dejeselamawuyan.
By z way w/t is going on around sereke?
MK Had Decided 2 accuse legally aba sereke 4 his bad words against MK, What is going on?
AGE

Orthodoxawi said...

Thanks to the Almighty!
I can see that a good time is coming. We can see that the majority have understood who is the true "Enemy" of our church.
But it took us too long to come to this common understanding. The next step is how to protect our church from the gangsters (mafia group = Aba Paulos + the Tehadso group).
BTW: Sereke Tsilmet, Ejigayehu Elzabel, Pastor Begashaw, Yared Ademe, Pastor Ashenafi G/Mariam ....are only the front ends of the tehadso group. There are many more to be kicked out.

Dejeselamawuyan:- keep on expanding the truth, and creating awarness.

With the help of God, we will clean our church from all the insergents (Sergo geboch).

Long Live Tewahedo!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)