June 4, 2011

የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ‹‹ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› አመራሮች ላይ የእስር ቅጣት ወሰነባቸው

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 4/2011)፦ የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚያዝያ ወር ውስጥ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ባስነሡት ብጥብጥ በንጹሐን ምእመናን ላይ ከፍተኛ የድብደባ ወንጀል ፈጽመዋል ባላቸው አራት የ‹‹ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› ማኅበር አመራር በሆኑ ተከሳሾች ላይ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሐሙስ፣ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት ገዛኸኝ አበራ እና አየነው የተባሉት ግለሰቦች በ8 ዓመት፣ ተስፋዬ በ5 ዓመትና ጌታሁን የተባሉት ደግሞ በ3 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡


ውሳኔው በተላለፈበት ዕለት ምሽት የእኒሁ ወንጀለኞች ጥቂት ደጋፊዎች በገዳሙ ዐውደ ምሕረት ላይ በመውጣት በድምጽ ማጉያ ‹‹ወንድሞቻችን ተፈረደባቸው፤ ታሰሩ፤›› እያሉ የከተማውን ደጋግ ምእመናንን እና የማኅበረ ቅዱሳንን ስም እየጠሩ ሲወነጅሉ እንደነበር ተገልጧል፡፡ እኒሁ ግለሰቦች በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተመርጠውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተመድበው የሄዱትን አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ ለመከላከል ሞክረው እንደነበር ታውቋል፡፡ ይሁንና በፖሊስ ኀይል ከአካባቢው እንዲርቁ ከተደረገ በኋላ ሥራ አስኪያጁ ሥራ ለመጀመር መቻላቸው ተመልክቷል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ አላግባብ ከተሰጣቸው ሥልጣን እንዲወገዱ የተደረጉት ‹‹ሊቀ ካህናት›› ጌታቸው ዶኒ በተሰራጨው ቪ.ሲ.ዲ ስሜ ጠፍቷል ያሉበትን ክስ በዚያው በሐዋሳ ከተማ ሆነው እየተከታተሉ ሲሆን ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ምክትል ሐላፊ ሆነው መሾማቸው ተነግሯል፡፡

18 comments:

Anonymous said...

June 4, 2011

Anonymous said...

Wey Egziabher Yegedamat asetdader lela yebase tifat ere min yeshalenal? Egziabher zim ale eko endew wedajoche minew hulachinm esti beyalenbetm hone be fecebook betsome hawariyat tselot enadreg ebakachu tifatu eyketel new yehdew asferi gize hone eko

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች፡-
በዮቲቭ የተለቀቀውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ በሐዋሳ የሚለውን ቪዲዮ ተከታትዬ ጉድ አየሁ። ከቻላችሁ በዚህ ሊንክ አድርጉት። በርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ሊያዩት የሚገባ ነው። የዚህ ሁሉ ምንጩ ራሳቸው አቡነ ጳውሎስ ይመስላሉ። ምን ማለት ነው ከሐዋሳ የቤተክርስቲያኒቱ ፀር ነው የተባለን ግለሰብ አምጥቶ ቤተ ክህነት ውስጥ መሾም! ከጠቅላይ ሚንስትሩ የቀሰሙት ልምድ ይሆን? በሕዝብ የተጠላ ካድሬአቸውን አምጥተው ለእርሳቸው አማካሪ ወይም ምናምን ብለው እንደሚሾሙት! ኦ አምላክ ሆይ ቤትህን አንተው አጽዳ። ጎልያድ ተርክቦ እየመዘበራት ይገኛልና። አምላክ ሆይ እባክህ ስለወዳጆችህ ብለህ አትጨክንብን። ቃል ኪዳንህን አስብ። ጥሬ እየቆረጠሙ፤ ጤዛ ልሰው የሚለምኑ አባቶቻችንን አስበህ ይቅር በለን። ጌታ ሆይ ካንተ ወዴት እንሄዳለን?

sosena said...

''YEGZIABHERN SERA BECHLITA YEMIYADERG ERSU ERGUM YEHUN''

TIKISUN MIRAF KAGEGNACHUT CHMIRACHU POST ADRGUT. PLS
YALEW YENEBIU ERMIYAS TINBIT BENEABA PAULOS LAY MEDRSU AYKERIM

Anonymous said...

ኧረ ኡ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! እኒህ ሰዉዬ አሁንስ ሊያሳብዱኝ ነዉ። ምነዉ አምላከ ሠላም እድሜያቸዉን ቢያሳጥርልን እና ሠላማ ችንን ባገኘን።


በፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ደስ ብሎኛል። እስኪ ለሌሎች ትምህርት ቢሆናቸዉ።

Anonymous said...

God is Cleaning His Home!
Just let us keep on praying while we r doing w/t we should do!
(AGE)

Anonymous said...

ውድ ደጀሰላማውያንና የደጀሰላም ተከታታዮች፡- መቼም በየዕለቱ የቤተክርስቲያንን ግፍና መከራ የምትመለከቱት ነውና ላብራራላችሁ አልሻም። አሁን ግን እኛ በየግል ሕይወታችን ጭንቀት ውስጥ ስንገባ የማይተወን እግዚአብሔር ቤቱ በርግብ ሻጮች ትርምስ ስትናጥ ከሐሜት ባልዘለለ ወሬ ጊዜያችንን ከማጥፋታችንና አእምሯችንን ሰላም ከማሳጣት በዘለለ የምንፈይደው ነገር እንደሌለ ተረድቻለሁ።

ስለሆነም መረጃ ቁም ነገር ላይ ካልዋለ የደጀሰላም ሌት ከቀን መኳተን፣ የእኛስ ያለእረፍት ማንበብና መቃጠል ከጉዳት በቀር ምን ጥቅም አለው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ባለመቻሌ ነፍሴ ተጨነቀች።

ማለት የፈለግሁት ብዙውን ገሃድ የወጣ ጉድ እንተወውና ሰሞኑን ባለበት ኑፋቄ ከተሾመበት ሥልጣን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲነሳ የተደረገውን ጌታቸው ዶኒን ያውም በዚህ ሰዓት ለመናፍቃን ስስ ብልት በሆነው የገዳማት ጉዳይ ላይ ኃላፊ አድርገው መሾማቸው አንድም ቅዱስ ሲኖዶሱን ሁለትም ሕዝብን መናቃቸው ነውና እስከመቼ ዝም ብለን የሩቅ ተመልካች እንሆናለን?

እንደምታውቁት በስጋዊ ጉልበት ከእኛ ጋር ካሉት ይልቅ ከሰውዬው ጋር ያሉት እንዲበልጡ እናውቃለንና ሕጋዊ በሆነ መንገድ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈጸሙ ያሉትን አምባገነናዊ አስተዳደር መጠየቅ የምንችልበት መንገድ የለም ወይ? እባካችሁን ደጀሰላማውያን ከምትደክሙት ድካም ሁሉ ይህ አይከፋምና ብትችሉ የሕግ ባለሙያዎችን አማክራችሁ አቅጣጫ ብታስይዙን፣ የብሎጓ ተከታታዮች የሆናችሁና በዚህ ጉዳይ ላይ የተሻለ ግንዛቤ ያላችሁ ግለሰቦችስ ምናለበት በዚህ ዙሪያ ቁምነገር ብትጽፉልን።

ይህ ካልሆነ ትኩስ መረጃ በየዕለቱ የምንኮመኩም እኛ መረጃ ከማያገኘው ጠረፍ የሚኖር ምዕመን ምን ይለየናል?

ተጨነቅሁ!!
ቢንያም ዘባህር ዳር

mahiberekidusan said...

God bless the church.

Asrat said...

ውድ ደጀሰላማውያን፡- የተወሰነው ውሳኔ ያንሳል የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ ሆኖም እነዚህ የተሃድሶ አቀንቃኞች ከዚህ መማር አለባቸው፡፡ ከእውነት ጋር መታገል ለመውደቅ መሆኑን ሊረዱ ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የቅዱሳን አባቶቻችንን ዘመን ይመልስልን!! ብስራት

Peace for EOTC said...

Here is the link Please share it:
http://www.youtube.com/watch?v=ldoU-V-2GtM&feature=related

Anonymous said...

"Sime teftual" alu.Yemitefa sim alachew??

Anonymous said...

I believe the government made the right descion. Our church has to be free from these kind of people. In addition I will ask the congreation of the church to give ultimate care for the monks, Deacons of the Hawassa Church. I beleve most of not understood how much the innocent Monks and Deacons suffer, Some of them not paid for their service, and some of them are hardly beated and forced to leave the church.

God be with you.

samueldag said...

የቅዱሳን፡አምላክ፡ክብር፡ምስጋና፡ይድረሰው፡፡

Anonymous said...

yeawasa miemenan jegna nachu...araya honachu malet new ....enibachu gena yitabesal...hibretachihun atitewu amlakachin ale mehalachu...kegnam gar endihon tseliyulin

Anonymous said...

and ken lenisiha endemitibeka tesfa alegn esum maraki metsihet lay keabune gorgorios endetekanu silemelesu....and ken and ken

Anonymous said...

ግን ለምን ይሆን ይህ ሁሉ ትዕቢት? እውነት ክርስቶስን ለመስበክ ነው? ወይስ ምን አላማ አላቸው? ካላመኑበት እኮ ጥለው መውጣትና ወደ መሰላቸው መሄድ ይችላሉ። ለምን ያውኩናል? ማገልገል ካልተቻለ እኮ መገልግልም ይቻላል። ቤተክርስቲያን ናትና። በሐይማኖት ደክማችሁ ከሆነ ቁጭ ብላችሁ ተማሩ፤አንብቡ። ችግሩ ደግሞ የገንዘብ ጉዳይ ከሆነ ሌሎች ቦታዎች አሉ። እዚያ መስራት ይቻላል። ለምን የሌባ አይነ ደረቅ ትሆናላችሁ። በውኑ አውሬው ማን ነው? በተዋህዶ ጸንቶ ስብሐት በእየ ሰዓዩ የሚያደርሰው ወገኔ ይሆን? እውነት እናተ ናችሁ ወንጌል ለዚህ ሕዝብ የተበካችሁት? ቤተ ክርስቲያኗ እድሜ ለቀደሙት አባቶቻችን ሰባኪ እንድትሆን አድርገው ነው ያስረከቡን። የእናተ አጉራ ዘለል ስራ ነው አሁን ያስደፈራት። እርሷ ማ ሁሌም ሰንዱ እመቤት ናት!አርጅታም አታዉቅም!! ሳራ እኛን ወልዳለች እያላችሁ በመድረኳ አትዘባበቱ! ወንጌልን ለመስበክ ተግባር እንጂ ጎርናና ወይም ለስላሳ ድምጽ አይደለም ቅድመ ሁኔታው። እስኪ እምነታችሁን በተግባር አሳዩኝ? እስኪ ወደ አንዱ ገዳም ገብታችሁ ሱባዬ ያዙ? አውደ መረቷን ለቀቅ አድርጉት! እኛ እንኳን አባ ጳዉሎስን መለስን ብትይዙት አንፈራም!እምነት ነውና! በጋሻው ያኔ ያዋረድሃቸውን አባት ዛሬ ሃዉልት አቁመህ ግራ የምታጋባቸው ለራስህ ብለህ እንጅ ለተዋህዶ እንዳልሆነ ልቦናህ ያውቀዋል። እንዳትረሳ አንተ አደባባይ ላይ ማንም ያወቀህ አባቶችን ስትዘልፍ እንጅ ለወንጌል በለህ ራስህን አሳልፈህ ስትሰጥ አይደለም።
የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድብን! የስራችንን ይስጠን!

Anonymous said...

የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለማስፈጸም ምን ማድረግ አለብን:: መንግስት ለከፋት ለሙስና እና ከቤተ ክርስቲያናችን ለቆሙት ለአባ ፓውሎስ መቆሙን ከቀጠለ እኛ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ለማስፈጸም አንድ ነገር ማድረግ አለብን ህግን መጠቀም ሕግ ካልሰራ ደግሞ ቀጣዩን እርሱም ሲኖዶሱ ውሳኔውን ማስፈጸም እንዲችል ሁሉን አቀፍ የሆነ ድጋፍ መስጠት:: ውሳኔያቸውን ለአባ ፓውሎስ ያስፈጽማሉ ብሎ ማሰብ ስለማይገባ እዛው ቤተ ክህነት ቆ ይተው ማስፈጸም እንዲችሉ ማድረግ በወሮበላዎቹ ና በልማደኞቹ አደጋ እንዳይደርስባቸው እዛው አምስት ኪሎ አደባባዩ ላይ መስፈርና መጠበቅ ወይንም መሳብሰባችን የማይመቸው መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማድረግ:: ለመንግስትም የኃይማኖት ጉዳይ ከስኳር ና ዘይት ዋጋ መጨመር በተለየ አደገኛ መሆኑን ቢያውቅ እና የክፋት አባት የሆኑትን መደገፉን አቁሞ የሕዝብ መሆን ቢች ል ይሻለዋል :: እንዲህ ይሆናል ብለን አላሰብንም ማለት በኋላ ዋጋ የለውም::

Anonymous said...

http://www.ethiotube.net/video/14292/TEHADISO-BE-AWASSA-PART-1-OF-10

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)