June 24, 2011

ሲኖዶሱ እየሠራ ነው፤ እኛስ? ለፓትርያርክ ጳውሎስ ፲፱ኛ በዐለ ሲመት የተበከረተ

 ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ ከፌስቡክ የተገኘ ሲሆን ፀሐፊው ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ ናቸው። መልካም ንባብ።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ታሪከ-ጡመራ
በዓመት ፪ ጊዜ በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ለሕዝብ መገለጥ ያለባቸውን ያህል ሳይገለጡ በመቆየታቸው ብዙ ችግሮች በወረቀት ላይ እንጂ በተግባር ባለመፈታታቸው ሲደመሩ ቆይተዋል። ፈጣሪ ፈቀደና ደጀሰላምም ፋና ወጊ ሆና ስለውሳኔዎቹ መስማትና ሀሳቡን መከታተል ተጀመረ፤ በእርግጥ ጥቂት ውሳኔዎች በሬድዮኖች በጣም ጥቂቱ ዘገባ ደግሞ በጋዜጦች ሲቀርቡ ቆይተዋል። ከዚያ ወዲህ ምእመናን የትኛው ሀሳብ ለምን ተወሰነ? ይኼኛው ለምን ቀረ? ወዘተ እስከማለት ደርሰዋል። በዚህም ሁላችንም የየግላችንን ሀሳብ ተለዋውጠናል። የእስከዛሬውን ወጥ አድርገን ብንገመግመውስ ለነገውም ጭምር የሚጠቅም አይመስላችሁም?


ውሳኔዎችና እኛ
ብዙዎች የውሳኔዎችን ጥንካሬ የምንመለከተው  ለእውነት ያለውን ግልጥ ድጋፍ ወይም ለስህተት ያለውን የፈጠጠ ተቃውሞ ይመስላል። ለምሳሌ «ሐውልቱ ይፍረስ» የሚለው ውሳኔ ብዙዎችን ያስፈነደቀና «ጀግናው ሲኖዶስ» ያስባለ ሲሆን የ«አባ» ሠረቀ/ሰረቀ አለመነሣት፣ /ፊደሉ ሰ ይሁን ሠ አላጣራሁም፤ ትርጉሙ ግን እንደሚለያይ አውቃለሁ/ የ«ሊቀካህናት» ጌታቸው ዶኒ አለመወገዝና የፓትርያርክ ጳውሎስ አለመነካት ብዙዎችን አላስደሰተም፤ «ሲኖዶሱ ታሪክ መሥራት አልቻለም፤ የሚፈሩት ነገር አለ...» ያልንም አለን። ሌላም፣ሌላም።

እዚህ ጋር ወጥነት ያለውና የተንኮል ዕቅድ ላይ መሰናክል የሚፈጥሩ፣ በአጸፋው የሚያወግዙና የቤ/ክ/ንን ሞገስ የሚጠብቁ፣ ጊዜውን ያገናዘበ መርሕ የሚከተሉና በግልጥ ባለማስቀመጥ ብዙዎችን የሚያድኑ ሊባሉ ይችላሉ፤ ሳብራራው ጊዜያችሁን አልወስድም። በአጭሩ ለመግለጥ ያህል፡- የተሐድሶን የማንሸራተት ስልት የአዳራሽና የስታዲየም ጉባኤን በመከልከል ማገድ፣ አድራሻ የሌላቸውን የግል ሰባኪዎች «ሕገወጥ» በማለት፣ ለቤ/ክ/ መዳከምና ለተሐድሶ መጠናከር ድጋፍ የሚያደርጉበትን የፓትርያርክ ጳውሎስን ሥረወጥ አካሄድ ማንነትን በሚያጣጥል መጠን «ሐውልተ ስምዑ»ን እንዲፈርስ፣ ቢል ቦርዶች እንዲነቀሉ፤ በፓትርያርክ ጳውሎስ የተሾሙትን ጌታቸው ዶኒ፣ «አባ» ሰ/ሠረቀና የሐዋሳ ገብርኤል አለቃን ከምድባቸው በማንሣት/የሚነሡበት ጥያቄ ውስጥ በማስገባት፤ ወዘተ ብናያቸው በቂ ውሳኔዎች ናቸው። አብዛኛዎቻችን ደግሞ የየራሳችን ደስታና ሐዘን፤ ኩራትና የአፈጻጸም ጥርጣሬ ውስጥ ገባን እንጂ ትንታኔውን አላየነውም እናም የሚቀረን፣ ያልገባን አለ ባይ ነኝ ።

ሲኖዶስና ምሥጢረ ክህነት

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያን ጠባቂና የበላይ መሪ በመሆኑ እንደ አንድ አካል ፍጹሙ ካህን ነው፤ ሥልጣኑም የማይገሠስና ሉዐላዊ ነው። በምድር የወሰነው በሰማይ የሚጸና ያለምንም ለውጥ ሁሉም /ፓትርያርኩ ጭምር/ ሊያከብሩት የሚገባ የመንፈስ ቅዱስ ውሳኔ ነው፤ «እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤» እንዲል። ግብ ፲፭፥፳፰ ይህን የመፈጸምና የማስፈጸም ኃላፊነት የሁሉም ግዴታና ድርሻ ነው፤ ከፓትርያርኩና ብፁዓን አባቶች እስከ ምእመን ድረስ። ለዚህ ውሳኔ የሚታዘዝ ጌታችን «ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።» ያለውን የሚፈጽም ነው፤ ቸል የሚልም ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።» ማቴ ፯፥፳፮ እንዳለ ለእኛም በመጠኑ እንደምንረዳው የ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት መሰብሰቢያ ቁስጥንጥንያ የዛሬዋን የቱርኳ ኢስታንቡል፣ የስምኦን ባለመስቀሉና ብዙ ቀኖናዎች የተደነገጉባት ቀሬና የሸሪኣዋ የዓለም ስጋት ሊቢያን እንዳስገኙ የዛሬዋ አክሱም ጽዮን ወደ ሙዚየምነት፣ አዲስ አበባም እንደባግዳድ፣ እነ፬ ኪሎ ቅድስት ሥላሴም የአውሮፓዎቹ አዳራሾቹን እንዳይሆኑ ማለትም ወቅታዊ የመጽሐፉ አንድምታ ነው። አወዳደቃቸው/አወዳደቃችን ታላቅ እንዳይሆን «ቤተክርስቲያናችንን እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን ለመጠበቅ ለምን የሲኖዶሱን ውሳኔ አንፈጽምም?» ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን፤ ያለመታዘዝ ውጤቱ እንደቃሉ ነውና። ይህ የሲኖዶስን ሥልጣነ ክህነት ላመነ ደግሞ አብሮት የሚሠራ መንፈስ ቅዱስ አለና በአንድስ እንኳ ሊጠራጠር አይገባም።

እኛ
አሁን ደጋፊና ተቃዋሚ በመሆን ሳይሆን፣ ከየግላችን ቅድመ ግምት በመስማማቱና በመለያየቱ ከመተቸት ወጥተን ነገሮችን በሰከነ ልቦና በማድመጥ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በጥብዓት መፈጸምና ማስፈጸም ይጠበቅብናል። የሚቸግረን የሚመስለን በስም ያልተጠቀሱ ጉዳዮችና ግለሰቦች ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ጌታ ራሱ ምልክትን አልሰጠንም? ድንግል አልጸነሰችም? ከጠላት ቀስት የምናመልጥበት መስቀል አልተሰጠንም? ከፍሬያቸውስ አንለያቸውም? የቤ/ክ/ አንድነት በሚጠብቀው፣ ወጣኒውን በሚያተጋውና ፍጹሙን በትሕትና በሚገዛው ቀኖና ላይ ሲያላግጡብን፣ የራሴ የሚሏትን ቤ/ክ/ በየመድረኩና በየኅትመቶቻቸው ሲተቹ የተባበሯቸው አልነበሩም? ምንኩስናውንና ክህነቱን አቃለው የተናገሩበትንና ራሳቸውን አዲስ ጥቅም ያደረጉበትን አሠራር ከዐይናችን ሊሰውሩ እንኳ መች ፈሩ? «ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።» ማቴ ፯፥፲፭-፲፰ የተባለውን የግድ መመርመሪያው ጊዜ አሁን ነው።


ፓትርያርክ ጳውሎስና ብፁዐን አበው

የጥቂቶች ትግል ፈተና ውስጥ የወደቀበት ያለፈው ዘመን ይበቃናል። አሁን ፓትርያርክ ጳውሎስም ይጠየቁ፡- ለምን ሲኖዶሱን ሲበጠብጡና ሲቃወሙ፣ ሊቃውንትን ሲያስወግዱና ወዳጆችዎን ሲሰገስጉ ከረሙ? ተማሩ የተባሉትን ፒኤችዲ የሚገልጥ የቤ/ክ/ንን አሠራር ማዘመን ትተው የአደረጃጀትና የኢኮኖሚ /አንጻራዊ/ ግዙፍ ውድቀት ሲግተለተል ምነው ማየት የተሣኖ? ምነውስ አንድ እንኳ መጽሐፍ ማበርከት ተሣኖ? ነጭ መልበሱና ከቢል ቦርድ እስከሐውልት ሲያስተክሉ ያልደከሞትን ለመምህሮችዎ የአብነት መምህራን ምነው መልሚያቸውን ባለማቀድ መጥፊያቸውን አበዙባቸው? ምናልባት ከጥቂቶቹ ወይም ከአንዱ ጋር በዓላማ ብትስማሙም ከአሜሪካዎቹ አበው ጋር እንዲፈጸም የተደከመበትን ዕርቅ በማጓተት ልዩነት እንዲስፋፋና እንዲጠናከር ምነው በተዘዋዋሪ ረዱ? የአንዲት ቤ/ክ/ አንድ ፓትርያርክና አንድ ቅዱስ ሲኖዶስን አክብሮ የሚኖረውና ዘመኑን ለመዋጀት የሚታትረው ማኅበረ ቅዱሳን ለምን የጠዋት ማታ ራስ ምታት ሆነብዎ? በመቅደሱ የኖረ ሳይወድ ፈሪሐ እግዚአብሔርን የሚረዳበት ቀኖና ሞልቶለት እያለ ምነው ድፍረትዎ በዝቶ እስከመቃብር ዘገዩ? ዛሬ እንኳ ሲደክሙ የሚቃወሞትን ኅሊና እና የሥልጣን ባለቤት መንፈስ ቅዱስ ለምን አይታመኑለትም? ይህን ሁሉ ግፍ ለፈጸሙበት በዐለ ሲመቶም ቅኔ ለሚያበረክቱልዎ የወርቅ ሽልማት የሰጠኁዋቸው ይመስለኛል፤ ምናልባት በቅኔዎቹ ሰም ብቻ የሚደሰቱበት ቀን ፲፱ኛው በዐልዎት ላይ ቢበቃስ?

ብፁዓን አበውም በሕይወታችሁ የለፋችሁለትን ክህነት በቸርነቱ ሃይማኖታችሁን በመጠበቅና በማስጠበቅ እስካሁን የተጋችሁ እንዲሁ ደግሞ አሁንም በርቱ፣ ጠንክሩ፣ ፍጹማንም ሁኑልን፤ ጊዜው መሥዋእት እንድትከፍሉ ስለሚጠይቃችሁ ስለጌታ ክርስቶስ ሁሉን መተዋችሁ እንደጥንቱ ዛሬም ጥቅም ይሁንላችሁ። ስህተቶችን ካልተቹ አይታረምምና ብዙዎች ውስጥ የተደበቃችሁና ተቆርቋሪ ብቻ ሳይሆን ዐዋቂም ለመምሰል ፍሬ አልባ መጻሕፍትን በማግተልተል፣ ከስህተትና ጉድለት ጋር ራሳችሁን ባስተዋወቃችሁባቸው ፊልሞች የዋሑን ማሳመን የሞከራችሁም ተመከሩ፤ ያደረጋችሁት የማያዋጣ ሞኝነት ነው፤ ጳጳስ ላይ አትዳፈር እያሉን ብናድግም «አባ» ጳውሎስን ያየ ለምን ዝም ይላል?» እላቸዋለሁ። ጊዜ ሲያገኙ ስለሥልጣን ሽኩቻ ሳይደክሙ የሚለፉ፣ ራሳቸውንም ስለዕውቀታቸውና ጠንካራ ተቆርቋሪነታቸው የሚያስተዋውቁ ጳጳሳት/ጳጳስ የግድ «አርፋችሁ ተቀመጡ፤ እናውቃችኋለን፣ ካልቻላችሁ ወደየመጣችሁበት አድራሻችሁ ተመለሱ» ልንላችሁ ያስፈልጋል።

ቤተክህነት

ታላቂቱን ሰማያዊት የክርስቶስ አካል ለማስተዳደር በየዘርፉና በየደረጃው የተመደባችሁም የተቀላቀለውን አሠራርና ሠራተኛ ለዩ፤ ሁሉን በፍቅር አድርጉት። ሳያውቁ የተጠለፉ አሉና ከእሳትም ነጥቃችሁ አድኑ። ሞት የሚገባውን ደግሞ ለሳኦል ያልራራ እግዚአብሔርን ጨካኝ አታድርጉት። እንግዲህ ከፓትርያርክ ጳውሎስ እርሾዎችና አሻራዎች ተጠበቁ እንጂ የአባቶቻችሁን ቀኖና ቸል አትበሉ።


በክርስቶስ ታናሽ ወንድማችሁ፣ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን አባሏ/የአካል ብልት፣ በፍርዱ ዙፋን ፊት እኩያችሁ ተፈራጅ

ዕጼ ምድር፣ ኃጥእ ገብር ቀሲስ

10 comments:

Anonymous said...

kesis you wrote good but . I think you are in postion of one side. E.O.T.C SHOULD BE REFORMED NOT HE DOGMA BUT THE DERSANAT , GEDELAT ETC . PLEASE RECOGNIZE THIS . NO APOSTLE PREACH EXCEPT BIBLE . THAT IS IT.

Anonymous said...

Exactly!!

That is what we need to do right now.

ACTION!!!!!!!!! ACTION!!!!!!!!!! ACTION!!!!!!!!!!

Anonymous said...

Enanet kelaye asteyaet yestachu ye aba serke berhan ena ye ato getachewe dony legoch ye hechen kedest bete kerstean ye gehanem degoch aychlweatem

wedlebachu temelesu

Anonymous said...

Dear Kesis,
I fully agree with what you have said except some reservation on the reconciliation of our Church fathers. That is, our church synod and our church fathers abroad. My reservation is on the contribution of Mahebere kidussan on this specific issue. Other than this, what kesis said is true and concrete current problem of our church. Concerning Mahebere kidussan, it is the main and well experienced Mahebere committed to serving our beloved church in many respect especially in exposing and fighting with our church dangerous enemy called TEHADESSO.
Coming to the first anonymous comment and his supporter next to him, I cannot even say you smell like TEHADESOO but you really are tehadesso. Therefore, you have no say on the church matter that you do not belong. I therefore would like to tell you to stop putting your figure on our church matter or you would rather need to take time to come to your sense and repaint.

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያን ቁርጠኛ አባቶችን ትፈልጋልች! ምሁራኑም መሥራት ያለባቸዉ አሁን ነው!
በሃገራችን እና አንድነታችን ላይ ብቻ አይደለም ጠላቶቻችን ጥቃታቸዉን የከፈቱብን በበለጠ ግን በሃይማኖታችን በእምነታችን እና በታሪካችን ላይ ጭምር ነው!

ጸሎት ብቻ በቂ አይሆንም! ጊዜው መሥዋዕትነትንም ይጠይቃል! በሚገባ የተቀነባበረ ጥቃት ነው በሃገራችንና ወገናችን ላይ የሚካሄደው! ሃገራችን እና ወገናችን ብቻ ሳይሆኑ ሃይማኖታችን እምነታችን እና ባህላችን ታሪካችን ሁሉ ለጥቃት ተጋልጠዋልና እያንዳንዳችን እንጠንቀቅ!

gondarew said...

I read what you write and i can say you are true christian,i don't know most of us we can not in the side of GOD i.e the law of GOD, rather we are in the opposite.Some of us we cheat ourself, I know GOD will foregive us, but how long we lie or until what, we are in a position of attacting those who practice the law of GOD.Please rise your hand say enought is enought, when you read this you may consider me as poletician I SWEAR TO GOD i am not,in stead i am the one who cry and pray to save our ortodox tewahido church. Again i went to say please do things in GOD way not other.

Anonymous said...

እኔ የምለው አባ ጳውሎስ እንዲህ ሆነው ሊያልፉ ነው?
ምን አለ አባታችን ይበቃዎታል፣ ንስሃ ይግቡ፣ እራስዎን ለማያልፈው ዓለም ያዘጋጁ ብሎ ደፍሮ የሚመክራቸው ቢገኝ::
ዝናው፣ ክብሩ፣ ዘመድን አለአግባብ መጥቀሙ፣ ለስጋ ከሚገባው በላይ አድሎቶ መኖሩ እኮ ሊያበቃ ቢበዛ አንድ አስር አመት እነደው እጅግ ቢበዛ ሁለት አስርት አመታት ናቸው የቀሩት::
እረ በዙሪያቸው ያላችሁ ከወደዳችኋቸው የሚጠቅማቸውን አሁን እንኳ ምከሯቸው ግዜው እያለቀ ነው::
እሳቸው እንጂ እቺ በተክርስቲያን እኮ ምንም አትሆንም ትፈተናለች እንጂ አትጠፋም የመሰረታት የማይሸነፈው የነገስታት ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ::
ብጹዓን አባቶችም እባካችሁ ቁረጡ፣ ለሞታችሁለት ዓለም ዳገም አትሳሱ::

Anonymous said...

ቀሲስ እውነት ብለዋል

ድሮ እንግሊዞች ኢትዮጵያን ለመግዛት አልሳካላቸው ብሎ ከቀረና ጣሊያንንም ኢትዮጵያውያን ከእነታቦታቸው ወጥተው ድል ካደረጓቸው በኋላ: አፍሪካውያንም የኢትዮጵያን ፈለግ ተከትለው ከነጮች የኮሎኒያሊዝም አገዛዝ ነፃ ሲሆኑ: እንግሊዞች በኢትዮጵያ ላይ መርዛቸውንና ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ የጥላቻ ቦምባቸውን በኢትዮጵያ ላይ ሲቀብሩ እንዲህ ነበር ያሉት:-

"ነጮች በጥቁሮች ላይ የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ ከፈለጉ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እና ኦርቶዶክስ የሚባል ሃይማኖት ከምድረ ገጽ መጥፋት አለባቸው" - ምክንያት ኢትዮጵያም አትንኩኝ ባይ አገር እና ኦርቶዶክስም አገር ወዳድ: የአንድነት እና የፍቅር አስተማሪ ሃይማኖት በመሆናቸው::

ለዚህ ነው - በዘር በጎሳ በሃይማኖት የመከፋፈል ድርጊት አገራችን ላይ በገዥዎቻችን እየተፈፀመብን የሚገኜው:: ለዚህ ነው -ኦርቶዶክስንም ለማጥፋት ስልጣን ላይ ባለው ጎሰኛው የወያኔ ሹም አባ ጳውሎስ አማካይነት ኦርቶዶክስን ለማፍረስ ሌት ተቀን ጥረት የሚደረገው::

ሚኒስትሮቹ በአደባባይ ኦርቶዶክስን የነፍጠኛ ሃይማኖት እያሉ ሲሳደቡና ሲዝቱበት - የዛቱበትንም በተግባር ሲተረጉሙት: አባ ጳውሎስ ለጀመሩት ሊቃውንትን የማባረርና የማሳደድ ተግባር በወያኔ ድጋፍ ጳጳሳትን ሲደበድቡ: ሥርዓተ-ቤተክርስቲያን: ሕገ-ቤተክርስቲያን ሲደፈርና ሲጣስ: ቤተክርስቲያናትና ገዳማት ሲቃጠሉና ሲዘረፉ: ምእመናን ሲሰየፉ እያየን እንዳላየን ሁነን ቆየን::

አሁንስ አባ ጳውሎስ በአደባባይ መናፍቁን ጌታቸው ዶኒን ሲሾሙ የአዋሳ አካባቢ ሕዝበ-ክርስቲያን በጽናት ባይታገል ኖሮ እንደተሾሙ አይቀሩም ነበር? የጌታቸው ዶኒን ከስልጣን መሻር አባ ጳውሎስ ሲቃወሙ እርሳቸውስ መናፍቅ መሆናቸውን ወይም ኦርቶዶክስን ለማፍረስ እንደተሰለፉ አያስረዳም??? ሌላ ምን ማስረጃ ይጠበቃል??? እስከመቸስ ነው ዝምታው???

ሁሉን ማድረግ የማይሳነው አምላክ እግዚአብሔር እውነቱንና ፍርዱን ሳይዘገይ ይግለጥ !!!

Dn Haile Michael said...

በወቅቱ የቤተክርስቲያን ችግር አቡነ ጳውሎስን ሳያስወግዱ ችግሩን እፈታለሁ ማለት ልክ የማብራት አደጋ ስነሳ master switch ሳያጠፉ እያንዳንዱን መስማር በመቁረጥ አደጋውን እከላከላለሁ ማለት ነው ::ይህ ደግሞ አደጋውን መከላከል ከለመቻሉም በላይ ሌላ ተጨማሪ አደጋ ያስከትላል ::አሁን በቤተክርስቲያን እያየን ያለውም ይህንን ነው ::
አቡነ ጳውሎስ ‘ተሐዲሶ የለም” ከሚለው ዓይነን ግንባር ያድርገው ዓይነት አቁዋማቸው በተጨማሪ ለ”ተሐዲሶዎቹ” ድጋፍ በማድረግ ተሐዲሶ አለ የሚላውንና የሚያጋልጠውን ለማሰጣት ጥረት እያደረጉ ነው ::የቤተክርስቲያኒቱ ትልቁ የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስም ጥርስ የሌላው አንበሳ ከሆነ ቆይቶአል ::
ስለዚህ አሁን መወያየት ያለብን አቡነ ጳውሎስን እንዴት አስወግደን ቤተክርስቲያንን ከተደቀነባት አደጋ እንታደግ በሚለው ነው :: ከዚህ ቀጥሎ ያለውን እንደ መነሻ በጥቅሉ እነሆ
1 .በቅድሚያ ምዕመናን ሁሉ በቤተክርስቲያን ላይ ስለ ተጋረጠው አደጋ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መረጃ በማዳረስና በመግለጽ መሥራት
2. ይህ ሁሉ ከተደረገ በሁዋላ ምዕመናን በተወካዮቻቸው የአቡነ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን የማዳከም ሤራ በዝርዝር ለመንግሥት አካላት በመግለጽ ጉዳዩ የሃይማኖት እንደሆነና ቤተክርስቲያናችንን የመታደግ ጉዳይ ስለሆነ መንግሥት ሲሆን ድጋፍ እንዲያደርግ ሳይሆን በጭፍን አቡነ ጳውሎስን ከመደገፍ እንዲቆጠብ
3 ምናልባት መንግሥት ከዚህ በሁዋላ አቁዋሙን የማይቀይርና አቡነ ጳውሎስን የሚደግፍ ከሆነ ለሰማዕትነት መዘጋጀት ነው

ዘሐመረኖህ said...

ቀሲስ ወንድምስሻ ቃለ ሕየወት ያሰማልን ዲያቆን ኃይለ ሚካኤል ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ ጥሩ ነው በሳቸው ላይ አንዳንድ ሃሳቦች ታክለውበት በአፋጣኝ ወደ ድርጊት የምንገባበትን መንገድ ደጀ ሰላምና መሰል የመገናኛ ብዙሃኖች እንድታስተባብሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ እግዚአብሔር ይርዳን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)