June 9, 2011

የተወደዳችሁ የ ቪኦኤ አዘጋጆች

(ጸጋ ብሩክ ነኝ ከአሜሪካ):- የፕሮግራማችሁ የዘወትር ተከታታይ ነኝ:: ስለዝግጃትችሁ ሁለ ገብነት እና አስተማሪነት ሁሌም ቢሆን በልበ ሙሉነት የምመሰክረው ሃቅ ነው:: በ6/08/2011 ዝግጅታችሁ ላይ አለማየሁ ከተባሉ አድማጭ የተላከ መልዕክት ብላችሁ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ያስተላለፋችሁት መልዕክት ግን እጅጉን አሳዝኖኛል:: ደብዳቤው የያዘውን ጭፍን ወቀሳ እና ክስ፣ ጭብጥ የሌለው በማስረጃ  ያልተደገፈ አስተያየት ምንም ሳትመዝኑና የሚመለከተውን ወገን ለጥያቄ ወይንም ላስተያየት ሳታዘጋጁ የዚህ ማኅበር አባልና ደጋፊ የሆኑ አድማጮቻችሁን ከግምት ሳታስገቡ በማቅረባችሁ ምንም እንኳን የጋዜጠኝነት ሙያ ባይኖረኝም እጅግ  ስህተት እንደሰራችሁ ይሰማኛል::

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የማውቀውን ያህል ለመናገ እና ለመመስከር ያህል፣
ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እኔን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ብዙ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጣትነት ሊያጋጥማቸው ከሚችል የአፍላነት ፈተና በመታደግ ወደ ክርስትና  እንዲመለሱ ያደረገ፣ ወጣቱ ትውልድ ዲግሪ፣ ዲፕሎማ ይዞ የቤተክርስቲያን አስቀዳሽ፣ ዘማሪ፣ አገልጋይ መባልን እንደ እፍረት ሳይሆን እንደ ይወት መርህ አድርጎ እንዲይዝ ያደረገ፣ መቀደሻ ጧፍ ጣን አጥተው ሊዘጉ የደረሱ ገዳማት እና አድባራትን በልማት ራሳቸውን እንዲችሉ እያደረገና  ከተመጽዋችነት ያወጣ፣ አገልጋይ አባላቱ ዛሬ ዛሬ እንደተነሱት በየከተማው በሁለትና ሶስት መኪና እየተንደላቀቁ ይሄን ያህል ካልተከፈለን ጉባኤ ላይ አንገኝም ሳይሉ በእግር እና በፈረስ ይወታቸውን ሰውተው ለወንጌል አገልግሎት የሚተጉ፣ ከቤተክርስቲያን ተወልደው የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ እና ቀኖና እናድሳለን ከሚሉ ወገኖች ጋር ታግሎ የቤተክርስቲያንን ህልውና ለማስጠበቅ ከአባቶቹ የተሰጠውን አደራ በተለያዩ  ጊዜ በመፈጸም የቤተክርስቲያን ህልውና  እንዲጠበቅ ያደረገ ማኅበር ነው::

አቶ አለማየሁ የተባሉ አድማጫችሁ ያነሱትን ነጥቦች መሰረት ቢስ መሆናቸውን ለማየት ያህል:-
በአገር ውስጥ ያሉትን ጳጳሳት የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ እና ተቃዋሚ በማለት ማኅበሩ ለሁለት እንደሚከፍል የተናገሩት ንጭዎ ምን እንደሆነ ባላውቅም ማኅበሩ ደጋፊ እና ተቃዋሚ ብሎ ያሰለፋቸው ጳጳሳት የሉም እርስዎ እንዳሉትም ጳጳሳት በሲኖዶስ እንዲጨቃጨቁ የማድረግ ማኅበሩ ልጣንም አቅምም የለውም። በተለያዩ  የማኅበሩ ሚዲያዎች ላይ እንዳነበብነው ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድ ትልቅ የአገልግሎት ማኅበር እንደመሆኑ መጠን ለራዬ እንቅፋት ሆነውብኛል ያላቸውን የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ላፊው የአባ ሰረቀን ጉዳይ እልባት እንዲያገኝለት ለቅዱስ ሲኖዶስ በጽሑፍ አቅርቧል ቅዱስ ሲኖዶስም ጥያቄውን ተቀብሉ አጣሪ ኮሚቴ ሰይሟል:: ከዚህ በቀር ግን በዜናዎች ላይ እንዳነበብነው እና ከአባቶች እደተረዳነው ሁሉም አጀንዳ የቀረበው እና የሲኖዶስ አባላት የተወያዩት በቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ት እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን በሰጣቸው መመሪያ አይደለም::

ስለ ደጀ ሰላምም አንስተዋል፣ ክስዎ ደጀ ሰላምን ከሆነ በደጀ ሰላም ላይ የሚወጡትን ጽፎች መተቸት ይችላሉአስተያየትም መስጠት ይችላሉ:: ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን ነው ለሚለው ድምዳሜ ማስረጃዎ ምን እንደሆነ ባላውቅም፣ እንደኔ እንደኔ ደጀ ሰላምን ልክ እንደ አንድ የመረጃ ምንጭ በማየት የሚጠቅመንን በመውሰድ ትክክል ያልመሰለንን ደግሞ አስተያየ በመስጠት ወይንም ባለመቀበል ልናልፈው ይገባል እንጂ የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ከደጀ ሰላም ጋር በማያያዝ እልህ መወጫ ማድረግ ግን ተገቢ አይመስለኝም::  አቶ  አለማየሁ ቅንነቱ ካለዎት በተለይ እንዳሉት አዲስ አበባ ካሉ ለምን የማኅበሩን አገልግሎት በየገዳሙ እና በየአድባራቱ እየሄዱ አያዩም ምን አልባት ገዳማቱ እና አድባራቱ እንዲኖሩ ከማይፈልጉት ወገን ካልሆኑ በማኅበሩ ስራ እጅግ እረክተው ይህን ደብዳቤ በሌላ እንደሚተኩት እርግጠኛ ነኝ::

አቶ አለማየሁ የቤተ ክርስቲያንንም መዋቅር የሚከሱትንም ማኅበር መዋቅር በቅጥ የሚያውቁት አልመስለኝም፣ በአንደኛው ክስዎ ላይ ማኅበሩ የሰንበት ትምህርት ቤት አባል አይደለም ሲሉ ይሰማሉ፣ የሰንበት ት/ቤት አባል የሚሆ ነው እኮ ግለሰብ ነው እንጂ ማኅበር አይደለም። ማኅበሩ ይህን ከርስዎ  የተሻለ ስለተረዳ የማኅበሩ አባላት የሆኑ ግለሰቦች በማኅበሩ አባል ሆነው ለማልገል በየአጥቢያ  ቤተ ክርስቲያናቸው የሰንበት ት/ቤት ወይንም የሰበካ ጉባኤ አባል የመሆን ግዴታ አለባቸው::

ማኅበሩም የራሱ ቃለ አዋዲ እንዳለው ጠቅሰዋል፣ ይሄ በሬ ወለደ ስለሆነ ለማስረዳትም ጭብጥ ስሌለው አልፈዋለሁ:: ግለሰቦችን ተሃድሶ  እና ጴንጤ እያለ ስም ሲያጠፋ በተጨባጭ በሊቃውንት ጉባኤ ሳይሆን በእኔ ስም ማጥፋት ይወገዙልኝ ይላል  ያሉት ግን እጅግ መሰረተ ቢስ ነው:: እኔ እስከማውቀው ማኅበሩ በ1990 ዎቹ መታት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ እና ቀኖና አፋልሰል ያላቸውን ያቀረበው ለሊቃነ ጳጳሳት እና ለቤተክርስቲያን ሊቃውንት ሲሆን እንዲወገዙ ወይንም በቀኖና ቤተክርስቲያን እንዲመለሱ ያለው ማኅበሩ ሳይሆን የሊቃውንት ጉባኤ ነው:: የማኅበሩ ድርሻ መረጃዎችን አቀነባብሮ ለቤተክርስቲያን አባቶች ማቅረብ ነው:: እርስዎ ድንገት ቢያስቡት ይህ ማኅበር እኮ  ብዙ የተማሩ የግ እና የአሰራር ባለሙያዎችን የያዘ ነው፣ እነ እከሌ ስሜን አጥፍተዋል ይወገዙልኝ ብሎ  የሚደክመው የትኛው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ጆሮ ሰጥቶ እንዲሰማው ነው? ነገሩ ለየቅል ነው፣ የማያራ ውስጥ በመግባት ለመዳከር ማኅበሩ ጊዜ ያለው አይመስለኝም:: በነገራችን ላይ፣ በአሁኑ ሰዓት ማኅበሩ ማንንም ተሃድሶ ብሎ አልወነጀለም ግን ሁላችንም እንደምረዳው ቤተ ክርስቲያን በጥቅም እና በእናድሳላን ባይ ወገኖች እየታመሰች እንደሆነ እያየን ነው:: በዚህ ጊዜ ማኅበሩ ዝም ብሎ ይቀመጣል የሚል እምነት የለኝም:: እርስዎም እሱ አስፈርዎት ከሆነ  መፍትው ንስሃ መግባት እንጂ እውነትን ጥላሸት በመቀባት የቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን ማምታታት  አይደለም::

አቶ አለማየሁ፣ ማኅበሩ በኢትዮጵያ እና ውጪ ባለው ሲኖዶስ መካከል እርቅ እንዳይፈጸም እንቅፋት እንደሆነ አንስተዋል፣ እንዳሉት ኢትዮጵያ  ካሉ የአሜሪካውን ችግር በደንብ ላይረዱት ስለማይችሉ አስተያየት ባይሰጡ ጥሩ ነው:: ማኅበሩ በሁለቱ አባቶች ያለው እርቅ እንዲሰምር በሽምግልና ከሚደክሙ አባቶች እና ወንድሞች ጋር ያቅሙን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ነው:: ይህን ለበለጠ ለመረዳት የሽምግልና ኮሚቴውን ማነጋገር በቂ ይሆናል::

ማኅበሩ በሁሉ ቦታ ላይ መግባቱ እንዳሰሰብዎትም ይገልጻሉ በጽሁፍዎ፣ የማኅበሩ አገልግሎት መስፋት እጅግ ካሳሰብዎት ያ እንግዲህ የተመሰረተበት ላማ ነውና አሁን ብንከራከር ምንም አንፈይድም:: ግን መንግስት ወይንም ቤተ ክርስቲያን አንድ እልባት ሊሰጡ ይገባል ላሉት ግን፣ መንግስት ለአገር እና  ለወገን የሚያስብ ከሆነ ይሄ ማኅበር ብዙ ጥሩ ዜጋዎችን ያፈራ ደሃ የሚበድሉ ሳይሆን ለድሃ  የሚያዝኑ፣ ጉቦ የሚቀበሉ ሳይሆን ለተቸገሩ የሚለግሱ፣ ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ እንጂ እኔ ምን ገዶኝ የሚሉ ሳይሆኑ ለሃገር ለወገን የሚያስቡ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያላቸው ዜጋዎችን ያፈራ ማኅበር ስለሆን በእንክብካቤ ሊይዘው ይገባል ባይ ነኝ:: ቤተ ክርስቲያንማ እንደሚያስፈልጋት አምናበት መተዳደሪያ  ደንብ ሰጥታው ከሯ ይዛዋለች::

ኅበሩ በቃለ አዋዲ እንደማይመራ ደጋግመው ሲጠቅሱ ሰምቻለሁ ግን ማኅበሩ እኮ የሚተዳደረው በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀለት የራሱ የመተዳደሪያ ደንብ ነው:: ከመክሰሰዎ በፊት ማኅበሩ የሚተዳደርበትን ደንብ ቢያዩ ና እየሰራ ያለውን ነገር ከመተዳደሪያው አንጻር ቢገመግሙ ገንቢ አስተያየት ለመስጠት የሚያግዝዎ  ይመስለኛል::

ለአቶ አለማየሁ የምሰጠውን አስተያየት በዚህ ላብቃና ቪኦኤዎች ግን የሚመለከተውን ሁሉ በማነጋገር ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በማስረጃ የተደገፈ ዝግጅት ብታቀርቡና አደማጮቻሁ እውነታውን ቢያውቁ ጥሩ ነው እላለሁ::
ሠላም ሰንብቱ!!
ጸጋ ብሩክ ነኝ ከአሜሪካ
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)