June 8, 2011

ስምዐ ጽድቅ ታተመች

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 7/2011)፦ ከሥርዓት ውጪ በተደረገ ደብዳቤ እና የስልክ ልውውጥ ሕትመቷ ተስተጓጉሎ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጋዜጣ ስምዐ ጽድቅ በዛሬው ዕለት በሌላ ማተሚያ ቤት ታት መሠራጨ ጀምራለች። ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በመታተም በሕትመት ብዛት እና ረዥም ዓመታት በማሳለፍ ቀዳሚ የሆነው ይህ ጋዜጣ ለብዙ ጊዜያት ያለመታተም እንቅፋት ቢገጥማትም እንደ አሁኑ ከፍ ያለ ፈተና እንዳልደረሰት ምንጮች አስረድተዋል። ብዙዎች ምዕመናን “መምህራችን” የሚት ጋዜጣ መቋረ በደጀ ሰላም ከተዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱን የተረዳን ሲሆን ቤተ ክህነቱ አሁን በያዘው መልኩ የሚሔድ ከሆነ ምዕመናን የራሳቸውን መፍትሔ ወደ መፈለግ እና በደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንደታየው ዓይነት “ጉልበት ወደ መጠቀም” የመሰለ አላስፈላጊ መፍትሔ እንዳይዘዋወሩ አስግቷል።

78 comments:

Anonymous said...

elelelelelelelele
Temesgen Geta hoy!!!

samueldag said...

አምላከ፡ቅዱሳን፡ምስጋና፡ይድረሰው፡፡አሜን

Anonymous said...

egziyabher yetemesegene yihun . eskahun altegnahum neber 10 gize yihonal websaitun semeleket bestemecheresha eneho yemeserach alachihun betam tedesechalehu belu ahun litegna yekedusan amlak betekerestyanachinen yitebeklen amen!!!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

እስቲ አንድ መናፍቅ መነኩሴ ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈፅም ቁጭ ብለን መጠበቃችን ምን ይባላል?
ክርስቲያኖች እንሁን! ሰማዕትነትን ለመለማመድ ለእውነት ያለፍርሀት እንቁም! ፍርሀት እኔስ በቃኝ፡፡

tadessse said...

የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስግን! ስምዐ ጽድቅ ታተመች!!!

Anonymous said...

This is more than ከፍተኛ ቁጣ . I will fight to death when it comes to my faith and I do not care about any one's politics. Do not touch my teacher and food ስምዐ ጽድቅ . Do not toch my religion. Government should also know the danger that comes from such situation and fix the problem to the interest of the laity (mihimen).

May God bring his peace to our mother church.
Dani

Anonymous said...

መንግስት በሰረቀ አይነት ከይሲዎች እና በአባ ፓውሎስ አይነት የሙስና ቁንጮ እየተታለለ በሕዝብ ዘንድ የሚጠላበትን ዶሴ ማብዛት የለበትም:: የመንግሥት ደህንነት መስሪያ ቤትም ስራው እንድህ አይነት ቀጣፊዎችን መንግሥታቸውን በተሳሳተ ሁኔታ እየተጠቀሙበት መሆኑን መመርመር ነው እንጅ:: ነገር ግን እነ ፓውሎስ ከመንግሥት በላይ ስለሚከፍሉ ተዘናግተው ይሆናል:: ለማንኛውም መንግሥት መንግሥትን ሁነህ ተገኝ እላለሁ::

Anonymous said...

ቸር ወሬ ያሰማልን !

leba(sereke) never wins said...

They better do the rt thing. Ato Melese better watch those who mess up our churchs i do not care abt poltics but i do for my church

Anonymous said...

Qele Hiwotin Yasemaln
KeVienna

Anonymous said...

God is great,we will win.

yemelaku bariya said...

የመለስ የቅርብ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ምን ያክል ኃላፊነት የጎደለው እንደነበር የምታስታውሱት ነው "በኃይማኖት ድርጅቶች ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና አስመልክቶ " የሱ ቅድሚያ በመንግሥት መዋቅር ላይ ያለውን ነው ግን እዚህ እኮ እየተፈጸመ ያለው በመንግሥት ከምዝበራ እጅጉን ይልቃል እና አሁንም መንግሥት የማስፈጸም አቅም ችግር ካለበት አቅሙን ማጠናከር ይጠበቅበታል ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያለፈውን መልሳቸውን ቢያሻሽሉ ይሻላል:: ሙስናን በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የመንግሥትም ይሁን የግል ወይንም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ ሁሉ መዋጋት ያስፈልጋል:: ይህ ካልሆነ ግን ወይ እያየን እየተመዘበርን መኖር ካልሆነ ደግሞ ንብረታችንን ኃይማኖታችንን እና ማንነታችንን ማስከበር የግድ ይለናል እና እነ አባ ፓውሎስ ይህ ህዝብ ከተነሳ ወየውልዎት እርስዎን ሳይሆን በእጅዎ ያለውን መስቀል አክብሮ ነው::

Anonymous said...

TEMESGEN...WEY ABA SEREREKE.
Yeaba Sereken Yemecheresha eta Fenta Yakiriblin

Anonymous said...

የሀይማኖታችንን ነገር ለድርድር አናቀርብም::
alex

Anonymous said...

Come on guys, by prohibitng publication of ስምዐ ጽድቅ, they (the Serekes group) are testing our level of confidence and courage to confront them. If they are successful with this, they will move to the highest level such as closing gedamat and adbarat, sunday schools, and blocking any spiritual services. Therefore, we shall act boldly right now.
The government should also be aware of any consequences that comes from such kind of moves. There is no deal in our faith, no deal on my religion. I do not touch others and others should not touch mine.
Government: if u do not want to mess up with your power and stability, take a big measure on those corrupted guys like Sereke, Ejigayehu, and their teams.
Government, I advise to think twice regarding your security guys. They are also highly corrupted, they are not doing what they are supposed to do....and this costs you alot by detaching you with the people. I can post their names online with a good evidence if you want.

Take care and we all are at the point of no return.

Tatek

henon said...

temesgen 1 selam eleki beente mahibere kidusan sirawan gemerech.

Anonymous said...

ስምዐ ጽድቅ ተሐትመት እንዳንሆን

Anonymous said...

Thank god for all this. Amlake qidusan yetemesegene yihun. Ahunim egziabhier haymanotachinin yitebkal. Emebetachin qdist dingil maraim yeasrat hagerua yehonechiwin ethiopian ena haymanotuan titebkalech. Let us all pray for our holy mother church. god protect our religion.

AGNATIWOS THE GASCHA said...

THIS IS WHAT WE NEED TO HEAR. OUR CHURCH WILL NEVER BE THE CAVE FOR DEVIL PEOPLE, LIKE SEREQE. WE NEED TO CONTINUE CLEANING OUR CHURCH AND OUR FAITH FROM THOSE HERETICS AND DECEPTIVES. MAHABERE KIDUSAN IS FORMED BY THE WILL OF GOD,THEREFORE NOBODY CAN SHAKE IT.
GLORY TO GOD .

Anonymous said...

Aye Sereke Alarfe Yaleche Tate/////

Anonymous said...

A YE SELAM AMELAK LIUL EGZIABHER HOYE MELKAM YEHON NEGER HULU KANTE NEWENA MELKAM /SENAY/ ZENA ASEMAN AMEN.

Anonymous said...

ተመስገን

Anonymous said...

First of all I thank God for his work;
some of us are trying to be politically correct when we say "መንግስት በሰረቀ አይነት ከይሲዎች እና በአባ ፓውሎስ አይነት የሙስና ቁንጮ እየተታለለ በሕዝብ ዘንድ የሚጠላበትን ዶሴ ማብዛት የለበትም"
I think Meles and his friends Paul and Serke are trying to intimidate an organization in their eyes poses threat to their respective powers. it is politics, I feel sorry for the poor Tigrians in their name these thugs are playing dirty games.

Anonymous said...

በጣም ደስ ይላል። እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን። ነገር ግን ስምዐ ጽድቅ ታተመች ማለት ፈተናዉ አበቃ ማለት ስላልሆነ እነ "አባ" ሰረቀን ከጥፋታቸው እንዲታረሙ የምናደርግበትን መንገድ ሁላችንም እናስብበት። እንዳንዘናጋ እነሱ ሌላ ሴራ ከመሸረብ ወደኋላ አይሉም። ነቅተን ቤተክርስቲያናችንን እንጠብቅ። እግዚአብሄር ይርዳን።

Haimanote said...

God is Present.
(AGE)

ßuruk-USA said...

Now MahibereKidusan Should Move on Processing 2 Establish His Own Printing Enterprise!
No time 2 think!
Just ßring z issue on z website, Some1 'll do it!!!
(Buruk-USA)

Anonymous said...

Thnxs 2 GOD.
By z way i don't know z no of persons following this Current Faith issues.
We Should Exchange informations on Mobiles also.
Like 4 example 'read this & that paper'
'Visit Dejeselam' etc

Anonymous said...

amlakachin eyasayehen new.enamesegnihalen ahun degmo bebytehe yalutin fire yemayaferutin astagsilin bicha sayhon yemenfesihin fire betikikil enditekemu adirgilin

Anonymous said...

hulachihum balachihubet begeza betachin libachinin yademutin befikir tenekitual enibelachew min yasferanal zare egna endezi zim kalin nege lig lijochachin yeethiopia orthodox betekiristianin sayhon lela new yemirekebun yeagere lig tseliyina tenes amlak yiketelihal

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን መልካም ዜና ነው።ግን እዚህ ግባ የማይባል ተራ መለኩሴፊት መስጠት አያስፈልግም ፤፡፤ለመሆኑ እርሱ ማነው። ሲያዩት ራሱ ሌባ ፊት ነው ።ከዚህ እስከ ሞያሌ ፊት ምን ይመስላል ይሄ ጦጣ ፊት;።

Anonymous said...

bekirbi ken yetehadiso sibseba alebachew lereportachew gibiat neber altesakam

አንድነት ለተዋህዶ said...

እልልልልልልልልልልል!!!!!!!!!!!!!!
ሰይጣን አፈረ!!! ገና ያፌራልም!!!
የክፉ ስራ ጭንቅላቶች ሆይ ተመለሱ እውቀትን ልበሱዋት ራሳችሁን አትካዱት!!!

አምላከ ቅዱሳን ምስጋና ይገባሃል!

Anonymous said...

With God everything is possible. Let us be strong. We should see the root cause of the problem not the symptom.We need to be united so that God will work through us.I now understand who is good and who is bad. Mahibere kidusan be firm.You are the one for our Church. With the will of God, I will be a member and recieve the merits of the blessing of God with you.

Anonymous said...

እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን
ዲያብሎስ አፈረ!
የእመቤታችን ምልጃ የቅዱሳን በረከት አይለየን::

Anonymous said...

በጣም ደስ ይላል። እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን።
ላዕከ ኢየሱስ ነኝ::

Anonymous said...

እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን
ዲያብሎስ አፈረ!
የእመቤታችን ምልጃ የቅዱሳን በረከት አይለየን::
Laek Eyesus

frew said...

egziabiher yimesgen!

Anonymous said...

Cherinetun kegna yalareke Amlak yimesgen!! Good news that compensated our sadend heart from yesterday

Now we have alot of home work. We shouldnt spend time. We have to face Sereke and his colleagues until they are cleared from there

Anonymous said...

Are we kids? We haven't yet solved the ROOT problem yet! Why are we satisfied with this????

Lets not lose sight that the ROOT problem of the Church is Abune Paulos and his junta, sereke! Please lets do by any means to remove him from power. Abune Paulos is not doing any good thing for Tewahido anymore. He is always sponsoring those who are against Our Church!

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይመስገን። ግን እስከመቼ? ለምንድነው ማህበረ ቅዱሳን በሃገር ውስጥም በውጭም ያሉትን ማዕከላት በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ የማያደርገው? እነዚህ መነኮሳት ተብዬዎች ቤተክርስቲያኒቱን ጥለው መውጣት አለባቸው። ለዚያ ደግሞ መፍትሄው ከጸሎት ጋር ለአለሙ ህብረተሰብ ድምጽን በማሰማት ይመስለኛል። ሲኖዶሱም ሆነ የተቋቋመው ኮሚቴ ፋይዳ ይኖረዋል ወይንም ደግሞ እነዚህን ሰዎች ያስወግዳል ብዬ አላስብም። የሲኖ ዶስ የበላይነት ባልታየበት ባልተከበረበት ሁኔታ እንዴት ኮሚቴው ውጤት ያመጣል ብለን እንጠብቃለን።

Abel said...

መታተሟ ያስመሰግናል። በቤተክርስቲያናችን የተደቀነው አደጋ ግን አሁንም እንዳለ ነው። መንግስት አንድ ሊለን ይገባል። እኒህ ግለሰቦች የገንዘብ ወይም የእውቀት አቅማቸው አይደለም የልብ ልብ ሰጦ በአደባባይ ሃይማኖታችን እያዋረዷትና የቅርምት ሴራቸውን የሚያራግቡት። መንግስት እኛን ይደግፋል ብለው ስለተማመኑ ነው። መንግስት የሚለውን ሁሉንም ነገር ከተቀበልነው ከማንኛውም ጥፋታችን ስራችን ከለላ ይሰጠናል ብለው ነው። ለዚህ ነው የማትደፈረውን ርዕትዕት ሃይማኖት እንዲህ ቅጡ እስኪጠፋቸው የሚያብጠለጥሏት። ይህን ሴራቸውን መንግስት ተረድቶ ሊያስቆማቸው ይገባል። ከነዚህ ሰዎች ጀርባ ያለው ጥቂት ባለጥቅመኛ ብቻ እንደ ሆነ ሊያውቅ ይገባዋል። ብዙሃኑ ምዕመናን ሁኔታውን ባንክሮ እየተከታተለ እንደሆነ መገንዘብ አለበት። እናም ሁኔተታው ከቀጠለ ሃይማኖቱን ለመታደግ ሕዝቡ ሆ ብሎ ከተነሳ በዃላ ለማረጋጋት ይቸገራል። ስለዚህ፡-
1. በአዋሳ ላይ ላደረሱት ጥፋት ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት
2. ሕዝቡን የሚያሳዝኑ የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋዮች አስፈላጊ የሆነውን ምክር መስጠት ይኖርበታል
3. እውነትን ለማፈን የሚሯሯጡ ግለሰቦችን በደህንነቱ በኩል ሊያስታግስልን ይገባል

ይህን ለማድረግ የተሳነው መንግስት ለእኔ መንግስት ሊሆን አይችልም። ሌላ ነገር አልጠየቅንም የሃይማኖታችንን ነጻነት። አገታችን ቀና አድርገን እንድንሄድ ያደረገችንን ርትዕት ሃይማኖት ለማንም ወሮ በላ አሳልፈን አንሰጥም። የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ--እንደ ሰረቀ አይነቶች ተሰደብን ይሉናል። እዉነትን ቢመሰክሩና ስለ ክርስቶስ ብለው ለእውነት ቢቆሙ ማንም አይሰድብዎትም። ሁሉም ከጎንዎ ነው። ስለዚህ ለምን ወቀሳ በዛብኝ ብለው እራስዎን ይጠይቁ። ይህን ማድረግ ካቃትዎ ይጸልዩ። ይህም ካልሆነ ስነ-አእምሮ ሐኪም ጋ ሂደው ሁኔታውን ያማክሩት። እውትን ሳይደብቅ ይንገሩት። የመፍትሔ ሐሳቦችን ያስጨብጥዎታል።
ልብ ይስጣችሁ።
አምላከ ቅዱሳን ሕዝባችን ሁሉ ነገር ሳይሟላለት የሚያመሰግንባት ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን። ጌታ ሆይ ጠብቋት ያልሃቸው ባለ አደራዎች አዚም ተጭኗቸዋል። ሊሰሙን አልቻሉም። ና ታምርህን ስራ።

Desalegn said...

ሰይጣን አፈረ! ሰረቀም ከሰረ! እግዚአብሔር በየትኛውም መንገድ የሚሰራውን ስራ ይሰራል:: ብዙ ምዕመናን በብስጭትና በሀዘን ላይ ሳሉ የስምዓ ፅድቅ መታተም የልብን ስብራት ጠግኗል እግዚአብሔር ይመስገን::
Desalegn

Anonymous said...

ይህ ሁሉ እኛ እንድንጠነክር እኛ እንድንበረታ ሆነ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሄር ሆይ ክብር ምስጋና ይግባህ ሲጨልምብን ታነጋልናለህና

Desalegn said...

ሰይጣን አፈረ! ሰረቀም ከሰረ! እግዚአብሔር በየትኛውም መንገድ የሚሰራውን ስራ ይሰራል:: ብዙ ምዕመናን በብስጭትና በሀዘን ላይ ሳሉ የስምዓ ፅድቅ መታተም የልብን ስብራት ጠግኗል እግዚአብሔር ይመስገን::

Anonymous said...

belwo legiziabher grum gbre.
May God Bless Ethiopia & May Angles protect our religion.
Yedingil milja ayleyen.
AMEN!!!

Anonymous said...

ሰረቀ አላማህ ታውቆብሃል… የመውጊውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል… ከነጭፍሮችህ ልብ ይስጥህ!

kal said...

amlake kidusan yetemesegene yihun bechinketachin hulu esu mels alewu yetamenewu amlak esu egna yeminamnewu kedingil yeteweledewu ena motin betensaewu yesharewu wedesemayim yaregewu amlak eko zim belo betecherestiyanen almeseretatim bedemu enji yewajat.

Silase yimesgen zarem negem wedefitim yetelatin sera yafersal bechinketachin hulu yidersal yidresilenim!!!

gammachiis said...

good news!!!mkidusan.org said >ለማስተጓጎል ተሞክሮ የነበረው የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ እትም ስርጭት ላይ ዋለ።> thank you dejeselam.

Wesebhat LeEgziabher said...

መልካሙን ዜና ለመስማት ያበቃን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!
እንደ ስምዓ ጽድቅ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ስርዓት በማስተማር ቀዳሚውን ስፍራ
የሚይዙ ጋዜጦችን ማገድ የቤተ ክርስቲያንን ልሳን ለመዝጋት መሞከር ነው:: ስምዓ ጽድቅ እንደስሟ
እውነትን የምትናገርና እውነትን የምትመሰክር በተቃራኒው ደግሞ ሀሰትንና ሀሰተኞችን የምትገስጽ
ስለሆነች ማንም እውነትን የሚከተል ሰው ሊጠላት አይችልም:: እሷን የሚጠሉ ጎራቸው ከየት እንደሆነ
መረዳት ከባድ አይሆንም::

ጋዜጣዋን ከምዕመናን ጉያ ለመለየት በ"አባ" ሰረቀ የተደረገው ጥረት የሰውየውን አምባገነንነት ቁልጭ
አድርጎ የሚያሳይ አጋጣሚ ስለሆነ ደስ ብሎኛል:: የሚያሳዝነው ግን ማተሚያ ቤቱ አንድ ግለሰብ የጻፈውን
ደብዳቤና የስልክ ትዕዛዝ ተቀብሎ ላለማተም መወሰኑ ነው:: እንዲህ አይነት ትልቅ የማተሚያ
ድርጅት ሕግና ስርዓት ባለበት አገር በአንድ ሰው ፍላጎት መገዛቱ በጣም ያሳፍራል::

ለመንገዳችን ብርሐን የሆነውን መልካሙን የወንጌል ቃል የምታሰሚን ስምዓ ጽድቅ ሆይ ምንም
እንኳን ጠላቶችሽ ቢበዙም እግዚአብሔር ኃይልሽ ነውና ደስ ይበልሽ!

Anonymous said...

aba pawlos, sereke, ato begasshaw ena seitanawyan hulu woyolachihu.

gmt from Dilla said...

እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል
አምላካ እስራኤል ለንተ ምን ይሳነሃል ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን
በአማለጅነትሽ የልተለየሽን ድንግል ማሪያም ሆይ ምስገናን ይገባሻል
ትላንት ጩህ ጩህ ነበር የሰኛኝ እጅግ አዝኜ ነበር፤ ዘሬ ግን ተጽናነው እግዚአብሔር ይመስገን
አሁንም ግን ዘለቂ መፍትሔ እንፈልገለን አበቶቻችን ሆይ ስለእግዚአብሔር ብላችሁ የአበሰረቀንና የአቡና ጳውሎስን ግፍና በደል ዝም አትበሉ ተሪክ ልበለሽ ነው፤ቤተክርስቲያን ልትወረስ ነው ዝም አትበሉ ከአቅመችሁ በላይ ከሆነ የለችሁት እውነተኛ አበቶች እንዳ አቡነ ሽኖዳ ጥለችሁ ገዳም ብትገቡ እኮ ህዝቡ ችግሩን ይረዳል መፍትሄ ይመጠል፡፡ ስለዚህ የእነንተ ጠንካራ አÌም በአሁኑ ሰዓት ለቤተክርስቲያን የስፈልጋተልና ዝም አትባሉ፡፡
አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ከሃገራችንና ከቤተክርስቲያነችን ጋር ይሁን አሜን!!!!!!!!!!!!!

Dn Haile Michael said...

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶክሳውያን:-
አሁን የበደል ጽዋው ሞልቶ ተርòል :: የቤተክርስቲያናችን ህልውናና አገራዊ ተደማጭነ~ በዚህ ዓይነት በቅርብ ጊዜ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ለመገመት ነቢይ መሆን አያሻም :: አሁን ዋናው ስራችን መሆን ያለበት ለምዕመኑ ስለ ተሐዲሶ ሴራ መረጃ ማዳረስና ግንዛቤ መፍጠር ነው:: ከዚያ በ=ላ መናፍቃን ጵጵስና እንዲሾሙ አቡነ ጳውሎስ በጥቅምቱ ስኖዶስ እስኪያቀርቡ እርምጃ እንውሰድ :: ያለው አማራጭ እሄና እሄ ብቻ ነው:: አሁን ከሹመት የቀሩት መናፍቃን ‘መነኮሳት” ስለ ጉቦኣቸው አቡነ ጳውሎስን በመጨቅጨቅ ጵጵስና ከተሾሙ ይህችን ቤተክርስቲያን በዚሁ ዓይነት ሁኔታ ማግኘት አስቸጋሪ ነው :: ‘ተቀምጠው የሰቀሉት ቆሞ ለማውረድ ይቸግራል” ዓይነት እንዳይሆንብን::

Anonymous said...

the cursed SEREKE did evil doings in order to conceal his minfikina

Anonymous said...

Glory to Lord. እንፍገመገማለን እንጂ አንጣልም፤ እንጣላለን እንጂ አንረሳም፣ ድሆች ስንሆን በክርስቶስ ደስተኞች ነን፡፡ እንፍገመገማለን እንጂ አንጣልም፤ እንጣላለን እንጂ አንረሳም፣ ድሆች ስንሆን በክርስቶስ ደስተኞች ነን፡፡

Anonymous said...

OH GOD what i can say to you?what i have to give?just thank you!!!i was crying yesterday but i am peaceful to day.you did this to me, i belive that you dosent want me to cry oh my lord thanks again,i know no one can face to you but i was scared please my lord forgive me to not lye on you. please keep our church from devil please keep mahbere kidusan on your hand???THANKS MY LORD!!!

Anonymous said...

ከተባበርን ብዙዎች ነን

እግዚአብሔር ይመስገን ግን ከእኛ አሁን ስራ ይጠበቃል
ክርስቲያኖች እስኪ እናሳፍራቸዉ መቸም ኢትዮጵያ ዉስጥ
ያለ ሰዉ ኑሮ ከብዶበታል እኛ በዉጭ ያለን ሰወች ስራ
እንጀምር ከ1€,1$ ጀምረን ልባችን ደስ ያለዉን እንስጥ
ከተባበርን ብዙዎች ነን እንኮን ለሐይማኖታችን ለሌላ እንተርፋለን እኛ ኢትዮጵያዊያን ጠላትም ልኩን ይወቅ ለበጎ ይሆናል እኮ እስከ መቼ በልመና ክፉ ጎረቤት እቃ ያስገዛል እንዲሉ አበዉ ክፉ ጎረቤት ሁልጊዜ አይጠላም ማህበረ ቅዱሳን እናንተም ባንክ አካዉንት ከፍታችሁ ቁጥሩን አሳዉቁን መፍትሄ ካልፈለግንለት ነገ መደገሙ ስለማይቀር
thank you አባ ሰረቀ እንበላቸዉ ክርስቲያኖች እኛ እንተባበር እግዚአብሔር ያሳካዋል።

ዘዮ said...

“…ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 9

“…ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።

ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።

አሁንም እላችኋለሁ። ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤
ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።

ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።
እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤

ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።”
የሐዋርያት ሥራ 5 : 36-42

ዘሐመረኖህ said...

የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው
መዝ 19 9 ገና ይፈርዳል እባካችሁ እውነተኞቹ ብጹአን አባቶች ምን እየጠበቃችሁ ነው እንደ ሐዋርያት ሰማእትነትን ለትውልድ ማስተላለፍ አትፈልጉም ማለት ነው ምእመናን ሆይ ሰው ለሃይማኖቱ ብቻ ሳይሆን ለሚያምንበት ፖለቲካ ውድ ሕይወቱን ሲከፍል አይተናልና እኛ ግን እንደጥንቶቹ አባቶቻችን ለሃይማኖታችን ለሰማእትነት እንነሳ ካህናትንና ብጹአን አባቶችን አንጠብቅ እነሱ የሥጋ ነገር ጎትቷቸዋልና ንቃ መዋቲ ንቃ መዋቲ ንቃ መዋቲ

ወልዳ ለተዋህዶ said...

ኦ ሕዝበ ክርስቲያን ኢትፍርሁ ወኢትደንግጹ ኢይክል መዊኦቶሙ ለማኅበረ ቅዱሳን ቤልሆር ወለሰራዊቱ አባ ሰረቀ ወእጅጋየሁ ወኩሎሙ/ ሀሎ አቃቢሃ ለበተክርስቲያን ትጉህ ዘኢይነውም ፈጣሪ ዘኢይደክም እግዚእ ስሉጥ ላእለ ኩሉ አምላክ ዘኢይትኃባእ ባህቱ ጸልዩ ውሉዳ ለቤተክርስቲያን

Anonymous said...

I am Glad to hear this new.

Since we are always with the winner we have been won yesterday, we are winning now, we will tomorrow and forever!!!
ድሮም በእነ ቅዱስ ጴጥሮስ መሰረት ላይ የተመሰረተቺውን ቤተ ክርስቲያን የ ሲኦል ደጆች አያናውፁዓትም !!!
አምላከ ቅዱሳን ይክበር ይመስገን አሜን !!!

Anonymous said...

እግዚአብሔር መቼም ቢሆን ሥራውን አያቋርጥም:: ፀረ ተዋህዷውያንንም ማሳፈሩን አያስታጉልም:: ሆኖም ደስታችን ልክ ያለፈና ጥቂት ጊዜ ብቻ የሚቆይ መሆኑን የዘነጋን ይመስለኛል:: አቅመ ደካማዋ የሰረረረቀ ሥልጣን የስምዐ ጽድቅን ህትመት የማገድ ደረጃዋን ያልጠበቀ አሠራሯ ከሥሯ እስካልፈለሰ ድረስ የትናንትናውን እንጉርጉሮ ከ15 ቀን በኋላ መድገማችን የማይቀር መሆኑን መዘንጋት የለብንም::

ስለሆነም ጣያቄያችን በማሕበሩ አስተባባሪነት ባስቸኳይ ለፓትርያርኩ ቀርቦ መፍትሔ የማያገኝ ከሆነ የመንግሥትን ፈቃድ ጠይቀን አንድ ወንድሜ እንደገለጸው ሰላማዊ ሰልፍ ብንወጣ መልካም ይመስለኛል:: ያለዚያ እነርሱ ለክፋት እንቅልፍ ሲያጡ የእኛ ሌት ከቀን መተኛት አሳማ ከመሆን የተለየ ትርጉም አይኖረውም::

ማሕበሩ የወንጌል አገልግሎቱን ለማሳካት በቢሮክራሲ የተጠላለፉ የቤተክህነት አሠራሮችን ለዘመናት በብስለት ለመፍታት ሲጥር መቆየቱ ብልህነትና ግቡንም የመታ መሆኑን እረዳለሁ:: ምክንያቱም በእግዚአብሔር አጋዥነት ያንን ችግር በብልሃት ማለፍ ባይቻል ኖሮ የማህበረቅዱሳን ታሪክ ከሦስትና አራት ዓመት ዕድሜ አይዘልም ነበርና:: አሁን ግን በዚህ መሠረታዊ የወንጌል አገልግሎት ላይ ከመጡ እስከየት ድረስ እንታገሳለን?

የማህበሩን ክብር እንተወውና የቤተክርስቲያናችን ክብር በየዕለቱ በውስጧ በተኮለኮሉ አድርባይ ሙሰኞች በገሃድ እየተመዘበረ ምንም ነገር ሳንፈይድ ዜና አድማጭ መሆናችንና ለመልካም ዜና መፈንጠዝ ለክፉ ወሬ ደግሞ መተከዛችን ብቻ ቤተክርስቲያናችንን ወደጉድጓድ ስትገፋ ዓይናችን እያየ ዝም ከማለት ተለይቶ የሚታይ አይመስለኝም::

ስለሆነም ወንድሞቻችን የቆየ የብልህነት ልምዳችሁን ተጠቀሙና የነበረው አካሄዳችን ሌላ መልክ ይኖረው ዘንድ እንትጋ:: ማለትም መንግሥት ማህበራችን ለአገራችን ያለው አወንታዊ አስተዋጽኦ እንዲረዳና ቅንጣት ታክል ፖለቲካዊ አቋም እንደሌለው በማስገንዘብ ለቤተ ክርስቲያናችን ህልውና ያለን ጽኑ አቋም የት ድረስ ንደሆነ እንዲረዳ እንሥራ:: እናም ህጋዊ በሆነ አግባብ መብታችንን እንጠይቅ:: ከዚህ በኋላ እስካሁን የቆየንበት ጉንጭ አልፋ ውዝግብ ዘመኑን የሚዋጅ አይመስለኝም::

ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር ብርታትን ያድለን!
ብንያም ዘባህር ዳር

Anonymous said...

Egzi'abehere yetekellewun maneme lineklew ayechelemena dese yebelachehu dese belognale. Letefate lejochem lebona yadelelen elalehu.

Anonymous said...

እግዚአብሑር ይመስገን ወርቅ በእሳት ይፈተናል ወርቅ መሆኑ ከታወቀ በኋላ በክብር እና በጥንቃቄ ይይዙታል የወርቅ ደግሞ ጠባቂውና ተመልካቹ ብዙ ነውና ጠንቀቅ ማለቱ አይከፋም እባካችሁ ትዕግስትም ልክ አለውና አትፈትኑን በመንገዳችሁ እንድንጓዝ አታስገድዱን በፈጣሪያችን ፊት በቆምን ጊዜ የምንለው አታሳጡን እባካችሁ እባካችሁ የኛ ባልሆነ መንገድ አታስሄዱን ማ/ቅ ለማንኛውም የዛሬው በዚህ ታለፈ የነገ ባለቤት እኛ ባንሆንም እንደ ሰው በተመሳሳይ ውጥረት ውስጥ ላለማለፍ ከወዲሁ መሆን ያለበትን ማሰብ ያስፈለጋል በጸሎት እንትጋ የቅዱሳን አምላክ መንገዳችንን ይባርክ ይምራን

ዘሐመረኖህ said...

እባካችሁ ደጀ ሰላሞች በሰይጣን ፈተና የታገደችውንና በእግዚአብሔር ኀይል መታተመ የቀጠለችውን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ሙሉውን እንድታስነብቡን በእግዚአብሔር ስም እንማፀናለን

Anonymous said...

አባ ሰረቀ አንዲትን ነገር ልጠይቅዎት እግርዎንና ጉልበትዎን ስሞ በመስቀልዎ መባረክን የሚሻ ይህ ሁሉ ምእመን በምድር ላይ ኤይንዎ ላፈር ካለዎት እግዚአብሔርስ ምን ... ? ዋ ከማይችሉት ጋር አይታገሉ። ለታመኑት እኮ በወጀብና በ ዐዉሎ ዉስጥ መንገድ አለና እግዚአብሔር የተከለዉን ለመንቀል ከመትጋት ይልቅ ዉሃ ያጠጡ፤ይኮትኩቱ፡ያሳድጉ። በምድርም በሰማይም ዋጋ አለዉና።በተረፈ ማስተዋሉን ለርስዎና ለልጆችዎ ያድላችሁ!!
ከአትላንታ

123... said...

Metatemua ahun ayamokegn ayaberdegn.Ende ABRHAM MESWAET (YSHAKN LISEWA ENDEWESEDEW) SIMEA TSIDK EKO BE TELATOCHUA HILINA TESEWTALECH.Ye gleseboch fekad ena yhunta enji Hig yemaykeberbat hagere-Ethiopia mehonua yasaznegnal.yilik mechiw yasegagnal.

getachew said...

amilak temesigen memerachin tatemech

YaredKahin said...

When novices or unfaithful prevail, destruction takes root.

"በደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንደታየው ዓይነት “ጉልበት ወደ መጠቀም” የመሰለ አላስፈላጊ መፍትሔ እንዳይዘዋወሩ አስግቷል። "

Look how can anyone who claims to be a Christian plan this kind of action? Are you trying to convert the religion to Islam? Christianity is not about violence... You better approach it differently.

Anonymous said...

thanks to your news, please those guys, the problem is not only MK, it is all of the EOTC members. papi(paulos) and the teaf serek are now struggling to make our church protestantism. lets unit and avoid the husband(papi) of Ejigayehu and teaf serek.
the DireDawa

MelikamKene said...

Satan firmly straggle us till we called the name of God and his Saint.
St. Afomiya called St. Michael Satan run way from her face!
Dear brothers and Sisters please pray God will take all the problem!
WELADITE AMILAKE ETOC TITEBIKILINE!
AMEN

ayyaanaa said...

oh nice! i have got simea tsidk. the contents are
1.
sile gubaew Bitsui Abune Hiskiel, B. ABUNE Lukas, B. Abune Gebriel, B. Abune Markos ena B. Abune kelemintos hasabachewun setewal.
2. sile <aba< sereke meglecha higewetinet BITSUI ABUNE KELEMINTOS, ye senbet timihirt betoch maderaja memiria like papas geltewutal
3. ye afrika derasian sile GEEZ kunkua
4. .......
5.......yiketilal!!!
ye Tewahedo lijoch enkuan dess alachihu! SERAW LEKA YE KURTEGNOCHU ABATOCHACHININ HASAB INDANISEMA TASIBOM NEBBER!!!ZE YIGERRIM!!!

Anonymous said...

It is not how long and how many copies it has been published, what matters most is how value was the news paper in peoples life. Not only the users but also the publishers (the writers)life is the focus, are they changed, gets the peace and joy that the lord is promised us to have?

Anonymous said...

amen

ርብቃ ከጀርመን said...

የቅዱሳን አምላክ የተባረከይሁን መልካም ዜና ነው የተሰማው ህትመቱ አለመቅረቱ ነገርግን እስከመቸ
እንዲህእያስፈራሩን እንኖራለን እስከመቸስ እነሱ (ያናችንቀለም ደስሳይላቸው) ሲቀር እነርሱ እንደሚሉትእየደነበርን እንኖራለን መፍትሄው ያለመቀዝቀዝ እስከመጨረሻው በሰላማዊ ትግላችን መቀጠልና በጸሎትም መበርታት ይኖርብናል ስምዐ ጽድቅንና ሐመርን በተመለከተ ተባብረን የማተሚያ ማሽን የግላቸው እንዲኖራቸው ብናደርግ ሰረቀምሆነ ሌላው ትቢተኛ በተነሳቁጥር ከመረበሽና ከመደናገጥ እንድናለን እና እባካችሁ ይሄን ነገር እንወያይበት በተረፈ ግን ለጥርሳቸውንክሻ ያለደረገን ቸሩአምላካችን የተመሰገነይሁን

Anonymous said...

I don't want to see any of the religious newspaper or books that stands for the church's dogma and discipline to be banned from publishing. But I was amazed by the reaction of all the commentators on this blog which is obviously by the majority of the members of the mahibere kidusan. WHERE HAVE THE REACTION BEEN ALL THESE DAYS WHEN THE CHURCH WAS IN A GREAT DANGER??? WHERE HAVE YOU BEEN WHEN THE MONKS WERE SHOT AND KILLED AT ST. ESTIFANOS CHURCH??WHERE HAVE YOU GUYS BEEN WHEN THERE WERE HUGE FIGHT AT THE LIDETEA CHURCH??WHERE HAVE YOU GUYS BEEN WHEN THE "LIQAWENTS" WERE KICKED OUT OF THE CHURCH? WHERE HAVE YOU GUYS BEEN WHEN THE MEMBERS OF THE HOLY SYNOD WHERE BEATEN AT NIGHT WHILE THEY WERE AT THEIR HOUSE??
Please don't claim by mentioning the "timing of God". This is a lame excuse comes from a lame Christian. Don't offer God lame excuse for your failure of not acting properly on time and not fulfilling your responsibility. There’s never a wrong time to do the right thing…or to return to what you know God is calling you to do.

Mahibere kidusan did not say a word on their newspaper on all these problems AFRAIDING that the association will be in a great danger or shuts down if they said so. And now you guys are all have to take these agonize because of all your past retreat.

It will be good if you guys can stands for the millions of the church's parishioners and feel their pain while they are in danger anytime than getting upset or worried when the mahiber that you are in are in danger. Let us all worship the Lord who is always in our midest and give all the grace to Him, instead of worshiping the group or the association or our good name.Otherwise the mahiber or the good name or the group that we are in will be like pagan symbol or an IDOL

"If this blog doesn't belong to Mabebere kidusan "you will definitely post it.

Anonymous said...

ፍቅረማርያም
ጭንቀታችንን ያስተነፈሰ መልካም ዜና ነዉ፤ ግን አሁን ያለዉ ችግር እኮ የስምዓጽድቅ መታገድ/መታተም አንዳንድ ወንድም/እህቶቼ እንዳላችሁት ደግሞ የማተሚያ ማሽን እጦት አይደለም፡፡ ይህ መንደርደሪያ ነዉ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ላለፉት አመታት አንድም በትህትና አሊያም በጥበብና በጸሎት ስራዉን ሲሰራ እንደነበረ ግልጥ ነዉ፡፡ ሌሎቻችን ለራሳችን በትጋት የምናከናዉነዉ የቤትስራ ለራሳችን እንስጥ፤ እኔ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ይተያኛል፤
1. ይቺ ተዋህዶ ሐይማኖት ዛሬ የደረሰቺዉ በድሎት አይደለም ቀድሞ ነገር ለቤተክርስተያን ምቾት መች ይስማማታል? (To see how Orthodox reached here, go to http://www.tewahedo.org/daniel.html and listen to Negere kidusan part one and two by our big bro Dn Daniel Kibret) ምቾትና ሐይማኖትስ መቼ አብረዉ ይሄዳሉ? አባ ጳዉሎስና አባ ፋኑኤልስ አሜሪካ ኖረዉ መጥተዉ ቤትክረስቲያኒቱን መምነሸነሻ ሊያደርጉ መፈለጋቸዉ ነዉ መስመር ያሰተቸዉና ህዝብ እያለቀሰ/እያዘነ እነሱ ሌላ የሚያስቡት:: በሶስቱ ወፎች ቪሲዲ ላይ አላያችሁም (ካላያችሁ እዩት እኔ በተለይ አባ ጳዉሎስ ፊት እኒያ ትጉ የአዋሳ ምዕመናን ሲያለቅሱ አብሬ አልቅሼ አይቸዋለሁ) ….. እና ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ ከምንም በላይ በጸሎት እንትጋ:: ሌላዉ የጸሎት ልምዳችን እንዳለ ሆኖ ይህን ጉዳይ በማስመልከት ወደ ለይ ማንጋጠጥ አንዱ የኛ ድርሻ ነዉ፡፡ ለምሳሌ አንዱ ወንድሜ በመንገድ ሲያልፍ ቤተክርስቲያን ከገጠመዉ ስለወቅቱ ጉዳይ ሰላም ለኪ ሳይል አያልፍም ለጸሎት በቆመ ቁጥር ደግሞ መዝ24ን ሁሌ ያደርሳል፡፡ ቢቻል እኮ እያለቀስንም የምንጸልይበት ወቅት ነዉ፡፡ እኒህ ሰዎች ከሰዉ በላይ ሲሆኑ እንደ አሪዎስ አሟሟታቸዉ እንኳ የከፈ ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተላላቅ ወንድሞቻችን ይህ በዚህ ሰዓት ቢጸለይ ይህ ደግሞ እንደህ ቢሆን በሉን እንጂ በተለይ ከመዝሙረ ዳዊት………
2. ሌላዉ ደግሞ መረጃ ነዉ፡፡ የወቅቱ አሳዛኙ ነገር ደግሞ ብዙሓኑ ምዕመን ስላለዉ አሳሰቢ ጉዳይ ያለዉ መረጃ በጣም ትንሽ ወይም ምንም ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ሌላዉ የኛ ድርሻ ይህ ይመስለኛል:: በተለይ የዘወትር ኢንተርኔት ተጣቃሚዎችም ሆናችሁ እግር ጥሏችሁ መረጃ የምታገኙ ለሌላዉ አዳርሱ ይህ ለወሬ ወዳዱ ሳይሆን አሳስቦት ለሚጸልየዉ ነዉ መሆን ያለበት፡፡ የሚያወረማ ሞልቶናል፡፡
3. ሌላዉ ደግሞ ወንድሜ ብንያም ዘባህር ዳር እንዳለዉ እንደ አዋሳ ምዕመናን ያለመሰልቸት ማሰባሰብ የምትችሉ ሁላችሁ አሰባስቡንና ለስጋ ገዢዎቻችን አቤት የምንልበትና ሌላዉንም የምናናቃበት መንገድ እንዲመቻች እንነሳ፡፡ የአዋሳ ምዕመናን ከበቂ በላይ የሆኑ ምሳሌዎች ናቸዉ፤ ደከመኝ ገንዘቤ አለቀ ሳይሉ ተመላልሰዉ ሲብስም አልቅሰዉ ለወቅቱ ጥያቄዎቻቸዉ መልስ አግኝተዋል፡፡ ዋናዉ ሁሉም ነገር በስርዓትና በአግባቡ እንዲሆን መጠንቀቅ ብቻ ነዉ፡፡
4. በመጨረሻ ግን የማግኘት ዕድሉ ቢኖረኝ ለብጹኣን አባቶቼ ማለት የምወደዉ ሐይማኖት ድርድር ዉስጥ አይገባምና አለምን ትታችሁ ወደምንኩስናዉ ህይወት የገባችሁት ስለሐይማኖታችሁ ለመኖር ነዉና ከምንም በላይ ዲያብሎስን ተቃወሙት፡፡ በጸሎት ትጉ ብዬ ብናገር መቸም አያምርብኝም “ልጅ ለናቷ …” ይሆንብኛልና፡፡ አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ስለእናቱ ስለቅድስት ድንግል ማርያም ስለጻድቃን ወዳጆቹ ሲል ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን!

Anonymous said...

"ቤተ ክህነቱ አሁን በያዘው መልኩ የሚሔድ ከሆነ ምዕመናን የራሳቸውን መፍትሔ ወደ መፈለግ እና በደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖ
ት ቤተ ክርስቲያን እንደታየው ዓይነት “ጉልበት ወደ መጠቀም” የመሰለ አላስፈላጊ መፍትሔ እንዳይዘዋወሩ አስግቷል። "

ይህ፡አጻጻፍ፡እራሱ፡"አላስፈላጊ"፡ነው።ፍርሃትን፡
ከሃይማኖት፡መጠቃት፡ጋር፡ማዳበል፡በተለምዶ፡የ
ሉተር፡ሰዎች፡ሥራ፡እንደሆነ፡ከተገነዘብን፡ቆይተ
ናል።

ከደጀሰላም፡ብሎግ፡አዘጋጅ፡ይህን፡የአሳልፎ፡መስ
ጠት፡ዘገባ፡አልጠበቅንም፡ነበር!

ትግላችን፡ከዲያቢሎስ፡ጋር፡ነው።አመፃቸውን፡ጓዳ
ችን፡ድረስ፡ይዘው፡የመጡት፡ሉተራውያን፡ናቸው።
ይህን፡ሃቅ፡ተረድተንና፤ጥቃቱ፡እየበዛብን፡ስለመጣ፡
እርምጃችን፡ይቀጥላል።

ይህ፡የደጀስላም፡ዘገባ፡የተክልዬን፡ልጆች፡ቆራጥ፡
አቋም፡ለማዳከም፡የተሰነዘረ፡ይመስላል።ጥቅሙ፡ለ
ሉተር፡ቅጥረኞች፡እንጂ፡ለተጠቃነው፡የተዋሕዶ፡
ልጆች፡አይደለም።እናዝናለን።

እየፈሩ፡መታገልና፡ማታገል፡ስለማይቻል፣የደጀሰ
ላም፡አዘጋጅ፡እንዲህ፡ያለውን፡አሳዛኝ፤አስተያየ
ት፡ሌሎቻችን፡እንደምንጽፈው፡በግሉ፡መሰንዘር፡
ሲችል፡በሉተራውያን፡ግፊት፡እንደ፡ደጀሰላም፡አቋ
ም፡አድርጎ፡ማቅረቡ፡ስህተት፡ነው፤ይታረም!

በተርፈ፡የአዘጋጁን፡በጎ፡ጥረት፡ሁሉ፡የምናከብር፣
መሆናችንን፡እንገልጻለን።

የተክልዬ፡ልጆች፡ቤተ፡ክርስቲያናችንን፡ለመታደ
ግ፡የሚያደርጉትን፡ጥረት፡ለመደገፍ፡የተቋቋመ፡
ማህበር፣አዲስ፡አበባ፣ኢትዮጵያ።

Anonymous said...

አቤል (Abel)
መንግስት ሁሉንም ነገር በደንብ አድርጎ ያውቃል። ለመሆኑ ይህን ሁሉ ፈተናና ችግር በሀገራችን አልፎ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያማጣው ማን ሆነና? ሳይጣንንም ታሃድሶንም ኑፋቄውንም ታግሎ ማሸነፍንና ማጥፋት ቤተክርስቲያን ታውቅበታላች። ያስቸገራት ለሙሰኛ ግለሰቦች፣ ለካድሬዎች፣ ቤተክርስቲያንን ከውስጥ ሁነው ለሚቦጠቡጧት ሆዳሞች፣ እንደ አቡነ ጳውሎስ ላሉት አባትነት ይቅርና በቅጡ ኃላፊነት ለማይሰማቸው አባቶች ሽፋን መስጠቱ ነው። ይህ ደግሞ ለራሱ ለመንግስት የታዳፈና እሳት ሁኖ ጊዜው ሲመጣ ያሚያቃጥለው ነበልባል እንደሚሆን ማናችንም አንጠራጠር። እግዚአብሔር ምን ጊዜም አሻናፊ ነው። ሕዝቦቹም እንዲሁ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)