June 15, 2011

አትሌት ኃይሌ የለንደን ኦሊምፒክ ማራቶንን ካሸነፈ ሽልማቱን ለገዳም እንደሚሰጥ ቃል ገባ

(ዘሪፖርተር ጋዜጣ/ Wednesday, 15 June 2011):- አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደውን የለንደን ኦሊምፒክ ማራቶን ካሸነፈ የሚያገኘውን ሽልማት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኘው ጥንታዊው የአቡነ መልከ ጸዴቅ ገዳም በስጦታ እንደሚያበረክት ቃል ገባ፡፡


ከጥቂት ሳምንታት በፊት ገዳሙን የጎበኘው ኃይሌ በገዳሙና በገዳሙ ቅርሶች እጅግ ተደምሟል፡፡ በተለይ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት በገዳሙ የተቀበሩ አስከሬኖች ሳይበሰብሱና ሳይፈርሱ መቀመጣቸው አስገርሞታል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ያልተጎበኙ ቦታዎች አሉ፡፡ በዚህ ገዳም ለብዙ ዓመታት ሳይፈርሱ የተቀመጡ አስከሬኖች ይገኛሉ፡፡ ይህ ከሳይንቲስቶች ምላሽ ያልተገኘለት ነው፡፡ እኔ እጅግ ደንቆኛል፤ በማለት በገዳሙ መደነቁን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

የአቡነ መልከ ጸዴቅ ገዳም በዞኑ ሚዳ ወረሞ ወረዳ ውስጥ ስራቲ ቀበሌ ይገኛል፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ ተራራማና በግዙፍ ቋጥኞች የተከበበ ሲሆን፣ ገዳሙም የሚገኘው በተራራማ ቋጥኝ ሥር በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ነው፡፡

ሪፖርተርም ማየት እንደቻለው በገዳሙ ውስጥ የሚገኙ አስከሬኖች አልፈረሱም፡፡ አፈር አልበላቸውም፡፡ ኃይሌም ሁኔታው አስደንቆት ለንደን ማራቶን ላይ ካሸነፈ ለገዳሙ ወርቁን እንደሚያበረክት ቃል ገብቷል፡፡

የዚህ ጥንታዊ ገዳም ቤተክርስቲያን በአሁኑ ወቅት ሕንፃው ከእርጅና ብዛት ፈርሶ በአዲስ መልክ እየተገነባ ነው፡፡ ይሁንና የተሠራበት የኮንስትራክሽን ግብዓት ጥንታዊነቱን የሚያንፀባርቅ ሳይሆን የአሁኑን ዘመን ጥበብ የተላበሰ ነው፡፡

ባለሙያዎች፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ  ባለሥልጣን በጉዳዩ ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለበትና በተቻለ መጠን የጥንቱን ይዘት ባልለቀቀ መልኩ መሠራት እንደሚኖርበት ይጠቁማሉ፡፡

በውድነህ ዘነበ
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)