June 25, 2011

ነጋድራስ ጋዜጣ ስለ ዘማሪ እስጢፋኖስ


  • Read in PDF.
  • ደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥቢያ ወጣቶች “በአስተሳሰባቸው ትክክል ናቸው” ብሏል፤
  • ከሕገ ወጥ ቡድኑ አባላት ጋራ “በሃይማኖትም እንደማይገናኝ” መስክሯል፤
  • የቅኔ፣ የድጓ እና የመጻሕፍት ሊቃውንት በየበረሓው ወድቀው እኛ ግን በገንዘብ ከብረናል፤ በስምም ታውቀናል፤ መተዳደሪያችንም ቤተ ክርስቲያን ናት፤ ሆኖም ተሐድሶ በሚል ስያሜ የቤተ ክርስቲያንን መሠረት ለመናድ መሞከር አሳዛኝ ገጽታ ነው፡፡” (ዘማሪ እስጢፋኖስ ለነጋድራስ ጋዜጣ)
(ነጋድራስ ጋዜጣ፤ ዐርብ፣ ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ.ም)፤ ከኦርቶዶክስ ዘማርያን አንዱ የሆነው እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ)፣ “የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ለመለወጥ ከተሰለፉ ተሐድሷውያን ጋራ አለመሆኔ ይታወቅልኝ” ሲል ገለጠ፡፡


እስጢፋኖስ (ቄሴ) ለነጋድራስ እንደገለጠው፣ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቁ ዝማሬዎችን ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሶ፣ ይሁንና ራሳቸውን “ተሐድሶ” ብለው ከሚጠሩ ወገኖች ጋራ በቅርብ መታየቱ በሚያውቁት ምእመናን እና አባቶች ዘንድ ቅሬታ እንዳስነሣበት ተናግሯል፡፡

ደጆችሽ አይዘጉበሚል በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዶ በነበረው መርሐ ግብር በንቃት እንደተሳተፈ የገለጠው እስጢፋኖስ (ቄሴ)፣ “ያኔም ሆነ አሁን በምታወቅበት የዝማሬ አገልግሎት ስሕተት የሚገኝበት መዝሙር አልዘመርኩም፤ ምስክሮቼም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን ናቸው” ብሏል፡፡

እንደ እስጢፋኖስ (ቄሴ) ከሆነ፣ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም በደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጓደኛው የተክሊል ሥርዐት ላይ በሚዜነት በተገኘበት ወቅት በእርሱና በሁለት ጓደኞቹ ላይ ወጣቶች ተቃውሞ እንዳቀረቡባቸው ተናግሯል፡፡ የወጣቶቹ ተቃውሞ “ተሐድሶ ነን ከሚሉት ጋራ ግንኙነት አለህ” በሚል ሲሆን የደረሰበት ሁኔታ ስሜቱን እንደነካው ነው የገለጠው፡፡ “ጓደኝነት ሌላ ሃይማኖት ሌላ” የሚለው እስጢፋኖስ፣ “ቀደም ሲል በተሐድሶነት ከተጠረጠሩት ወንድሞች ጋራ የነበረኝ ግንኙነት ከተቋረጠ ቆይቷል፡፡ “በእምነቴም ከእነርሱ ጋራ የሚገናኝ ምንም ዐይነት ሁኔታ እንደሌለ ይታወቅልኝ” ነው ያለው፡፡

“በቤተ ክርስቲያን ተቃውሞ ያቀረቡብኝ ወጣቶች በአስተሳሰባቸው ትክክል ናቸው፤ ይሁንና በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሳሳቱ ወንድሞችን መመለስ የሚቻለው በፍቅር ነው፤ ስለዚህም አላግባብ የተቃወሙኝን ወጣቶች በእግዚአብሔር ፍቅር እወድዳቸዋለሁ” ብሏል፡፡

እስጢፋኖስ (ቄሴ) ጨምሮ እንደገለጸው የቅኔ፣ የድጓና የመጻሕፍት ሊቃውንት በየበረሓው ወድቀው ሳለ እኛ ግን በገንዘብ ከብረናል፤ በስምም ታውቀናል፤ መተዳደሪያችንም ቤተ ክርስቲያን ናት፤ ሆኖም ተሐድሶ በሚል ስያሜ የቆየውን የቤተ ክርስቲያን መሠረት ለመናድ አሳዛኝ ገጽታ ነው” ሲል አብራርቷል፡፡ “ከዚህ በኋላ የእኔ ትግል ቤተ ክርስቲያኗን ከከበቧት ከለባት ጋራ ነው” ያለው እስጢፋኖስ (ቄሴ)፣ “ተመራጩ መንገድ በትሕትና መመላለስ እንጂ ከሥርዐት ያለፈ ነገር ማካሄድ ለማንም አይጠቅምም” ሲል ተናግሯል፡፡

11 comments:

Welete silase said...

If Egiziabher yibarkih yazliqlh sew hulu yatefal wanaw mmls new yqrutnim yimeliseln
Amen

Anonymous said...

temesgen yedengle lij EWNET ENA ...EYADER YITERAL new.ahunim ke guyawa beltew,be awde mihretwa tawkew,be ersuaw tadsew enadsesh lemilut hulu amlak yenisha lib yistachew.

Anonymous said...

‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዝም በማለታቸው ይህን ርምጃ ለመውሰድ ተገደናል፤ የተክለ ሃይማኖት ድል በዮሴፍም ይደገማል፤ ሕገ ወጦቹን ከአዲስ አበባ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት በማጽዳት የሐዋሳን ምእመናን እምባ እናብሳለን፤ ሃይማኖታችንን መጠበቅ ብቻ ማእከል ያደረገው ርምጃችን ሕገ ወጦቹ ስሕተታቸውን አርመው የበደሉትን ምእመን ይፋዊ ይቅርታ እስኪጠይቁ አልያም ለይቶላቸው ወደ መናፍቃኑ ጎራ እስኪገቡ ድረስ ይቀጥላል!!›› (የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ወጣቶች)

MelkamKene said...

Dear Brother, Remember the way of DEMASE with St. Apostle Paul! If you are honest, I will advice you go to ''MEMERE NISEHA'' then finally the seed and the thrush will be separated by the sieve of the church, Lord of Lords; Master of Masters Jesus Christ.
GETA ANTENEM YITSINAHI ENTIFA YEMILUTENEM YIMELISELEN!
God bless our Church and all Ethiopians

Anonymous said...

ጥሩ ነው ወደ ልቦና መመለስ ግን ብዙ ነገሮች ማድረግ ያለበት ይመስለኛል። እንደ ጓደኛ ብዙ ቅርበት ስለነበረው ብዙ ተንኮላቸውን ያውቃል። ስለዚህ ስለ እምነቱ ብሎ የተንኮል ስራቸውን በመረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ያኔ ነው እውነተኛና ለእምነቱ ቀናኢ መሆኑ የሚረጋገጥ። ብዙ የማስፈራሪያ ነገሮች ሊደርሱበት እንደሚችሉ አውቃለሁ። ነገር ግን አምላካችን እውነትን ስለ እኔ የመሰከረ አይደል የሚለው? እውነት መውጣት አለበት። ልጆቹ ታፈርኩ አይመልሰኝ አይነት ስራቸውን ቀጥለውበታል። የመጨረሻ የሚሉትን የማወናበጃ ስልትም በመተግበር ላይ ይገኛሉ። ግን ከማን ጋር እንደ ገጠሙ አላወቁትም። ተዋህዶ በርካታ ና በቀጥታ ከአምላካቸው ጋር ልዩ ግንኙነት ያላቸው ተከታዮች አሏት። የነዚህ ጸሎት ስንት ነገር እንደ ሰራ ታሪክ ይነግረናል። ችግሩ ታሪክን ወይ በስህተት ተርጉመውታል ወይም ለማንበብ ጊዜ አላገኙም።
ልብ ይስጣቸው።

Anonymous said...

Can you please post the article written by መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ስለ ተሃድሶ … (በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ሰኔ 2003)
I read an excerpt on a Facebook page, which says
"… በአሁኑ ጊዜ ያለው አገልግሎቱ እየተዳፈነ አገልጋዮቹ እየወጡ ከአገልግሎቱ ይልቅ አገልጋዮቹ እየታወቁ ነው ከወንጌሉ ይልቅ ወንጌላውያኑ … የአንድ አገልጋይ ስራ ሕዝቡን ከክርስቶስ ጋር ማገናኘት ነው አሁን …ሕዝቡ ወደእኛ ነው የሚመጣው … እግዚአብሔርን አያገኝም፡፡ አንድ ጳጳስ አንድ ሰባኪ አንድ መነኩሴ አንድ ዘማሪ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ የግል ሃሳቡን ቤተክርስቲያን ላይ ሊጭን ሳይሆን ሃሳቧን ተቀብሎ እንደ ቧንቧ ለሕዝብ ሊያዳርስ ነው፡፡ … ቤተክርስቲያንን ካህን ቤተመንግስትን ወታደር ነው የሚደፍረው …ሰው ራሱን መለወጥ ሲያቅተው ሥርዐት ለመለወጥ ይታገላል ራሱን ማደስ ሲያቅተው ሃይማኖትን ለማደስ ይታገላል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተሰርታ ያለቀች ናት ተሰርቶ ባለቀ ቤት ገብቶ መኖር እንጂ ይቀየር የማለት መብት የለህም በዝቷል ይቀነስ ረዝሟል ይጠር ተጣሟል ላቃና የሚባል ነገር የለም፡፡ ቤተክርስቲያን ሰውን ታድሳለች እንጂ ሰው ሊያድሳት አይችልም፡፡ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት አሁን ተሃድሶ ያነጣጠረባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የሚወጡ ናቸው መምህር ካህን መነኩሴና ጳጳስ የሚሆኑት እነዚህን ከያዝን በቃ ቤተክርስቲያኑን ተቆጣጠርን በሚል ሥርዐተ ትምህርቱን ጉዳት እያደረሱበት ነው፡፡ አንዳንዶቹን መምህራን ሲችሉ በጥቅም እየገዙ ደቀመዛሙርቱ ከሀገረ ስብከት ሲላኩ ሆነ ተብሎ በዚህ ደረጃ እንዲመረጡ እያደረጉ ነው … አንድ ስብከት ኦርቶዶክሳዊ የሚባለው ክርስቶስን ግንድ ቅዱሳንን ጻድቃን ሰማዕታትን ቅርንጫፍ አድርጎ ብሉይን ሓዲስን መጻህፍተ ሊቃውንት መጻህፍተ መነኮሳትን መሰረት የሥራ መጻህፍትን ቅርንጫፍ አድርጎ መስበክ ሲችል ነው ይሄን መስበክ ካልቻለ ችግር አለበት ማለት ነው፡፡ …ተሃድሶ ቤተክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ የማድረግ ስልት ነው፡፡ "
God Bless!

YeAwarew said...

Selam All:

I want to say "Bravo!" to the brave youth of TekleHaimanot EOTC. You are one fine example that we should all follow. Please Keep It Up. At least there are some(like you) who care enough to defend their atbia church. Of course, we cant say that to the many who are embracing the "tehadisso - menafiqans" and think they are still true "tewahedo".

God bless,
May God protect His Church and the true followers

Thanks DS, as always, keep it up.

YeAwarew

Anonymous said...

Betam tiru new! Endetebalew gin bemereja serachewun magalet alebet.

DEJESELAM:
Negadiras gazetan muluwun asnebibun

Anonymous said...

What surprises me is the accident occuring on Mirtinesh and the protestant guy, Asegid Sahle. I am not delighted with the accident, but amazed that Mirtinesh is already gone far to join Protestantism. So awful to spend her time with a declared protestant. What was she doing?

Anonymous said...

እስጢፋኖስ (ቄሴ) ጨምሮ እንደገለጸው የቅኔ፣ የድጓና የመጻሕፍት ሊቃውንት በየበረሓው ወድቀው ሳለ እኛ ግን በገንዘብ ከብረናል፤ በስምም ታውቀናል፤ መተዳደሪያችንም ቤተ ክርስቲያን ናት፤ እውነት ነው

Anonymous said...

Egziabeher lebona yisteh ! yalkewnem lemefetsem yabekah!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)